top of page

ስለ እኛ

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡ ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ!ሸገር የእናንተ ነው!

23004430_10157336969774616_5269416509748584004_o.jpg

ታሪካችን

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬዲዮ መስከረም 23 ቀን 2000 ዓ.ም ሥራ የጀመረ

የመጀመሪያው የኢትዮጵያ የግል ኤፍ ኤም ሬዲዮ ጣቢያ ነው፡፡

የረጅም ጊዜ የሬዲዮ ሥራ ልምድ ባላቸው ባለሙያዎች የተቋቋመው ሸገር ኤፍ ኤም

102.1 ሬዲዮ በአድማጭ ዘንድ ተወዳጅነቱን ይዞ ለዓመታት ዘልቋል፤ ወደፊትም በዚሁ ይቀጥላል፡፡

ሸገር 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡ ሸገር በዚህ ረገድ ከኋላው ለተከተሉት የግል ሬዲዮ ጣቢያዎች ጭምር የይዘትም ሆነ የባለሙያ አበርክቶው ከፍተኛ ነው፡፡ የሸገር ዓላማ ዛሬም ሆነ ወደፊት ከወገናዊነት የነፃ ትክክለኛ የሕዝብ ድምፅ መሆን፣ ሥነ ምግባርን የጠበቀ የጋዜጠኝነት መርህን መከተልና የተሣካለት የኢንፎቴይመንት (Information & Entertainment) ሬዲዮ ጣቢያ መሆን ነው፡፡ ጣቢያችን ለማንም ባለመወገን ለሁሉም በታማኝነትና በመልካም ሥነ ምግባር መልካም አገልግሎት በመስጠት የሚያምንና ለእነዚህም እሴቶች ትልቅ ክብር የሚሰጥ ሬዲዮ ጣቢያ ነው:: በዚህ አጋጣሚ ጣቢያችን ሁልጊዜም ‹‹ሸገር የናንተ ሬዲዮ›› ለሚላቸው አድማጮቹ፣ አገልግሎታቸውንና ምርቶቻቸውን በማስተዋወቅ ለሚደግፉት አጋሮቹ ከፍተኛ ምስጋናውን ያቀርባል፡፡ እንደናንተ ያለ አድማጭና እንደናንተ ያለ አጋር ስላለን እድለኞች ነን፡፡

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!

bottom of page