top of page

በሕገ-ወጥ መንገድ ሰዎችን ወደ ስደት ልከዋል፣ ከተጎጂዎችም ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ተቀብለዋል ተብለው በተጠረጠሩ 16 ሰዎች ላይ ብይን ለመስጠት ፍርድ ቤት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

  • 22 hours ago
  • 2 min read

ሐምሌ 22 2018


በሕገ-ወጥ መንገድ ሰዎችን ወደ ስደት ልከዋል፣ ከተጎጂዎችም ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ተቀብለዋል ተብለው በተጠረጠሩ 16 ሰዎች ላይ ብይን ለመስጠት ፍርድ ቤት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።



በአደገኛ ሕገወጥ ሰው አዘዋዋሪነት ተጠርጥረው በፖሊስ ተይዘው ክስ የተመሠረተባቸው 16 ተከሳሾች ዛሬ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ቀርበው ክሳቸው ተሰምቷል።


ተጠርጣሪዎቹ በሰው ልጅ ለመነገድ በማሰብ የወንጀል ቡድን በማደራጀት፣ የሕገወጥ ሰዎች ዝውውር መረብ በመዘርጋት እንዲሁም ተጎጂዎቹ በየመን በኩል ወደ ሳዑዲ ዓረቢያ ገብተው የተሻለ ኑሮ እንደሚኖሩ ሐሰተኛ ተስፋ በመስጠትና በማሳመን ከተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች በመመልመል ሲልኩ እንደነበር በአቃቤ ሕግ የክስ መዝገብ ተጠቅሷል።


በሕገወጥ መንገድ የተወሰዱ ተጎጂዎች የኢትዮጵያን ድንበር እንደተሻገሩ ወደ ጅቡቲ ተወስደው፣ በየመን ሀገር በሚገኙ ለዚሁ ዓላማ በተዘጋጁ መጋዘኖች ታጉረው ከፍተኛ ኢ-ሰብአዊ ድርጊቶች ይፈጸሙባቸው እንደነበር በክሱ ተብራርቷል።


ተጠርጣሪዎቹ ተጎጂዎችን ወደ ቤተሰቦቻቸው ስልክ በማስደወል ከፍተኛ ገንዘብ ሲጠይቁ እንደነበር እና ገንዘብ መክፈል ላልቻሉ ቤተሰቦች ተጎጂዎችን እየደበደቡ፣ እንዲሁም እያሰቃዩ ቪዲዮ በመቅረጽ የሥነልቦና ጫና ሲፈጥሩ እንደነበርም ተረጋግጧል ይላል የአቃቤ ሕግ ክስ።


በዚህ መልኩ ከተጎጂዎች ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ በሕገ-ወጥ መንገድ መሰብሰባቸውን፣ ከ40,000 በላይ ሰዎችን በሕገ-ወጥ መንገድ ማዘዋወራቸውን፣ በሂደቱም ከ60 በላይ ሰዎች እንደሞቱ እንዲሁም በርካታ ሴቶች መደፈራቸውን በአቃቤ ሕግ የክስ መዝገብ ሰፍሯል።


አቃቤ ህግ በጠርጣሪዎቹ ላይ በሰው የመነገድ፣ በሕገ-ወጥ ሐዋላ እና በሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር (Money Laundering) በሚሉት 6 የክስ መዝገቦች ክስ አቅርቦባቸዋል፡፡


በዚህ መሠረት የ61 ሰዎች ሕይወት አልፏል፤ የ13 እና የ15 ዓመት ሕፃናትን ጨምሮ የ10 ሰዎች ደግሞ ደብዛቸው ጠፍቷል፤ ተደፍረው ያረገዙ ሴቶችም አሉ ሲል አቃቤ ሕግ ዛሬ ለችሎቱ አስረድቷል።


ተከሳሾቹ የዋስትና መብታቸው ቢከበርላቸው ከሀገር ሊወጡ ይችላሉ ሲልም የዋስትና መብታቸው ተከብሮ ከእስር እንዳይለቀቁ ጠይቋል፡፡


በተጨማሪም የተከሰሱበት ወንጀል ተደራራቢና ሦስቱም የክስ መዝገቦች ከ15 እስከ 25 ዓመት የሚያስቀጡ በመሆናቸው የዋስትና መብታቸው ቢከበርላቸው ዋስትናውን አክብረው ሊገኙ ስለማይችሉ ሊከለከሉ ይገባል ሲልም አስረድቷል፡፡


የተከሳሽ ጠበቆች በበኩላቸው ተከሳሾች ቋሚ የመኖሪያ አድራሻ ያላቸውና ቤተሰብ የመሠረቱ በመሆናቸው የዋስትና መብታቸውን አክብረው አይገኙም የሚለው የአቃቤ ሕግ ሀሳብ የሕግ መሠረት የለውም ሲሉ ተከራክረዋል።


በተደራራቢ ወንጀል ቢከሰሱም የዋስትና መብት ግዙፍ ሕገመንግሥታዊና ሰብአዊ መብት በመሆኑ ሊከለከል አይገባውም ሲሉም ለችሎቱ አመልክተዋል።


የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ወንጀል ምድብ ችሎት መዝገቡን መርምሮ በዋስትና ክርክሩ ላይ ብይን ለመስጠት ለሐምሌ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።


የፌዴራል ፖሊስ በአደገኛ ሕገወጥ አዘዋዋሪ መሐመድ ጣሂር አደን (ወርዲ) የሚመሩ 17 የተደራጁ የወንጀል ቡድን አባላትን በቁጥጥር ሥር አውሎ የምርመራ መዝገብ በሰውና በሰነድ ማስረጃ በማደራጀት ክስ ይመሠረትባቸው ዘንድ ለፍትሕ ሚኒስቴር መላኩን መናገሩን ይታወሳል።


ገዛ ጌታሁን

Recent Posts

See All
የሐምሌ 23 2018 የውጪ ሀገር ወሬዎች

#ግብፅ በግብፅ የሜዴትራኒያን የባህር ዳርቻ የነበረ የአሜሪካ የጋዝ ማጠራቀሚያ መርከብ በድሮን ተመታ ተባለ፡፡ ሁለት የደህንነት ምንጮች መርከቡ በድሮን እንደተመታ አረጋግጠውልኛል ሲል ሬውተርስ ፅፏል፡፡ መርከቡ በድሮን እንደተመታ በእሳት መያያዙ ታውቋል፡፡ ቃጠሎው ወደ ሌላ መርከብም ተጋብቶ ነበር ተብሏል፡፡ ኋላ ግን

 
 
 
የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን ማሳደግ፣አፍሪካዊያን የጋራ መጪ እድላቸውን እንዲቀርፁ ማገዝ ያስፈልጋል ተባለ።

ሐምሌ 23 2018 የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን ማሳደግ፣አፍሪካዊያን የጋራ መጪ እድላቸውን እንዲቀርፁ ማገዝ ያስፈልጋል ተባለ። የአፍሪካ ሀገሮች እርስ በእርስ፣በአፍሪካና በሩሲያ እንዲሁም አፍሪካ ከተቀረው ዓለም ጋር ያላትን የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ማሳደግን ዓለማው ያደረገ ዓለም አቀፍ ጉባኤ በተባበሩት መንግስታት የአ

 
 
 
Sheger App Logo
iOS Store
Google Play
  • Facebook
  • X
  • Youtube
  • TikTok
  • Telegram
  • Whatsapp

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page