top of page

የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን ማሳደግ፣አፍሪካዊያን የጋራ መጪ እድላቸውን እንዲቀርፁ ማገዝ ያስፈልጋል ተባለ።

  • 2 hours ago
  • 2 min read

ሐምሌ 23 2018


የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን ማሳደግ፣አፍሪካዊያን የጋራ መጪ እድላቸውን እንዲቀርፁ ማገዝ ያስፈልጋል ተባለ።


የአፍሪካ ሀገሮች እርስ በእርስ፣በአፍሪካና በሩሲያ እንዲሁም አፍሪካ ከተቀረው ዓለም ጋር ያላትን የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ማሳደግን ዓለማው ያደረገ ዓለም አቀፍ ጉባኤ በተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ የኢኮኖሚ ኮሚሽን መሰብሰቢያ አዳራሽ መካሄድ ጀምሯል።


ይህ "ወርልድ ፐብሊክ ሰሚት" በሚል የሚጠራው የፓን አፍሪካን ጉባኤ በአፍሪካ ምድር ሲካሄድ የመጀመሪያው ነው ተብሏል።


ከፍተኛ የወጣት ቁጥር፣የተፈጥሮ ሀብት፣ባህል እና ቅርስ ያላት አፍሪካ የአህጉሩ ብቻ ሳይሆን የዓለምን መንገድም የመወሰን አቅም ያላት ነች ተብሏል።


ሩሲያም የአፍሪካን ሀገሮች እርስ በእርስ፣ አፍሪካን ከሩሲያና ከተቀረው ዓለም ጋር በህዝብ ለህዝብ ግንኙነት የማስተሳሰር ፍላጎት አላት ተብሏል።


ጉባኤውን ማካሄድ ያስፈለገው ይህንን ግንኙነት ለማሳደግ በማሰብ ነው ብለዋል አዘጋጆቹ።


ጉባኤውን መቀመጫውን በሩሲያ ሞስኮ ያደረገው እና ከዘጠኝ ዓመት በፊት የተቋቋመው ወርልድ ፒፕልስ አሴምብሊ የተባለ አለም አቀፍ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት ያዘጋጀው መሆኑ ተነግሯል።


ግሎባል ሰርቭ እና ግሎባል ብላክ ሴንተር የተባሉ ድርጅቶችም ጉባኤውን በትብብር ያዘጋጁ ድርጅቶች መሆናቸው ተነግሯል።


ከ700 በላይ ሰዎች ተሳታፊ የሆኑበት ይህ የፓን አፍሪካን ጉባኤ ከ400 በላይ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅት ተወካዮች ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገሮች የተገኙ ሲሆን በመቶዎች የሚቆጠሩ ወጣቶችም የጉባኤው እየተሳተፉበት ነው።


ባለፈው አመት የጉባኤው አዘጋጅ ወርልድ ፒፕልስ አሴምብሊ ከ160 በላይ ሀገሮች የታደሙበትን የመጀመሪያ አለም አቀፍ ጉባኤውን በዚሁ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ዙሪያ በሩሲያ ካደረገ በውሃላ ጉባኤው ወደ ተለያየ የዓለም ክፍል እየዞረ መካሄድ መጀመሩ ሲነገር ሰምተናል።


ይህ የህዝብ ለህዝብ ጉባኤ በህንድ እንዲሁም ብራዚል ከዚህ ቀደም የተደረገ ሲሆን ሶስተኛው እና በአፍሪካ የመጀመሪያው የሆነው ከ700 በላይ ተሳታፊዎች የታደሙመት ጉባኤ ዛሬ በአዲስ አበባ ማካሄድ ጀምሯል።


በዚህ የፓን አፍሪካን ጉባኤ ላይ ከ20 በላይ ሀሳቦች ለፓናል ውይይት የተመረጡ ሲሆን ባህል ፣ በትምህርት ፣ ወጣቶች፣ ቅርፅ እና ሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ ያተኩራሉ ተብሏል፡፡


የትምህርት ተቋሞች፣የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች፣የቢዝነስ ተቋማት ተወካዮችና ሌሎችም ከመላው አፍሪካ በጉባኤው ላይ ተሳታፊ መሆናቸው ተነግሯል።


ዛሬ በተጀመረውና ነገም ይቀጥላል በተባለው ዓለም አቀፍ ጉባኤ መክፈቻ ላይ የተገኙት በኢትዮጵያ የሩሲያው አምባሳደር ኢቭጌኒይ ቴሬክሂን የአዲስ አበባው ጉባኤ በመጪው መስከረም ወር በሩሲያ ሞስኮ ለሚካሄደው ሁለተኛው የዓለም የህዝብ ለህዝብ ጉባኤ የሚሆን ተጨማሪ ሀሳብ የሚገኝበት እንደሆነ ተናግረዋል።


የጉባኤው አካል የሆነ የአንድነት ድምፅ የሚል መጠሪያ የተሰጠው የኪነ ጥበብ ዝግጅት ነገ በአዋ የመታሰቢያ ሙዚየም እንደሚደረግም ተነግሯል።


ከአፍሪካ የተመረጡና የላቁ ተብለው የተለዩ የኢትዮጵያ የካሜሩን ፣ የጋና ፣ የኬኒያ እና በአጠቃላይ የ16 የአፍሪካ ሀገር አርቲስቶች ይሰባሰቡበታል የተባለ ኢግዚቢሽን ይሆናል ተብሏል።


በህዝብ ለህዝብ የዲፕሎማሲ ስራ የላቁ ተብለው የሚመረጡ 10 አፍሪካዊያን ሰዎችም በዝግጅቱ ላይ ተመርጠው እውቅና ይሰጣቸዋል መባሉም ተውርቷል።


የጉባኤው አዘጋጅ የሩሲያው ወርልድ ፒፕልስ አሴምብሊ ከዘጠኝ አመት በፊት በሩሲያ የተመሰረተ ድርጅት ሲሆን በስሩ ከ150 በላይ ሀገሮች የተወጣጡ በ3 ሺህ በላይ ድርጅቶችን አባል አድርጎ የያዘ መሆኑን ከአዘጋጆቹ ሰምተናል።


ቴዎድሮስ ወርቁ

Recent Posts

See All
የሐምሌ 23 2018 የውጪ ሀገር ወሬዎች

#ግብፅ በግብፅ የሜዴትራኒያን የባህር ዳርቻ የነበረ የአሜሪካ የጋዝ ማጠራቀሚያ መርከብ በድሮን ተመታ ተባለ፡፡ ሁለት የደህንነት ምንጮች መርከቡ በድሮን እንደተመታ አረጋግጠውልኛል ሲል ሬውተርስ ፅፏል፡፡ መርከቡ በድሮን እንደተመታ በእሳት መያያዙ ታውቋል፡፡ ቃጠሎው ወደ ሌላ መርከብም ተጋብቶ ነበር ተብሏል፡፡ ኋላ ግን

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play
  • Facebook
  • X
  • Youtube
  • TikTok
  • Telegram
  • Whatsapp

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page