በኢትዮጵያ እያንዳንዱ ብሄረሰብ የራሱን ታሪክ ብቻ ለይቶና አጉልቶ የሚያቀርብበት ስርዐት መቀየር እንዳለበት የታሪክ ምሁር ፕሮፌሰር ባህሩ ዘውዴ ተናገሩ ።
- 2 hours ago
- 1 min read
ሐምሌ 23 2018
በኢትዮጵያ እያንዳንዱ ብሄረሰብ የራሱን ታሪክ ብቻ ለይቶና አጉልቶ የሚያቀርብበት ስርዐት መቀየር እንዳለበት የታሪክ ምሁር ፕሮፌሰር ባህሩ ዘውዴ ተናገሩ ።
በኢትዮጵያ የብሄረሰቦች ታሪክ ጥልቅ ትስስር እና መስተጋብር ያለው ነው ብለዋል።
የኢትዮጵያ የታሪክ ባለሞያዎች ማህበር ከላይፍ ኤንድ ፒስ ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር ያዘጋጀው እና ትኩረቱን በኢትዮጵያ ታሪክ ዙሪያ ያደረገ ጉባዔ እየተካሄደ ነው፡፡
"ኢትዮጵያን ከፖለቲካ አመፃ ታሪክ እንዴት ነፃ ማውጣት ይቻላል" በሚል ርዕስ እየተካሄደ ባለው በዚህ ጉባዔ ላይ የተለያዩ ጥናታዊ ፅሁፎች እየቀረቡ ነው ።
የማህበሩ ፕሬዚዳንት የሆኑት የታሪክ ምሁር ፕሮፌሰር ባህሩ ዘውዴ ጉባዔው በኢትዮጵያ ታሪክ አፃፃፍ ዙሪያ ያሉ ችግሮችን የሚጠቁም እንደሆነ ነግረውናል።
አሁን ያለው የታሪክ አቀራረብ እያንዳንዱ ብሄረሰብ የራሱን ብቻ ለይቶና አጉልቶ የሚያቀርብበት እንደሆነ ጠቅሰዋል ።
ንጋቱ ረጋሳ
_edited.jpg)


Comments