top of page
በመጪው ዓመት ከአዲስ አበባ ከተማ ግብር ከፋዮች 380 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ውጥን መያዙን የከተማዋ ገቢዎች ቢሮ ተናገረ።
ሐምሌ 29 2018 በመጪው ዓመት ከአዲስ አበባ ከተማ ግብር ከፋዮች 380 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ውጥን መያዙን የከተማዋ ገቢዎች ቢሮ ተናገረ። በ2019 በጀት ዓመት በአዲስ አበባ ከተማ ደረጃ በአጠቃላይ 502.2 ቢሊዮን ብር ይሰበሰባል የተባለ ሲሆን ከዚህም ውስጥ የገቢዎች ቢሮ ድርሻ 380 ቢሊዮን ብር መሆኑን ቢሮው ዛሬ በሰጠው መግለጫ ተናግሯል። የከተማ አስተዳደሩም ከሚሰበሰበጡ ግብር 72 በመቶውን ከተማዋን ለማልማት እንደሚያውለው መግለጫውን የሰጡት የገቢዎች ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ሰውነት አየለ አስረድተዋል። በከተማዋ በንግድ ትርፍ፣ በኪራይና በሜትር ትራንስፖርት ዘርፍ የተሰማሩ 456 ሺህ የደረጃ ለ - ግብር ክፋዮች አሉኝ ያለው ቢሮው፤ በተሻሻለው የገቢ ግብር አዋጅ መሰረት የግብር ግዴታቸውን ከሐምሌ 1 እስከ ሐምሌ 30/2018 ዓ
5 days ago1 min read
እንደ ጣና ያሉ ሀይቆችና የውሃ አካላት ላይ ተንሰራፍቶ ከሚገኘው የእምቦጭ አረም የነዳጅ ምርቶችን ለማምረት ይሰራል ከተባለ ከአምስት አመት በላይ ሆኖታል።
ሐምሌ 29 2018 እንደ ጣና ያሉ ሀይቆችና የውሃ አካላት ላይ ተንሰራፍቶ ከሚገኘው የእምቦጭ አረም የነዳጅ ምርቶችን ለማምረት ይሰራል ከተባለ ከአምስት አመት በላይ ሆኖታል። ይተገበራል በተባለው ፕሮጀክትም ነጭ ጋዝ፣ ቤንዚን ፣ኪሮሲን፣ የአውሮፕላን ነዳጅ እና ሚቴን ማምረት የሚለው ይገኝበታል ። ተረፈ ምርቱ ከነዳጅ ምርቱም ጎን ለጎን ለከሰል እና ለእደጥበብ ውጤቶችም ይውላል መባሉ ይታወሳል። ከእምቦጭ ነዳጅም ሆነ ሌሎች ምርቶችን ለማምረት ከውጪ ሀገራት ጋር አብሮ ለመስራት ስምምነት እንደነበረም መረጃዎች ያሳያሉ። ለመሆኑ ነዳጅን ከእምቦጭ አረም ለማግኘት ተይዞ የነበረው እቅድ ከምን ደረሰ ? የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴርን ጠይቀናል። አቶ ወንድወሰን አበጀ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የኢኮ ሃይድሮሎጂ ፕሮጀክትና የመጤ አረሞች ማስወገድ እና መከላከል አስተባባሪ
5 days ago1 min read
ኢትዮጵያ ሁለት ዓይነት የመሬት አስተዳደር ሥርዓትን እንደምትከተል ይነገራል::
ሐምሌ 29 2018 ኢትዮጵያ ሁለት ዓይነት የመሬት አስተዳደር ሥርዓትን እንደምትከተል ይነገራል:: ይህም የከተማ የመሬት አስተዳደር ሥርዓትና የገጠር የመሬት አስተዳደር ሥርዓት ተብሎ እንደሚጠራም ሰምተናል:: በዚህም የከተማው በአንድ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት የገጠሩም እንዲሁ በሌላ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት እየተመራ ይገኛል:: ከመሬት ባለቤትነት ጉዳይ ባለፈ የአጠቃቀም ጉዳይም ያልተፈቱ ችግሮች እንዳሉበት ይነገራል። የገጠሩን መሬት አስተዳደር በአግባቡ እየተመራ መሆኑ ይነገራል፡፡ በአተገባበሩ ላይ ግን መደበላለቅ እንዳለ ሰምተናል፡፡ ይህ የሀላፊነት መደበላለቅ ምን አስከተለ? ስትል ማርታ በቀለ ጠይቃለች ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ....
5 days ago1 min read


ነዳጅ ቀሽበው የተገኙ የቦቴ ሾፌሮች በእምነት ማጉደል በህግ መጠየቅ ሲገባቸው የቦቴው ባለቤቶች ባልተሳፍንበት ወንጀል ክልሎች ንብረታችንን ያላግባብ እየወረሱ ነው ሲሉ ባለንብረቶቹ ቅሬታቸውን ተናገሩ::
ሐምሌ 29 2018 ነዳጅ ቀሽበው የተገኙ የቦቴ ሾፌሮች በእምነት ማጉደል በህግ መጠየቅ ሲገባቸው የቦቴው ባለቤቶች ባልተሳፍንበት ወንጀል ክልሎች ንብረታችንን ያላግባብ እየወረሱ ነው ሲሉ ባለንብረቶቹ ቅሬታቸውን ተናገሩ:: የተወረሰውን ነዳጅም ያላግባብ እንድንከፍል በክልሎች እየተጠየቅን ነው ይላሉ፡፡ በሾፌሮች የሚፈፀም ነዳጅ ቅሸባ ተገቢ ያልሆነ ሌብነት ነው የሚሉት ባለንብረቶች ተጠያቂ መሆን አለባቸውም ይላሉ፡፡ አንዳንድ ክልሎች ግን መንግስት ያወጣውን ህግ ሽረው ንብረታችንን በመውረሳቸው እየተቸገርን ነው ሲሉ ባለንብረቶቹ አማረዋል፡፡ የነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን በበኩሉ የነዳጅ ጉዳይ በአንድ መስሪያ ቤት ብቻ የሚመራ እንዳልሆነና ቅሸባን በተመለከተ ችግሩንም ለመከላከል በጋራ እንደሚሠራ ተናግሯል:: ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ.... ማርታ በቀለ
5 days ago1 min read


ታሪክን በፎቶግራፍ የመሰነድ ባህል ዝቅተኛ መሆኑ ፣አብዛኞቹ የታሪክ ፎቶግራፎች በውጭ ዜጎች የተነሱ በመሆናቸው ታሪክን ከእነሱ እይታ አንጻር እንድንረዳ አድርጎናል ሲሉ ቱሪዝምና ታሪከን የሚሰንድ ተቋም የመሰረቱ ባለሞያ ነግረውናል፡፡
ሐምሌ 29 2018 ታሪክን በፎቶግራፍ የመሰነድ ባህል ዝቅተኛ መሆኑ ፣አብዛኞቹ የታሪክ ፎቶግራፎች በውጭ ዜጎች የተነሱ በመሆናቸው ታሪክን ከእነሱ እይታ አንጻር እንድንረዳ አድርጎናል ሲሉ ቱሪዝምና ታሪከን የሚሰንድ ተቋም የመሰረቱ ባለሞያ ነግረውናል፡፡ ፎቶግራፍ የታሪክ ክስተቶችን በፎቶ ከመሰነድ በተጨማሪ፣ የሀገር ውስጥ ቱሪዝምን ለማስፋፋት አንደሚያግዝ አስርድተዋል፡፡ ፎቶግራፍ የሀገርን ታሪክ ሰንዶ ለቀጣይ ትውልድ በማሸጋገር ረገድ እንደ ከሥነ ፅሑፍና ሌሎችም የኪነ ጥበብ ዘርፎች ያልተናነሰ አቅም እንዳለው ይነገራል። ፎቶግራፍ በአንድ ዘመን የነበረን የማህበረሰብ የአኗኗር ዘይቤ፣የከተማ ዕድገት፣የሀገር ገፅታና ታሪካዊ ማንነትን ይዞ የሚቀር፣ለትውልድም የሚያሸጋግር የጥበብ ዘርፍ ነው ይላሉ ባለሙያዎች። ፎቶግራፍ ሀገር ትናንት የት እና እንዴት ነበረች የሚ
5 days ago1 min read


በፋብሪካ የሚመረቱ አልኮሎችና ትንባሆ ላይ የኤክሳይዝ ታክስ መጣል የምርቶቹን ዋጋ አንዲጨምር በማድረጉ የምርቶቹ የተጠቃሚዎች ቁጥር መቀነሱን ጥናት አሳየ፡፡
ሐምሌ 29 2018 በፋብሪካ የሚመረቱ አልኮሎችና ትንባሆ ላይ የኤክሳይዝ ታክስ መጣል የምርቶቹን ዋጋ አንዲጨምር በማድረጉ የምርቶቹ የተጠቃሚዎች ቁጥር መቀነሱን ጥናት አሳየ፡፡ በሌላ በኩል ግን ጠጅ ፣ ጠላ ፣ አረቄ የመሳሰሉት ምርቶች ተጠቃሚያቸው መብዛቱን በጥናቱ ግኝት ተጠቅሷል፡፡ ጥናቱን ያጠናው በጤናው መስክ ጥናትና ምርምሮችን የሚያካሂደው ፍኖት የተሰኘ ድርጅት ነው ። ድርጅቱ ይህን ጥናት ይፋ ያደረገው ከስድስት ዓመት በፊት በአልኮል እና በትንባሆ ላይ የተጣለው ኤክሳይዝ ታክስ ምን ውጤት እንዳመጣ በአማራ፣ኦሮሚያና በአዲስ አበባ ላይ ያካሄደው ዳሰሳዊ ጥናት ነው ። በአልኮልና በትንባሆ ምርቶች ላይ የተጣለው ኤክሳይዝ ታክስ የተጠቃሚዎችን ቁጥር ከ10 እስከ 20 በመቶ እንዲቀንስ አድርጓል ሲሉ በፍኖት አሶሼት የሄልዝ ኬር ፋይናንሲንግ ባለሙያና አማካሪ
5 days ago1 min read


በአዲስ አበባ የነዳጅ ማደያዎች ተሰፍሮ የተሰጣቸውን ነዳጅ ከስፍር እያጎደሉና እየሰረቁ ማስቸገራቸው ተነግሯል፡፡
ሐምሌ 29 2018 በአዲስ አበባ የነዳጅ ማደያዎች ተሰፍሮ የተሰጣቸውን ነዳጅ ከስፍር እያጎደሉና እየሰረቁ ማስቸገራቸው ተነግሯል፡፡ ከ133 ማደያዎች ለተጠቃዎች በታማኝነት ከሊትር ያልጎደለ ነዳጅ የሚሸጡት 42 ብቻ መሆናቸውን የከተማዋ ንግድ ቢሮ ተናግሯል፡፡ በዚሁ ምክንያት ከስራ እስከማገድ የደረሰ እርምጃ የተወሰደባቸውም አሉ፡፡ የነዳጅ መቅጃ ማሽኖቻቸውን ቴክኒካዊ በሆነ መንገድ ሆን ብለው ሊትር ቀንሰው እንዲቀዱ ማድረጋቸውን ባደረግኩት ፍተሻ ደርሼበታለሁ ሲል የነዳጅ ግብይትን የሚቆጣጠረው የከተማዋ ንግድ ቢሮ ነግሮናል፡፡ በዚህም በአዲስ አበባ ካሉት 133 ማደያዎች ከቅሸባ ነፃ የሆኑት 42 ብቻ ናቸው፡፡ 91ዱ በዚህ ቅሸባ በተባለው ሊትርን የማጉደል ተግባር ሲፈፅሙ ተገኝተው ከመካከላቸው 64ቱ በማስጠንቀቂያ ታልፈዋል፤21ማደያዎች የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ
5 days ago1 min read
የሐምሌ 29 2018 የውጪ ሀገር ወሬዎች
#አፍጋኒስታን በአፍጋኒስታን የተለያዩ ግዛቶች የደረሰ የጎርፍ አደጋ 29 ሰዎችን ገደለ ተባለ፡፡ አደጋው በ130 ያህል ሌሎች ሰዎች ላይ ደግሞ አካላዊ ጉዳት ማድረሱን አናዶሉ ፅፏል፡፡ 4 ሰዎች ደግሞ የደረሱበት አልታወቀም ተብሏል፡፡ ጎርፉ በብዙ ቤቶች እና መሰረተ ልማቶች ላይ ውድመት ማስከተሉ ታውቋል፡፡ በአፍጋኒስታን የተለያዩ ግዛቶች የጎርፍ አደጋው የደረሰው በዶፍ ዝናብ ምክንያት እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡ በአደጋው ምክንያት ብዙ ሰዎች እርዳታ እንደሚያሻቸው ተነግሯል፡፡ የአለም የጤና ድርጅት 3 ተዘዋዋሪ የጤና ባለሙያዎች ቡድኖችን በማሰማራት ድጋፍ እያደረኩ ነው ማለቱ ተሰምቷል፡፡ #የመን በየመን የውሃ ክልል በመንሳፈፍ ላይ የነበረች መርከብ ፈንጂ በተጫነ ጀልባ ተገጭታ ሰጠመች ተባለ፡፡ መርከቧ ብትሰጥም ሁሉንም 14 ባህረኞቿን ማትረፍ እንደተቻለ አለም አ
5 days ago2 min read
ያልተደራጀ የመረጃ አያያዝ እና ተቀናጅቶ አለመስራት የዓመቱ የባህል፣ስፖርት እና ኪነ ጥበብ ዘርፍ ክፍተት መሆኑን ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ተናገረ ።
ሐምሌ 29 2018 ያልተደራጀ የመረጃ አያያዝ እና ተቀናጅቶ አለመስራት የዓመቱ የባህል፣ስፖርት እና ኪነ ጥበብ ዘርፍ ክፍተት መሆኑን ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ተናገረ ። ከስፖርት ዘርፍ ስኬት አንፃር የሚቀርቡ ትችቶችን ለማስተካከል በሀገር ደረጃ በዚህ ዓመት ለመጀመሪያ ጊዜ የፀደቀው የስፖርት ልማት እና አስተዳደር አዋጅ ተስፋ ተደርጎበታል። ይህ የተባለው የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የ2018 ዓ.ም ጠቅላላ ጉባኤ እያደረገ ባለበት መድረክ ላይ ነው። በጉባኤው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት ባህልና ስፖርት ሚንስትር ወ/ሮ ሸዊት ሻንካ ዘንድሮ ክፍተት የታየባቸውን የመረጃ አያያዝ እና ተቀናጅቶ የመስራት ችግሮችን በቀጣዩ ዓመት ትኩረት ሰጥተን አሰንሰራበታለን ብለዋል። በኪነ ጥበብ ዘርፍ የሚታዩ ችግሮችን ለመፍታት የጥበብ ምክር ቤት ፖሊሲ እየተዘጋጀ መሆኑንም ሚንስ
5 days ago1 min read
በፊንቴክ ኢንቨስትመንት ማጭበርበር የተጠረጠሩ አርቲስቶችና ቲክቶከሮች በክስ መቃወሚያቸው ላይ ብይን ተሰጠ::
ሐምሌ 29 2018 በፊንቴክ ኢንቨስትመንት ማጭበርበር የተጠረጠሩ አርቲስቶችና ቲክቶከሮች በክስ መቃወሚያቸው ላይ ብይን ተሰጠ:: ተከሳሾቹ በማህበራዊ ሚዲያ የሰጡትን መግለጫ በተመለከተም ዐቃቢ ህግ አቤቱታ አቅርቧል። በ"ፊንቴክ" ኢንቨስትመንት ሽፋን በተፈጸመ መጠነ-ሰፊ የማጭበርበር ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ውለው የነበሩ ታዋቂ አርቲስቶችና ቲክቶከሮች፣ የዋስትና መብታቸው ተከብሮላቸው በውጭ ሆነው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ መወሰኑ ይታወሳል። የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ተከሳሾች ያቀረቡትን የክስ መቃወሚያ እና ዐቃቤ ሕግ የሰጠውን መልስ መርምሮ ብይን ለመስጠት ለዛሬ፣ ሐምሌ 29 ቀን 2018 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቶ ነበር። በዛሬው የችሎት ውሎ፣ ተከሳሾቹ "እኛ የሠራነው የማስታወቂያ ሥራ እንጂ ኮምፒውተር ተጠቅመን የፈጸምነው የማ
5 days ago1 min read
በሌላ ሰው የመሬት ይዞታ ላይ ባለይዞታው ፈቅዶለት ቤት የሰራ ሰው የቤቱ ባለቤት ይሆናል የሚለውና ፍርድ ቤቶች እንደ አስገዳጅ ህግ ሲጠቀሙበት የቆየው ውሳኔ በፌዴሬሽን ምክር ቤት ትርጉም ተሻረ፡፡
ሐምሌ 29 2018 በሌላ ሰው የመሬት ይዞታ ላይ ባለይዞታው ፈቅዶለት ቤት የሰራ ሰው የቤቱ ባለቤት ይሆናል የሚለውና ፍርድ ቤቶች እንደ አስገዳጅ ህግ ሲጠቀሙበት የቆየው ውሳኔ በፌዴሬሽን ምክር ቤት ትርጉም ተሻረ፡፡ ከዚህ ቀደም የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰጠው በዚሁ አስገዳጅ ውሳኔ በስር ፍርድ ቤቶች ሲሰራበት የቆየው ድንጋጌ የተሻረው የፌዴሬሽን ምክር ቤት ባለፈው ሰኔ 29 ቀን 2018 ባካሄደው መደበኛ ስብሰባወ ባሳለፈው ውሳኔ ነው፡፡ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የሚሰጣቸው የህግ ትርጉምን መሰረት ያደረጉ አስገዳጅ ውሳኔዎች በስር ፍርድ ቤቶች እንደ ህግ ሆነው የሚሰራባቸው ሲሆን በሌላ ሰው ይዞታ ላይ ባለቤቱ ፍቅዶለት ቤት የሰራ ሰው ንብረት እንዳፈራ ተቆጥሮ የቤቱ ባለቤት ይሆናል የሚል አስገዳጅ ውሳኔ ሰጥቶ ለፍር
5 days ago2 min read
በብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ዋና ስራ አስኪያጅነትና በተለያዩ መስሪያ ቤቶች ከ40 አመታት በላይ በሀላፊነት ሲሰሩ የነበሩት ወይዘሮ መዓዛ ቅጣው አረፉ፡፡
ሐምሌ 28 2018 በብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ዋና ስራ አስኪያጅነትና በተለያዩ መስሪያ ቤቶች ከ40 አመታት በላይ በሀላፊነት ሲሰሩ የነበሩት ወይዘሮ መዓዛ ቅጣው አረፉ፡፡ ሙሉውን ለማድመጥ.... እሸቴ አሰፋ
6 days ago1 min read
በኢትዮጵያ ተላላፊ ባለሆኑ እንደ ልብ ያሉ ሕመሞች ምክንያት የሚመጣ የጤና ችግር ለሀገሪቱ የጤና ሥርዓት ተጨማሪ ሥጋት ሆኗል ተባለ።
ሐምሌ 28 2018 በኢትዮጵያ ተላላፊ ባለሆኑ እንደ ልብ ያሉ ሕመሞች ምክንያት የሚመጣ የጤና ችግር ለሀገሪቱ የጤና ሥርዓት ተጨማሪ ሥጋት ሆኗል ተባለ። ከልብ ሕመም ጋር በተያያዘ የሚደርስ የጤና ቀውስን ለመቀነስ ሕክምናው እንዲሁም ቅድመ - መከላከሉ ላይ በስፋት መሠራት አለበት ተብሏል። ከልብ ሕክምና ተደራሽነት፣ የጤና ፖሊሲን ማሻሻል እና ምርምር ላይ የሚሠራው የፓን አፍሪካን የልብ ሕክምና ማኅበር ሰሞኑን በአዲስ አበባ ባካሄደው ዓመታዊ ጉባኤ ከልብ ሕመም ጋር የተገናኙ የጤና ችግሮች የአፍሪካ ከፍተኛ የጤና ሥጋት እየሆኑ ነው ብሏል። ኢትዮጵያን ጨምሮ በአህጉሪቱ ከልብ ሕክምና ጋር በተገናኘ ያሉ ፈተናዎችን በመለየት፣ ሰፊ የጥናትና ምርምር ሥራዎች እና የፖሊሲ ማሻሻያ እንዲደረግ ለመንግሥታት ግብዓት የሚያቀብል ውይይት እንደሆነ የነገሩን የኮንፈረንሱ ሊቀ
6 days ago2 min read
ባለፉት 10 ዓመታት ኤል ኒኖ በኢትዮጵያ ሁለት ጊዜ ተከሰቷል።
ሐምሌ 28 2018 ባለፉት 10 ዓመታት ኤል ኒኖ በኢትዮጵያ ሁለት ጊዜ ተከሰቷል። በ2007/08 እና ከሦስት ዓመታት በፊት በተወሰኑ ቦታዎች ላይ አጋጥሟል። በእነዚህ ጊዜያት እንስሳት ሞተዋል፤ የግብርና ምርት መጠን አሽቆልቁሏል፤ ገበሬውም ለገበያ እና ለቤቱ የሚያቀርበውን ምርት ለማግኘት መቸገሩን የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ይናገራል። ታዲያ ዘንድሮ ይከሰታል የተባለው የኤል ኒኖ ክስተት ጉዳት እንዳያደርስ ወይም ጉዳቱን ለመቀነስ የምርምር ተቋማት ምን ሠርተዋል? ከባለፉት ችግሮችስ ምን ያህል ትምህርት ተወስዷል? ጉዳዩን በተመለከተ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩትን ጠይቀናል። በኢንስቲትዩቱ የግብርና ኢኮኖሚ ምርምር ዳይሬክተር ታደለ ማሞ (ዶ/ር) ፤ እስካሁን ድረስ በኤል ኒኖ ከሚደርሰው ጉዳት አንጻር ሲታይ ተገቢውን ትምህርት ወስደን እየተዘጋጀን ነው ማለ
6 days ago2 min read
የሐምሌ 28 2018 የውጪ ሀገር ወሬዎች
#የመን አለም አቀፉ ዕውቅና አለው የሚባለው የየመን መንግስት ወታደሮቼ በጣም ብዙ የሁቲ ታጣቂዎችን ገደሉ አለ፡፡ በደፈናው በጣም ብዙ የሁቲ ታጣቂዎችን ሙት እና ቁስለኛ አድርገናል ቢልም ብዛታቸውን በአሃዝ ይሄን ያህል ነው እንዳላለ ሚድል ኢስት ሞኒተር ፅፏል፡፡ የሁቲ ታጣቂዎቹ የተገደሉ በደቡባዊ ምዕራቧ ታይዝ ግዛት በተካሄዱ ውጊያዎች ነው ተብሏል፡፡ በጣም ብዙ ታጣቂዎቻቸው ተገድለዋል ስለመባሉ ሁቲዎቹ ምንም ዓይነት አስተያየት እንዳልሰጡ ተጠቅሷል፡፡ አለም አቀፍ እውቅና አለው የሚባለው የየመን መንግስት መቀመጫው በደቡባዊቱ የወደብ ከተማ ኤደን ነው፡፡ የኢራን ሽርካዎች ናቸው የሚባሉት ሁቲዎቹ ርዕሰ ከተማዋ ሰንዓን ጨምሮ አብዛኛውን የየመን ሰሜናዊ ክፍል ሲያስተዳድሩ ከ10 አመታት በላይ ሆኗቸዋል፡፡ #እስራኤል ሁለት እስራኤላዊያን ሚኒስትሮች ጠቅላይ ሚኒ
6 days ago2 min read
ከፒያሳ ሰራተኛ ሰፈር የጋራ መኖሪያ ቤት ተነስተው ቃሊቲ የገቡ ሰዎች ከሁለት አመት በኋላ በቀድሞውና በአሁኑ መኖሪያ ቤታቸው መካከል ያለው የቤት ስፋት ልዩነት ተሰልቶ ክፈሉ መባላቸውን ተቃወሙ ፡፡
ሐምሌ 28 2018 ከፒያሳ ሰራተኛ ሰፈር የጋራ መኖሪያ ቤት ተነስተው ቃሊቲ የገቡ ሰዎች ከሁለት አመት በኋላ በቀድሞውና በአሁኑ መኖሪያ ቤታቸው መካከል ያለው የቤት ስፋት ልዩነት ተሰልቶ ክፈሉ መባላቸውን ተቃወሙ ፡፡ ነዋሪዎቹ ከሁለት ዓመት በፊት ከፒያሳ ስንነሳ ቃል የተገባልን ይህ አልነበረም ይላሉ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በበኩሉ ቅሬት አቅራቢዎቹ የተሰጣቸው ቤት ከቀድሞው ጋር ሲነፃፀር ስፋቱ እንደሚበልጥ ክፍያም የተጠየቀው በቀድሞው ዝቅተኛ ተመን መሆኑን ተናግሯል፡፡ አሁን ክፈሉ የተባለው የካሬ ልዩነት የተሰላው በአሁኑ ዋጋ ሳይሆን በበፊቱ ነው ይህ የተደረገው እንዳይጎዱ በማሰብ ነው የሚል ምላሽ ተሰጥቶናል። ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ... ቴዎድሮስ ወርቁ
6 days ago1 min read
ታሪክን_የኋሊት
ባለ ብዙ ገድሉ አፍሪካ አሜሪካዊ ስፖርተኛ ጄሲ ኦውንስ በዘመኑ ድንቅነቱን አስመስክሯል፡፡ በተለይም ከ90 አመታት በፊት በጀርመን በተካሄደው የበርሊን ኦሎምፒክ ታላቁን ታሪክ የሰራበት ነበር፡፡ በዚያ ኦሎምፒክ ኦውንስ በተለያዩ ስፖርታዊ ክንውኖች አራት የወርቅ ሜሊያዎችን አጥልቋል፡፡ በዚህ ኦሎምፒክ በመቶ ሜትር ሩጫ የመጀመሪያዋን የወርቅ ሜዳሊያ ያገኘው ከ90 አመታት በፊት በዛሬዋ እለት ነበር፡፡ ሁለገቡ ኦውንስ በበርሊን ኦሎምፒክ ከመቶ ሜትር ሩጫ በተጨማሪ በአግድመት ዝላይ ፣ በ200 ሜትር እንዲሁም 4 በ 4 መቶ ሜትር የዱላ ቅብብል 3 የወርቅ ሜዳሊያዎችም አሸንፏል፡፡ ጄ ሲ ኦውንስ ከ90 አመታት በፊት በበርሊን ኦሎምፒክ ከየትኞቹም ተፎካካሪ ስፖርተኞች በበለጠ በድል ያሸበረቀ ሆኖ አጠናቋል፡፡ ዘመኑ ናዚ ጀርመን አለምን በጦር አስገበራለሁ በሚል እብሪ
7 days ago1 min read
በኤሌክትሪክ እጦት ምክንያት የእለት ተእለት ተግባራቸውን መከወን ዳገት እንደሆነባቸው የምዕራብ ጎጃም ዞን ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡
ሐምሌ 27 2018 በኤሌክትሪክ እጦት ምክንያት የእለት ተእለት ተግባራቸውን መከወን ዳገት እንደሆነባቸው የምዕራብ ጎጃም ዞን ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡ የኢትዮጵያ ኤሌክትክ አገልግሎት በበኩሉ ማህበረሰቡ የሚያነሳው ችግር ተገቢ ነው እሱን ለማስተካከልም እየሰራሁ ነው ብሏል፡፡ ከ1.3 ሚሊየን በላይ ህዝብ ያለበት የምዕራብ ጎጃም ዞን ኤሌክትሪክ እያገኘን ያለነው በሳምንት አንዴ ነው፤ 6ቱን ቀናት ደግሞ በጨለማ ማሳለፍ ከጀመርን ከራርመናል ሲሉ ቅሬታቸውን ነግረውናል፡፡ ለረጅም ጊዜ ስንፈተንበት ለቆየነው ችግርም መፍትሄ ለማግኘት የአማራ ሪጅን ማስተባበሪያ ቢሮን ጨምሮ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በአካል በመቅረብ ጥያቄያችንን አቅርበናል ያሉት ቅሬታ አቅራቢዎቹ የፍኖተ ሰላም ሰብስቴሽን ሥራውን በአግባቡ ለማከናወን በአስቸኳይ አዲስ ትራንስፎርመር የሚያፈልግ በመ
7 days ago1 min read
ጥብቅ እንደሆነ የሚነገርለት የኢትዮጵያ የባንኮች ብድር አሰጣጥ ሥርዓት አሁንም ሊሻሻሉ የሚገቡ ጉዳዮች ያሉበት ነው ተባለ።
ሐምሌ 27 2018 ጥብቅ እንደሆነ የሚነገርለት የኢትዮጵያ የባንኮች ብድር አሰጣጥ ሥርዓት አሁንም ሊሻሻሉ የሚገቡ ጉዳዮች ያሉበት ነው ተባለ። ሰዎች ከዚህ በፊት የወሰዷቸውን ብድሮች የከፈሉበት መልካም ታሪክ እየታየ ከባንኮች ገንዘብ የሚያገኙበት ሥርዓት በኢትዮጵያም ሊለመድ እንደሚገባ የዘርፉ ባለሙያዎች ተናግረዋል። በኢትዮጵያ የባንኮች ብድር መመርያና ፖሊሲ ከባንክ ባንክ የተለያየ በመሆኑ የብድር አሰጣጥ ሂደቱም በተወሰነ መልኩ ከተቋም ተቋም እንደሚለያይ ተነግሯል፡፡ ከብድር ጋር ተያይዞ በኢትዮጵያ ያሉ ባንኮች ዋና ዋና የብድር መስፈርቶችን ያስቀምጣሉ፡፡ ከእነዚህ መካከል የብድር መያዣ ፣ ካፒታል፣ የስራ ዕቅድ፣ የገንዘብ አቅም ፣ የብድር ስጋት ደረጃ እንዲሁም አስፈላጊ የሰነዶችና ቅድመ ሁኔታዎችን ማሟላት የሚሉት እና ሌሎችም ይገኙበታል፡፡ ሆኖም እነዚህ
7 days ago1 min read
የመኖሪያ ቤት ችግር በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ የብዙዎች ራስ ምታት ሆኖ ቀጥሏል።
ሐምሌ 27 2018 የመኖሪያ ቤት ችግር በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ የብዙዎች ራስ ምታት ሆኖ ቀጥሏል። በሪል እስቴት ዘርፍ ከተሰማሩ አልሚዎች መካከል አንዱ የሆነውና የቤት ችግርን ለመፍታት እሰራለሁ የሚለው አባይ ሆምስ ሪል እስቴት፤ ከሰሞኑ በ2 ቢሊዮን ብር የግንባታ ወጪ አዲስ የመኖሪያ ህንፃ ፕሮጀክት ይፋ አድርጓል፡፡ ከቄራ ወደ ጎተራ በሚወስደው መንገድ ፔፕሲ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ (kings residence) ኪንግስ ሬዚደንስ ሲል የሰየመውና 80 የሚሆኑ አፓርትመንት ቤቶች ሚገነቡበት ፕሮጀክት ገዢዎች በተገኙበት ባሳለፍነው ቅዳሜ የመሬት ቁፋሮ ስራውን አስጀምሯል፡፡ የአባይ ሆምስ ሪልእስቴት አማካሪ የሆኑት አቶ ልኡል ደረጀ በሪል እስቴት ዘርፉ ከሚስተዋሉ ችግሮች መካከል የግንባታ ግብአት የዋጋ ግሽበት ዋነኛው ነው፤የግንባታ ወጪ ስለጨመረብኝ ገን
7 days ago2 min read
የሐምሌ 27 2018 የውጪ ሀገር ወሬዎች
#ኢራን በኢራን ለጠላት ሲሰልሉ ተደርሶባቸዋል የተባሉ ሁለት ግለሰቦች በሞት ተቀጡ፡፡ ሁለቱ ሰዎች በሞት የተቀጡት በፍርድ ቤት የእስራኤል ሰላዮች በመሆን ጥፋተኝነታቸው ስለተረጋገጠባቸው ነው መባሉን አልጀዚራ ፅፏል፡፡ በሞት የተቀጡት ግለሰቦች የወታደራዊ እና የደህንነት ተቋማትን መገኛ አመልካች መረጃዎችን ለእስራኤሉ የውጭ የስለላ ተቋም ሞሳድ ባልደረቦች ሲያቀብሉ ነበር ተብሏል፡፡ የፅሁፍ እና የምስል መረጃዎችን ለሞሳድ እንደላኩ ተረጋግጦባቸዋል ተብሏል፡፡ እስራኤል ኢራን ውስጥ የስለላ እጇ በጣሙን የረዘመ እንደሆነ ይነገራል፡፡ ኢራን ውስጥ ከዚህ ቀደምም ለእስራኤል ሰለላ ሲያቀላጥፉ ነበር የተባሉ በርካታ ሰዎች በሞት መቀጣታቸው መረጃው አስታውሷል፡፡ #ሱዳን በሱዳን ዳርፉር በባህላዊ የፍርድ ስፍራ በተፈፀመ የድሮን ጥቃት 35 ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውን የሰ
7 days ago2 min read
ፕሮግራሞች
bottom of page
_edited.jpg)
