top of page

የሐምሌ 23 2018 የውጪ ሀገር ወሬዎች

  • 9 minutes ago
  • 2 min read



በግብፅ የሜዴትራኒያን የባህር ዳርቻ የነበረ የአሜሪካ የጋዝ ማጠራቀሚያ መርከብ በድሮን ተመታ ተባለ፡፡


ሁለት የደህንነት ምንጮች መርከቡ በድሮን እንደተመታ አረጋግጠውልኛል ሲል ሬውተርስ ፅፏል፡፡


መርከቡ በድሮን እንደተመታ በእሳት መያያዙ ታውቋል፡፡


ቃጠሎው ወደ ሌላ መርከብም ተጋብቶ ነበር ተብሏል፡፡


ኋላ ግን ቃጠሎው በቁጥጥር ስር መዋሉ ተጠቅሷል፡፡


በእሳት ተያይዘው የነበሩት መርከቦች ባህረኞች አንዳችም ጉዳት ሳይገጥማቸው እንዲወጡ ተደርጓል ተብሏል፡፡


ለጥቃቱ ሀላፊው እኔ ነኝ ያለ ወገን እንደሌለ መረጃው አስታውሷል፡፡




በኢራቅ ካታኢብ ሔዝቦላህ የተሰኘው ታጣቂ ቡድን መንግስት የአገሪቱን ሉአላዊነት ሊያስከብር ይገባል አለ፡፡


ቡድኑ ለመንግስት ያቀረበው ጥያቄ በማስጠንቀቂያ ጭምር የታጀበ እንደሆነ አልጀዚራ ፅፏል፡፡


የቡድኑ ማስጠንቀቂያ የተሰማው አሜሪካ እና ሳውዲ አረቢያ በይዞታው ላይ ያነጣጠረ ጣምራ ድብደባ መፈፀማቸውን ተከትሎ ነው፡፡


በቡድኑ ይዞታ ላይ ድብደባ የተፈፀመው ቀደም ሲል ሳውዲ አረቢያ የኢራቅ ታጣቂዎች በነዳጅ አውታሮቼ ላይ ያነጣጠረ የድሮን ጥቃት ሰንዝረዋል የሚል ክስ ካሰማች በኋላ ነው፡፡


ካታኢብ ሔዝቦላህ ለእነ ሳውዲ ጥቃት የአፀፋ ምላሽ በመስጠት የአገሪቱን ሉአላዊነት እንዲያስከብር ማስጠንቀቁ ተሰምቷል፡፡


የሳምንት የጊዜ ገደብም አስቀምጧል ተብሏል፡፡


ታጣቂ ቡድኑ አፍቃሪ ኢራን መሆኑ ይነገራል፡፡



ሳውዲ አረቢያ በቀይ ባህር የመርከቦችን ጉዞ ደህንነት አረጋጋጭ አለም አቀፍ የጦር ጥምረት እንዲመሰረት ትሻለች ተባለ፡፡


ስለ አለም አቀፍ ጥምረቱ ውስጥ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ሹሞች ነግረውኛ ብሎ ሬውተርስ እንደዘገበ አልጀዚራ ፅፏል፡፡


የየመን ሁቲዎች በቅርቡ በዛው በቀይ ባህር በሳውዲ አረቢያ የጭነት መርከቦች ላይ ጥቃት መሰንዘራቸውን መረጃው አስታውሷል፡፡


ሰሚናዊውን የየመን ክፍል የሚያስተዳድሩት ሁቲዎቹ የሳውዲ አረቢያን ወደቦች በሙሉ እንከረቻችምባታለን ብለው ከዛቱ ከሳምንት በላይ ሆኗቸዋል፡፡


አሁን ሳውዲ በቀይ ባህር የመርከቦችን ሰላማዊ ጉዞ ለማረጋገጥ አለም አቀፍ የጦር ጥምት እንዲመሰረት በስም ካልተጠቀሱ አገሮች ጋር ንግግር እያደረገች ነው ተብሏል፡፡


ይሁንና የሳውዲ አረቢያ የኮሙኒኬሽን መስሪያ ቤት ስለ ጉዳዩ እንዲያብራራ በሬውተርስ ቢጠየቅም ምላሽ እንዳልሰጠ በመረጃው ተጠቅሷል፡፡


የየመኖቹ ሁቲዎች የኢራን ሁነኛ የፖለቲካ ሸሪኮች እና የጦር አጋሮች መሆናቸው ይነገራል፡፡



የአሜሪካ ጦር ኢራንን ዳግም መደብደብ ጀመረ፡፡


ኬሽም ፣ ኪሽ ፣ ባንዳር አባስ ፣ አባዳን እና ቡሸር በአሜሪካ ጦር ከተደበደቡት የኢራን ከተሞች መካከል እንደሚገኙበት አልጀዚራ ፅፏል፡፡


ቀደም ሲል የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን ከትናንት በስቲያ በዮርዳኖስ በሚገኝ የአሜሪካ የጦር ተቋም ላይ ያነጣጠረ ጥቃት በመሰንዘሯ በከባዱ እንቀጠቅጣታለን ሲሉ ዝተው ነበር፡፡


የአሜሪካ የድብደባ ዒላማዎች ምንነትም ሆነ በድብደባው ስለደረሰ ጉዳት በዝርዝር የተጠቀሰ ነገር የለም፡፡


ሆኖም ከባባድ ፍንዳታዎች የተሰሙባቸው ከተሞች እንዳሉ የኢራን መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል ተብሏል፡፡


አሜሪካ ድብደባዋን የቀጠለችው ሁለቱም አገሮች ለጥቂት ቀናት በጦር መጠቃቃታቸውን ገትተው ከሰነበቱ በኋላ ነው፡፡


የኢራኑ ጦርነት ቆመ ሲባል የማገርሸት አባዜ እንደተጠናወተው መረጃው አስታውሷል፡፡



የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራቅ ውስጥ በኢራን ደጋፊ ታጣቂዎች ላይ ከሳውዲ አረቢያ ጋር በጣምራ የፈፀምነው ድብደባ በኢራቅ መንግስት እውቅናና ትብብር ጭምር ነው ማለታቸው ተሰማ፡፡


ትራምፕ በአፍቃሪ ኢራኖቹ የኢራቅ ታጣቂዎች ይዞታዎች ላይ የተፈፀመው የሳውዲ እና የአሜሪካ ድብደባ ከባግዳድ አስተዳደርም ጋር በቅንጅት የተፈፀመ ነው ማለታቸውን ፎክስ ኒውስ ፅፏል፡፡


አሜሪካ ጦር ጥምር ድብደባው በአፍቃሪ ኢራኖቹ የኢራቅ ታጣቂዎች የስንቅ እና ትጥቅ ማከማቻዎች ላይ ያነጣጠረ ነበር ብሏል፡፡


ሳውዲ አረቢያ ቀደም ሲል የኢራቆቹ ታጣቂዎች በነዳጅ አውታሮቼ ላይ የሰነዘሩትን የድሮን ጥቃት አምክኛለሁ ማለቷን መረጃው አስታውሷል፡፡


ትራምፕ ድብደባውን የፈፀምነው በኢራቅ መንግስት እውቅና ጭምር ነው ቢሉም የኢራቅ መንግስት ግን ድብደባውን ማውገዙን የፃፈው ደግሞ አልጀዚራ ነው፡፡



የኔነህ ከበደ

Recent Posts

See All
የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን ማሳደግ፣አፍሪካዊያን የጋራ መጪ እድላቸውን እንዲቀርፁ ማገዝ ያስፈልጋል ተባለ።

ሐምሌ 23 2018 የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን ማሳደግ፣አፍሪካዊያን የጋራ መጪ እድላቸውን እንዲቀርፁ ማገዝ ያስፈልጋል ተባለ። የአፍሪካ ሀገሮች እርስ በእርስ፣በአፍሪካና በሩሲያ እንዲሁም አፍሪካ ከተቀረው ዓለም ጋር ያላትን የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ማሳደግን ዓለማው ያደረገ ዓለም አቀፍ ጉባኤ በተባበሩት መንግስታት የአ

 
 
 
Sheger App Logo
iOS Store
Google Play
  • Facebook
  • X
  • Youtube
  • TikTok
  • Telegram
  • Whatsapp

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page