top of page
በአገራዊ ምክክሩ እየተሳተፉ ያሉ ቤተ እስራኤላውያን ከምክከሩ በኋላ እውቅና ይሰጠናል ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉ ተናገሩ፡፡
ነሐሴ 1 2018 በአገራዊ ምክክሩ እየተሳተፉ ያሉ ቤተ እስራኤላውያን ከምክከሩ በኋላ እውቅና ይሰጠናል ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉ ተናገሩ፡፡ በኢትዮጵያ እስከሁን ድርሶብናል ላሉት "መገለል እና መገፋት "በዓይነትም፣ በገንዘብ ካሣ እንፈልጋለን ሲሉ በኢትዮጵያ የቤተ እስራኤል የልማት ድርጅት ፕሬዚዳንት አቶ በላይነህ ታዘብኩ ነግረውናል። እየተካሄደ በሚገኘው የምክክር ሂደት ላይ እየተሳተፉ ያሉ 26 ቤተ እስራኤላውያን በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የነበራቸው ድርሻ በአግባባቡ እንዲሰነድላቸው እና ማንነታቸውም እንዲታወቅላቸው መጠየቃቸውን አስረድተዋል፡፡ የኢትዮጵያ ቤተ እስራኤላውያን የማንነት እውቅና እና የሃይማኖት መሰል ጥያቄዎቻችን በምክከሩ ይፈታል የሚል ተስፋ አለን ብለዋል አቶ በላይነህ፡፡ ቤተ እስራኤላዊያን ህጋዊ እውቅና ያለው የአምልኮ እና የቀብር ስፍራ እ
7 hours ago1 min read
በፊንቴክ ኢንቨስትመንት ማጭበርበር የተጠረጠሩ አርቲስቶች በፍርድ ቤት በተያዘ ጉዳይ ላይ በማኅበራዊ ሚዲያ መግለጫ መስጠታቸውን ተከትሎ ፍርድ ቤቱ በከባድ ማስጠንቀቂያ እንዲታለፉ ወሰነ።
ነሐሴ 2018 በፊንቴክ ኢንቨስትመንት ማጭበርበር የተጠረጠሩ አርቲስቶች በፍርድ ቤት በተያዘ ጉዳይ ላይ በማኅበራዊ ሚዲያ መግለጫ መስጠታቸውን ተከትሎ ፍርድ ቤቱ በከባድ ማስጠንቀቂያ እንዲታለፉ ወሰነ። የተላለፈው መግለጫ ከዩቲዩብ እንዲወርድ እና ይቅርታ እንዲጠየቅ ፍርድ ቤቱ አዟል። ዐቃቤ ሕግ አርቲስቶቹ በፍርድ ቤት በተያዘ ጉዳይ ላይ በማኅበራዊ ሚዲያ መግለጫ በመስጠታቸው የዋስትና መብታቸው ተነስቶ በቁጥጥር ሥር እንዲውሉና ጉዳያቸውን በማረሚያ ቤት ሆነው እንዲከታተሉ ያቀረበውን አቤቱታ ፍርድ ቤቱ ውድቅ አድርጎታል። ዛሬ ነሀሴ 01 2018 ዓ/ም ጠዋት በነበረው ችሎት ተጠርጣሪ አርቲስቶቹ በጠበቆቻቸው አማካኝነት ለዐቃቤ ሕግ አቤቱታ በጽሑፍ ምላሽ የሰጡ ሲሆን፣ በፍርድ ቤት በተያዘ ጉዳይ ላይ ለምን መግለጫ እንደሰጡም ለችሎቱ የቃል ማብራሪያ አቅርበዋል። አ
7 hours ago1 min read
በቅርቡ የፀደቀውን ‘‘የቁልፍ መሠረተ ልማቶች የሳይበር ደህንነት አዋጅ‘‘ መመሪያን ባለመተግበር ሳይበር ጥቃት በተቋሙ ላይ የአገልግሎት መቋረጥን፣ የሀገር ደህንነት ማናጋት እና በዜጎች ህይወት ላይ ጉዳት ካደረሰ ሀላፊዎች ወይንም ሰራተኞች ከ7 አመት እስከ 10 አመት ፅኑ እስራት እንደሚቀጡ በአዋጁ መደንገጉ ተነገረ።
ነሐሴ 1 2018 በቅርቡ የፀደቀውን ‘‘የቁልፍ መሠረተ ልማቶች የሳይበር ደህንነት አዋጅ‘‘ መመሪያን ባለመተግበር ሳይበር ጥቃት በተቋሙ ላይ የአገልግሎት መቋረጥን፣ የሀገር ደህንነት ማናጋት እና በዜጎች ህይወት ላይ ጉዳት ካደረሰ ሀላፊዎች ወይንም ሰራተኞች ከ7 አመት እስከ 10 አመት ፅኑ እስራት እንደሚቀጡ በአዋጁ መደንገጉ ተነገረ። የደረሰው የሳይበር ጥቃት በቸልተኝነት የተፈፀመ ስህተት ከሆነ ደግሞ በሀላፊው ወይንም በተቋሙ ሰራተኛ ከ3 እስከ 5 አመት ቀላል እስራት እንደሚቀጡ በአዋጁ ተቀምጧል። የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ፣ በቅርቡ የፀደቀውን “የቁልፍ መሠረተ ልማቶች የሳይበር ደህንነት አዋጅ ”አስመልክተው ዛሬ ለመገናኛ ብዙኃን ማብራሪያ ሰጥተዋል። ዋና ዳይሬክተሯ በማብራሪያቸው በቁልፍ መሰረተ ልማቶ
9 hours ago2 min read


ከ500 በላይ አምራቾች፣ አስመጪና ላኪዎች ፣ የንግድ ወኪሎች እና አገልግሎት ሰጪዎች ይሳተፉበታል የተባለ ኤክስፖ በኤግዚቢሽን ማዕከል ሊካሄድ ነው፡፡
ነሐሴ 1 2018 ከ500 በላይ አምራቾች፣ አስመጪና ላኪዎች ፣ የንግድ ወኪሎች እና አገልግሎት ሰጪዎች ይሳተፉበታል የተባለ ኤክስፖ በኤግዚቢሽን ማዕከል ሊካሄድ ነው፡፡ ኤክስፖው የሚካሄደው ከነሀሴ 15 እስከ ጳጉሜ 5/2018 ዓ.ም ለ21 ተከታታይ ቀናት መሆኑን አዘጋጆቹ ከላኩልን መግለጫ ላይ ተመልክተናል፡፡ ሴንቸሪ ፕሮሞሽንና ኤቨንት አዘጋጅነት በተሰናዳው የአዲስ አመት ኤክስፖ የ2019 አዲስ አመትን በተለየ መልኩ ከንግዱ ህብረተሰብ ከጎብኚና ሸማቾች ጋር በአንድነት ፣ በሰላም፣ በፍቅር፣ በደስታ ለመቀበል የተዘጋጀ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡ ጎብኚዎች እና ሸማቾችን ወደ ኤክስፖው በሚያስገባቸው ትኬት ዕጣም የቤት አውቶሞቢል፣ ሞተር ሳይክል አንዲሁም ብስክሌት ይሸለማሉ ተብሏል፡፡ ሴንቸሪ ፕሮሞሽን እና ኤቨንትስ ባለፉት 27 ዓመታት ከ60 በላይ ኤግዚብሽኖች፣ የንግ
10 hours ago1 min read
በፊንቴክ ኢንቨስትመንት ማጭበርበር የተጠረጠሩ አርቲስቶች ላይ ዐቃቤ ሕግ ባቀረበው አቤቱታ ላይ ብይን ለመስጠት ለዛሬ ከሰዓት ቀጠሮ ተሰጠ።
ነሐሴ 1 2018 በፊንቴክ ኢንቨስትመንት ማጭበርበር የተጠረጠሩ አርቲስቶች ላይ ዐቃቤ ሕግ ባቀረበው አቤቱታ ላይ ብይን ለመስጠት ለዛሬ ከሰዓት ቀጠሮ ተሰጠ። በ"ፊንቴክ" ኢንቨስትመንት ሽፋን በተፈጸመ መጠነ ሰፊ የማጭበርበር ወንጀል ተጠርጥረው ክስ የተመሠረተባቸው ታዋቂ አርቲስቶች፣ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ሐምሌ 29 ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት ብይን ለመስጠት ለጥቅምት 2 ቀን 2019 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱ ይታወሳል። ነገር ግን ተከሳሾቹ "እግረኛው" በተሰኘ የማኅበራዊ ሚዲያ ገጽ ላይ ቀርበው መግለጫ መስጠታቸውን ተከትሎ፣ ዐቃቤ ሕግ ባለ 5 ገጽ የክስ አቤቱታ አቅርቦ ስለነበር ጉዳዩ ከሰዓት በኋላ በሌላ ችሎት እንዲታይ ተደርጎ ፣ ለዛሬ ነሐሴ 1 ቀን 2018 ዓ.ም. ጠዋት 4፡00 ሰዓት ቀጠሮ ሰጥቶ ነበር። ጠዋት በነበ
10 hours ago2 min read
በኢትዮጵያ ምግብ ነክ ባልሆኑ ምርቶች የሚታየው የዋጋ ግሽበት ላለፉት ስምንት ዓመታት እየጨመረ መምጣቱን አንድ የዘርፉ ባለሞያ ተናገሩ።
ነሐሴ 1 2018 በኢትዮጵያ ምግብ ነክ ባልሆኑ ምርቶች የሚታየው የዋጋ ግሽበት ላለፉት ስምንት ዓመታት እየጨመረ መምጣቱን አንድ የዘርፉ ባለሞያ ተናገሩ። ምግብ ነክ ያልሆኑ ምርቶች የዋጋ ግሽበት እንደ ትምህርት ፣ ጤና ፤ መኖሪያ ቤት ፣ ውሃና ፣ ኤሌክትሪክ ፣ ያሉ አገልግሎቶችን እንዲሁም አልባሳት እና ንጽህና መጠበቂያዎችን ያካትታል። በሚያዝያ 2018 ዓ ም ምግብ ነክ ባልሆኑ ምርቶች የተመዘገበው የዋጋ ግሽበት 9 ነጥብ 1 በመቶ እንደሆነ የኢትዮጵያ ስታስቲክስ አገልግሎት በጊዜው ተናግሯል። የግንቦት ወር ደግሞ 11 ነጥብ 1 በመቶ የዋጋ ግሽበት ምግብ ነክ ባልሆኑ ምርቶች ላይ ታይቷል ብሏል በሰኔ ወርም ምግብ ነክ ባልሆኑ ምርቶች ላይ የተመዘገበው የዋጋ ግሽበት 12 ነጥብ 2 በመቶ እንደሆነ የአገለግሎቱ መረጃ ያሳያል። ምግብ ነክ ባልሆኑ ምርቶች ላይ የ
11 hours ago1 min read
የነሐሴ 1 2018 የውጪ ሀገር ወሬዎች
#ሳውዲ_አረቢያ የሳውዲ አረቢያው የመከላከያ ሚኒስቴር በቀይ ባህር ለንግድ እና ለጭነት መርከቦች ሰላማዊ ምልልስ ከለላ የሚሰጥ አለም አቀፍ ጥምረት መመስረቱ በቀጠናው የደህንነት ስጋቱን የሚያሳይ ነው አለ፡፡ ሳውዲ አረቢያ እና ሌሎች 13 አገሮች ባለፈው ሳምንት አለም አቀፉን ጥምረት መመስረታቸውን አረብ ኒውስ ፅፏል፡፡ ጥምረቱ የተመሰረው የየመን ሁቲዎች የሳውዲ አረቢያን ወደቦች በሙሉ እንከረቻችምባታለን ብለው ከዛቱ እና በተወሰኑ መርከቦቿ ላይ ጥቃት መፈፀማቸውን ተከትሎ ነው፡፡ ሁቲዎቹ በሳውዲ መርከቦች ላይ ጥቃት ማድረሳቸውን ገፍተውበታል ተብሏል፡፡ ሳውዲ ከራሷ ባለፈ በአሁኑ ወቅት በኤደን ባህረ ሰላጤ ፣ በባብኤል መንደብ ወሽመጥ እና በመላው ቀይ ባህር ለአለም አቀፍ የንግድ መርከቦች ደህንነት አስጊ እየሆነ መምጣቱን እያጎላቸው ነው፡፡ ርዕሰ ከተማዋ ሰ
11 hours ago2 min read
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በ2018 በጀት አመት 118.91 ቢሊዮን ብር ሰበሰብኩ አለ።
ነሐሴ 1 2018 የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በ2018 በጀት አመት 118.91 ቢሊዮን ብር ሰበሰብኩ አለ። ገቢውም ከ2017 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር 88.4 በመቶ እድገት አሳይቷል ተብሏል። ይህ የተባለው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የ2018 በጀት አመት የስራ አፈፃፀሙን እና የ2019 በጀት አመት እቅዱን በተመለከተ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው። አገልግሎቱ ከኢነርጂ ሽያጭ፣ ከአዲስ ደንበኞች መስተንግዶ፣ ከማያገለግሉ ንብረቶች ሽያጭ እና ከሌሎች ልዩ ልዩ የገቢ ምንጮች 115.86 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ ሲሰራ እንደነበር ያነሱት የተቋሙ ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢንጅነር ጌቱ ገረመው 118.91 ቢሊዮን ብር በመሰብሰብ 103 በመቶ አፈፃፀም ማስመዝገብ ተችሏል ብለዋል። በበጀት ዓመቱ ከኢነርጂ ሽያጭ 75.17 ቢሊዮን ብር ለ
11 hours ago2 min read


ጥብቅ የገንዘብ ፖሊሲው መቀጠሉ አላሰራ ያሉ የህግ ማዕቀፎች እና ሌሎች የግሉን ዘርፍ እየፈተኑት ነው፡፡
ነሐሴ 1 2018 መንግስት ከአለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት ጋር በጋራ ስራ ላይ እያዋለው ያለው የኢኮኖሚ ማሻሻያ አንዱ ዓላማ የግሉን ዘርፍ በማበርታት የኢኮኖሚው ቀዳሚ ተዋናይ እንዲሆን ማስቻል ነው፡፡ በተግባር ደግሞ ጥብቅ የገንዘብ ፖሊሲው መቀጠሉ አላሰራ ያሉ የህግ ማዕቀፎች እና ሌሎች የግሉን ዘርፍ እየፈተኑት ነው፡፡ መፍትሔው ምንድነው? ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ.... ትዕግስት ዘሪሁን
13 hours ago1 min read
ፕሮግራሞች
bottom of page
_edited.jpg)
