top of page
የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን ማጠናከረን አላማው ያደረገ የፓን አፍሪካን ጉባኤ በመጪ ሳምንት በአዲስ አበባ ይካሄዳል ተባለ፡፡
ሐምሌ 16 2018 የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን ማጠናከረን አላማው ያደረገ የፓን አፍሪካን ጉባኤ በመጪ ሳምንት በአዲስ አበባ ይካሄዳል ተባለ፡፡ ይህ "ወርልድ ፐብሊክ ሰሚት አፍሪካ" በሚል የሚጠራ ጉባኤ በመጪው ሳምንት ከሐምሌ 22-23 2018 ዓ.ም በአፍሪካ የኢኮኖሚ ኮሚሽን መሰበሰቢያ ይካሄዳል ተብሏል፡፡ ጉባኤውን መቀመጫውን በሩሲያ ሞስኮ ያደረገው ወርልድ ፒፕልስ አሴምብሊ የተባለ አለም አቀፍ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት፣ግሎባል ሰርቭ እና ግሎባል ብላክ ሴንተር ከተባሉ ድርጅቶች ጋር በትብብር ያዘጋጁታል ተብሏል፡፡ ከ700 በላይ ሰዎች ተሳታፊ ይሆኑበታል የተባለውን የፓን አፍሪካን ጉባኤ በተመለከተ ዛሬ በኢሊሌ ሆቴል ለጋዜጠኞች መግለጫ ተሰምቷል፡፡ ያኒና ዱቤይኮቭስካያ የጉባኤው አዘጋጅ ኮሚቴ ሀላፊ ናቸው፡፡ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት የአንድን ሀገር ህዝብ
Jul 242 min read
የሐምሌ 17 2018 የውጪ ሀገር ወሬዎች
#ብሪታንያ የብሪታንያ መንግስት በኬንያ ላካሂድ የነበረውን አመታዊ የጦር ልምምድን ትቼዋለሁ አለ፡፡ የብሪታንያ ሰራዊት አመታዊ የኬንያ የጦር ልምምዱን የተወው ከምስራቅ አፍሪካዊቱ አገር መንግስት ፈቃድ ባለማግኘቱ ነው መባሉን አፍሪካ ኒውስ ፅፏል፡፡ የብሪታንያ ጦር ከዚህ ቀደም በኬንያ በየአመቱ በመደበኛነት የጦር ልምምዱን ሲያደርግ መቆየቱን መረጃው አስታውሷል፡፡ የኬንያ መንግስት ለብሪታንያ አመታዊ የጦር ልምምድ ፈቃድ የነሳበት ምክንያት አልተጠቀሰም፡፡ የሚመለከታቸው ሹሞችም ከAFP ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ከመስጠት ተቆጥበዋል ተብሏል፡፡ የብሪታንያ ጦር ይሄንኑ አመታዊ ወታደራዊ ልምምዱን በሌላ አፍሪካ አገር ያካሂዳል ተብሏል፡፡ የልምምዱ አስተናጋጅ የአፍሪካ አገር ማን እንደሆነች በስም አልተጠቀሰችም፡፡ #አሜሪካ የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ በ
Jul 242 min read


10 አባላት ያሏቸው ቡድኖች በሚያጠናቅሩት ሪፖርት ላይ ከነገ ጀምሮ ምክክሩ እንደሚቀጥል የሃገራዊ ምክክር ኮሚሽን ተናገረ።
ሐምሌ 16 2018 10 አባላት ያሏቸው ቡድኖች በሚያጠናቅሩት ሪፖርት ላይ ከነገ ጀምሮ ምክክሩ እንደሚቀጥል የሃገራዊ ምክክር ኮሚሽን ተናገረ። የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ የምክክሩን ያለፉት 3 ቀናት ውሎ ያብራሩበትን መግለጫ ሰጥተዋል። ከሰኞ ሐምሌ 13 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ 50 ተመካካሪዎችን በያዙ ንዑሰ ቡድኖች በመከፋፈል በተመደቡበት አጀንዳዎች ላይ ሲመካከሩ መቆየታቸውን አስታውሰዋል፡፡ በእያንዳንዱ ንዑስ ቡድን 50 ተመካካሪዎችን የያዙ 80 አነስተኛ ቡድኖች ሲወያዩ ቆይተዋል ብለዋል። ለምክክሩ አመቺነት ሲባልም ኮሚሸኑ ባስቀመጠው አሰራር መሰረት 50 ተመካካሪዎች ባሉበት ቡድን ውስጥ ተሳታፊዎች አስር አስር በመሆን የምክክር ሂደቱ መቀጠሉንም ፕሮፌሰር መስፍን ጠቅሰዋል። የነበረው የምክክር ሂደት ተመካካሪዎች ስለተለያዩ ርዕሰ ጉ
Jul 231 min read


ናይጀሪያዊው ባለሀብት አሌኮ ዳንጎቴ በኬንያ የላሙ ኮሪደር አቅራቢያ የነዳጅ ማጣሪያን ለመገንባት መወጠናቸው ተሰምቷል፡፡
ሐምሌ 16 2018 ናይጀሪያዊው ባለሀብት አሌኮ ዳንጎቴ በኬንያ የላሙ ኮሪደር አቅራቢያ የነዳጅ ማጣሪያን ለመገንባት መወጠናቸው ተሰምቷል፡፡ ለመሆኑ ከኬንያ የሚገነባው ግዙፍ የነዳጅ ማጣሪያ ለኢትዮጵያ ምኗ ነው? የምጣኔ ሀብት ባለሙያው ሰመረ ቃለአብ ፕሮጀክቱ ኢትዮጵያን፣ ደቡብ ሱዳንን እና ኬኒያን በሚያገናኘው የላሙ ኮሪደር አቅራቢያ የሚገነባ በመሆኑ ለኢትዮጵያ ትልቅ ፋይዳ አለው የሚል ሃሳብ ያነሳሉ። ባለ ሀብቱ አሊኮ ዳንጎቴ ፕሮጀክቱን ሲያቅዱ የኢትዮጵያን ገበያ ታሳቢ ሳያደርጉ እንዳልቀረ ባለሙያው ይገምታሉ። ከዚህ ፕሮጀክት ተጠቃሚ ለመሆን ግን ኢትዮጵያ ከወዲሁ የላሙ ኮሪደርን ማልማት አለባት ይላሉ። ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ.... ንጋት መኮንን
Jul 231 min read
በኢትዮጵያ በቆዳና ሌጦ ዘርፍ ሲሰሩ ከነበሩ 31 ፋብሪካዎች ውስጥ አሁን በስራ ላይ ያሉት ሰባት ብቻ ናቸው ተባለ።
ሐምሌ 16 2018 በኢትዮጵያ በቆዳና ሌጦ ዘርፍ ሲሰሩ ከነበሩ 31 ፋብሪካዎች ውስጥ አሁን በስራ ላይ ያሉት ሰባት ብቻ ናቸው ተባለ። ይህን ያለው የኢትዮጵያ ጥሬ ቆዳ እና ሌጦ አቅራቢዎች ማህበር ነው ። እነዚህ ፋብሪካዎች የወጡት በግብር እና በቫት መጨመር እንደሆነም ማህበሩ ነግሮናል። ፋብሪካዎቹ ላይ ቫት እንዲጨመር የተደረገው የቆዳው ዘርፍ አካባቢን እየበከለ ከመሆኑ ጋር በተያያዘ እንደሆነ ሰምተናል። ይህንን የነገሩን የኢትዮጵያ ጥሬ ቆዳና ሌጦ አቅራቢዎች ማህበር የቦርድ ፀሐፊ አቶ መስፍን ለገሠ ናቸው ። ይህ ችግር እንዲፈታ ለተለያዩ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ጥያቄ አቅርበናል ያሉት አቶ መስፍን ለጥያቄያቸውም ምላሽ እየጠበቁ መሆኑም ነግረውናል። በሌላ በኩል በቆዳ እና ሌጦ ዘርፍ ያሉ የጥሬ እቃ ችግሮች ከሞላ ጎደል እየተፈቱ ቢሆንም አሁንም ከዘርፉ የ
Jul 231 min read


ኢትዮ ቴሌኮም በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 215.8 ቢሊዮን ብር ገቢ አገኘሁ አለ።
ሐምሌ 16 2018 ኢትዮ ቴሌኮም በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 215.8 ቢሊዮን ብር ገቢ አገኘሁ አለ። የደንበኞች ቁጥርም ባለፈው ዓመት ከነበረበት በ8.3 በመቶ አድጎ 90.1 ሚሊዮን ደርሶልኛል ብሏል። ተቋሙ ይህንን ያለው የ2018 በጀት ዓመት አፈፃፀሙን በተመለከተ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ነው። በበጀት አመቱ በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን የተናገሩት የተቋሙ ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬሕይወት ታምሩ በዓመቱ 215.8 ቢሊዮን ብር ገቢ መገኘቱን አንስተዋል። ይህም የእቅዱን 99.7 በመቶ ነው ብለዋል፡፡ ገቢው ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲመሳከር ደግሞ የ33.2 በመቶ እድገት ከፍ ያለ ነው። ለተመዘገበው ከፍ ያለ ገቢ ከፍተኛውን ድርሻ ካበረከቱ የአገልግሎት ዓይነቶች መካከል ቀዳሚው ኢንተርኔት አገልግሎት 31በመቶ ድርሻ ሲኖረው በሁለተኛነት የሞባይል ድምፅ አ
Jul 231 min read


የእንቦጭ አረም አሁንም ያልተፈታ የኢትዮጵያ ችግር ሆኖ ቀጥሏል ተባለ፡፡
ሐምሌ 16 2018 የእንቦጭ አረም አሁንም ያልተፈታ የኢትዮጵያ ችግር ሆኖ ቀጥሏል ተባለ፡፡ የተወሰኑ ሀይቆችን ሸፍኖ የሚገኘው አረም በትኩረት ካልተሰራ ለህዳሴው ግድብም ስጋት ሊሆን ይችላል ተብሏል፡፡ በተለይ በአባያ እና ቆቃ ሐይቆች ላይ ስጋትነቱ አሁንም እንደቀጠለም ተነግሯል። በሌላ በኩል በአመቱ የእምቦጭ አረምን ለማስወገድ ከታቀደው በላይ ስራ የተሰራ ቢሆንም ከችግሩ ስፋት አንጻር ግን በቂ አይደለም ተብሏል ። ሁሉም የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ ትኩረትም ሊሰጠው እንደሚገባም ተነግሯል ። ይህንን የነገሩን በውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢኮ ሀይድሮሎጂ ፕሮጀክት እና የመጤ አረሞች ማስወገድ እና መከላከል አስተባባሪ አቶ ወንድወሰን አበጀ ናቸው ። በተጠናቀቀው በጀት አመት የእምቦጭ አረምን ለማስወገድ በተሰራ ስራ ከባለፈው አመት ስጋትነቱ መቀነስ የታየባቸው አ
Jul 231 min read


#ታሪክን_የኋሊት
የኢትዮጵያ የመጨረሻው ንጉሠ ነገሥት፣ አጼ ኃይለ ስላሴ የተወለዱት፣ በ1884 ዓ.ም በዛሬው ቀን ነበር፡፡ ከመንገሳቸው በፊት “ተፈሪ” በሚለው ስማቸው የሚታወቁት አጼ ኃይለ ሥላሴ፣ የአስተዳደር ስልጣን የጀመሩው ገና በ14 አመታቸው ነበር፡፡ አባታቸው የሃረሩ ገዥ ራስ መኮንን ወልደሚካኤል የጋራሙለታ አውራጃ ገዥነትን በእንደራሴ እንዲያስተዳድሩ ከሾሟቸው በኋላ፣ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ፈቃድ የሰላሌን የሲዳማን ግዛት አስተዳድረዋል፡፡ ለአልጋ ወራሽነት በጦር አለቆች ከመመረጣቸው በፊትም የሐረር ጠቅላይ ገዥ ነበሩ፡፡ ለአልጋ ወራሽነት ለመመረጥ የበቁት፣ የጦር አዛዦቹ ልጅ ኢያሱን ተቃውመው ከመንግስት ስራ ሲያስወጣቸው፣ ባህሪያቸውንና የቀድሞ የሥራ ልምዳቸውን ገምግመው ፣ከንግስት ዘውዲቱ ህልፈት በኋላ ንጉሥ እንደሆኑ ሰየሟቸው፡፡ ራስ ተፈሪ፣ አንድ ጊዜ የሥልጣን
Jul 232 min read
የሐምሌ 16 2018 የውጪ ሀገር ወሬዎች
#ሊቢያ በሊቢያ የተለያዩ የፖለቲካ ማህበራት አገሪቱ ወደ አንድነቷ እንድትመለስ ጥሪ አቀረቡ፡፡ የፖለቲካ ማህበራቱ በጋራ የህውደት ጥሪውን ያቀረቡት የሊቢያን የወደፊት እጣ ፈንታ በተመለከተ ምክክር ባደረጉበት ወቅት እንደሆነ TRT አፍሪካ ፅፏል፡፡ በሊቢያ የቀድሞው መሪ የኮሎኔል ሙአመር ጋዳፊ አስተዳደር ከ15 አመታት በፊት በትጥቅ አመፅ ከተወገደ በኋላ ብሔራዊ አንድነቷ ሊፀና አልቻለም፡፡ አገሪቱ በምስራቅ እና ምዕራብ እንደተከፋፈለች ነው፡፡ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የሊቢያ የብሔራዊ አንድነት ጥሪ እየጎላ ነው፡፡ የፖለቲካ ማህበራቱ ሊቢያ ወደ ብሔራዊ አንድነቷ እንድትመለስ አጋዥ የሆነ ፕሬዘዳንታዊ እና የፓርላማ ምርጫ እንዲከናወንም ጥሪ ማቅረባቸውን መረጃው አስታውሷል፡፡ #የመን የየመን ሁቲዎች አንሳር አላህ ንቅናቄ በሁለት የሳውዲ አረቢያ የነዳጅ መጫኛ መ
Jul 232 min read
ኢትዮጵያ ለዘመናት የባህላዊ ህክምና ዘርፍን ስትጠቀምበት ብትቆይም ዘርፉ በብዙ ምክንያቶች የሚጠበቀውን ያህል ርቀት አለመጓዙ ይነገራል፡፡
ሐምሌ 16 2018 ኢትዮጵያ ለዘመናት የባህላዊ ህክምና ዘርፍን ስትጠቀምበት ብትቆይም ዘርፉ በብዙ ምክንያቶች የሚጠበቀውን ያህል ርቀት አለመጓዙ ይነገራል፡፡ የባህል ህክምና ለመስጠት የሚያግዙ የእጽዋት ዓይነቶች በተለይም በብዛት የማይገኙት ዝርያቸው መመናመኑ ባለሙያዎቹ ዕውቀቱን በቤተሰብ ብቻ በማጠር ሚስጥር ጠባቂነት በሚል ሙያውን አለማስፋፋታቸው በባህል ህክምና ዘርፉ ከሚነሱ ችግሮች ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ ይህንን ለማስቀረት የባህላዊ ህክምና ሥርዓትን ከዘመናዊው ጋር በማዋሃድ መስራት ለእጽዋቱም ጥበቃና እንክብካቤ ማድረግ ላይ ቢሰራ ለውጥ እንደሚመጣ ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡ ለመሆኑ ዘመናት ያስቆጠረው የኢትዮጵያ የባህላዊ ህክምና ሥርዓት ለምን ከሌሎች አገራት አንፃር ወደኋላ ቀረ ችግሮቹስ ምንድናቸው ስንል ባለሙያ ጠይቀናል፡፡ ዶክተር ጌታቸው አዲስ የዕጽዋት ሳ
Jul 231 min read


ኢትዮጵያ በካርበን ንግድ ገበያ ከሚሳተፉ ሀገሮች ተርታ መሆኗ ይነገራል፡፡
ሐምሌ 16 2018 ኢትዮጵያ በካርበን ንግድ ገበያ ከሚሳተፉ ሀገሮች ተርታ መሆኗ ይነገራል፡፡ በዓለም ዙሪያ በዓመት ከ800 ቢሊዮን ዶላር በላይ ሀብት ከሚገላበጥበት ፣ አካባቢን በመጠበቅ ወደ ከባቢ አየር የሚለቀቅ የበካይ ጋዝ መጠንን በመቀነስ ንግድ የበለጠ ለመሰማራት ኢትዮጵያ የካርበን ገበያ አዋጅን አሻሽላለች፡፡ ለመሆኑ የተሻሻለው አዋጅ ምን ይዞ ይሆን? ኢትዮጵያ አካባቢን በመጠበቅ ከካርበን ገበያ የበለጠ መጠቀም የምትችለውስ እንዴት ነው? ሙሉ ዘገባውን ያድም... ፍቅሩ አምባቸው
Jul 231 min read
በየክልሉ ቆመው የነበሩ ለብዙ ችግር እና እንግልት ምክንያት የሆኑ 316 ሕገ-ወጥ ኬላዎች መነሳታቸው ተነገረ።
ሐምሌ 16 2018 በየክልሉ ቆመው የነበሩ ለብዙ ችግር እና እንግልት ምክንያት የሆኑ 316 ሕገ-ወጥ ኬላዎች መነሳታቸው ተነገረ። አሁንም ግን በየአካባቢው ያለው የኬላዎች ችግር ሙሉ በሙሉ አለመፈታቱ ተነግሯል። ሕግ አክብረው መስራት ሲኖርባቸው ከዛ ወጪ በሆነ ተግባር ተሰማርተው ተገኝተዋል በተባሉ 347 ሺህ 679 ነጋዴዎች ላይ እርምጃ መወሰዱ የተነገረ ሲሆን 781.3 ሚሊዮን ብር የገንዘብ ቅጣትም ተጥሎባቸዋል ተብሏል። የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትሩ ዶክተር ካሳሁን ጎፌ ገበያን ለማረጋጋት፣ የምርት አቅርቦትን ለማሻሻል እና የኑሮ ውድነትን ለመቀነስ የተከናወኑ ተግባራትን በተመለከተ ለብልፅግና ፓርቲ መድረክ ሪፖርት አቅርበዋል። ከንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ባገኘነው መረጃ በዓመቱ የምርት አቅርቦትን ለማሻሻል እና የኑሮ ውድነትን ለመቀነስ የሚያግ
Jul 232 min read


የማስተር ካርድ ፋውንዴሽን ለከፍተኛ ት/ት ተቋማት የሚሰጠውን ሽልማት የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ማሸነፉ ተነገረ፡፡
ሐምሌ 15 2018 የማስተር ካርድ ፋውንዴሽን ለከፍተኛ ት/ት ተቋማት የሚሰጠውን ሽልማት የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ማሸነፉ ተነገረ፡፡ 3 ሚሊዮን ዶላር ሽልማት በሚያስገኘው በዚህ ፕሮግራም የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲን ጨምሮ 5 የአፍሪካ ዩኒቨርስቲዎች ማሸነፋቸው ተነግሯል፡፡ ከዩኒቨርስቲው ገፅ ያገኘነው መረጃ እንደሚያሳየው የማስተር ካርድ ፋውንዴሽን የ3 ሚሊዮን ዶላር ሽልማቱ "African Higher education for transformation prize" በሚል ፕሮግራም ስር የሚሰጥ ሲሆን ገንዘቡም የትምህርት እድል ፣ ፈጠራ እና ምርምርን ለማጠናከር ተግባር የሚውል ነው ተብሏል፡፡ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲም በምርምር እና ፈጠራ ባሳየው ልህቀት መሸለሙ ተነግሯል፡፡ የአካዳሚው የምርምር ስራዎች በሀገር ደረጃ ቅድሚያ ከተሰጠው አካሄድ ጋር የተስማማ መሆኑ ፣ ሳ
Jul 221 min read
የሐምሌ 15 2018 የውጪ ሀገር ወሬዎች
#ሞሪታንያ በሞሪታንያ የባህር ዳርቻ አቅራቢያ በደረሰ የባህር አደጋ 144 ጥገኝነት ፈላጊዎቹ ሳይሞቱ አልቀረም ተባለ፡፡ የአደጋው ሟቾች መነሻዋን ከጋምቢያ በማድረግ ወደ ስፔን በማምራት ላይ በነበረች ጀልባ የተሳፈሩ ጥገኝነት ፈላጊዎች እንደሆኑ አፍሪካ ኒውስ ፅፏል፡፡ በጀልባዋ ተሳፍረው የነበሩት በሙሉ ከተለያዩ የአፍሪካ አገሮች የመጡ ጥገኝነት ፈላጊዎች መሆናቸው ታውቋል፡፡ 38 ጥገኝነት ፈላጊዎችን በሕይወት ማትረፍ እንደተቻለ የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኮሚሽን /UNHCR/ መረጃ ያሳያል፡፡ አፍሪካውያን ጥገኝነት ፈላጊዎች ወደ ስፔኗ ካናሪ ደሴት በመናኛ ጀልባዎች የሚደርጉት የባህር ጉዞ አደጋ እንደሚደጋገምበት መረጃው አስታውሷል፡፡ አደጋውን ለማስቀረት ገፊ ምክንያቶቹ በወጉ ሊመረመሩ ይገባል መባሉ ተሰምቷል፡፡ #የመን የየመን ሁቲዎች የትኞቹም የመር
Jul 222 min read
በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የህፃናት እንክብካቤ ማዕከላት ወይም ማቆያዎች ላይ ለውጦች እየመጡ ነው ተባለ፡፡
ሐምሌ 15 2018 በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የህፃናት እንክብካቤ ማዕከላት ወይም ማቆያዎች ላይ ለውጦች እየመጡ ነው ተባለ፡፡ ከጥቂት አመታት በፊት የህፃናት ማቆያዎቹ ጥቂት ነበሩ ያለው የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት አሁን ላይ ከፍተኛ መሻሻሎች ታይተውበታል ብሏል፡፡ ጥናቱም በግል እና በመንግስት ማቆያዎች ላይ ያሉ ለውጦችን እና መሻሻሎችን ለማየት ሞክሯል የተባለ ሲሆን በመንግስት የሚሰሩት ማዕከላት የስራ ቦታ እና የህዝብ ማቆያዎች ናቸው ብሏል፡፡ በዚህም የህዝብ የሚባሉት ማቆያዎችን መንግስት ከምግብ ጀምሮ መሰረተ ልማቶችን እና ሌሎች ለህፃናቱ የሚያስፈልጉ ነገሮችን አሟልቶ የሚያቀርብ መሆኑ የተነገረ ሲሆን ሌላኛው በመንግስት ተቋማት ለሚሰሩ ሰራተኞች ልጆች የተዘጋጀው የስራ ቦታ የህፃናት ማቆያዎች ነው፡፡ የጥናቱ ውጤት የሚያሳየውም የተ
Jul 221 min read


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግል ትምህርት ቤቶችን የክፍያ ጭማሪ ጉዳይ በተመለከተ አምና ያወጣው ደንብ ትምህርት ቤቶች እንደ ደረጃቸው እስከ 68 በመቶ የዋጋ ጭማሪ እንዲያደርጉ ፈቅዷል።
ሐምሌ 15 2018 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግል ትምህርት ቤቶችን የክፍያ ጭማሪ ጉዳይ በተመለከተ አምና ያወጣው ደንብ ትምህርት ቤቶች እንደ ደረጃቸው እስከ 68 በመቶ የዋጋ ጭማሪ እንዲያደርጉ ፈቅዷል። የዋጋ ጭማሪውም ለሁለት ዓመት የሚያገለግል ቢሆንም ለሁለተኛ ጊዜ ጭማሪ ያደረጉና የተጋነነ ክፍያ የሚጠይቁ እንዳሉ እየተሰማ ነው። ይህ በፍፁም ህጋዊ አይደለምም ተብሏል። ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ... ፋሲካ ሙሉወርቅ
Jul 221 min read


የነዳጅ የሚያጓጉዙ ቦቴ ባለንብረቶች በየሁለት አመቱ የትራንስፖርት ታሪፍ እንዲሻሻልላቸው ህግ ቢኖርም ስራ ላይ እየዋለ ባለመሆኑ የባንክ እዳ መክፈል አልቻልንም አሉ፡፡
ሐምሌ 15 2018 የነዳጅ የሚያጓጉዙ ቦቴ ባለንብረቶች በየሁለት አመቱ የትራንስፖርት ታሪፍ እንዲሻሻልላቸው ህግ ቢኖርም ስራ ላይ እየዋለ ባለመሆኑ የባንክ እዳ መክፈል አልቻልንም አሉ፡፡ የመኪና መለዋወጫ ውድነትና ሌላም ጫና ቢኖርብንም በሚገባን ልክ ክፍያ እያገኘን ባለመሆኑ ከስራው ለመውጣት እየተገደድን ነው ይላሉ፡፡ የኢትዮጵያ የፈሳሽ ጭነት ማጓጓዣ ባለንብረቶች ማህበር የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን በተገኘበት በጉዳዩ ላይ ውይይት አድርጓል፡፡ በዘርፉ ላይ ጥናት አድርጋቸው አምጡ ብንባልም ከአንዴም ሁለቴ ጥናት አድርገን ለሚመለከተው አካል ብንሰጥም ምንም የተለወጠም የተሻሻለው ነገር የለም ሲሉ ያስረዳሉ፡፡ የባንክ እዳ የኢንሹራንስ የመኪና መለዋወጫና የአሽከርካሪ ክፍያ እና ሌላም ሌላም ተደማምሮ ኪሳራ ውስጥ ገብተናል መንግስት ሊመለከተን ይገባል ሲሉ ባለ
Jul 221 min read
በአዲስ አበባ ደረሰኝ ያልቆረጡ ከ4ሺህ 100 በላይ የጭነት መኪኖች ከ3 ቢሊዮን ብር በላይ ተቀጡ፡፡
ሐምሌ 15 2018 በአዲስ አበባ ደረሰኝ ያልቆረጡ ከ4ሺህ 100 በላይ የጭነት መኪኖች ከ3 ቢሊዮን ብር በላይ ተቀጡ፡፡ የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ በከተማዋ ጭነት ይዘው የሚገቡና የሚወጡ ተሸከርካሪዎች ለጫኑት እቃ በእለቱ የተቆረጠ ደረሰኝ መያዛቸውን እየተከታተለ ካለፈው ዓመት ጀምሮ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን ተናግሯል፡፡ ይህንን መቆጣጠር ያስፈለገውም ነጋዴዎች ደረሰኝ ላለመቁረጥ እቃዎችን በየመጋዘኑ በማከማቸት ሽያጩን ከዚያው ከመጋዘን እያደረጉ በመሆኑ ነው የሚለው ቢሮው፤ እየተገባደደ ባለው ዓመትም ቁጥጥሩን ጠንከር አድርጎ መቀጠሉን ነግሮናል፡፡ በገቢ ግብር ህጉ መሰረት ደረሰኝ ያልተቆረጠበትን እቃ ጭኖ የተገኘ ነጋዴ ለያዘው እቃ ደረሰኝ እንዲቆርጥ እንዲሁም ደረሰኝ ባለመቁረጥ የሚጣልበትን የ100 ሺህ ብር ቅጣት እንዲከፍል ይደረጋል፡፡ ቢሮው ባለፉት
Jul 221 min read


የኢትዮጵያን የተቆላ ቡና በኢ-ኮሜርስ ንግድ ለአለም ገበያ ማቅረብ የሚቻልበት የንግድ መድረክ ዛሬ ስራ መጀመሩ ተነገረ፡፡
ሐምሌ 15 2018 የኢትዮጵያን የተቆላ ቡና በኢ-ኮሜርስ ንግድ ለአለም ገበያ ማቅረብ የሚቻልበት የንግድ መድረክ ዛሬ ስራ መጀመሩ ተነገረ፡፡ ይህ አዲስ መድረክ በአለም ዙሪያ ያሉ ቡና ወዳጆች የኢትዮጵያን የተቆላ ቡና ባሉበት ቦታ ሆነው በኦንላይን በማዘዝ በጥቂት ቀናት ውስጥ መረከብ እንዲችሉ የሚያደርግ ነው ተብሏል፡፡ ዛሬ በሃያት ሪጀንሲ ሆቴል በተካሄደ ዝግጅት ዲ.ኤች.አል ኤክስፕረስ ኢትዮጵያ እና ኢ.ኤክስ.ኤም ግሎባል ኃላ.የተ.የግ.ማህበር የኢ-ኮሜርስ የውጭ ንግድ መድረኩ መጀመሩን ይፋ አድርገዋል፡፡ ዲጂታል የግብይት መድረኩ አስር የኢትዮጵያ የቡና ብራንዶችን ይዞ ስራ የጀመረ ሲሆን ለግል መጠቀሚያ የሚሆኑ ስፔሻሊቲ ትዕዛዞችን እንዲሁም ከፍተኛ መጠን ያለው ትዕዛዝን ለመፈፀም ያስችላል ተብሏል፡፡ ይህ የተለያየ የኢትዮጵያን የተቆላ የቡና ብራንድ በአን
Jul 222 min read
በአለም ዙሪያ ከ30 በላይ ሀገሮች የኒውክሊየር የሀይል ማመንጫን ለኤሌክትሪክ የሀይል ምንጭነት ይጠቀማሉ፡፡
ሐምሌ 15 2018 በአለም ዙሪያ ከ30 በላይ ሀገሮች የኒውክሊየር የሀይል ማመንጫን ለኤሌክትሪክ የሀይል ምንጭነት ይጠቀማሉ፡፡ ለግንባታው የሚጠየቀው ገንዘብ ከሌሎቹ አማራጮች አንፃር ውድ ነው የሚባለው የኒውክለየር ሀይል ማመንጫ ዋጋው ከፍተኛ ከሆነ በሀገሮቹ ተመራጭ የሚሆነው ለምን ይሆን? በሩሲያ የኒውክለር ምህንድስናን ያጠኑት ኢንጂነር አሸብር ተስፋዬ የኒውክለር የኤሌክትሪክ ማመንጫ ጣቢያ ከሌሎቹ በተለየ ለተከታታይ 18 ወራት የማይዋዥቅ ኃይል ይሰጣል ይላሉ። ሌሎች ኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች በተለያየ ተግዳሮት የሚያመነጩት ኃይል ከፍ ዝቅ ይላል የሚሉት ባለሙያው ኒውክለር ግን 90 በመቶ አስተማማኝ እና ጥራት ያለው ኃይል ይሰጣል በማለት ያስረዳሉ። ከዚህ በተጨማሪ እንደ ነዳጅ እና ጋዝ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች የካርበን ልቀት የለውም ይላሉ። የ
Jul 221 min read


የግሉን ዘርፍ አላላውስ ያሉ የተለያዩ ችግሮች
ሐምሌ 14/2018 መንግስት ከአለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት ( #IMF ) ጋር የደረሰው የኢኮኖሚ ማሻሻያ አንዱ ግብ የግሉ ዘርፍ የሚመራው ኢኮኖሚን መገንባት ነው፡፡ የግሉ ዘርፍ በአቅም እያደገ ስለመሆኑ፣ የተለያዩ ምቹ ሁኔታዎችን እየፈጠሩ እንደሆነ መንግስት ይናገራል፡፡ ይሁንና አሁንም የግሉን ዘርፍ አላላውስ ያሉ የተለያዩ ችግሮች መኖራቸው ይነሳል፡፡ ስለመፍትሔው ጠይቀን ተከታዩን አሰናድተናል፡፡ ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ… ንጋቱ ረጋሳ የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… Website፡ https://www.shegerfm.com/ YouTube : https://shorturl.at/18TS1 Telegram : https://shorturl.at/68aeK Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4 WhatsApp : https://shortu
Jul 211 min read
ፕሮግራሞች
bottom of page
_edited.jpg)
