top of page


ጥቅምት 20 2018 የዳሸን ሱፐር አፕ ደንበኞች ቁጥር ከ1 ሚሊዮን በላይ መድረሱን ባንኩ ተናገረ።
የዳሸን ሱፐር አፕ አንድ ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በሚሊዮን የሚቆጠር ደንበኛና በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ዕለታዊ የገንዘብ ዝውውር እየተፈፀመበት ይገኛል ሲለሰ ባንኩ ከላከልን መግለጫ ላይ ተመልክተናል፡፡ ይህንን በዛሬው ዕለት በዳሸን ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላደረጉ አካላትና የሥራ ክፍሎች የእውቅና አሰጣጥና የፓናል ውይይት መርሃግብር መዘጋጀቱም ተጠቅሷል፡፡ የዳሸን ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ አስፋው ዓለሙ፣ ዳሸን ሱፐር አፕ ይፋ በተደረገ አንድ ዓመት ውስጥ አንድ ሚሊዮን ተጠቃሚዎች ይኖሩታል የሚለውን ዕቅድ በዘጠኝ ወራት ብቻ ማሳካት መቻሉን ተናግረዋል። የዳሸን ሱፐር አፕን ላበለፀገው የኤግላይን ሲስተም ቴክኖሎጂ ለባንኩና ለአገር ለሚያደርገው አስተዋፅኦ አቶ አስፉው ምስጋና አቅርበዋል፡፡ ዳሸን ባንክ ‘’ሱፐር አፕ’’ ባንኩ
16 minutes ago1 min read


ጥቅምት 19 2018 - ኢንፊኒክስ ኢትዮጵያ ከተግባረ ዕድ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ፡፡
ኢንፊኒክስ ኢትዮጵያ የአዲስ አበባ ተግባረ ዕድ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ተማሪዎቸን የተግባር ላይ ልምምድ ለመስጠት አንዲሁም መምህራኑን ለማሰልጠን የመግባቢያ ስምምነት ከኮሌጁ ጋር ተፈራረመ፡፡ ስምምነቱን የኮሌጁ ዲን ተስፋዬ አድማሱ(ዶ/ር ) እና ትራንሽን ማኑፋክቸሪንግ በመወከል Guo ZhongLei ተፈራርመውታል፡፡ በስምምነቱ መሰረት ኢንፊኒክስ ክለብ በተግባረ ዕድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ይቋቁማል፣ ይህም ለተማሪዎች ለተግባራዊ የኢንዱስትሪ ልምድ፣ ለክህሎት ግንባታ እና ለፈጠራ ፍለጋ እድሎችን ይሰጣል ተብሎለታል። በዚህ ትብብር ተማሪዎች በግል እና ሙያዊ እድገት ላይ ያተኮሩ ስለጠናዎቸን እና የማማከር ፕሮግራሞች ውስጥ ይሳተፉሉ፣ በኢንፊኒክስ እና ትራንሽን ባለሙያዎች የፈጠራ ተነሳሽ ትምህርት ይሳተፉሉ። ከዚህ በተጨማሪም የኮሌጁ ተማሪዎች በትራንሽን እና ኢንፊ
1 day ago1 min read


ጥቅምት 14 2018 - የባንክ ደንበኞች ከሚመለከተው ግብር ሰብሳቢ ከሰጣቸው ሂሳብ ውጪ በግላቸው ሂሳብ ግብይቶች እንደሚገላበጥ ተሰማ
ቁጥራቸው ቀላል የማይባል የባንክ ደንበኞች ከሚመለከተው ግብር ሰብሳቢ ከሰጣቸው ሂሳብ ውጪ በግላቸው ሂሳብ የተለያዩ ግብይቶች እንደሚገላበጥ ተሰማ። ይህን ያረጋገጠው የኢትዮዽያ ብሔራዊ ባንክ ነው። ባንኩ ባደረግሁት ምርመራ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ግለሰብ ነጋዴዎች በዚህ እንቅስቃሴ እንዳሉ አውቄያለሁ ብሏል። #የኢትዮጵያ_ብሔራዊ_ባንክ የተለያዩ የንግድ ድርጅቶችና ግለሰብ ነጋዴዎች የግብር ሰብሳቢ ተቋም ካስመዘገቡት የባንክ ሒሳቦች ውጪ ወደ ግል እና ሶስተኛ ወገን የገንዘብ እንቅስቃሴዎች እየፈፀሙ መሆናቸውን አረጋግጫለሁ ብሏል። ይህ አሰራርም ከግብር ሰብሳቢ ባለስልጣናት ቁጥጥር እና ክትትል ለመሸሽ የሚደረግ ተግባር እንደሆነ ባንኩ አስረድቷል። በተጨማሪም በዚህ መልኩ የሚፈፀሙ የፋይናንስ ግብይቶች እና የገንዘብ እንቅስቃሴዎች የወንጀል ፍሬ ሊሆኑ እንደሚችሉ ባ
6 days ago1 min read


ጥቅምት 14 2018 - ሕብረት ባንክ ከሚሰጠው ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት የሰበሰበውን 35 ሚሊየን ብር ለበጎ አድራጎት ድርጅቶች አበረከተ
35 ሚሊዮን ብሩ የተሰጠው ለ10 የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ነው፡፡ ድጋፍ የተርገላቸው አስሩ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች የተመረጡት በሸሪዓው መርህ መሰረት የሚሰሩ መሆናቸው ተመዝኖ፣ ከሚደርሱት የሕብረተሰብ ቁጥር እና የሚሰጠውን ድጋፍ ለምን ተግባር እንደሚያውሉትም ጭምር ታይቶ ነው ተብሏል። ድጋፉ ከተደረገላቸው ድርጅቶች መካከል፤ እማሙ ማሊክ ትምህርት ቤት፣ ወንድም ካሊድ ፋውንዴሽ፣ ባቡል ካኸር፣ ሜቄዶኒያ፣ ቢላሉ ሀበሺ እንዲሁም የኢትዮጵያ ሙስሊም የጤና ባለሞያዎች ማህበር ይገኙበታል። ሕብረት ባንክ የሸሪዓውን መርህ በተከተለ መልኩ ከወለድ ነፃ የባንክ እገልግሎት መስጠት ከጀመረ 10 ዓመታት እንዳለፈው አስታውሷል። በአሁኑ ሰዓትም ሕብረት ባንክ 23 ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ብቻ የሚሰጡ ቅርንጫፎች ከፍቼ እየሰራሁ ነው ሲል ጠቅሷል። ባንኩ ሸሪዓው
6 days ago1 min read


ጥቅምት 8 2018 "ልዩ ባስ" የሚል መጠርያ ያለው ለሀገር አቋራጭ መንገደኞች ዲጂታል የክፍያ ቴክኖሎጂ ይፋ ተደረገ
አዲስ ፔይ ፋይናንሻል ቴክኖሎጂ እና እንግዳ ትራቭል ቴክኖሎጂ በጋራ "ልዩ ባስ" የሚል መጠርያ ያለው ለሀገር አቋራጭ መንገደኞች ዲጂታል የክፍያ ቴክኖሎጂ ዛሬ ማስጀመራቸውን ተናገሩ። ይህ ቴክኖሎጂ ደንበኞች ወይም ተጓዦች ባሉበት ቦታ ሆነው ወደየሚፈልጉበት አካባቢ ለመጓዝ "የልዩ ባስ" የሞባይል መተግበሪያ በመጠቀም ቲኬታቸውን በኦንላይን መቁረጥ ይችላሉ ተብሏል። የእንግዳ ትራቭል ቴክኖሎጂ መስራች እና ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ባንተአብ አብይ እንደተናገሩት ቴክኖሎጂውን ስራ ላይ ለማዋል አራት ዓመት እንደፈጀ እና አገልግሎቱን ከደንበኞች በተጨማሪ የግል ባስ ባለንብረቶች ስራቸውን ለማቀላጣፍ መጠቀም የሚችሉበት ነው ብለዋል። ይህንን አገልግሎት ደንበኞች ቅንጡ ስልካቸውን በመጠቀም ወደቲኬት መቁረጫ ቦታ ሳይሄዱ ባሉበት ሆነው መቁረጥ እንደሚችሉም ሰምተናል።
Oct 181 min read


ጥቅምት 5 2018የመስከረም ወር የዋጋ ግሽበት 13.2 በመቶ ሆኖ ተመዘገበ፡፡
ያለፈው ወር ሀገር አቀፍ የዋጋ ግሽበት መጠን 13.2 በመቶ ሆኖ መመዝገቡን የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ተናግሯል። ከአጠቃላይ የዋጋ ግሽበት ውስጥ የምግብ ነክ ዕቃዎች (Food Items) የዋጋ ግሽበት 12.1 በመቶ ድርሻ ሲይዝ፣ ምግብ ነክ ያልሆኑ ዕቃዎች (Non-food Items) የዋጋ ግሽበት ደግሞ 14.8 በመቶ ሆኖ ተመዝግቧል። ይህ አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት ካለፈው ነሐሴ ወር ጋር ሲነፃፀር መጠነኛ ቅናሽ አሳይቷል፡፡ በነሐሴ ወር አጠቃላይ የግሽበት ምጣኔው 13.6 በመቶ ነበር፡፡ የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… 👇👇👇 🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/ 🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478 🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1 📘Faceb
Oct 151 min read


ጥቅምት 1 2018 ዘመን ባንክ በተጠናቀቀው 2017 በጀት ዓመት ያገኘው ትርፍ ከቀዳሚው ዓመት ጋር ሲነፃፀር ከእጥፍ በላይ መሆኑን ተናገረ።
የአንድ አክሲዮን ትርፍ ወደ 68.3 በመቶ ማደጉንም አስረድቷል። ዘመን ባንክ በ2017 በጀት ዓመት 14.4 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን በዛሬው እለት ዓመታዊ የባለአክሲዮኖች ጉባኤ ላይ ባወጣው ሪፖርት ተናግሯል።...
Oct 111 min read


መስከረም 29 2018 - ኢትዮጵያ ዛሬ የአፍሪካ ነፃ ንግድ ቀጣና ስምምነትን በይፋ ትቀላቀላለች።
ዛሬ ከሰዓት በኋላ የተለያዩ ምርቶች በየብስ እና በአየር በይፋዊ ስነ ስርዓት ወደ ተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት እንደሚሸኙ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ነግሮናል የንግድና...
Oct 91 min read


መስከረም 28 2018 - ግጭት ለኢንቨስትመንቱ እንቅፋት እንዲሆኑ የአሜሪካ መንግስት መናገሩ ይታወሳል
ኢትዮጵያ ሰፊ የሰው ሃይል፣ ግዙፍ አየር መንገድ እና ሌሎች ለ #ኢንቨስትመንት ምቹ የሚያደርጉ ሁኔታዎች ያሉባት ሀገር ብትሆንም ተለዋዋጭ ህግ፣ ግጭት እና የመሳሰሉት ግን ለኢንቨስትመንቱ እንቅፋት እንደሆኑ የአሜሪካ...
Oct 81 min read


መስከረም 27 2018 - ኮምፓስ ፕሮፐርቲስ እና ጎህ ቤቶች ባንክ በጋራ ሆነው በአይነቱ አዲስ ነው ያሉትን የቤት ግንባታ ፕሮጀክት ዛሬ ይፋ አድርገዋል።
ኮምፓስ ፕሮፐርቲስ እና ጎህ ቤቶች ባንክ በጋራ ሆነው በአይነቱ አዲስ ነው ያሉትን የቤት ግንባታ ፕሮጀክት ዛሬ ይፋ አድርገዋል። አሰራሩም በቅድሚያ አንድ ቤት ፈላጊ ወደ ኮምፓስ ፕሮፐርቲስ በመሄድ የሚፈልውን ...
Oct 71 min read


መስከረም 27 2018 - ኢትዮጵያ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ስምምነትን ማጠናቀቋን ተከትሎ በሸቀጦች ንግድ ዘርፍ መስከረም 29/2018 በይፋ ትጀምራለች ተባለ
ኢትዮጵያ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ስምምነትን ማጠናቀቋን ተከትሎ በሸቀጦች ንግድ ዘርፍ መስከረም 29/2018 በይፋ ትጀምራለች ተባለ፡፡ ይህንን ያሉት የንግድ ትስስርና ወጪ ንግድ ፕሮሞሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታዋ...
Oct 71 min read


መስከረም 23 2018 - በኢትዮጵያ ይሰራሉ ከተባሉ ግዙፍ ፕሮጀክቶች ውስጥ የብር ማተሚያም ይገኝበታል ተባለ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ትናንት በሶማሌ ክልል ስለሚሰሩ ፕሮጀክቶች ማብራሪያን ሲያቀርቡ ከግዙፍ የፕሮጀክት ስራዎች ውስጥ #የብር_ማተሚያ እንደሚገኝበት ተናግረዋል። የወርቅ ማጣሪያ ፕሮጀክትም ስራ መጀመሩን...
Oct 31 min read


መስከረም 22 2018 - ከአውሮፕላን ነዳጅ ውጭ ያሉ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል ተብሏል።
ከአውሮፕላን ነዳጅ ውጭ ያሉ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል ተብሏል። ይህንን ያለው የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ነው። የቤንዚን፣ የነጭ ናፍጣ፣ የኬሮሲን፣ የቀላል ጥቁር ናፍጣና የከባድ...
Oct 21 min read


መስከረም 13 2018 - ወጣቶች የራሳቸውን ስራ እንዳይፈጥሩ ፈተና የሚሆንባቸው ምንድነው?
መንግስት በየጊዜው ከት/ት ተቋማት ለሚመረቁ ሁሉ ስራ መስጠት ስለማይቻል ወጣቱ የራሱን የስራ እድል ይፍጠር ሲል ይሰማል፡፡ መንግስት ወጣቶችን በሚመለከት ከተቀጣሪነት ወደ ስራ ፈጣሪነት ተሸጋገሩ ቢልም በርካታ ወጣቶች...
Sep 232 min read


መስከረም 13 2018 - የተገኙ 10 የሂሳብ ባለሙያዎችና ኦዲተሮች የሙያ ፈቃድ እንዲሰረዝ ጥያቄ ቀረበ።
የመንግስትን ጥቅም ለማሳጣት የሚያስችል ግድፈት ፈፅመው የተገኙ 10 የሂሳብ ባለሙያዎችና ኦዲተሮች የሙያ ፈቃድ እንዲሰረዝ ጥያቄ ቀረበ። ይህንን ያለው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ነው። ቢሮው የ2017...
Sep 231 min read


መስከረም 8 2018 - የስራ ክህሎት እና የፈጠራ ሀሳብ ያላቸው ነዋሪዎችን ለማሰልጠን ከ4,000 በላይ አሰልጣኞች ተሰማርተዋል ተባለ
በየመንደሩ ቀጭቃጭ፣ ሸክላ ሰሪ እና ሌላም ሌላ እየተባሉ ቦታ የማይሰጣቸውና መሰል የተለያየ የስራ ክህሎት እና የፈጠራ ሀሳብ ያላቸው ነዋሪዎችን ለማሰልጠን ከ4,000 በላይ አሰልጣኞች ተሰማርተዋል ተባለ፡፡ ይህም ሀገር...
Sep 181 min read


መስከረም 7 2018 - በኢትዮጵያ አሁንም በገበያው ውስጥ ያሉ ግን ግብራቸውን በአግባቡ የማይከፍሉ ነጋዴዎች ብዙ መሆናቸው ይነገራል
የገንዘብ ሚኒስቴር ባስጠናው ጥናት 63 በመቶው #ነጋዴ ዛሬም በየዓመቱ ግብሩን በአግባቡ አይከፍልም ተብሏል፡፡ ኮንትሮባንድ ሌላውም ችግር በገበያ በስፋት ይታያል፡፡ የተመሳቀለውን የገበያ ስርዓት ለማስተካከል በየጊዜው...
Sep 171 min read


መስከረም 7 2018 - ኢትዮጵያ የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነትን ለመተግበር ከስትራቴጂ ዝግጅት እስከ ታሪፍ ህትመት ያሉ ስራዎችን ጨርሳለች ተባለ።
በጣም ባጠረ ጊዜ ይፋዊ በሆነ ሥነ ሥርዓት የንግድ ስምምነቱን ተግባራዊ ማድረግ እንደምትጀምርም የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ተናግሯል። የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና ስምምነትን በመፈረም እና በፓርላማ በማፀደቅ...
Sep 171 min read


መስከረም 5 2018 - ኮርፖሬት ታክስ አለመሻሻሉ ምን ተፅእኖ ይኖረው ይሆን?
ኢትዮጵያ በቅርቡ በተሻሻለው የገቢ ግብር አዋጅ የኩባንያ የገቢ ግብር (Corporate tax) የመቀነስ ሀሳብ ቢቀርብም ለጊዜው ይህንን ለማድረግ ጊዜው አይፈቅድም ብላ ባለበት እንዲቀጥል ወስናለች፡፡ በሌላ በኩል...
Sep 151 min read


ጳጉሜ 3 2017 - ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የሞባይል ኢንተርኔት እያቀረበ ያለው ካወጣው ዋጋ ከእጥፍ በላይ እየቀነሰ ወይም እየከሰረ መሆኑንን ተናገረ
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የሞባይል ኢንተርኔት እያቀረበ ያለው ካወጣው ዋጋ ከእጥፍ በላይ እየቀነሰ ወይም እየከሰረ መሆኑንን ተናገረ፡፡ ኩባንያው ስራውን እያስፋፋ፣ አገልግሎቱን እያቀረበ ያለውም በባለ አክሲዮኖቼ ድጋፍ ነው...
Sep 81 min read


ነሀሴ 27 2017 - ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ለ 125,000 ወጣቶች የዲጂታል ስልጠና እድል ማመቻቸቱን ተናገረ፡፡
ዲጂታል ስልጠናው ቴክስታርት (Techstart) የሚል ስያሜ የተሰጠው ሲሆን ዛሬ ይፋ የተደረገ ነው፡፡ ስልጠናው በኢንተርኔት አማካይነት በኦንላይን የሚሰጥ ሲሆን በመጭዎቹ 3 ዓመታት ውስጥ የሚጠናቀቅ መሆኑን በላከልን...
Sep 21 min read
ፕሮግራሞች
bottom of page








