top of page


መንግስት አዳዲስ ፕሮጀክቶችን ከመጀመር ይልቅ የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን መጨረስ ላይ ትኩረት አድርጓል፡፡
ሐምሌ 27 2018 መንግስት አዳዲስ ፕሮጀክቶችን ከመጀመር ይልቅ የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን መጨረስ ላይ ትኩረት አድርጓል፡፡ በጀት ሲያዝም ለአዳዲስ ፕሮጀክቶች ሲመደብ አይታይም፡፡ አለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት IMFም ለአዳዲስ ፕሮጀክቶች መንግስት እንዳይበደር አስጠንቅቋል፡፡ በሌላ በኩል ግን የስራ አጥነት ምጣኔ 25 በመቶ በሆነበት፤ ምርትና ምታማነት በእጅጉ በሚያስፈልግበት በዚህ ወቅት አዳዲስ ፕሮጀክቶች አለመጀመር ለኢኮኖሚው ምን ማለት ነው? ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ.... ትዕግስት ዘሪሁን
6 days ago1 min read


በአማራ ክልል ያለው ጦርነት አሁንም ያለ ሁነኛ መፍትሄ እንደቀጠለ ነው፡፡
ሐምሌ 27 2018 በአማራ ክልል ያለው ጦርነት አሁንም ያለ ሁነኛ መፍትሄ እንደቀጠለ ነው፡፡ ጦርነቱ ከቦታ ቦታ መጓጓዝን ፣ ግብርናን ፣ ትምህርትን ሌላውንም እያስተጓጎለ ይገኛል፡፡ የክልሉ መንግስት የፀጥታውን ሁኔታ “አንፃራዊ ሰላም” ሲል ገልፆታል፡፡ መሳሪያ ያነሱ አካላትን በሚመለከት በሀገራዊ ምክክሩ አጀንዳ ሆኖ መቅረቡ የአማራ ክልልን የጸጥታ ችግር ይፈታው ይሆን? የክልሉ ፀጥታ ሁኔታስ አሁን በምን ሁኔታ ላይ ይገኛል? ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ.... ያሬድ እንዳሻው
6 days ago1 min read


የዓለም ጤና ድርጅት ለካላ-አዛር ሕመም አዲስና አጭር የሕክምና መመሪያ ይፋ ማድረጉ ተሰማ፡፡
ሐምሌ 24 2018 የዓለም ጤና ድርጅት ለካላ-አዛር ሕመም አዲስና አጭር የሕክምና መመሪያ ይፋ ማድረጉ ተሰማ፡፡ የካላ-አዛር ሕመም በአሸዋ ዝንብ ንክሻ የሚተላለፍ፣ የውስጥ አካላትን የሚጎዳ እና በወቅቱ ሕክምና ካልተደረገለት ገዳይ ሊሆን የሚችል ከባድ የጤና ችግር ነው። በሽታው ከፍተኛ ትኩሳት፣ የክብደት መቀነስ፣ የደም ማነስ፣ እንዲሁም የጣፊያ እና የጉበት ማብጥ የሚያስከትል ነው። በአሁኑ ወቅት ካላ-አዛር በ80 በሚጠጉ ሀገራት በወረርሽኝ መልክ የሚገኝ ሲሆን፣ በየዓመቱ ከ50,000 እስከ 90,000 የሚደርሱ አዳዲስ ታካሚዎች ይመዘገባሉ። በተለይም ምስራቅ አፍሪካ የበሽታውን ከፍተኛ ዓለም አቀፍ ጫና የምትሸከም ቀጠና ስትሆን፣ እ.ኤ.አ በ2024 ከተመዘገቡት በሽተኞች መካከል 79 በመቶ የሚሆኑት የዚሁ ቀጠና ናቸው። ኢትዮጵያም በሽታው አሁንም ከፍተኛ የ
Jul 312 min read
የሐምሌ 24 2018 የውጪ ሀገር ወሬዎች
#ኮንጎ በኮንጎ ኪንሻሣ በኢቦላ የሚያዙ ሕሙማንና ወረርሽኙ የሚገድላቸው ሰዎች ብዛት በጣሙን እየጨመረ ነው ተባለ፡፡ በበሽታው መያዛቸው የተረጋገጠው ሰዎች ብዛት ከ3 ሺህ 400 መብለጡን አናዶሉ ፅፏል፡፡ ወረርሽኙ የገደላቸው ሰዎች ብዛት ከ1 ሺህ 500 በላይ መድረሱ ተነግሯል፡፡ በአገሪቱ በኢቦላ በሽታ የሚያዙ ሰዎች ብዛት በየ20 ቀኑ በእጥፍ እያደገ መምጣቱን የጤና ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ መረጃ ያሳያል፡፡ ወረርሽኙ የመግደል አቅም ከ44 በመቶ በላይ እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡ ወረርሽኙ ወደ አዳዲስ ስፍራዎችም በመዛመት ላይ ነው ተብሏል፡፡ በኮንጎ ኪንሻሣ ኢቦላ በወረርሽኝ ደረጃ መቀስቀሱ ከተነገረ ወደ 3ኛ ወሩ ተቃርቧል፡፡ #አሜሪካ ከ130 በላይ የዮርዳኖስ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች የአሜሪካ ጦር ከአገሪቱ እንዲወጣላቸው ጥያቄ አቀረቡ፡፡ ተፅዕኖ ፈጣሪዎቹ ቀደም ሲል ከ
Jul 312 min read


በኢትዮጵያ መንግስት ትንበያ መሰረት ከስድስት ወራት በኋላ የዋጋ ግሽበት ወደ ነጠላ አሃዝ ይወርዳል፡፡
ሐምሌ 24 2018 በኢትዮጵያ መንግስት ትንበያ መሰረት ከስድስት ወራት በኋላ የዋጋ ግሽበት ወደ ነጠላ አሃዝ ይወርዳል፡፡ የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ማህበር ትንበያ ግን ከዚህ ይለያል፡፡ የብር የመግዛት አቅም አምስት በመቶ ሲዳከም ግሽበት ሁለት በመቶ ከፍ ይላል የሚለውን የመንግስት ሪፖርትና ሌሎችንም መለኪያዎች መሰረት በማድረግ ከአምስት አመት በኋላ እንኳን የግሽበት ምጣኔው 15 በመቶ ይሆናል ሲል ተንብየዋል፡፡ ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ... ንጋቱ ረጋሣ
Jul 311 min read
በኢትዮጵያ እያንዳንዱ ብሄረሰብ የራሱን ታሪክ ብቻ ለይቶና አጉልቶ የሚያቀርብበት ስርዐት መቀየር እንዳለበት የታሪክ ምሁር ፕሮፌሰር ባህሩ ዘውዴ ተናገሩ ።
ሐምሌ 23 2018 በኢትዮጵያ እያንዳንዱ ብሄረሰብ የራሱን ታሪክ ብቻ ለይቶና አጉልቶ የሚያቀርብበት ስርዐት መቀየር እንዳለበት የታሪክ ምሁር ፕሮፌሰር ባህሩ ዘውዴ ተናገሩ ። በኢትዮጵያ የብሄረሰቦች ታሪክ ጥልቅ ትስስር እና መስተጋብር ያለው ነው ብለዋል። የኢትዮጵያ የታሪክ ባለሞያዎች ማህበር ከላይፍ ኤንድ ፒስ ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር ያዘጋጀው እና ትኩረቱን በኢትዮጵያ ታሪክ ዙሪያ ያደረገ ጉባዔ እየተካሄደ ነው፡፡ "ኢትዮጵያን ከፖለቲካ አመፃ ታሪክ እንዴት ነፃ ማውጣት ይቻላል" በሚል ርዕስ እየተካሄደ ባለው በዚህ ጉባዔ ላይ የተለያዩ ጥናታዊ ፅሁፎች እየቀረቡ ነው ። የማህበሩ ፕሬዚዳንት የሆኑት የታሪክ ምሁር ፕሮፌሰር ባህሩ ዘውዴ ጉባዔው በኢትዮጵያ ታሪክ አፃፃፍ ዙሪያ ያሉ ችግሮችን የሚጠቁም እንደሆነ ነግረውናል። አሁን ያለው የታሪክ አቀራረብ እያ
Jul 311 min read
በ2018 በጀት ዓመት ከ1.2 ቢሊዮን ኩንታል በላይ ምርት መገኘቱን የግብርና ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል።
ሐምሌ 23 2018 በ2018 በጀት ዓመት ከ1.2 ቢሊዮን ኩንታል በላይ ምርት መገኘቱን የግብርና ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል። በየዓመቱ በሀገሪቱ የሚገኘው የምርት መጠን እያደገ እንደሚመጣ ሪፖርቶች ያመልክታሉ። በገበያው ውስጥ ግን የምርት ዋጋ ከአመት አመት እየጨመረ እንጂ ሲቀንስም አይታይም። ይህ ለምን ሆነ? እውነትስ ምርቱ ከተመረተ በገበያው ውስጥ ገብቶ ለምን የምርት ዋጋ አይቀንስም? ስንል ባለሙያን ጠይቀናል። ከተማ በቀለ (ዶ/ር) በሐሮማያ ዩኒቨርሲቲ የአግሮ ኢኮኖሚክስ መምህርና ተመራማሪ ናቸው። በኢትዮጵያ የሚመረተው የግብርና ምርት እየጨመረ ቢመጣም ዋጋ ሊቀንስ ያልቻለው የማምረቻ ወጪ በዚያው ልክ እየጨመረ በመምጣቱ እንደሆነ ከተማ በቀለ (ዶ/ር) ይናገራሉ። ለምሳሌነትም ከአምስት ዓመት በፊት አንድ ኩንታል ማዳበሪያ በ5,000 ብር ይሸጥ የነበረ ሲ
Jul 312 min read
እድሜያቸው ከ14 እስከ 24 የሆኑ አፍላ ወጣቶች በተለይም ሴቶች ላይ እየታየ ያለው የኤች አይ ቪኤድስ ስርጭት በከፍተኛ ፍጥነት እየጨመረ መምጣቱን፣ ይህም ከፍተኛ ትኩረትእንደሚያስፈልገው ኔፕ ፕላስ (NEP+) የተባለ ድርጅት ተናገረ።
ሐምሌ 23 2018 እድሜያቸው ከ14 እስከ 24 የሆኑ አፍላ ወጣቶች በተለይም ሴቶች ላይ እየታየ ያለው የኤች አይ ቪኤድስ ስርጭት በከፍተኛ ፍጥነት እየጨመረ መምጣቱን፣ ይህም ከፍተኛ ትኩረትእንደሚያስፈልገው ኔፕ ፕላስ (NEP+) የተባለ ድርጅት ተናገረ። Network of Networks of HIV Positives in Ethiopia ወይም ኔፕ ፕላስ ይህንን ያለው ከወር በኋላ የሚያካሂደውን ጠቅላላ ጉባኤውን በማስመልከት ዛሬ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሲሰጥ ነው። የኤች አይ ቪ/ኤድስ ስርጭት መጠን በሀገር አቀፍ ደረጃ ከአንድ በመቶ በታች ቢሆንም፤ እንደ አዲስ አበባ፣ ጋምቤላ፣ ትግራይ፣ አማራ ባሉ ክልሎች ዋና ዋና ከተሞች ስርጭቱ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱን ድርጅቱ ጠቅሷል። በተለይ ደግሞ እድሜያቸው ከ14 እስከ 24 ያሉት ወጣቶች፣ ከዚህም ውስጥ ሴቶች ለቫ
Jul 312 min read
ከፍተኛ የትምህርት ዝግጅት ያላቸው ኢትዮጵያውያን በደላሎች ተታልለው በደቡብ ምስራቅ እስያ ለአስገዳጅ የበየነ-መረብ ማጭበርበር ወንጀል እና ለእንግልት እየተዳረጉ ነው ተባለ።
ሐምሌ 23 2018 ከፍተኛ የትምህርት ዝግጅት ያላቸው ኢትዮጵያውያን በደላሎች ተታልለው በደቡብ ምስራቅ እስያ ለአስገዳጅ የበየነ-መረብ ማጭበርበር ወንጀል እና ለእንግልት እየተዳረጉ ነው ተባለ። በቀን እስከ 18 ሰዓት ያለ እረፍት እንዲሰሩ ይገደዳሉ የተባሉት እኝህ ወጣቶች ለመሄድ ከ1 ሺህ እስከ 4 ሺህ 500 ብር መክፈል እንደሚጠበቅባቸው ተነግሯል። የተሻለ ክፍያ የሚያስገኝ የስራ እድል አለ በሚል በደላሎችና በበይነ-መረብ (ኦን ላይን) በሚለቀቁ ሀሰተኛ ማስታወቂያዎች ተታልለው ከሀገር ከወጡ በኋላ በበይነ-መረብ በሚካሄዱ የተለያዩ የማጭበርበር ስራዎች ላይ እንዲሰማሩ ይገደዳሉ። በህገ-ወጥ መንገድ ከሀገር ወጥተው የተለያየ ጉዳት ደርሶባቸው የተመለሱትን በማገዝና ድጋፍ በማድረግ ላይ ትኩረቱን ያደረገው "ንጋት ግሎባል" የተሰኘው ድርጅት ባጠናው ጥናት፤ ተታ
Jul 312 min read
የባህር ትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 157.2 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ ገቢ ማግኘቱን ተናገረ ።
ሐምሌ 23 2018 የባህር ትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 157.2 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ ገቢ ማግኘቱን ተናገረ ። ከታክስ በፊት የተገኘው ትርፍም 28.2 ቢሊየን ብር መሆኑ ተነግሯል። በመካከለኛው ምስራቅ እና በቀይ ባህር ዙሪያ ያለው ጦርነትና ውጥረት ለስራው ፈተና እንደነበር፣ የነዳጅ እጥረትም እንደልብ ለመንቀሳቀስ መቸገርን ጨምሮ የተጠናቀቀው በጀት ዓመት ፈተና እንደነበሩ አስረድቷል። የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢንጂነር አብዱልበር ሸምሱ የተቋሙን የ2018 በጀት ዓመት አፈፃፀም እና የ2019 በጀት ዓመት እቅድ በተመለከተ ዛሬ ከሰዓት ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል። ዋና ስራ አስፈፃሚው ዓመቱ ለዘርፉ ፈታኝና ከባድ ጊዜ ቢሆንም በብዙ መለኪያዎች ግን የተሻለ ሊባል የሚችል ስራ የተሰራበት እንደነበር ጠቁመዋ
Jul 312 min read
"አሁን ያለው የፌደራሊዝም ስርዓት የተወሰነ ማሻሻያ ተደርጎበት ይቀጥል" የሚለው ሀሳብ በአብዛኞቹ ተመካካሪዎች መነሳቱን ያነጋገርናቸው የአገራዊ ምክክር ጉባዔተኞች ተናገሩ።
ሐምሌ 24 2018 "አሁን ያለው የፌደራሊዝም ስርዓት የተወሰነ ማሻሻያ ተደርጎበት ይቀጥል" የሚለው ሀሳብ በአብዛኞቹ ተመካካሪዎች መነሳቱን ያነጋገርናቸው የአገራዊ ምክክር ጉባዔተኞች ተናገሩ። 16ኛ ቀኑን ትናንት ሐምሌ 23 ቀን 2018 ዓ.ም የያዘው የምክክር ጉባዔ፣ በጥቃቅን እና ንዑሳን ቡድኖች የተነሱ ምክረ ሀሳቦች 250 አባላት ላሉት ስልታዊ ቡድን በቀረቡበት ወቅት ሳይካተቱ የቀሩ ተጨማሪ ምክረ ሀሳቦችን ሲቀበል ውሏል። ተጨማሪ ምክረ ሀሳቦችን ሲቀበሉ ካረፈዱ ስልታዊ ቡድኖች ውስጥ አንዱ የመንግስት አደረጃጀት እና የፖለቲካ ስርዓት አጀንዳ ላይ የሚወያየው ቡድን ሁለት ነው። በዚህ ቡድን ስር "የመንግስት ስርዓት ምን ይሁን?" ለሚለው ጥያቄ ሶስት አማራጮች መቅረባቸውን ተሳታፊዎች ነግረውናል። እነሱም አህዳዊ፣ ፌደራላዊ እና ኮንፌደራል የሚሉ መሆናቸውን
Jul 312 min read


የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኤርትራ ውስጥ የተያዘበትን ገንዘብ ለማስለቀቅ ወደ ክስ ቢያመራም በፖለቲካ ውሳኔ ምክንያት ገንዘቡ እንደተያዘበት መሆኑን ተናገረ፡፡
ሐምሌ 23 2018 የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኤርትራ ውስጥ የተያዘበትን ገንዘብ ለማስለቀቅ ወደ ክስ ቢያመራም በፖለቲካ ውሳኔ ምክንያት ገንዘቡ እንደተያዘበት መሆኑን ተናገረ፡፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለአለም አቀፍ ተጓዦች በአብዛኛው የበረራ ትኬት የሚሸጠው በየሃገሩ ገንዘብ እንደሆነና ሃገራት ሲፈቅዱ ብቻ ትኬቶችን በዶላር እንደሚሸጥ ተናግሯል፡፡ ከሽያጩ በኋላ ትኬት የተሸጠለት ሃገር ገንዘቡን በዶላር ወይም በዩሮ እንዲቀይንልን እንጠይቃለን፤ አብዛኞቹ ይቀይራሉ፤ አንዳንዶች የውጭ ምንዛሪ የለንም በሚል ለረጅም ጊዜ ሳይቀይሩንን ይቆያሉ ያሉት የአየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው፤ በኤርትራም የገጠመን ይኸው ነው፤በኤርትራ ገንዘብ የሸጥነውን የትኬት ገንዘብ ወደ ዶላር ቀይረን ማውጣት ሳንችል የኢትዮጵያ ኤርትራ ውጥረት ውስጥ ገባ፤ ጉዳ
Jul 302 min read
የሐምሌ 23 2018 የውጪ ሀገር ወሬዎች
#ግብፅ በግብፅ የሜዴትራኒያን የባህር ዳርቻ የነበረ የአሜሪካ የጋዝ ማጠራቀሚያ መርከብ በድሮን ተመታ ተባለ፡፡ ሁለት የደህንነት ምንጮች መርከቡ በድሮን እንደተመታ አረጋግጠውልኛል ሲል ሬውተርስ ፅፏል፡፡ መርከቡ በድሮን እንደተመታ በእሳት መያያዙ ታውቋል፡፡ ቃጠሎው ወደ ሌላ መርከብም ተጋብቶ ነበር ተብሏል፡፡ ኋላ ግን ቃጠሎው በቁጥጥር ስር መዋሉ ተጠቅሷል፡፡ በእሳት ተያይዘው የነበሩት መርከቦች ባህረኞች አንዳችም ጉዳት ሳይገጥማቸው እንዲወጡ ተደርጓል ተብሏል፡፡ ለጥቃቱ ሀላፊው እኔ ነኝ ያለ ወገን እንደሌለ መረጃው አስታውሷል፡፡ #ኢራቅ በኢራቅ ካታኢብ ሔዝቦላህ የተሰኘው ታጣቂ ቡድን መንግስት የአገሪቱን ሉአላዊነት ሊያስከብር ይገባል አለ፡፡ ቡድኑ ለመንግስት ያቀረበው ጥያቄ በማስጠንቀቂያ ጭምር የታጀበ እንደሆነ አልጀዚራ ፅፏል፡፡ የቡድኑ ማስጠንቀቂያ የተ
Jul 302 min read
የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን ማሳደግ፣አፍሪካዊያን የጋራ መጪ እድላቸውን እንዲቀርፁ ማገዝ ያስፈልጋል ተባለ።
ሐምሌ 23 2018 የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን ማሳደግ፣አፍሪካዊያን የጋራ መጪ እድላቸውን እንዲቀርፁ ማገዝ ያስፈልጋል ተባለ። የአፍሪካ ሀገሮች እርስ በእርስ፣በአፍሪካና በሩሲያ እንዲሁም አፍሪካ ከተቀረው ዓለም ጋር ያላትን የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ማሳደግን ዓለማው ያደረገ ዓለም አቀፍ ጉባኤ በተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ የኢኮኖሚ ኮሚሽን መሰብሰቢያ አዳራሽ መካሄድ ጀምሯል። ይህ "ወርልድ ፐብሊክ ሰሚት" በሚል የሚጠራው የፓን አፍሪካን ጉባኤ በአፍሪካ ምድር ሲካሄድ የመጀመሪያው ነው ተብሏል። ከፍተኛ የወጣት ቁጥር፣የተፈጥሮ ሀብት፣ባህል እና ቅርስ ያላት አፍሪካ የአህጉሩ ብቻ ሳይሆን የዓለምን መንገድም የመወሰን አቅም ያላት ነች ተብሏል። ሩሲያም የአፍሪካን ሀገሮች እርስ በእርስ፣ አፍሪካን ከሩሲያና ከተቀረው ዓለም ጋር በህዝብ ለህዝብ ግንኙነት የማስተሳሰ
Jul 302 min read


የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በ "ሁሉ ስፖርት" የኦንላይን ውርርድ ድርጅት ላይ ተላልፎ የነበረውን የንግድ ፈቃድ ስረዛ ውሳኔ በሙሉ ድምፅ ሻረ።
ሐምሌ 23 2018 የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በ "ሁሉ ስፖርት" የኦንላይን ውርርድ ድርጅት ላይ ተላልፎ የነበረውን የንግድ ፈቃድ ስረዛ ውሳኔ በሙሉ ድምፅ ሻረ። ሆኖም የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት በውሳኔው ላይ ይግባኝ ማቅረቡን ተከትሎ፣ ከ14/11/2018 ዓ.ም. ጀምሮ ለ15 ቀናት የሚቆይ ጊዜያዊ የእግድ ትዕዛዝ ተሰጥቷል። የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ከህዳር 25 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ የ22 የስፖርት ውርርድ ድርጅቶችን የሥራ ፈቃድ ማገዱ ይታወሳል። ፈቃዱ ከተሰረዘባቸው ድርጅቶች አንዱ የሆነው "ሁሉ ስፖርት"፣ ውሳኔው የመሰማት መብቱን የጣሰና ሕገ-ወጥ ነው በማለት በሎተሪ አገልግሎቱና በገቢዎች ሚኒስቴር ላይ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክስ መስርቶ ነበር። የተጠቀሱት የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በበኩላቸው ድርጅቶቹ በከፍተኛ የግብር ስወራ፣ ሕገ-ወጥ
Jul 302 min read


በሕገ-ወጥ መንገድ ሰዎችን ወደ ስደት ልከዋል፣ ከተጎጂዎችም ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ተቀብለዋል ተብለው በተጠረጠሩ 16 ሰዎች ላይ ብይን ለመስጠት ፍርድ ቤት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
ሐምሌ 22 2018 በሕገ-ወጥ መንገድ ሰዎችን ወደ ስደት ልከዋል፣ ከተጎጂዎችም ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ተቀብለዋል ተብለው በተጠረጠሩ 16 ሰዎች ላይ ብይን ለመስጠት ፍርድ ቤት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። በአደገኛ ሕገወጥ ሰው አዘዋዋሪነት ተጠርጥረው በፖሊስ ተይዘው ክስ የተመሠረተባቸው 16 ተከሳሾች ዛሬ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ቀርበው ክሳቸው ተሰምቷል። ተጠርጣሪዎቹ በሰው ልጅ ለመነገድ በማሰብ የወንጀል ቡድን በማደራጀት፣ የሕገወጥ ሰዎች ዝውውር መረብ በመዘርጋት እንዲሁም ተጎጂዎቹ በየመን በኩል ወደ ሳዑዲ ዓረቢያ ገብተው የተሻለ ኑሮ እንደሚኖሩ ሐሰተኛ ተስፋ በመስጠትና በማሳመን ከተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች በመመልመል ሲልኩ እንደነበር በአቃቤ ሕግ የክስ መዝገብ ተጠቅሷል። በሕገወጥ መንገድ የተወሰዱ ተጎጂዎች የኢትዮጵያን ድንበ
Jul 292 min read
አስተማማኝ የጤና ሥርዓት ለመገንባት በሀገር ውስጥ የመድኃኒት ምርትን ማጠናከርና የፀረ-ተሕዋስያን መድኃኒቶችን አጠቃቀም ቁጥጥር ማጠናከር እንዲሁም የፋርማሲ ዘርፍ ጥናትና ምርምር ማሳደግ ያስፈልጋል ተባለ።
ሐምሌ 22 2018 አስተማማኝ የጤና ሥርዓት ለመገንባት በሀገር ውስጥ የመድኃኒት ምርትን ማጠናከርና የፀረ-ተሕዋስያን መድኃኒቶችን አጠቃቀም ቁጥጥር ማጠናከር እንዲሁም የፋርማሲ ዘርፍ ጥናትና ምርምር ማሳደግ ያስፈልጋል ተባለ። አስተማማኝ የጤና ሥርዓት ለመገንባት ኢትዮጵያ በመድኃኒት ምርት ራሷን መቻል እንዳለባት፣ በተጨማሪም በዓለም አቀፍ ደረጃ እየተባባሰ በመጣው የፀረ-ተሕዋስያን መድኃኒቶችን የመቋቋም ችግር ለመቀነስ የፋርማሲ ባለሙያዎችና የመድኃኒት ኢንዱስትሪው ወሳኝ ሚና እንዳላቸው ተነግሯል። ዓመታዊው የኢትዮጵያ ፋርማሲ ማህበር የሳይንስ ኮንፈረንስ እና ጠቅላላ ጉባኤ ዛሬ በኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ዋና መስሪያ ቤት ተጀምሯል። በዚህ ዓመት የተመረጠው የኮንፈረንሱ መሪ ቃል በዓለም አቀፍ የጤና ዘርፍ አንዱ ከፍተኛ ስጋት ተብሎ በሚታየው የፀ
Jul 292 min read


ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ፣ በፋሽስት ጣሊያን ሰማዕትነት የተቀበሉት በ1928 ዓ.ም በዛሬው ቀን ነበር፡፡
#ታሪክን_የኋሊት ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ፣ በፋሽስት ጣሊያን ሰማዕትነት የተቀበሉት በ1928 ዓ.ም በዛሬው ቀን ነበር፡፡ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ፣ መስቀልና ወንጌል ብቻ ይዘው የወራሪውን የኢጣሊያ ፋሽስት ፣ ነውሩንና ግፉን ፊት ለፊት ታግለው፣ ለሃገራቸውና ለሃይማኖታቸው ሕይወታቸውን አሳልፈው የሰጡ ፣ በጳጳስ ናቸው፡፡ አባ ኃይለማርያም፣ ከመጀመሪያዎቹ አራት ኢትዮጵያውያን ጳጳሳት አንዱ ሆነው ሲመረጡ ስማቸው ብፅዕ አቡነ ጴጥሮስ ሆነ፡፡ በቅኔ ፣ በዜማ ፣ በመፃህፍት ትርጓሜ የተመረቁት አቡነ ጴጥሮስ፣ በ1921 ዓ.ም ጳጳስነት ከተሾሙ በኋላ፣ የኢጣሊያ ወረራ እስከገፋበት ድረስ ወሎንና ከሸዋ መንዝን እና ኤፍራታን፣ ግሺንና አንጾኪያን ሃገረ ስብከታቸው አድርገው ቆይተዋል፡፡ ከዚያ በፊትም በወላይታና በዝዋይ በመምህርነት አገልግለዋል፡፡ በማይጨው ዘመቻ ጊዜ ፣ ከን
Jul 292 min read
ኢትዮጵያ የምታመነጨው የኤሌክትሪክ ሀይል መጠን 9 ሺህ 730 ሜጋ ዋት ደርሷል፡፡
ሐምሌ 22 2018 ኢትዮጵያ የምታመነጨው የኤሌክትሪክ ሀይል መጠን 9 ሺህ 730 ሜጋ ዋት ደርሷል፡፡ ከዚህ ውስጥ ከውሃ የሚመነጨው ድርሻው ከ95 እስከ 96 በመቶ ነው ተብሏል፡፡ ኢትዮጵያ ከውሃ በተጨማሪ እንደ ነፋስ ፣ ፀሀይ እንፋሎት ካሉና ሌሎች አማራጮች ተጨማሪ የኤሌክትሪክ ሀይል በማመንጨት ስብጥሩን የማስፋት ውጥን ይዛለች፡፡ ባለፉት አመታትም በርካታ ከነፋስና ከፀሐይ ሀይል የሚያመነጩ ፕሮጀክቶች ተመርቀዋል፡፡ በግንባታ ሂደት ላይ ያሉም ብዙ ናቸው፡፡ ግን አሁንም ከውሃ የሚመነጨው ሀይል ድርሻው ከፍተኛ መሆኑ ይነገራል፡፡ በውሃ ላይ ብቻ ጥገኛ የሆነ የሀይል ማመንጫ መንገድን መከተል በዚህ ዘመን አስተማማኝ አይደለም ይላሉ በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጂ ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታው ኢንጅነር ሱልጣን ወሊ። በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት በውሃ የሀይል
Jul 291 min read


የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዓመቱ 9.1 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቱን ተናገረ።
ሐምሌ 22 2018 የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዓመቱ 9.1 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቱን ተናገረ። የሆርሙዝ ሰርጥ መዘጋት ለስራው እንቅፋት እንደነበርና የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት በዚህ ከቀጠለ ትርፋማነቱን ሊቀንሰው እንደሚችል ጠቅሷል። አየር መንገዱ የ2018 ዓመት አፈፃፀሙን አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጠው መግለጫ በዓመቱ 9.1 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ማግኘቱንና ገቢው ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲመሳከር የ20 በመቶ እድገት እንዳለው ተናግሯል። ሆኖም ግን በመካከለኛው ምስራቅ በነበረው ጦርነት ምክንያት የበረራዎች እቀባ ስለነበር ተጓዦችንም ሆነ ጭነት ማጓጓዝ ባለመቻሉ የእቅዱን 96 ከመቶ እንዲፈፅም ምክንያት እንደሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው አስረድተዋል። በጦርነቱ ምክንያት የነዳጅ ዋጋ በመጨመሩ
Jul 291 min read
የሐምሌ 22 2018 የውጪ ሀገር ወሬዎች
#አሜሪካ አሜሪካ እና ሳውዲ አረቢያ ኢራቅ ውስጥ በአፍቃሪ ኢራን ታጣቂዎች ይዞታ ላይ ድብደባ ፈፀሙ፡፡ ሰሞኑን ሳውዲ አረቢያ በኢራቅ የሚገኙ አፍቃሪ ኢራን ታጣቂዎች በድሮን ጥቃት አድርሰውብኛል ስትል እንደነበር አልጀዚራ አስታውሷል፡፡ ሳውዲ ጥቃቱን ከማውገዝ በተጨማሪ መበቀሌ አይቀርም በሚል ዝታ ነበር፡፡ በኢራቆቹ አፍቃሪ ኢራን ታጣቂዎች ላይ አሜሪካ እና ሳውዲ በፈፀሙት ጥምር ድብደባ ከ20 የማያንሱት መገደላቸው ተሰምቷል፡፡ በሌላ መረጃ አብዮታዊ ዘብ የተሰኘው የኢራን የጦር ክፍል በዮርዳኖስ በሚገኝ የአሜሪካ የጦር ተቋም ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ሰንዝሬያለሁ ማለቱ ተሰምቷል፡፡ የዮርዳኖስ ጦር አምስት ሚሳየሎችን መትቼ አሰናክያለሁ ማለቱ ተሰምቷል፡፡ ስለ ዮርዳኖሱ ጥቃት ከአሜሪካ በኩል የተሰጠ አስተያየት የለም፡፡ የወደፊቱን የሆርሙዝ የባህር መተላለፊያ ወሽመ
Jul 292 min read
ፕሮግራሞች
bottom of page
_edited.jpg)
