የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኤርትራ ውስጥ የተያዘበትን ገንዘብ ለማስለቀቅ ወደ ክስ ቢያመራም በፖለቲካ ውሳኔ ምክንያት ገንዘቡ እንደተያዘበት መሆኑን ተናገረ፡፡
- 41 minutes ago
- 2 min read
ሐምሌ 23 2018
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኤርትራ ውስጥ የተያዘበትን ገንዘብ ለማስለቀቅ ወደ ክስ ቢያመራም በፖለቲካ ውሳኔ ምክንያት ገንዘቡ እንደተያዘበት መሆኑን ተናገረ፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለአለም አቀፍ ተጓዦች በአብዛኛው የበረራ ትኬት የሚሸጠው በየሃገሩ ገንዘብ እንደሆነና ሃገራት ሲፈቅዱ ብቻ ትኬቶችን በዶላር እንደሚሸጥ ተናግሯል፡፡
ከሽያጩ በኋላ ትኬት የተሸጠለት ሃገር ገንዘቡን በዶላር ወይም በዩሮ እንዲቀይንልን እንጠይቃለን፤ አብዛኞቹ ይቀይራሉ፤ አንዳንዶች የውጭ ምንዛሪ የለንም በሚል ለረጅም ጊዜ ሳይቀይሩንን ይቆያሉ ያሉት የአየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው፤ በኤርትራም የገጠመን ይኸው ነው፤በኤርትራ ገንዘብ የሸጥነውን የትኬት ገንዘብ ወደ ዶላር ቀይረን ማውጣት ሳንችል የኢትዮጵያ ኤርትራ ውጥረት ውስጥ ገባ፤ ጉዳዩን ወደ ኤርትራ ፍርድ ቤት ወስደን ገንዘቡን ለመጠየቅ ብንሞክርም እዚያ ባለው የፖለቲካ ውሳኔ ምክንያት ጉዳያችን በፍርድ ቤትም እንዳይንቀሳቀስ ተደርጎ ገንዘቡ እንደተያዘ ነው፤አመቺ ጊዜ ሲመጣ እንጠይቃለን ብለዋል፡፡
ከዚህ ቀደም እንደተዘገበው በኤርትራ የተያዘው ገንዘብ 3.7 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ሲሆን በዚህ መንገድ በተለያዩ ሃገራት የተያዘባቸው ገንዘብ እንዳለ የጠቆሙት ዋና ስራ አስፈፃሚው አቶ መስፍን፤ የተጠራቀመ በጣም ብዙ ሲሉ የገለፁት የገንዘብ መጠን በተመሳሳይ በሩሲያና በሞዛምቢክ ሃገራት ተይዞብናል ለማስለቀቅ ጥረት ላይ ነን ብለዋል፡፡ የአብዛኞቹ ሃገራት የትኬት ሽያጭ በስምምነት እየተከወነ መሆኑን በመጥቀስ፡፡
በሌላ በኩል አየር መንገዱ ለሃገር ውስጥ በረራ የቲኬት ዋጋ የተመነው በብር ነው፤ በዶላር ያላደረግነው የምንዛሪ ዋጋ ከፍና ዝቅ ሲል ተጓዦች ጫና እንዳይፈጥርባቸው ነው ብሏል፡፡
የሃገር ውስጥ በረራ ከጊዜ ወደ ጊዜ ዋጋው እንዲጨምር አድርገናል፤ይህም የሆነበት ምክንያት ከምናወጣው ወጪ ጋር አልጣጣም እያለ እያከሰረን ስለሆነ ነው፤አሁን የምንሸጥበት ዋጋ አትራፊ አይደለም የሚሉት አቶ መስፍን፤በበዓላት ወቅት ጠብቃችሁ የቲኬት ዋጋ ትጨምራላችሁ እንባላለን፤ነገር እኛ ዋጋ የምንጨምረው በበዓሉ ምክንያት በመደብናቸው ተጨማሪ አውሮፕላኖች ላይ እንጂ፤ለበዓላቱም ቢሆን የሚቆርጡት ቲኬት መደበኛውን ከሆነ የዋጋ ጭማሪ አይኖረውም ሲሉም አስረድተዋል፡፡
በሃገር ውስጥ ከቀን በተጨማሪ በባህር ዳር፣ ጎንደርና መቀሌ የማታ በረራ ተጀምሮ የነበረ ቢሆንም በፀጥታ ችግር ምክንያት ተቋጧል ተብሏል፡፡
ይሁንና በክልሎች ያሉ አየር ማረፊያዎች ማታ ለመብረር አመቺ እንዲሆኑ መብራትና ሌላ ሌላውም እየተሟላ ነው፤ከመጪው 2019ዓ.ም ጀምሮ የሃገር ውስጥ የምሽት በረራ ይጀመራል መባሉን ሰምተናል፡፡
አየር መንገዱ 150 በደረሱት አለም አቀፍ የበረራ መዳረሻዎቹና በ25 የሃገር ውስጥ መዳረሻዎቹ በተጠናቀቀው ዓመት ከ20 ሚሊዮን በላይ መንገደኞችን ማጓጓዙንም ተናግሯል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ...
ምንታምር ጸጋው
_edited.jpg)


Comments