top of page


ኢትዮጵያ ባለፈው አመት ከካርበን ሽያጭ 4.8 ሚሊየን ዶላር ገቢ አገኘች፡፡
ሐምሌ 22 2018 ኢትዮጵያ ባለፈው አመት ከካርበን ሽያጭ 4.8 ሚሊየን ዶላር ገቢ አገኘች፡፡ በአራት ዓመታት ውስጥ ከ140 ሺህ ቶን በላይ የካርበን ጋዝ ልቀት መቀነሱ ተሰምቷል፡፡ ይህ ገቢ የተገኘውም ከ2013-2017 ዓ.ም በተተገበረ የታዳሽ ሀይል ፕሮጀክቶች መሆኑም ተነግሯል። ይህንን የነገሩን በፕላንና ልማት ሚኒስቴር የአየር ንብረት ለውጥ አማካሪና የካርበን ገበያ አስተባባሪ አቶ መንሱር ደሴ ናቸው። ኢትዮጵያ ላለፉት አራት አመታት በተገበረቻቸው የባዮጋዝና የፀሐይ ሃይል ፕሮጀክቶች ኢትዮጵያ ገቢ እንድታገኝበት ከማድረግ ባሻገር የሀይል አቅርቦት የማያገኘው ህብረተሰብም ተጠቃሚ እንዲሆን አስችሏል ብለዋል። ወደ አየር ሊለቀቅ የነበረውን የሙቀት አማቂ ጋዝ እንዲቀንስ ማድረጉም ሌላኛው ውጤት ነው ይላሉ። በባዮጋዝ እና በፀሐይ ሃይል ላይ የተሰሩ ፕሮጀክቶ
Jul 291 min read
«የኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር እንዴት ይሁን? የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ ከተሞች ባለቤትነትስ ለማን ይሰጥ? የክልሎች አወቃቀር እንዴት ይሁን እና የጸጥታ ተቋማት እንዴት ገለልተኛ ይሁኑ?» ለሚሉት ጥያቄዎች በአዲስ አበባ እየተካሄደ ባለው ምክክር ላይ የተሳተፉ ጉባኤተኞች የተለያዩ ምክረ ሃሳቦችን አስቀምጠዋል።
ሐምሌ 21 2018 «የኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር እንዴት ይሁን? የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ ከተሞች ባለቤትነትስ ለማን ይሰጥ? የክልሎች አወቃቀር እንዴት ይሁን እና የጸጥታ ተቋማት እንዴት ገለልተኛ ይሁኑ?» ለሚሉት ጥያቄዎች በአዲስ አበባ እየተካሄደ ባለው ምክክር ላይ የተሳተፉ ጉባኤተኞች የተለያዩ ምክረ ሃሳቦችን አስቀምጠዋል። የተቀመጡት ምክረ ሃሳቦች በጉባኤተኞች የጸደቁ ሳይሆኑ፣ በሂደት ላይ ባለው ምክክር በንዑሳን እና ጥቃቅን ቡድኖች ደረጃ ከተሳታፊዎች የቀረቡ አማራጭ ምክረ ሃሳቦች ናቸው። የኢትዮጵያን የዘመን አቆጣጠር በተመለከተ የተለያዩ አማራጮች ቀርበዋል። በኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር ውስጥ የሂጅራ ወይም የእስላማዊ የዘመን አቆጣጠር ይካተት፣ «ዓመተ ምህረት» የሚለው ይቅርና አሁን ያለው አቆጣጠር ይቀጥል፣ እንዲሁም ከእስልምናም ሆነ ከክርስት
Jul 292 min read


የንግድ ህጉን ተላልፈው ተገኝተዋል ያላቸውን ከ24 ሺህ 500 በላይ ነጋዴዎች መቅጣቱን የንግድ ቢሮ ተናገረ።
ሐምሌ 21 2018 የንግድ ህጉን ተላልፈው ተገኝተዋል ያላቸውን ከ24 ሺህ 500 በላይ ነጋዴዎች መቅጣቱን የንግድ ቢሮ ተናገረ። ቢሮው የ2018 ዓ.ም የእቅድ አፈፃፀሙን በገመገመበት ወቅት የቢሮ ሃላፊዋ ወ/ሮ ሃቢባ ሲራጅ ነጋዴዎቹን ለቅጣት ያበቃቸው ያለ ንግድ ፈቃድ መነገድ፣ ባልታደሰና በተሰረዘ ንግድ ፈቃድ መነገድ ጭምር መሆኑን ተናግረዋል። የንግድ ህጉን አክብሮ ያለመስራት በዚህ ዓመትም ችግር ሆኖ ቀጥሏል የሚሉት ሃላፊዋ ከተቀጡት ነጋዴዎች አብዛኞቹ የፈጠሩትን ችግር እስከሚያስተካክሉ ድረስ የማሸግና ማስጠንቀቂያ የመስጠት ነው፤ በዚህም ከ24 ሺህ 500 በላዩ 90 በመቶዎቹ አስተካክለው ወደ ስራቸው ተመልሰዋል ብለዋል። ይሁንንና አሁንም ያለ ንግድ ፈቃድ መነገድ፣ ኪሎ ቀንሶ መሸጥ፣ ባዕድ ነገሮችን መቀላቀልና ሌልውም ችግር ሆኖ መቀጠሉንና በመጪው ዓመት
Jul 281 min read


በኢትዮጵያ ጥምር ዜግነት እንዲፈቀድ ለማድረግ እንደሚሟገቱ በሃገራዊ ምክክሩ እየተሳተፉ ያሉ የዳያስፖራ ተወካዮች ተናገሩ፡፡
ሐምሌ 21 2018 በኢትዮጵያ ጥምር ዜግነት እንዲፈቀድ ለማድረግ እንደሚሟገቱ በሃገራዊ ምክክሩ እየተሳተፉ ያሉ የዳያስፖራ ተወካዮች ተናገሩ፡፡ አላግባባ ያሉና አንገብጋቢ ናቸው ተብለው በተመረጡ 8 አጀንዳዎች ላይ ሃገራዊ ምክክር መካሄድ ከጀመረ ቀናት ተቆጥረዋል፡፡ በምክክሩ ተሳታፊ ከሆኑ 4ሺህ ተመካካሪዎች 100 ያህሉ የዳያስፖራ ተወካዮች ናቸው፤ ከመካከላቸው ሁለቱን ምክክሩ ላይ ስላላቸው ተሳትፎ ጠይቀናቸዋል፡፡ በአባይ ጉዳይ ላይ በአረቢኛ ቋንቋ በግብፅ ሚዲያዎች የሚሰሩ ዘገባዎችን ወደ አማርኛ እየተረጎሙ በሚዲያቸው በማቅረብ የሚታወቁት ኡዝታዝ ከማል በሽር ተፅዕኖ ፈጣሪ ዳያስፖራዎችን በመወከል በምክክሩ እየተሳተፉ እንደሆነ ነግረውናል፡፡ በምክክሩ በአጀንዳነት ከተያዘው የሃገር ግንባታ ስር ካሉት ንዑሳን አጀንዳዎች አንዱ የዳያስፖራው አንገብጋቢ ጥያቄ የ
Jul 281 min read


ዓለም እንድትቀጥል አንዲት ሴት በሕይወት ዘመኗ 2.1 ልጅ እንድትወልድ ቢያስፈልግም፣ አሁን ያለው ግን 1.1 መሆኑን ጥናት አሳየ።
ሐምሌ 21 2018 ዓለም እንድትቀጥል አንዲት ሴት በሕይወት ዘመኗ 2.1 ልጅ እንድትወልድ ቢያስፈልግም፣ አሁን ያለው ግን 1.1 መሆኑን ጥናት አሳየ። የዓለም የሕዝብ ዕድገት ምጣኔ እያሽቆለቆለ መምጣቱን ያሳየውን ጥናት ያጠናው የተባበሩት መንግሥታት የሥነ ሕዝብ ተቋም ወይም UNFPA ነው። UNFPA የዓለም የሥነ ሕዝብ ቀንን በማስመልከት፣ ትዳር የመመሥረት፣ ልጅ የመውለድ የመሳሰሉ የወጣቶች ፍላጎቶችን በተመለከተ ያጠናውን ጥናት አዲስ አበባ ላይ ይፋ አድርጓል። ጥናቱ 73 አገሮችን እና ዕድሜያቸው ከ18 እስከ 39 ዓመት የሆኑ 108 ሺህ ወጣቶችን በመጠየቅ እንደ ተጠናቀቀም ተነግሯል። የጥናቱ ውጤትም ዓለም እንድትቀጥል አንዲት ሴት በሕይወት ዘመኗ መውለድ ከሚጠበቅባት በግማሽ ያነሰ እየወለደች መሆኑን ማሳየቱን፣ በUNFPA የወጣቶች ተሟጋች ቤዛዊት እድሉ
Jul 282 min read
በአዲስ አበባ በተጠናቀቀው በበጀት አመት 117 ሺህ ህፃናት ተወልደው የልደት ማረጋገጫ ሰጥቻቸዋለው ሲል የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ተናገረ፡፡
ሐምሌ 21 2018 በአዲስ አበባ በተጠናቀቀው በበጀት አመት 117 ሺህ ህፃናት ተወልደው የልደት ማረጋገጫ ሰጥቻቸዋለው ሲል የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ተናገረ፡፡ ይህም ህፃናቱ ተወልደው በ90 ቀናት ውስጥ የተመዘገቡ ናቸው ሲሉ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ዮሴፍ ንጉሴ አስረድተዋል፡፡ ዘግይተው የልደት ምዝገባ ካደረጉት ጋር ተደምሮ በ2018 የሲቪል ምዝገባ አገልግሎት ያገኙ ህፃናት ቁጥር ግን 385 ሺህ መሆኑን ሰምተናል፡፡ እንዲሁም 40 ሺህ 668 የጋብቻ ምዝገባ ለማድረግ አቅዶ 37 ሺ 149 መመዝገቡን መቻሉንም ሰምተናል፡፡ በዚህም ጋብቻ በተደረገ በወቅቱ የተመዘገቡት 10 ሺህ 972 ናቸው ተብሏል፡፡ በበጀት አመቱ 9 ሺ 558 ፍቺ ለመመዝገብ ታቅዶ ከ13 ሺ በላይ መመዝገባቸው ተነግሯል፡፡ በወቅታዊ የፍቺ ምዝገባ ያደረጉት 4 ሺህ
Jul 281 min read


ከሃያ አመት በፊት በኢንቨስትመንት ስም ወደ ኢትዮጵያ ገብቶ ጉዳት እያስከተለ ባለው የማንጎ ዝርያ ላይ የትምህርት ተቋማት ምርምር እያካሄዱ ናቸው ተባለ።
ሐምሌ 21 2018 ከሃያ አመት በፊት በኢንቨስትመንት ስም ወደ ኢትዮጵያ ገብቶ ጉዳት እያስከተለ ባለው የማንጎ ዝርያ ላይ የትምህርት ተቋማት ምርምር እያካሄዱ ናቸው ተባለ። መነሻውን ጋምቤላ አካባቢ በነበሩ ጥቂት እርሻዎች ላይ አድርጎ የነበረው ዝርያው አሁን ላይ መላ ኢትዮጵያን ማዳረሱ ተጠቅሷል። ተክሉ በፍጥነት በመባዛት ነባሩን የማንንጎ ዝርያ እያጠፋ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ወንዳለ ሃብታሙ ነግረውናል። አሁን ላይ የምርምር ተቋማት ተክሉ የሚያመጣውን ችግር እንዴት ማስቀረት ይችላል በሚለው ላይ እየሰሩ ናቸው ብለውናል። በአማራ እና ትግራይ ክልሎች በሰፊው ይታወቅ የነበረው የበለስ ተክልም ከውጪ በገባ ኩችኔት በተባለ በሽታ እየተመናመነ እንደሚገኝ ተነግሯል። ሰዎች ከውጪ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ የተሻለ ምርት
Jul 281 min read
የሐምሌ 21 2018 የውጪ ሀገር ወሬዎች
#ጃፓን የጃፓን ደቡባዊ ምዕራብ ክፍል በርዕደ መሬት ተመታ፡፡ ርዕደ መሬቱ የደረሰው ኩማማቶ የተባለው የአገሪቱ ክፍል እንደሆነ ኒኪ እስያ ፅፏል፡፡ የመሬት ነውጡ የተቀሰቀሰው ከምድር በ10 ኪሎ ሜትር ጥልቀት መሆኑ ታውቋል፡፡ ነውጡ በርዕደ መሬት መለኪያ /ሬክተር ስኬል/ 7 ነጥብ 1 ሆኖ መመዝገቡ ታውቋል፡፡ ቀደም ሲል የባህር ማዕበል /ሱናሚ/ ሊቀሰቀስ ይችላል በሚል ተሰጥቶ የነበረው ማስጠንቀቂያ ወዲያው መታጠፉ ተጠቅሷል፡፡ ያም ሆኖ ሰዎች ራሳቸውን ከባህር ዳርቻዎች እንዲያርቁ ተመክረዋል፡፡ በኩማማቶው ርዕደ መሬት በሰው እና በንብረት ላይ ስለደረሰ ጉዳት የተጠቀሰ ነገር የለም፡፡ በዚሁ ስፍራ ከ10 አመታት በፊት ደርሶ የነበረ ርዕደ መሬት 300 ያህል ሰዎችን እንደገደለ መረጃው አስታውሷል፡፡ #ጋና ጋና ተጨማሪ 1 ሺህ ዜጎቿን ከደቡብ አፍሪካ አስወጣች፡
Jul 282 min read
ከህዳሴ ግድብ ከ11 ሚሊዮን ኪሎ ግራም በላይ ዓሣ ተመረተ፡፡
ሐምሌ 21 2018 ከህዳሴ ግድብ ከ11 ሚሊዮን ኪሎ ግራም በላይ ዓሣ ተመረተ፡፡ የዓሣ ምርቱ ወደ መሃል ሃገር እየተጫነ ለአዲስ አበባ ገበያ እየቀረበ ነውም ተብሏል፡፡ ታላቁ የህዳሴ ግድብ መገንባቱን ተከትሎ በተፈጠረው ንጋት ሰው ሰራሽ ሃይቅ በኢትዮጵያ ትልቁና ከ70 በላይ ደሴቶች ያሉት የውሃ አካል ነው፡፡ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በሃይቁ ዓሣ እየተመረተ ወደ መሃል ሃገር እየተላከ መሆኑንን ሰምተናል፡፡ በስፍራው ዓሣ ወደ ማስገር ስራ በገቡ 12 ባለሃብቶች ከተደራጁ ወጣቶች ጋር በመሆን እንደሚሰሩ የነገሩን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ግብርና ቢሮ የዓሣ ሃብት ባለሙያ የሆኑት አቶ ቡሼን ቡፋ ናቸው፡፡ 2018 ዓ.ምን ስንጀምር ከግድቡ እናመርታን ብለን ውጥን የያዝነው ከ9 ሺህ 600 ቶን ወይም 9.6 ኪሎ ግራም ዓሣ ያልበለጠ ነበር፤ ይሁንና እየተገባደደ ባለው
Jul 282 min read
የሐምሌ 20 የውጭ ሀገር ወሬዎች
#ቀይ_ባህር በቀይ ባህር የባብኤል መንደብ ወሽመጥ የሚተላለፉ መርከቦች ብዛት በእጅጉ እየቀነሰ ነው ተባለ፡፡ በወሽመጡ የሚተላለፉ መርከቦች ብዛት የቀነሰው የየመን ሁቲዎች ባለፈው ሳምንት የሳውዲ አረቢያን ወደቦች እንከቻችምባታለን ብለው ከዛቱ በኋላ እንደሆነ ሬውተርስ ፅፏል፡፡ ለምሳሌም ትናንት በባብኤል መንደብ የባህር ወሽመጥ በኩል ያለፉት የጭነት መርከቦች 11 ብቻ እንደሆኑ የባህር ጉዞ መረጃ አጠናቃሪው የኬፕለር መረጃ ያሳያል፡፡ ይሄም በወሩ በባብኤል መንደብ ወሽመጥ ከተላለፉት መርከቦች ብዛት እጅግ ዝቅተኛው መሆኑ ተጠቅሷል፡፡ የየመን ሁቲዎች እና ሳውዲ አረቢያ ዳግም ወደ ጦር ፍጥጫቸው ከተመለሱ ሰንብተዋል፡፡ ርዕሰ ከተማዋ ሰንዓን ጨምሮ የየመንን አብዛኛውን ሰሜናዊ ክፍል የሚያስተዳድሩት ሁቲዎቹ የኢራን ሁነኛ የፖለቲካ ሸሪኮች እና የጦር አጋሮች እን
Jul 272 min read
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት 30.65 ቢሊዮን ዶላር የሚጠይቅ የኃይል ማስፋፊያ ዕቅድ ይፋ አደረገ።
ሐምሌ 20 2018 የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት 30.65 ቢሊዮን ዶላር የሚጠይቅ የኃይል ማስፋፊያ ዕቅድ ይፋ አደረገ። እቅዱ የኔትወርክ ማሻሻያ እና ማስፋፊያ፣ የሰብስቴሽን እና ተያያዥ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች፣ ስማርት ግሪድ እና ቆጣሪ ማስፋፋትን እንደሚያካትት አገልግሎቱ ዛሬ ይፋ አድርጓል፡፡ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የመጭውን የ25 አመት የሀይል ፍላጎት ለማወቅ የሚያግዝ ጥናት ማስጠናቱን ጠቅሷል፡፡ በፍጥነት እያደገ የመጣውን የሀይል ፍላጎት ለመሸከም፣ የኔትዎርክ ችግርን ለመፍታትና የሥርጭት ሥርዓትን ወደ ዘመናዊ እና ዲጅታል አሰራር ለማሸጋገር የ25 አመታት ሀገር አቀፍ የስርጭት ስርዓት ማሻሻያና ማስፋፊያ ማስተር ፕላን ጥናት መጠናቱ ተጠቅሷል፡፡ ጥናቱም በአለም ባንክ የገንዘብ ድጋፍ እና ሞኔንኮ ኢራን ኢንጅነሪንግ ኮንሰልቲንግ በተሰኘ
Jul 271 min read


የአፍሪካን የሠላም እና ደህንነት ጉዳይ ዘርፈ ብዙ ችግሮች ለመፍታት የሎጀስቲክስ እና ኮሚዩኒኬሽን አለመቀላጠፍ እስከዛሬም ያልተፈታ ትልቅ ፈተና ሆኖ ቀጥሏል ተባለ።
ሐምሌ 20 2018 የአፍሪካን የሠላም እና ደህንነት ጉዳይ ዘርፈ ብዙ ችግሮች ለመፍታት የሎጀስቲክስ እና ኮሚዩኒኬሽን አለመቀላጠፍ እስከዛሬም ያልተፈታ ትልቅ ፈተና ሆኖ ቀጥሏል ተባለ። አፍሪካ ሽብርተኝነት፣ ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ፣ ሰው ሰራሽ እና የተፈጥሮ አደጋዎች በየጊዜው የሚፈትኗት አህጉር ብትሆንም እነዚህን ችግሮች ለመፍታት መሰረታዊ ለሆነው የሎጅስቲክስ ዘርፍ ትኩረት እንዳልተሰጠው ተነግሯል። ይህ የተነገረው ኢትዮጵያ እና አሜርካ በጋራ ባዘጋጁት የ2026 የአፍሪካ ሎጅስቲክስና ኮሚውኒኬሽን ሲምፖዚየም ላይ ነው። በሲፖዚየሙ ንግግር ያደረጉት የአሜሪካ ጦር የአፍሪካ ኮማንድ ተወካይ ጀነራል "ዳግቪን አንዴርሰን" ዓለም የተራቀቀ የቴክኖሎጂ ዕድገት ላይ ቢሆንም፣ የሎጅስቲክስ አለመቀላጠፍ ለውትድርናው ዘርፍ አሁንም ፈተና ሆኖ ቀጥሏል ብለዋል። ሽብርተኝ
Jul 272 min read


የተከለከሉ ፕላስቲኮችን ሲያከፋፍሉ የተገኙ 46 የምርት አከፋፋዮች እንዲዘጉ መደረጉ ተሰማ።
ሐምሌ 18 2018 የተከለከሉ ፕላስቲኮችን ሲያከፋፍሉ የተገኙ 46 የምርት አከፋፋዮች እንዲዘጉ መደረጉ ተሰማ። ይህንን የሰማነው የአዲስ አበባ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዛሬ ባስጀመረው 3ኛ ዙር “ፅዱ ኢትዮጵያ ለትውልድ “ የከተማ አቀፍ መድረክ ላይ ነው። ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በፕላስቲክ ብክለት መከላከል ቁጥጥር ስራ 150 ልዩ ልዩ አካላትን ቀጥቼ ከ5 ሚሊዮን ብር በላይ ከቅጣት ገቢ መሰብሰቡ ችያለው ሲል ተናግሯል። በሌላ በኩል በወንዝ ብክለት መከላከል ቁጥጥር ላይ ሰፊ ስራ ሰርቻለሁ ያለው ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በተጠናቀቀው በጀት አመት ፍሳሻቸውን ወደ ወንዝ በለቀቁ ተቋማት ላይ ከተወሰደ እርምጃ ከ110 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡ ተነግሯል። የፍሳሽ ብክለት ያስከትላሉ የተባሉ 12ሺህ ግለሰብ እና ተቋማት ላይ የመለየት ስራ መሰራቱም ተነግሯል።
Jul 252 min read


የዚህ የስደት ነገር ማስታገሻው ምን ይሆን?
ሐምሌ 18 2018 የስደት ነገር የማያቋርጥ ሆነ፡፡ የውጭ ሀገር ጉዞ በህጋዊ መንገድ እንዲከናወን ስራ ቢጀመርም አሁንም ህገ-ወጡን መንገድ እየተከተሉ ችግር ላይ የሚወድቁት ዜጎች ቁጥር እንደበዛ ነው፡፡ ኑሮ አቀበት የሆነበት ፣ የግጭት ስጋት ያስጨነቀው የደላሎች ማግባቢያ ያመላለጡ ሁሉ ህገ-ወጡን መንገድ እየተከተሉ ለአደጋ እየተጋለጡ ነው፡፡ የዚህ የስደት ነገር ማስታገሻው ምን ይሆን? ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ... ፋሲካ ሙሉወርቅ
Jul 251 min read
የሐምሌ 18 የውጪ ሀገር ወሬዎች
#ስፔን በስፔኗ ርዕሰ ከተማ ማድሪድ አቅረቢያ ነዋሪዎች በመዛመት ላይ በሚገኘው ከባድ የሰደድ እሳት ምክንያት ለቅቀው እንደወጡ ታዘዙ፡፡ የማድሪድ ምዕራባዊ ክፍል አቅራቢያ የሰደድ እሳቱ በጣሙን ያየለበት እንደሆነ ቢቢሲ ፅፏል፡፡ እስከ ትናንት ምሽትም ከ19 ሺህ በላይ ሰዎች ለቀው መውጣታቸው ተጠቅሷል፡፡ በስፔን ወቅታዊ የሰደድ እሳት ምክንያት በአገሪቱ ብሔራዊ የአደጋ ጊዜ መታወጁ ታውቋል፡፡ ፈረንሳይም በሰደድ እሳት መዛመት እየተፈተነች ነው፡፡ የሰደድ እሳቱ በሁለቱም አገሮች ከ220 ሺህ በላይ ሰዎችን የመኖሪያቸው አፈናቅሏል ተብሏል፡፡ በአውሮፓ የሰደድ እሳቱ ለመባባሱ ወቅታዊው የሙቀት ማዕበል በዋና ምክንያትነት እየቀረበ ነው፡፡ #አሜሪካ የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቻይና እና ሩሲያ ለኢራን የጦር መሳሪያ እንዳይሰጡም ሆነ እንዳይሸጡ በብርቱ ማ
Jul 251 min read
በኮንጎ ኪንሻሣ በፍጥነት በመዛመት ላይ የሚገኘውን የኢቦላ ወረርሽኝ ለመከላከል የታለመ የሙከራ ክትባት ለአንድ ፈቃደኛ የሙከራው ተሳታፊ መሰጠቱ ተሰማ፡፡
ሐምሌ 18 2018 በኮንጎ ኪንሻሣ በፍጥነት በመዛመት ላይ የሚገኘውን የኢቦላ ወረርሽኝ ለመከላከል የታለመ የሙከራ ክትባት ለአንድ ፈቃደኛ የሙከራው ተሳታፊ መሰጠቱ ተሰማ፡፡ የሙከራው የመጀመሪያው ተሳታፊ የእንግሊዙ ኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ ፈቃደኛ ተማሪ እንደሆነ አለም አቀፉ የክትባት ጥምረት ጋቢ በድረ ገፁ ባሰፈረው መረጃ እወቁልኝ ብሏል፡፡ የሙከራ ክትባቱ የኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ የጤና ልሒቃን ውጤት መሆኑ ታውቋል፡፡ የሙከራው ውጤታማነት ለማረጋገጥ ተጨማሪ 49 ፈቃደኞች ይመለመላሉ ተብሏል፡፡ ከተከሰተ ከ2 ወራት በላይ ያስቆጠረው የኮንጎ ኪንሻሣው የቡንዲ ቡጉዮ የኢቦላ በሽታ ከ1 ሺህ በላይ ሰዎችን መግደሉ ተረጋግጧል፡፡ ከ2 ሺህ 500 የሚልቁ ሰዎች ደግሞ በበሽታው እንደተያዙ ተጠቅሷል፡፡ ዩንጋዳ የወረርሽኙን መዛመት በፍጥነት መቆጣጠሯ ተነግሮላታል፡፡ የአ
Jul 251 min read


ኢትዮጵያኖች አብሮ የሚያኖራቸውን መላና ሥርዓት ተስማምተው ለማበጀት እየሞከሩ ነው፡፡
ሐምሌ 18 2018 ኢትዮጵያኖች አብሮ የሚያኖራቸውን መላና ሥርዓት ተስማምተው ለማበጀት እየሞከሩ ነው፡፡ 4 ሺህ የሚሆኑት ዜጎች በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ለመምከር የሚያቀርቧቸው ሀሳቦች የተለያዩ ምናልባትም ፅንፍ የሚዳረሱ መሆናቸው የሚገመት ነው፡፡ የራቀውን አቅርበው የተወጠረውን አርግበው ውጤት ላይ ለመድረሱ የጀመሩት ሂደት እንዴት ከርሟል? ምንታምር ፀጋው ከተካፋዮቹ ውስጥ አነጋግራለች፡፡ ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ...
Jul 251 min read


አለም አቀፍ የገንዘብ ተቆጣጣሪ ድርጅት IMF በኢትዮጵያ ምጣኔ ሐብት ያሳየውን መሻሻልንና ያንዣበበትንም ስጋት በወቅታዊ በሪፖርቱ መዝግቧል፡፡
ሐምሌ 18 2018 አለም አቀፍ የገንዘብ ተቆጣጣሪ ድርጅት IMF በኢትዮጵያ ምጣኔ ሐብት ያሳየውን መሻሻልንና ያንዣበበትንም ስጋት በወቅታዊ በሪፖርቱ መዝግቧል፡፡ IMF እንደተነበየው ከሆነ ከመጭው አመት ጀምሮ ተጨማሪ ታክሶች እንዲከፈሉ የሚደረጉ መሆኑ የጥቁር ገበያውና መደበኛው ምንዛሬ ዋጋ አለመጥበቡ ፣ በገበያ እቃዎቹ የሚጣለው ከፍተኛ ግብር የኑሮ ውድነቱን እያናረው ነው፡፡ የኢራን ጦርነትና ከኤርትራ ጋር የተፈጠረው ውጥረት ስጋት ናቸው ብሏል፡፡ የትዕግስት ዘሪሁን ዘገባ የIMF ሪፖርትና የባለሙያ አስተያየት ያካትታል፡፡ ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ...
Jul 251 min read
በምክክሩ ሂደት የሚታዩ ክፍተቶች ከስር ከስር መፍትሄ እንዲሰጣቸው የሃገራዊ ምክክር ተሳታፊዎች ጠየቁ።
ሐምሌ 17 2018 በምክክሩ ሂደት የሚታዩ ክፍተቶች ከስር ከስር መፍትሄ እንዲሰጣቸው የሃገራዊ ምክክር ተሳታፊዎች ጠየቁ። ከገጠማቸው ችግር አንዱ የአስተርጓሚዎች እጥረት መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ የቋንቋ ችግር ሃሳብን እንዳይገድብ በምክክሩ መሃል በተለያዩ ቋንቋዎች አስተርጓሚዎች የተመደቡ ቢሆንም ከቡድኖቹ ብዛት አንፃር በቂ አስተርጓሚ የለም፤ ኮሚሽኑ ለዚህ አፋጣኝ መፍትሄ ቢፈልግ ሲሉ ጠይቀዋል። ከኦሮሚያ ክልል እንደመጡ የነገሩን አቶ ያዕቆብ በላይነህ ምክክሩ እንደርሳቸው አይነት አካል ጉዳተኞችን በሚገባ ማሳተፉ የሚያስመሰግነው ነው፤ነገር ግን እርሳቸው ባረፉበት የሲቪል ሰርቪስ ዩንቨርሲቲ በቂ የህክምና አገልግሎት የለም፤ከመናበብ ችግር የተነሳም አካል ጉዳተኞች 4ኛ ፎቅ ድረስ ወጥተው እየተሰበሰቡ ነው፤ እነዚህ ችግሮች ቢስተካከሉ መልካም ነው ብለዋል። ከሰሞኑ
Jul 241 min read
በተደጋጋሚ ተለዋጭ ቀጠሮ ሲሰጥበት የቆየው የእነ አቶ ክርስቲያን ታደለ መዝገብ የዋናው ክስ ብይን ዛሬም በድጋሚ ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠበት።
ሐምሌ 17 2018 በተደጋጋሚ ተለዋጭ ቀጠሮ ሲሰጥበት የቆየው የእነ አቶ ክርስቲያን ታደለ መዝገብ የዋናው ክስ ብይን ዛሬም በድጋሚ ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠበት። ተለዋጭ ቀጠሮው ለሚቀጥለው ዓመት ጥቅምት ወር ይሁን ብሏል ችሎቱ። ተከሳሾቹ በበኩላቸው በተደጋጋሚ በሚሰጡ ቀጠሮዎች ምክንያት «ፍትህ እየተጓተተብን ነው» ሲሉ ለችሎቱ ቅሬታ አቅርበዋል። በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው በማረሚያ ቤት የሚገኙት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባሎቹ አቶ ክርስቲያን ታደለ፣ አቶ ዮሐንስ ቧያለው እና ሌሎች ተከሳሾች የክስ ብይን ይሰጣል ተብሎ ተደጋጋሚ ቀጠሮዎችን ሲያስተናግድ ቆይቶ፤ ዛሬም በተመሳሳይ ለሚቀጥለው ዓመት ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል። ከዚህ በፊት በነበረው ቀጠሮ «ተከሳሾቹ መከላከያ ማስረጃ ያቅርቡ ወይስ በነፃ ይሰናበቱ?» በሚለው ላይ ብይን ለመስጠት እንዲሁም የዶክተር
Jul 242 min read
የአጠቃላይ የትምህርት ዘርፍ የትምህርት ቤቶች ፍቃድ አሰጣጥ እና እድሳት መመሪን ለማሻሻል የትምህርት ሚኒስቴር ያወጣውን መመሪያ ፍርድ ቤት ሻረው፡፡
ሐምሌ 17 2018 የአጠቃላይ የትምህርት ዘረፍ የትምህርት ቤቶች ፍቃድ አሰጣጥ እና እድሳት መመሪን ለማሻሻል የትምህርት ምኒስቴር ያወጣውን መመሪያ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድቤት ሻራው ፡፡ በትምህርት ሚኒስቴር ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ስራ ላይ እንዲውል የተወሰነው እና በፍርድ ቤት የተሻረው መመሪያ አንድ ንዑስ አንቀጽ አካቷል፡፡ በመመሪያ መሻሻያው የተካተተው በአንቀጽ ሁለት ስር ንዑስ አንቀስ 18 ሲሆን፤"የትምህርት ክፍያ ጭማሪ ማለት፣ አንድ ትምህርት ቤት በቀደመው ዓመት በሚያስከፍለው የትምህርት ክፍያ ላይ አዲስ ክፍያ መጨመር ማለት ሲሆን፣ በአንድ ትምህርት ቤት ውስጥ ለተመሳሳይ ትምህርት ወይም የክፍል ደረጃ የሚከፈሉ የተለያዩ ክፍያዎችን በማስተካከል ለተመሳሳይ ትምህርት ወጥ ወይም አንድ አይነት ክፍያ እንዲኖር የማድረግን የክፍያ ማጣጣም አሰራርን (
Jul 242 min read
ፕሮግራሞች
bottom of page
_edited.jpg)
