top of page


ጥብቅ የገንዘብ ፖሊሲው የዋጋ ግሽበቱ ነጠላ ድጅት እስኪደርስ ድረስ ይቀጥላል ተባለ፡፡
ታህሳስ 21/2018 ጥብቅ የገንዘብ ፖሊሲው የዋጋ ግሽበቱ ነጠላ ድጅት እስኪደርስ ድረስ ይቀጥላል ተባለ፡፡ ይህም የባንኮች የብድር አሰጣጥ ላይ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ተጥሎ የቆየው ገደብ እንደሚቀጥል ያሳያል፡፡ ባንኮች ለአስቀማጮች ይሰጡት የነበረው የ7 በመቶ ወለድ በብሔራዊ ባንክ የተወሰነ እንደነበር ይታወሳል፡፡ አሁን ባንኮች እና ቆጣቢዎች እንዲደራደሩበት ወይም ለገበያው እንዲተው የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ ወስኗል፡፡ በብሔራዊ ባንክ ስር የተቋቋመ የገንዘብ ፖሊስ ኮሚቴ ዛሬ አምስተኛ ዙር ስብሰባውን አካሂዶ መግለጫ አውጥቷል፡፡ ለዛሬ ስብሰባውም የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴው የተለያዩ 4 ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡ የብሄራዊ ባንክ የ15 በመቶ የፖሊሲ ተመን ባለበት እንዲቀጥል የሚለው የመጀመሪያው ውሳኔ ነው፡፡ በሌላ በኩል ኮሚቴው በባንኮች ያለው የጥሬ ገንዘብ ክ
Dec 30, 20252 min read


ምጣኔ ሐብት - ኢትዮዽያ የባቡር መሰረተ ልማት!
ታህሳስ 9/2018 ምጣኔ ሐብት - ኢትዮዽያ የባቡር መሰረተ ልማት! ኢትዮዽያ የባቡር መሰረተ ልማትን በአራቱም አቅጣጫ ገንብታ ወደ ኢኮኖሚው ብታስገባው የሚፈጥረው አቅም ቀላል የሚባል አይደለም። ቀድሞም ቢሆን በልዩ ልዩ ምክንያት የሚደነቀቃፈው የኢትዮዽያ የገቢና ወጭ ንግድ፤ አሁን ግን ወጥ በሆነ የሎጅስቲክስ አሰራር ለውጥ እየተቆጠረበት እንደሆነ ተሰምቷል። ከዚህ መአዘን ከገቢ እቃዎች መካከል፤ የኢትዮጵያን ግዙፍ ማሽነሪዎች፣ የኮንስትራክሽን እቃዎች፣ ማዳበሪያ ዘይት ነዳጅ እና ሌላውንም የሚያጓጉዘው የኢትዮ ጅቡቲ ምድር ባቡር የሎጅስቲክስ ስራውን እያቃለለ እንደሆነ ተናግሯል። በተለይ በባቡር መሰረተ ልማት ላይ የተንጠለጠለ የሎጅስቲክስ እና ጠንካራ ኢኮኖሚ ለመገንባት ምድር ባቡሩ መንገድ መጀመሩ ተሰምቷል። ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ… ተህቦ
Dec 18, 20251 min read


ምርት ለማጓጓዝ ከፍተኛ ቢሮክራሲና የተጠላለፈ አንደኛው ፈተና
ጥቅምት 26 2018 #ምጣኔ_ሀብት ለዘመናት የኢትዮጵያን ወጪ ንግድ ሲረብሽ የነበረው ጉዳይ የኮንቴይነር እጥረት፣ የአስተሻሸግ ችግር እና ቅሸባ እንደሆነ ተደጋግሞ ይነሳል። ይኸው ችግር ኢትዮጵያ በዓለም ገበያ የምታቀርባቸውን ምርቶች እንዲወድቁ ወይም እንዲመለሱ አድርጓል። ከዚህም ባለፈ ምርት ለማጓጓዝ ከፍተኛ ቢሮክራሲና የተጠላለፈ የሎጅስቲክስ ስራም አንደኛው ፈተና ነው። በአየር፣ በየብስ፣ በባህር፣ በባቡር፣ የሎጅስቲክስ ስራዋን ማቀላጠፍ ያላወቀችበት ኢትዮዽያ አሁንም ከዚህ መዓዘን ብዙ ስራ ይጠብቃታል። ይህ በመሆኑም ከወጪ ንግድ የታሰበውን ያህል የውጪ ምንዛሪ ለመለቃቀም ፈትኖ ቆይቷል። በተለይ በወጪ ንግድና ሌላውም ንግድ የሚሳተፉ በሙሉ የሎጀስቲክስ መደነቃቀፍን አሁንም ያነሳሉ፡፡ ከዚህም በላይ የኢትዮዽያ ወጭ ንግድ የውድድር
Nov 5, 20251 min read


ምጣኔ ሀብት - ባንኮች ለአገልግሎት የሚጠይቁት ክፍያ
በተለያየ ጊዜ ባንኮች ለአገልግሎት የሚጠይቁት ክፍያ እየጨመረ ነው። ይህ የአገልግሎት ክፍያ በተለይ ተደጋጋሚ አገልግሎት የሚፈልጉ ደንበኞችን ቅር አሰኝቷል። የግል ባንኮች በአንድ በኩል የቢሮ እና የባንክ ስራው ላይ ተፎካካሪና ተወዳዳሪ መሆን ሲገባቸው፤ የህንፃ ግንባታና ኪራይ ላይ መግባታቸውም ጥያቄ ይፈጥራል። ለመሆኑ በዲጂታል ዘመን የወረቀት ስራና ሌላውም የቀለለላቸው ባንኮች እንዴት የአገልግሎት ክፍያቸው ከፍተኛና ቅር የሚያሰኝ ሊሆን ይችላል ተብሎ ይጠየቃል። አቶ ያዕቆብ በቀለ ፌደራሊዝም እና ኢኮኖሚክስ ተንታኝ ናቸው፡፡ ሙሉ ዘገባውንያድምጡ… ተህቦ ንጉሴ ጥቅምት 10 2018 የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… 👇👇👇 🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/ 🎥YouTube https://tinyurl.com/37
Oct 24, 20251 min read


ጥቅምት 13 2018 - የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ባለሞያዎች ማህበር የኢትዮጵያ ብድር እዳ ጫና ከአጠቃላይ ሀገራዊ ምርቱ 39 በመቶ ደረጃ እንዳለው ተናገረ
የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ባለሞያዎች ማህበር የኢትዮጵያ ብድር እዳ ጫና ከአጠቃላይ ሀገራዊ ምርቱ 39 በመቶ ደረጃ እንዳለው ተናገረ፡፡ የእርዳታና ድጋፍ መቀነስም ከቀጠሉ ግጭቶችና መሰል ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ጋር ተዳምሮ ችግሩን እንዲያከፋው ቅድሚያ የሚያስፈልገውን እየለዩ መፍትሄ ማበጀት ያስችላል ብሏል፡፡ ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ …. ተህቦ ንጉሴ የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… 👇👇👇 🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/ 🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478 🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1 📘Facebook፡ https://tinyurl.com/4tx8t8wm 💬WhatsApp ፡ https://tinyurl.com/ycxjmm3s 🐦X :...
Oct 23, 20251 min read


መስከረም 13 2018 - የብር የመግዛት አቅም በገበያው እንዲወሰን ከተደረገ በኋላ ከውጭ ምንዛሪ ጋር ተያይዞ ያለው ገበያ ምን ይመስላል?
በኢትዮጵያ የብር የመግዛት አቅም በገበያው እንዲወሰን ከተደረገ በኋላ አጠቃላይ በተለይ ከውጭ ምንዛሪ ጋር ተያይዞ ያለው ገበያ ምን ይመስላል? እኛ የጠየቅናቸው የኢትዮ ፎርኤክስ የውጭ ምንዛሪ ቢሮ ስራ ኃላፊ አቶ...
Sep 23, 20251 min read


ነሐሴ 26 2017 ኢትዮጵያ በገንዘብ እና አስተዳደሩ ዙሪያ የወሰደችው ጠበቅ ያለ መስመር ለፋይናንስ ሥርዓቱ ምን ዓይነት መልክ ሰጠው?
#ምጣኔ_ሐብት ኢትዮጵያ ገንዘብ ሥርዓቱን ይያዝ ወግና ደንቡን ይወቅበት፤ አገዛዙንም ይረዳበት ስትል ጥብቅ የገንዘብ መጓዣ መንገድ ለይታለች። አጠቃላይ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውንም በብሔራዊ ደረጃ በሀገር ውስጥ ልጆች...
Sep 1, 20251 min read


ነሐሴ 23 2017 - በባንኮች ላይ ተጥሎ የቆየው የብድር ገደብ ገበያው በሚፈልገው ልክ እየታየ ይለቀቃል ተባለ
በባንኮች ላይ ተጥሎ የቆየው የብድር ገደብ ከመጪው መስከረም ወር ጀምሮ ገበያው በሚፈልገው ልክ እየታየ ይለቀቃል ተባለ፡፡ በዚህም ከ2017 በጀት ዓመት 500 ቢልየን ብር ብልጫ ያለው 1.3 ትሪልዮን ብድር በባንኮች...
Aug 29, 20251 min read


ነሀሴ 20 2017 - መንግስት እንደዳለው የኢትዮጵያ ገበያ በቁጥጥር የሚታረም ይሆን?
መንግስት ለሰራተኞች የደመወዝ ጭማሪ ለማድረግ ማቀዱን አስቀድሞ መናገሩ በገበያው ላይ ሰው ሰራሽ የዋጋ ጭማሪ ሊኖር ይችላል? የሚል ስጋት ፈጥሯል፡፡ በእርግጥ ተቆጣጣሪ መስሪያ ቤቱም ይህን የሚያደርጉ ነጋዴዎች ላይ...
Aug 26, 20251 min read


ትምህርት የማህበረሰብ አገልግሎት መሆን ሲገባው እንዴት ወደ ንግድ መስመር ሊገባ ይችላል?
#ምጣኔ_ሐብት ሁሉም ፊቱን ወደ ትምህርት ያዙር፣ ትምህርት ከንግድ እና ቢዝነስ ጠባይ ይላቀቅ፣ ትምህርት ፈፅሞ ንግድ አይደለም ሊሆንም አይችልም ሲባል ምን ማለት ይሆን? በእርግጥ በኢትዮጵያ #ትምህርት ንግድ ነው፤...
Aug 14, 20251 min read


ነሀሴ 2 2017 - የኢትዮጵያ ባንኮች በመዋሃድ የተሻለ ካፒታልና ጉልበት እንዲኖራቸው እየተመከሩ ነው፡፡
የውጪ ባንኮች በኢትዮጵያ ስራ እንዲጀምሩ በሩ ከተከፈተ 3 ዓመት አለፈው፤ ግን እስካሁን ፍላጎት ካሳዩ ባንኮች በቀር ወደ ኢትዮዽያ ገብቶ ስራ የጀመረ የለም። ይህ ስራ በባንኮች መካከል ፉክክሩን እንደሚያጠናክረው...
Aug 8, 20251 min read


ሐምሌ 22 2017 - አለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት በማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው አተገባበር ላይ ስጋት አለኝ ብሏል
የፀጥታ ችግሮች እልባት አለማግኘታቸው፣ በጥቁር ገበያውና በመደበኛው የምንዛሪ ዋጋ መካከል ልዩነቱ እየሰፋ መሄዱ፣ የታሰበውን ያህል የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት አለመገኘቱ፣ እርዳታና ድጋፎች መቀነሳቸውና ሌላውንም...
Jul 29, 20251 min read


ሐምሌ 18 2017 - ኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ ለውጥ ለማምጣት ያለመችው እቅድ እንዲሳካ ከአጠቃላይ ዓመታዊ ምርቷ፤ ከ13 በመቶ በላይ ተጨማሪ ገንዘብ ያስፈልጋታል ተባለ
ኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ የመዋቅር ለውጥ ለማምጣት ያለመችው እቅድ እንዲሳካ ከአጠቃላይ ዓመታዊ ሀገራዊ ምርቷ፤ ከ13 በመቶ በላይ ተጨማሪ ገንዘብ ያስፈልጋታል ተባለ፡፡ ለዚህም ከፍተኛ ገቢ መሰብሰብ አለባት የተባለ ሲሆን...
Jul 25, 20252 min read


ሐምሌ 15 2017 - ''1 ዓመት የሞላው ጥብቅ የገንዘብ ፖሊሲ፤ እስካሁን በመሰረታዊ መልኩ የዋጋ ግሽበቱን አላስተካከለውም'' የብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ
ኢትዮዽያ የወሰደችው 1 ዓመት የሞላው ጥብቅ የገንዘብ ፖሊሲ፤ እስካሁን ድረስ በመሰረታዊ መልኩ የዋጋ ግሽበቱን አላስተካከለውም ተባለ። ይህን ያሉት የኢትዮዽያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ ናቸው። እሳቸው አያይዘውም...
Jul 22, 20252 min read


ሰኔ 24 2017 - ለዘመናት የኢትዮጵያን ወጪ ንግድ ሲረብሽ የነበረው ጉዳይ
ለዘመናት የኢትዮጵያን ወጪ ንግድ ሲረብሽ የነበረው ጉዳይ የኮንቴይነር እጥረት፣ የአስተሻሸግ ችግር እና ቅሸባ እንደሆነ ተደጋግሞ ይነሳል። ይኸው ችግር ኢትዮጵያ በአለም ገበያ የምታቀርባቸውን ምርቶች እንዲወድቁ ወይም...
Jul 1, 20251 min read


ሰኔ 21 2017 - ብሔራዊ ባንክ አንዳንዴ ሊከስር ሌላ ጊዜ ደግሞ ከልክ በላይ ሊያተርፍ ይችላል ሲሉ የባንኩ ገዢ ተናገሩ
የባንኩ ገዢ ይህን የተናገሩት፤ በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ቀርበው ለፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ዓመታዊ ሪፖርታቸውን ባቀረቡበት ወቅት ነው፡፡ ቋሚ ኮሚቴው፤ ብሔራዊ ባንክ በምንዛሪ ተመን ለውጥ...
Jun 28, 20252 min read


ሰኔ 18 2017 - ምጣኔ ሐብት - የማክሮ ኢኮኖሚ ስርዓት ለውጡ
#ምጣኔ_ሐብት የኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሪ ገበያው፤ ሽያጭ ልዋጩ በሶስት የተከፈለ ነው። አንደኛው መደበኛው በባንኮች የሚከናወነው የየእለት ምንዛሪ ገበያ ነው። ሁለተኛው ፍቃድ ያገኙት ስድስቱ የግል የውጭ ምንዛሪ ገዥ እና...
Jun 25, 20251 min read


ሰኔ 9 2017 - ምጣኔ ሐብት - ኢትዮጵያ የሎጅስቲክስ ስራውና መንገዱ እንዴት እየሆነላት ነው?
#ምጣኔ_ሐብት የግዙፍ አየር መንገድ ባለቤት ሐገር የ “ኢትዮዽያ አየር መንገድ” ፤ የግዙፍ ቴሌኮም ኦፕሬተር ባለቤት “ኢትዮ ቴሌኮም “ እንዲሁም መንገድ ቀድማ የገነባች የባቡር መንገድ ከሁሉ በፊት ያነጠፈችው...
Jun 16, 20251 min read


ግንቦት 14 2017 - የኢትዮጵያ ባንኮች ለውጭ ምንዛሪ አገልግሎቶች እንዲያስከፍሉ የተቀመጠው ጣሪያ
ባንኮች ለሚሰጧቸው የውጭ ምንዛሪ አገልግሎቶች የሚያስከፍሉት ገንዘብ ከአራት በመቶ እንዳይበልጥ ተወስኗል። ውሳኔው ጥሩ የሚባል ቢሆንም የኢትዮጵያ ባንኮች ለውጭ ምንዛሪ አገልግሎቶች እንዲያስከፍሉ የተቀመጠው ጣሪያ...
May 22, 20252 min read


መጋቢት 17 2017 - ብሔራዊ ባንክ በኢኮኖሚ ውስጥ የተጠናከረው ለውጥ አለ ቢልም እኛ የጠየቅናቸው ባለሞያ በዚህ አይስማሙም
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ በዳግም ስብሰባው የገንዘብ አቅርቦት፣ የፋይናንስ ዘርፍ እንቅስቃሴዎችን፣ የገንዘብ ዝውውር፣ የፊስካል፣ የዋጋ ግሽበት እና አጠቃላይ የማክሮ ኢኮኖሚ ሁኔታውን ገምግሟል።...
Mar 26, 20251 min read


የካቲት 20 2017 - የኢትዮጵያ ገንዘብ የመግዛት አቅም ከጀመረው የቁልቁለት ጉዞ የማቆሚው መላ ምን ይሆን?
ከዶላር አንፃር የኢትዮጵያ የመገበያያ ገንዘብ የመግዛት አቅም ከጀመረው የቁልቁለት ጉዞ የማቆሚው መላ ምን ይሆን? የብር የመግዛት አቅም ባለፉት 6 ወራት ብቻ ከመቶ በመቶ በላይ ወርዷል፡፡ ገበያ መር ነው የተባለው...
Feb 27, 20252 min read
ፕሮግራሞች
bottom of page








