top of page


ጥቅምት 20 2018 የዳሸን ሱፐር አፕ ደንበኞች ቁጥር ከ1 ሚሊዮን በላይ መድረሱን ባንኩ ተናገረ።
የዳሸን ሱፐር አፕ አንድ ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በሚሊዮን የሚቆጠር ደንበኛና በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ዕለታዊ የገንዘብ ዝውውር እየተፈፀመበት ይገኛል ሲለሰ ባንኩ ከላከልን መግለጫ ላይ ተመልክተናል፡፡ ይህንን በዛሬው ዕለት በዳሸን ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላደረጉ አካላትና የሥራ ክፍሎች የእውቅና አሰጣጥና የፓናል ውይይት መርሃግብር መዘጋጀቱም ተጠቅሷል፡፡ የዳሸን ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ አስፋው ዓለሙ፣ ዳሸን ሱፐር አፕ ይፋ በተደረገ አንድ ዓመት ውስጥ አንድ ሚሊዮን ተጠቃሚዎች ይኖሩታል የሚለውን ዕቅድ በዘጠኝ ወራት ብቻ ማሳካት መቻሉን ተናግረዋል። የዳሸን ሱፐር አፕን ላበለፀገው የኤግላይን ሲስተም ቴክኖሎጂ ለባንኩና ለአገር ለሚያደርገው አስተዋፅኦ አቶ አስፉው ምስጋና አቅርበዋል፡፡ ዳሸን ባንክ ‘’ሱፐር አፕ’’ ባንኩ
3 hours ago1 min read


ጥቅምት 20 2018 - የኮንሶ የእርከን ስራ ላይ አደጋ መደቀኑን፣ ማህበረሰቡም የአኗኗር ዘይቤው በአሉታዊ መልኩ እየተቀየረ መሆኑን ጥናት አሳየ
የአየር ንብረት ለውጥ በዓለም ቅርስነት የተመዘገበውን የኮንሶ የእርከን ስራ ላይ አደጋ መደቀኑን፣ ማህበረሰቡም የአኗኗር ዘይቤው በአሉታዊ መልኩ እየተቀየረ መሆኑን ጥናት አሳየ፡፡ የኮንሶ የድንጋይ እርከኖች በዩኔስኮ መዝገብ የሰፈሩ ማህበረሰቡንም ያስመሰገኑ ሆነው ዓመታት አልፈዋል። ገደላማውን፣ ፈታኝ ሆነውን መልካም ምድር አካፋና ዶማ ይዘው ባህላዊ እውቀታቸውን ተጠቅመው ለእርሻ ስራ አውለውታል፡፡ ተፈጥሮን ተንከባክበው ከትውልድ ትወልድ አስተላልፈውታል፡፡ በኮንሶ ምድር የሚሰራው የእርከን ስራ፤ ኢትዮጵያም መታወቂያዬ ብላ በዓለም ቅርስነት ካስመዘገበችው 15 ዓመታት ሆኗታል፡፡ ዛሬ ግን እዚያ ድንጋይ እየጠረቡ፣ መሬት እየቆፈሩ የሚሰሩ እጆች፣ የሚያርሱ ወጣቶች በአካባቢ ብዙም አይታዩም፡፡ ወጣቶቹ ፊታቸውን ራቅ ወዳሉ አካባቢዎች ሄደው
4 hours ago1 min read
ጥቅምት 20 2018 - የፍትህ ስርዓት ችግር ምክንያት ስራው ላይ እክል እየገጠመው መሆኑን የኢትዮጵያ ህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም ተናገረ
የሚሰጣቸውን ምክረ ሃሳቦች ያለ በቂ ምክንያት የማይፈፅሙ ተቋማት በህግ እንዲጠየቁ ለማድረግ ቢሞክርም ባለው የፍትህ ስርዓት ችግር ምክንያት ስራው ላይ እክል እየገጠመው መሆኑን የኢትዮጵያ ህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም ተናገረ፡፡ ተቋሙ የአስተዳደር በደል ደረሰብን እምባችን ይታበስልን የሚሉ አቤት ባዮችን ቅሬታ በመቀበልና በማጣራት እንዲሁም አስተዳደራዊ በደሎች መፈፀማቸውን ሲያረጋግጥ ማስተካከያ እንዲደረግ ለተቋማት ምክረ ሃሳቦችን ይሰጣል፡፡ ቅሬታ የቀረበባቸው ተቋማት አሰራሩ እንደሚፈቅደው በ1ወር ጊዜ ውስጥ ምክረ ሃሳቡን መፈፀማቸውን ወይም አለመፈፀማቸውን ከእነምክንያቱ ለእምባ ጠባቂ ተቋም ማሳወቅ እንዳለባቸው የተቋሙ ምክትል እምባ ጠባቂ የኔነህ ስመኝ (ዶ/ር )ነግረውናል። ምክረ ሃሳቡን ተቀብለው ማስተካከያ የሚያደርጉ ተቋማት እንዳሉ ሁሉ ያለ በቂ
4 hours ago1 min read
ጥቅምት 20 2018በፋብሪካ የተቀነባበሩ እንዲሁም ጤናማ ባልሆኑ ምግቦች ምክንያት የሚደርሱ የጤና ጉዳቶች ኢትዮጵያን ብዙ ወጪ እያስወጣት ነው ተባለ።
ሀገሪቱ በዚህ በየዓመቱ ከ31 ቢሊየን ብር በላይ ታወጣለች ተብሏል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተለወጠ የመጣው የአመጋገብ ሥርዓት ተላላፊ ያልሆኑ ህመሞች ጫና ከ52 በመቶ በላይ እንዲሆን ማድረጉ ተነግሯል። ይህንን ያስቀራል በሚል በዝግጅት ላይ ያለውን ተላላፊ ላልሆኑ በሽታዎች የሚያጋልጡ ምግቦችን የሚቆጣጠር ረቂቅ አዋጅ በተመለከተ የማህበረሰብ ጤናን የሚመለከቱ የተለያዩ ጉዳዮች ላይ የሚሰራው የተዋልዶ ጤና አገልግሎት ሰጪ ማህበራት ህብረት እና ሌሎች የሲቪል ማህበራት ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል። በጤና ሚኒስቴር እና በሌሎች አለም አቀፍ ተቋማት በትብብር እየተሰናዳ ያለው ረቂቅ አዋጅ ተላላፊ ባልሆኑ ህመሞች ምክንያት የሚደርሱ የጤና እንዲሁም ሌሎች ጫናዎችን ለመቀነስ የሚያግዝና ይህንንም በተለያዩ መንገዶች እንደሚደግፋ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶቹ ተናግረዋል። በኢት
8 hours ago1 min read
ጥቅምት 20 2018"ሰላም በሌለበት ኢንስትመንትም ሆነ የስራ እድል መፍጠር አይቻልም" ሲሉ የአዲስ አበባ ንግድ እና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ወ/ሮ ዘሃራ ሞሃመድ ተናገሩ።
ፕሬዝዳንቷ ይህ የተናገሩት ዛሬ ጥቅምት 20 ቀን 2018 ዓ.ም "የንግድ ሚና ለሰላም ግንባታ'' በሚል ሃሳብ አዲስ አበባ የንግድ እና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ባሰናዳው የፓናል ወይይት ላይ ነው። ለንግድ፣ ለኢንቨስትመንት ሆነ ለሌላ ስራ ሰላም መሰረት መሆኑን ያስረዱት ወ/ሮ ዘሃራ ሞሃመድ ያለ ሰላም ንግድን ማሰብ ከባድ እንደሆነ ጠቁመዋል። የሰላም መስፍን ለሀገር ችግር መፍትሔ ነውም ብለዋል። የሰላም እጦት ንግድ እንቅስቃሴ እንዳይኖር፣ ምርት ከቦታ መንቀሳቀስ እንዳይችል ማድረጉን ወ/ሮ ዘሃራ ሞሃመድ ተናግረዋል። ሰላም እንዲኖር ደግሞ የመግስት እና የግሉ ዘርፍ ምክክር አስፈላጊ ሲሉ ጠቁመዋል። የስራ እድል ኢንዲፈጠር፣ ኢንቨስትመንትም ኢንዲበረታታ ደግሞ ሰላም መሰረት መሆኑን የአዲስ አበባ ንግድ እና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ወ/ሮ ዘሃራ
9 hours ago1 min read


ጥቅምት 19 2018 - ኢንፊኒክስ ኢትዮጵያ ከተግባረ ዕድ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ፡፡
ኢንፊኒክስ ኢትዮጵያ የአዲስ አበባ ተግባረ ዕድ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ተማሪዎቸን የተግባር ላይ ልምምድ ለመስጠት አንዲሁም መምህራኑን ለማሰልጠን የመግባቢያ ስምምነት ከኮሌጁ ጋር ተፈራረመ፡፡ ስምምነቱን የኮሌጁ ዲን ተስፋዬ አድማሱ(ዶ/ር ) እና ትራንሽን ማኑፋክቸሪንግ በመወከል Guo ZhongLei ተፈራርመውታል፡፡ በስምምነቱ መሰረት ኢንፊኒክስ ክለብ በተግባረ ዕድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ይቋቁማል፣ ይህም ለተማሪዎች ለተግባራዊ የኢንዱስትሪ ልምድ፣ ለክህሎት ግንባታ እና ለፈጠራ ፍለጋ እድሎችን ይሰጣል ተብሎለታል። በዚህ ትብብር ተማሪዎች በግል እና ሙያዊ እድገት ላይ ያተኮሩ ስለጠናዎቸን እና የማማከር ፕሮግራሞች ውስጥ ይሳተፉሉ፣ በኢንፊኒክስ እና ትራንሽን ባለሙያዎች የፈጠራ ተነሳሽ ትምህርት ይሳተፉሉ። ከዚህ በተጨማሪም የኮሌጁ ተማሪዎች በትራንሽን እና ኢንፊ
1 day ago1 min read


ጥቅምት 19 2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች
#ብራዚል የብራዚል ፖሊስ የሬዮ ዴ ጄኒየሮ ከተማን ከተደራጁ ወሮበሎች ለማፅዳት ባካሄደው ዘመቻ በጥቂቱ 64 ሰዎች ተገደሉ ተባለ፡፡ ከተማይቱ በቅርቡ አለም አቀፋዊ የአየር ለውጥ ጉባኤን እንደምታስተናግድ ሬውተርስ ፅፏል፡፡ ፖሊስ ለዚህ ጉባኤ ቅድመ ዝግጅት ሬዮ ዴ ጄኔሮን ከወሮበሎች ለማፅዳት በዘመቻ ላይ ነው ተብሏል፡፡ በአጋጣሚው በተፈጠረው ግጭት ከተገደሉ 64 ሰዎች መካከል 4ቱ የፖሊስ መኮንኖች መሆናቸው ታውቋል፡፡ በትናንቱ ዘመቻ 2 ሺህ 500 ፖሊሶች እና ሌሎች የፀጥታ ባልደረቦች መካፈላቸው ተጠቅሷል፡፡ በግጭቱ በፀጥታ ባልደረቦቹ እና በተደራጁት ወሮበሎች መካከል የተኩስ ልውውጥ እንደነበር መረጃው አስታውሷል፡፡ ፖሊስ ከ80 በላይ የተደራጁ ወሮበሎችን አስሬያለሁ ማለቱ በመረጃው ተጠቅሷል፡፡ #ቤኒን በቤኒን የዋነኛው ተቃዋሚ
1 day ago2 min read


ጥቅምት 19 2018 - ኢትስዊች ባለፈው በጀት ዓመት ከግብር በፊት 1.42 ቢሊዮን ብር ማትረፉን ተናገረ
ከአንዱ ባንክ ወደ ሌላኛው ባንክ ገንዘብ ማስተላለፍ፣ በአንደኛው ባንክ ካርድ በሁሉም መጠቀም የሚያስችል ስርዓት የዘረጋው #ኢትስዊች ባለፈው በጀት ዓመት ከግብር በፊት 1.42 ቢሊዮን ብር ማትረፉን ተናገረ። ትርፉ ከቀዳሚው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲመሳከር የ34 በመቶ ብልጫ እንዳለው የኢትስዊች የዳሬክተሮች ቦርድ ሰብሳሲ አቶ ሰለሞን ደስታ ተናግረዋል። ይህንንም ተከትሎ የ1,000 ብር አክሲዮን የትርፍ ድርሻ 486.4 ብር ደርሷል ተብሏል። ኩባንያው በበጀት ዓመቱ በአጠቃይ 2.2 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ ገቢ ማግኘቱንም ይህም ከቀዳሚው ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ49 በመቶ ጭማሪ እንዳለው የቦርድ ሰብሳቢው ጠቅሰዋል። ይህም የሚያሳየው የኩባንያው ትርፋማነት ከጊዜ ወደጊዜ እያደገ መምጣቱን ነው ሲሉ አቶ ሰለሞን ጠቁመዋል። ኢትስዊች በበጀት ዓመቱ ብዛቱ 287.4
1 day ago1 min read


ጥቅምት 18 2018 - ኢትዮጵያና ኤርትራ ወደ ውጥረት የገቡት በቀይ ባህር ጉዳይ መሆኑን ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ ተናገሩ
ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ከ20 ዓመታት ፀብ በኋላ መልሰው ሰላም ባወረዱ በጥቂት ጊዜ ውስጥ ወደ ውጥረት የገቡት በቀይ ባህር ጉዳይ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተናገሩ፡፡ ውጥረቱ ወደ አደባባይ የወጣው ግን የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ከተፈረመ በኋላ መሆኑንም አስታውሰዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት በእርቁ ሰሞን በሁለቱ ሃገራት መካከል ድንበሮች ተከፍተው፣ የአሰብን ወደብም ኢትዮጵያ ልትጠቀም ሂደት ተጀምሮ እንደነበር በማስታወስ በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ እንዲሰጡ ከፓርላማ አባላት ለተነሳላቸው ጥያቄ በመሰጡት ምላሽ ነው፡፡ የቀይ ባህር ጉዳይ መልክአ ምድራዊ እና ታሪካዊ ጥያቄ በመሆኑ በሰከነ መንገድ ውይይት ማድረግ ያስፈልጋል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተናግረዋል፡፡ ኢትዮጵያን የባህ በር ያሳጣትን ታሪካዊ ዳራ ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስ
2 days ago1 min read


ጥቅምት 18 2018 - የአየር ንብረት ለውጥን የማቋቋም ግብርናን ለመፍጠር ሲከወን የቆየው የመረጃ ግብዓት የማቅረብ ስራ ተጠናቀቀ፡፡
ባለፉት 5 ዓመታት ሲተገበር የነበረው የመሬት፣ አፈር እና የሰብል መረጃን በተመለከተ ሲከወን የቆየው ስራ መጠናቀቁን የፕሮጀክቱ አስተባባሪዎች ተናግረዋል፡፡ ፕሮጀክቱ በኢትዮጵያ፣ ኬንያ እና ሩዋንዳ መተግበሩን የተነገረ ሲሆን በምስራቅ አፍሪካ የአየር ንብረት ተስማሚ ግብርናን ለመደገፍ ያለመ ነበር ተብሏል። ስራው በተሰራባቸው አካባቢዎች ስንዴ በሄክታር 15 ኩንታል ይገኝ የነበረ ሲሆን አሁን ወደ 34 ኩንታል አድጓል፣ ጤፍ 22 ኩንታል ደርሷል፡፡ የመሬት፣ የአፈርና የሰብል መረጃ አገልግሎት ፕሮጀክት በምርምር ተቋማት ውስጥ ዘላቂነት ያላቸው የመሬት ፣ የአፈርና የሰብል መረጃ ማዕከላትን ማቋቋምና ሀገራዊ የግብርና እውቀትና ማጠናከር ዓላማ አድርጎ የማሳያ ስራው ሲሰራ ነበር ተብሏል። እንደ ሀገር የሚታየው የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥና ግብርናውን ማሳ
2 days ago1 min read


ጥቅምት 18 2018 - መንግስት “ጽንፈኛ እና አሻባሪ” የሚላቸውን ቡድኖች ከመውጋት ባለፈ ፖለቲካዊ መፍትሄ ለመስጠት ለምን እንደማይሰራ ተጠየቀ፡፡
ጥያቄው የቀረበው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከምክር ቤት አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ ለመስጠት በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት በተገኙበት ወቅት ነው፡፡ የአብን ፓርቲ ተወካዩ የምክር ቤት አባል ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) በአማራ፣ በኦሮሚያ እና በሌሎች ክልሎች ያሉ ግጭቶች እና ጦርነቶች ተባብሰው በመቀጠላቸው ብዙዎችን እየጎዱ ነው ብለዋል፡፡ መንግስት የጸጥታ ችግሮችን ለመፍታት ጽንፈኛ እና አሻባሪ የሚላቸው ቡድኖች ከሙውጋት ባለፈ ለሁለቱ ክልሎች ማለትም ለአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች ከወታደራዊ አማራጭ ውጪ የተለየ ፖለቲካዊ መፍትሄ ለመስጠት ለምን እንደማይሰራ ጠይቀዋል፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ የእርስ በእርስ ጦርነት አንገፍግፎታል፣ በአገር ውስጥ ተንቀሳቅሶ መስራት እና ሰርቶ መብላትም ከብዶታል ፣ አገራችንም እንደ ኮሎምቢያ 50 ዓመታትን እየ
2 days ago2 min read


ጥቅምት 18 2018 - አስከፊውን የጦርነት ጠባሳ
አስከፊውን የጦርነት ጠባሳ ያዩ ኢትዮጵያዊያን ቁጥር ቀላል አይደለም፡፡ የሚወዷቸውን የተነጠቁ፣ አካላቸው የጎደለ፣ ንብረታቸውን ያጡ ብዙ ናቸው፡፡ ስለዚህም ጦርነት ውስጥ መግባቱን ይቅርብኝ ማለት አለበት ተብሏል፡፡ በጉዳዩ ላይ የተለያዩ የሀገር ሽማግሌዎች አነጋግረናል፡፡ ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ… ያሬድ እንዳሻው የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… 👇👇👇 🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/ 🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478 🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1 📘Facebook፡ https://tinyurl.com/4tx8t8wm 💬WhatsApp ፡ https://tinyurl.com/ycxjmm3s 🐦X : https://x.com/shegerfm?s=2
2 days ago1 min read


ጥቅምት 18 2018 - ባለፉት ዓመታት በነዳጅና ማዕድን ማውጣት ፈቃድ የሚወስዱት የሚበዙት ደላሎች ነበሩ ተባለ
በኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት በነዳጅና ማዕድን ማውጣት ፈቃድ የሚወስዱት የሚበዙት አልሚዎች ሳይሆኑ ደላሎች ነበሩ ተባለ። በዚህ ምክንያት ባለፉት ዓመታት የረባ ውጤት ሳይገኝ ቆይቷል ተብሏል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ተገኝተው ማብራሪያ እየሰጡ ነው። የማዕድን ሀብትን በተመለከተ ሲያነሱ የቀደመው መንገድ ትክክል እንዳልነበረ አንስተዋል። በ #ማዕድን እና ነዳጅ ማውጣት የሚበዙት ፈቃድ የሚወስወዱት ደላሎች ስለነበሩ ኢንቨስት የሚያደርግ ሲፈልጉ ዓመታትን ይወስዱ ነበር ብለዋል። ይህም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተደረገው ለውጥ መቀየር መቻሉን አንስተዋል። የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… 👇👇👇 🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/ 🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux
2 days ago1 min read


ጥቅምት 18 2018 በመንግስት ልዩ ትዕዛዝ የተሰጡትን በሺዎች የሚቆጠሩ ድሮኖችን ሊያመርት መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ተናገረ።
አስተዳደሩ ይህን የተናገረው የ3 ወር(የሩብ ዓመት) የስራ ክንውን ሪፖርቱን በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ለውጭ ግንኙነት እና ሰላም ጉዳይዎች ቋሚ ኮሚቴ ትናንት ጥር 17ቀን 2018 ዓ.ም ባቀረቡበት ወቅት ነው። የቋሚ ኮሚቴውን ጥያቄ በንባብ ያቀረቡት የምክር ቤት አባሉ አቶ ሳዲቅ አደም በሩብ ዓመቱ ተቋሙ ለማበልጸግ ከያዛቸው እቅዶች ውስጥ አንዱ #የድሮን_ቴክኖሎጂ መሆኑን አስታውሰው በ3 ወራት ውስጥ ተመርተዋል ስልተባሉ ድሮኖች ማብራሪያ ቢሰጥ? ሲሉ ጠይቀዋል። የአስተዳደሩ የስራ ሃላፊዎች በሰጡት ምላሽ የተቋሙ አንዱ ሃላፊንት በሀገራዊ አቅም ባልተሰራባቸው የቴክኖሎጂ ዘርፎች ላይ መስራት መሆኑን አስረድተው ይህንንም ታሳቢ አድርገን በድሮን ቴክኖሎጂ ላይ ምርምር የማድረግ፣ የማበልጸግ፣ የመቆጣጠር እና አገልግሎት የመስጠት ስራ እየሰራን ነው ሱሉ
2 days ago2 min read


ጥቅምት 19 2018 - ግብፅ በናይል ወንዝ ያላትን ጥያቄ የናይል ወንዝ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነትን ተቀብላ በጋራ ብታቀርብ ይበጃታል ተባለ።
ግብፅ በናይል ወንዝ ዙሪያ ያላትን ጥያቄ የናይል ወንዝ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነትን ተቀብላ በጋራ ብታቀርብ ይበጃታል ተባለ። የናይል የላይኛው ተፋሰስ ሀገራት በሰፊው ወደ የሀይል ማመንጫ ግድብ ግንባታ እየገቡ ነው ተብሏል። ይህንን ያሉት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ሀብታሙ ኢተፋ(ዶ/ር) ናቸው። 2ኛው የኢትዮጵያ የውሃና ኢነርጂ ሳምንት በሳይንስ ሙዚየም መካሄድ ጀምሯል። በዝግጅቱ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ ለኢትዮጵያ ድንበር ተሻጋሪ ወንዞቿ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ድንበር መለያ ሳይሆኑ መተሳሰሪያ ድልድይ ናቸው ብለዋል። የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ሀብታሙ ኢተፋ(ዶ/ር) የኢትዮጵያን መንገድ ተከትለው የናይል ተጋሪ የላይኛው የተፋሰሱ ሀገራት በስፋት ወደ ሀይል ማመንጫ ግንባታ እየገ
2 days ago1 min read


ጥቅምት 17 2018 - የፀጥታ አስከባሪ አካላትን የደንብ ልብስ ለብሰው የሚያጭበረብሩ ግለሰቦች
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የፀጥታ አስከባሪ አካላትን የደንብ ልብስ ለብሰው የሚያጭበረብሩ፣ አስፈራርተውም መዝረፍ እየተደጋገመ ይመስላል፡፡ አንድ ሰው እጅ ከፍንጅ ወንጀል ሲፈፀም እስካልተገኘ ድረስ ለጥያቄ እፈልግሃለሁ ያለውን ፖሊስ ሁሉ የፍርድ ቤት መጥሪያ አሳየኝ የማለት መብት ቢኖረውም ብዙዎች ይህን ስለማያደርጉ የወንጀል ሰለባ እየሆኑ ነው፡፡ ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ… ገዛ ጌታሁን የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… 👇👇👇 🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/ 🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478 🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1 📘Facebook፡ https://tinyurl.com/4tx8t8wm 💬WhatsApp ፡ https://tinyurl.com
3 days ago1 min read


ማህበራዊ ሚዲያ እና ሰው ሰራሽ አስተውሎት
ጥቅምት 17 2018 ጉዳያችን - ማህበራዊ ሚዲያ እና የሰው ሰራሽ አስተውሎት ( #AI ) የኤ.አይ.ቲ ቴክኖሎጂ ስራ አስኪያጅ እና የቴክኖሎጂ ባለሞያው አቶ እስራኤል ብሩክ፤ ማህበራዊ ሚዲያ እና የሰው ሰራሽ አስተውሎትን በተመለከተ የሰጡንን ማብራሪያ ያድምጡ… ቴዎድሮስ ወርቁ ለማብራሪያው አቶ እስራኤል ብሩክን እናመሰግናለን። የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… 👇👇👇 🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/ 🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478 🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1 📘Facebook፡ https://tinyurl.com/4tx8t8wm 💬WhatsApp ፡ https://tinyurl.com/ycxjmm3s 🐦X : https://x.com
3 days ago1 min read


ጥቅምት 17 2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች
#ቱርክ በቱርክ PKK የተሰኘው የኩርዶች የቀድሞ አማጺ ቡድን ታጣቂዎቹን ከቱርክ ወደ ኢራቅ ማስወጣት ጀመረ፡፡ PKK ታጣቂዎቹን ወደ ኢራቅ ማስወጣት የጀመረው ከቱርክ መንግስት ጋር በጀመረው የሰላም ሒደት መሰረት እንደሆነ አሶሼትድ ፕሬስ ፅፏል፡፡ የኩርዶቹ ታጣቂ ቡድን ከእንግዲህ የትጥቅ አመፅ እርም ይሁንብኝ ያለው ባለፈው አመት ግንቦት ወር ላይ እንደነበር መረጃው አስታውሷል፡፡ በትጥቅ መፍታት ሒደት ላይ ይገኛል ተብሏል፡፡ PKK ታጣቂነቱን ትቶ በሰላማዊ የፖለቲካ ትግል ብቻ የመቀጠል ፍላጎት እንዳለው ተጠቅሷል፡፡ ቡድኑ ለወሰደው እርምጃ አስተማማኝነት የቱርክ መንግስት PKK ወደ ሰላማዊ የፖለቲካ ማህበርነት የሚለወጥበትን ሁኔታ እንዲያመቻችለት መጠየቁ ተሰምቷል፡፡ PKK የትጥቅ አመፅ እርም ይሁንብኝ ያለው ከ40 አመታት በኋላ እንደሆነ መረጃው አስታውሷ
3 days ago2 min read


ጥቅምት 17 2018 - በዩኔስኮ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የጽሑፍ ቅርሶች አስመዝጋቢ ኮሚቴ ሥራ ጀምሯል።
ኮሚቴው የኢትዮጵያን አብያተ መዛግብት እና ታሪካዊ መጻሕፍትን በዩኔስኮ የዓለም የትውስታ ማህደር (Memory of the World) ላይ ያስመዘግባል ተብሏል። ኢትዮጵያ ከ20 ዓመታት በፊት 12 የሚደርሱ ጥንታዊ ፅሑፍና መዛግብቶቿን የዓለም የትውስታ ማህደር ላይ አስመዝግባለች። ይሁን እንጂ ሀገሪቷ ካላት ሰፊና የረጅም ዘመናት የሥነ ፅሑፍ ታሪክ አንፃር የተመዘገቡት ከቁጥር የሚገቡ አይደሉም ተብሏል። ለዚህም ሲባል ኮሚቴ አቋቁሞ መስራት አስፈላጊ መሆኑ ተነግሯል። ከአንድ ዓመት በፊት ተቋቁሞ የተባበሩት መንግስታት የሳይንስ ትምህርትና የባህል ማዕከል(UNSCO) ተወካይእና የቱሪዝም ሚኒስቴር የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ዛሬ ሥራ የጀመረው ኮሚቴው ሁለት ተጨማሪ መዛግብቶችን ለማስመዝገብ ተቃርቤያለሁ ብሏል። ንጋት መኮንን የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግ
3 days ago1 min read


ጥቅምት 17 201 - በጦርነትና በግጭቶች ተጋላጭ የሆኑ ሴቶች የደረሰባቸውን ግፍ ይዘው መደበቅ የለባቸውም ተባለ
በጦርነት እና በተለያዩ ግጭቶች ቀዳሚ የጉዳት ተጋላጭ የሆኑ ሴቶች የደረሰባቸውን ግፍ ይዘው መደበቅ የለባቸውም ተባለ፡፡ የደረሰባቸውን ግፍ በአደባባይ ያውጡ፣ ይብቃ ያሉ ፣ የተለያዩ ሀገር ሴቶች ሰላም እንዲመጣ ሚናቸውን ተጫውተዋል ተብሏል፡፡ በአፍሪካ ሴቶች ሰላምና ደህንነት ተቋም የሚሰሩ እና ኢትዮጵያንም በተለያየ ዘርፍ ለረዥም ጊዜ ያገለገሉ ሴቶን አነጋግረናል፡፡ ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…. ማርታ በቀለ የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… 👇👇👇 🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/ 🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478 🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1 📘Facebook፡ https://tinyurl.com/4tx8t8wm 💬WhatsApp
3 days ago1 min read


ጥቅምት 17 2018 - በአዋሽ ፈንታሌ የመሬት መንቀጥቀጥ አጋጠመ።
የመሬት መንቀጥቀጡ በሬክተር ስኬል 4.8 ሆኖ የተመዘገበ ነበርም ተብሏል። የመሬት መንቀጥቀጡ የተሰማው ትናንት ጠዋት 2 ሰዓት ከ24 ደቂቃ(2:24)ላይ እንደነበረም ተነግሯል። ይህንን የነገሩን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦፊቪክስ፣ ስፔስ ሳይንስ እና የአስትሮኖሚ ተቋም ተመራማሪ አታላይ አየለ(ፕ/ር) ናቸው። በፈንታሌ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረቱም በአዲስ አበባ፣ አዳማ ደብረሲና እና የአዋሽ ከተሞች የደረሰ ነበርም ብለውናል። በአዋሽ ፈንታሌ ባሳለፍነው አርብም የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ እንደነበረም ነግረውናል። መሬት በማያቋርጥ እንቅስቃሴ ውስጥ ስላለች የመሬት መንቀጥቀጥ የሚከሰትበቀት ጊዜ በርግጠኝነት መናገር እንደሚቸግርም አስረድተዋል። በተለይም የመሬት መንቀጥቀጥ በሚደጋገምባቸው አካባቢዎች ህንፃዎች ሲሰሩ መሰረታቸው እንዲጠናከሩም መክረዋል
3 days ago1 min read
ፕሮግራሞች
bottom of page








