ኢትዮጵያ የምታመነጨው የኤሌክትሪክ ሀይል መጠን 9 ሺህ 730 ሜጋ ዋት ደርሷል፡፡
- 53 minutes ago
- 1 min read
ሐምሌ 22 2018
ኢትዮጵያ የምታመነጨው የኤሌክትሪክ ሀይል መጠን 9 ሺህ 730 ሜጋ ዋት ደርሷል፡፡
ከዚህ ውስጥ ከውሃ የሚመነጨው ድርሻው ከ95 እስከ 96 በመቶ ነው ተብሏል፡፡
ኢትዮጵያ ከውሃ በተጨማሪ እንደ ነፋስ ፣ ፀሀይ እንፋሎት ካሉና ሌሎች አማራጮች ተጨማሪ የኤሌክትሪክ ሀይል በማመንጨት ስብጥሩን የማስፋት ውጥን ይዛለች፡፡
ባለፉት አመታትም በርካታ ከነፋስና ከፀሐይ ሀይል የሚያመነጩ ፕሮጀክቶች ተመርቀዋል፡፡
በግንባታ ሂደት ላይ ያሉም ብዙ ናቸው፡፡ ግን አሁንም ከውሃ የሚመነጨው ሀይል ድርሻው ከፍተኛ መሆኑ ይነገራል፡፡
በውሃ ላይ ብቻ ጥገኛ የሆነ የሀይል ማመንጫ መንገድን መከተል በዚህ ዘመን አስተማማኝ አይደለም ይላሉ በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጂ ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታው ኢንጅነር ሱልጣን ወሊ።
በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት በውሃ የሀይል ማመንጫ ላይ መገደብ አስተማማኝ አይሆንም ብለዋል።
ኢትዮጵያ አማራጭ የሀይል ምንጭ ብላ ከያዘችው መንገድ አንደኛው የጂኦተርማል /የእንፋሎት/ የሀይል ማመንጫ ነው፡፡
ኢትዮጵያ ከእንፋሎት /ጂኦተርማል/ እስከ 10 ሺህ ሜጋ ዋት ሀይል የማመንጨት አቅም እንዳላት በጥናት ተረጋግጧል፡፡
የስምጥ ሸለቆ አካባቢ ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ሀይልን ከዚሁ ከእንፋሎት የማመንጨት አቅም እንዳላት ሚኒስትር ዲኤታው ነግረውናል፡፡
ባለፉት አመታት በዚሁ ዘርፍ ይሰራሉ ስለተባሉ በርካታ ፕሮጀክቶች ሰምተናል፡፡
በመንግስት ይሰራል የተባለው አሉቶ ላንጋኖ እና ቱሉ ሞዬ፣ከርቤቲ ፕሮጀክቶች ደጋግመን ሰምተናል።
ግን ግንባታው ተጠናቆ ሀይል ማመንጨት የጀመረ እስካሁን የለም። ሚኒስትር ዲኤታው ኢንጂነር ሱልጣንን የእንፋሎት /ጂኦተርማል/ የሀይል ማመንጫ ፕሮጀክት ነገር አሁን በምን ደረጃ ላይ ነው ብለን ጠይቀናቸዋል።
ቴክኖሎጂው አዲስ መሆኑና ሌሎቹ ላይ ትኩረት በማድረጋችን ዘግይቷል ያሉት ሚኒስትር ዲኤታው በመንግስት የሚሰራው የማመንጨት አቅሙን አሳድጎ እንዲገነባ ለማድረግ መታሰቡን ነግረውናል።
ከሌሎቹ ፕሮጀክቶች ጋር በተገናኘም የተወሰነ የተፈጠረ ችግር ነበር ተፈቶ ወደ ስራ ይገባሉ ብለዋል።
ከደረቅ ቆሻሻ 25 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ሀይል እንደሚመነጭም ከተቋሙ ሪፖርት የተመለከን ሲሆን፤በቅርቡ ኢትዮጵያ ወደ ኒውክለር የሀይል ማመንጫ መግባቷም ይፋ መደረጉ ይታወሳል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ...
ቴዎድሮስ ወርቁ
_edited.jpg)



Comments