top of page


ጥቅምት 19 2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች
#ብራዚል የብራዚል ፖሊስ የሬዮ ዴ ጄኒየሮ ከተማን ከተደራጁ ወሮበሎች ለማፅዳት ባካሄደው ዘመቻ በጥቂቱ 64 ሰዎች ተገደሉ ተባለ፡፡ ከተማይቱ በቅርቡ አለም አቀፋዊ የአየር ለውጥ ጉባኤን እንደምታስተናግድ ሬውተርስ ፅፏል፡፡ ፖሊስ ለዚህ ጉባኤ ቅድመ ዝግጅት ሬዮ ዴ ጄኔሮን ከወሮበሎች ለማፅዳት በዘመቻ ላይ ነው ተብሏል፡፡ በአጋጣሚው በተፈጠረው ግጭት ከተገደሉ 64 ሰዎች መካከል 4ቱ የፖሊስ መኮንኖች መሆናቸው ታውቋል፡፡ በትናንቱ ዘመቻ 2 ሺህ 500 ፖሊሶች እና ሌሎች የፀጥታ ባልደረቦች መካፈላቸው ተጠቅሷል፡፡ በግጭቱ በፀጥታ ባልደረቦቹ እና በተደራጁት ወሮበሎች መካከል የተኩስ ልውውጥ እንደነበር መረጃው አስታውሷል፡፡ ፖሊስ ከ80 በላይ የተደራጁ ወሮበሎችን አስሬያለሁ ማለቱ በመረጃው ተጠቅሷል፡፡ #ቤኒን በቤኒን የዋነኛው ተቃዋሚ
1 day ago2 min read


ጥቅምት 17 2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች
#ቱርክ በቱርክ PKK የተሰኘው የኩርዶች የቀድሞ አማጺ ቡድን ታጣቂዎቹን ከቱርክ ወደ ኢራቅ ማስወጣት ጀመረ፡፡ PKK ታጣቂዎቹን ወደ ኢራቅ ማስወጣት የጀመረው ከቱርክ መንግስት ጋር በጀመረው የሰላም ሒደት መሰረት እንደሆነ አሶሼትድ ፕሬስ ፅፏል፡፡ የኩርዶቹ ታጣቂ ቡድን ከእንግዲህ የትጥቅ አመፅ እርም ይሁንብኝ ያለው ባለፈው አመት ግንቦት ወር ላይ እንደነበር መረጃው አስታውሷል፡፡ በትጥቅ መፍታት ሒደት ላይ ይገኛል ተብሏል፡፡ PKK ታጣቂነቱን ትቶ በሰላማዊ የፖለቲካ ትግል ብቻ የመቀጠል ፍላጎት እንዳለው ተጠቅሷል፡፡ ቡድኑ ለወሰደው እርምጃ አስተማማኝነት የቱርክ መንግስት PKK ወደ ሰላማዊ የፖለቲካ ማህበርነት የሚለወጥበትን ሁኔታ እንዲያመቻችለት መጠየቁ ተሰምቷል፡፡ PKK የትጥቅ አመፅ እርም ይሁንብኝ ያለው ከ40 አመታት በኋላ እንደሆነ መረጃው አስታውሷ
3 days ago2 min read


ጥቅምት 13 2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች
#ሱዳን በሱዳን የRSF ፈጥኖ ደራሽ ሀይል ከአገሪቱ ኤርፖርቶች የሚነሱ እና በኤርፖቶቹ የሚያርፉ አውሮፕላኖችን በሙሉ አወድማለሁ ሲል ዛተ፡፡ ዛቻውን ያሰሙ የፈጥኖ ደራሹ ሀይሉ አዛዥ ሌተና ጄኔራል ሞሐመድ ሐምዳን ዳጋሎ እንደሆኑ ሱዳንስ ፖስት ፅፏል፡፡ ፈጥኖ ደራሽ ሀይሉ ትናንት ወደ አገልግሎት ተመልሷል በተባለው የካርቱም ኤርፖርት ላይ ተደጋጋሚ የድሮን ጥቃት ሰንዝሯል ተብሏል፡፡ የካርቱም ኤርፖርት ትናንት ከ2 ዓመታት በኋላ የመጀመሪያውን የሀገር ውስጥ በረራ አውሮፕላን ማስተናገዱ ታውቋል፡፡ ፈጥኖ ደራሽ ሀይሉ ከሱዳን መንግስት ጦር ጋር ሲዋጋ ከ2 ዓመታት ከመንፈቅ በላይ ሆኖታል፡፡ ጦርነቱን ማቆሚያ አንዳችም ፍንጭ አይታይም፡፡ #አሜሪካ በአሜሪካ በሁለት የሩሲያ ታላላቅ የነዳጅ ኩባንያዎች ላይ ያነጣጠረ አዲስ ማዕቀብ ጣለች፡፡ ማዕቀቡ የተጣለባቸው ሮስ
Oct 232 min read


ጥቅምት 12 2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች
#ካሜሩን በካሜሩን ከሳምንት በፊት በተካሄደው ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ አረጋዊው የአገሪቱ መሪ ፖል ቢያ እንዳሸነፉ የቅድሚያ ውጤቱ አሳየ ተባለ፡፡ የአገሪቱ የምርጫ አከናዋኝ መስሪያ ቤት በቅድሚያ ውጤቱ ፖል ቢያ ለፕሬዘዳንታው ምርጫው ከተሰጠው ድምፅ 53 በመቶውን በማግኘት አሸንፈዋል ማለቱን አፍሪካ ኒውስ ፅፏል፡፡ የፖል ቢያ የቅርብ ተፎካካሪ ኢሳ ቺሮማ ባካሪ ያገኙት ድምፅ 35 በመቶ እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡ ባካሪ ከምርጫው በኋላ በተደጋጋሚ አሸንፌያለሁ ሲሉ ሰንብተዋል፡፡ ኢሣ ቺሮማ ባካሪ ውጤቱ በወጉ ይጣራልኝ ማለት መጀመራቸው ተሰምቷል፡፡ የ92 አመቱ አረጋዊ ፖል ቢያ የምርጫ ድላቸው ከፀናላቸው የ42 አመታት መሪነታቸውን በመ5 ዓመታት ይጨምርላቸዋል ተብሏል፡፡ የአገሪቱ ህገ መንግስታዊ ምክር ቤት ይፋዊ ውጤቱን ሰሞኑን እወቁት እንደሚል በመረጃው ተጠቅሷል፡፡
Oct 222 min read


ጥቅምት 11 2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች
#ፈረንሳይ የፈረንሳይ ሹሞች እጅግ ውድ የአገራችንን ቅርሶች ማስጠበቅ ተስኖናል ሲሉ በፀፀት ተናገሩ፡፡ የሹሞቹ አስተያየት የተሰማው በርዕሰ ከተማዋ ፓሪስ ከሚገኘው የሉቨር ቤተ መዘክር ውድ ጌጣ ጌጦች ከተሰረቁ በኋላ እንደሆነ ቢቢሲ ፅፏል፡፡ ጌጣ ጌጦቹ የአገሪቱ ቅርሶችም በመሆናቸው በዋጋ እንደማይታመኑ እየተነገረ ነው፡፡ ከተዘረፉት ቅርሶች መካከል የፈረንሳዩ ንጉሰ ነገስት ናፖሊዮን በናፖርት ለባለቤቱ አበርክቶለት የነበረ በአልማዝ የተንቆጠቆጠ ሐብልም ይገኝበታል ተብሏል፡፡ ዘራፊዎቹ ላይ በፍጥነት ካልተደረሰባቸው ቅርሶቹን በማወላለቅ በትንሽ በትንሹ ወደ ውጭ አገራት ሊያሸሿቸው ይችላሉ የሚል ስጋት አሳድሯል፡፡ የፓሪሱ ዘረፋ በመሰል ቤተ መዘክሮች የደህንነት ጥበቃው በእጅጉ እንዲጠናከር የማንቂያ ደወል ሆኗል ተብሏል፡፡ የቤተ መዘክሩ የቅርሶች ዘረፋ በአገሪቱ
Oct 212 min read


ጥቅምት 10 2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች
#እስራኤል እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ዳግም የአየር ድብደባዋን ፈፀመች ተባለ፡፡ የእስራኤል ጦር ዳግም የአየር ድብደባውን የቀጠለው በጋዛ ደቡባዊ ክፍል እንደሆነ ቢቢሲ ፅፏል፡፡ ለደቡባዊ ጋዛው የአየር ድብደባ እስራኤል በሐማስ ትንኮሳ ተፈፅሞብኛ የሚል ክስ ማቅረቧን ተሰምቷል፡፡ የእስራኤል ጦር በሐማስ ፀረ ታንክ ሚሳየል ተተኩሶብኛ ብሏል፡፡ የፍልስጤማውያኑ ታጣቂ ቡድን ሐማስ በፊናው አንዲትም ጥይት አልተኮስኩም ማለቱ ተሰምቷል፡፡ የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለጋዛ ሰላም ባቀረቡት ባለ 20 ነጥቦች የሰላም እቅድ ተፋላሚዎቹ በተኩስ አቁም ሰንብተዋል፡፡ ይሁንና እስራኤል እና ሐማስ በተኩስ አቁም መጣስ መካሰሳቸው ተደጋግሟል፡፡ የእስራኤል ጦር ከትናንቱ የጋዛ የአየር ድብደባ በኋላ ወደ ተኩስ አቁሙ ተመልሻለሁ ማለቱ ተሰምቷል፡፡ #ኬንያ የኬንያ የቀድሞ
Oct 202 min read


ጥቅምት 7 2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች
#ሕንድ የሕንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሕንድ የሩሲያን የነዳጅ ዘይት መግዛት እንደምታቆም ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራሞዲ ማረጋገጫ ሰጥተውኛ ስለማለታቸው የምናውቀው ነገር የለም አለ፡፡ ትራምፕ ከትናንት በስቲያ ሕንድ የሩሲያን ነዳጅ መግዛት እንደምታቆም ማረጋገጫ አግኝቻቸው ሲሉ መናገራቸውን ቢቢሲ አስታውሷል፡፡ የህንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ቃል አቀባይ በትራምፕ እና በናሬንድራ ሞዲ መካከል ይህን መሰል ንግግር ስለመደረጉ አላውቅም ማለታቸው ተሰምቷል፡፡ በጉዳዩ ላይ ከዚህ ቀደም ንግግረግ ቢደረግም ነዳጁ ግዢውን ስለማቆም የተደረሰ መደምደሚያ የለም ብለዋል፡፡ የህንድ መንግስት በዚህ ጉዳይ ባወጣው መግለጫ እኛ የምናስቀድመው የአገሪቱን ፍላጎት እና የኢነርጂ ዋስትና ነው ማለቱ ተጠቅሷል፡፡ ሕንድ ከቻይና በመቀ
Oct 172 min read


ጥቅምት 6 2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች
#የአፍሪካ_ህብረት የአፍሪካ ህብረት ወታደራዊ የመንግስት ግልበጣ የተደረገባትን ማዳጋስካርን ከአባልነት አግጃለሁ ማለቱ ተሰማ፡፡ በዚያ ካፕሳት የተሰኘው ልዩ የጦር ክፍል መኮንኖች የፕሬዘዳንት አንድሬይ ራጆሊናን መንግስት ማስወገዳቸውን እወቁልን ያሉት መሰንበቻው እንደሆነ አልጀዚራ ፅፏል፡፡ የጦር መኮንኖቹ መንግስታዊ ስልጣኑን የተቆጣጠሩት አገሪቱ ከ2 ሳምንታት በላይ በተቃውሞ ስትናጥ ከሰነበተች በኋላ ነው፡፡ የአገሪቱ ህገ መንግስታዊ ፍርድ ቤት የገልባጮቹ አለቃ ኮሎኔል ሚካኤል ራንድ ኒሪያናን ጊዜያዊ ፕሬዘዳንት እንዲሆኑ ፈቅዶላቸዋል፡፡ የገልባጮቹ አለቃ በነገው እለት ቃለ መሐላ በመፈፀም ሀላፊነታቸው ይረከባሉ ተብሏል፡፡ ከዚያ አስቀድሞ ግን የአፍሪካ ህብረት ማዳጋስካርን ከአፍሪካ ህብረት አባልነትዋ አግጃለሁ ማለቱ ተሰምቷል፡፡ #ቬኒዙዌላ የቬኒዙዌላው ፕሬ
Oct 163 min read


ጥቅምት 3 2018 - የባህር ማዶ ወሬዎች
#ማሊ ምዕራብ አፍሪካዊቱ አገር ማሊ አሜሪካውያንም ወደኛ ለመምጣት ለቪዛ ሲያመለክቱ እስከ 10 ሺህ ዶላር የሚደርስ የዋስትና ገንዘብ እንዲያሲዙ ልጠይቅ ነው አለች፡፡ ቀደም ሲል አሜሪካ ከተለያዩ የአፍሪካ አገሮች ቪዛ የሚጠይቁ ከ5 እስከ 10 ሺህ ዶላር የዋስትና ገንዘብ እንዲያሲዙ የሚጠይቅ አሰራር ተግባራዊ እንደምታደርግ እወቁልኝ ካለች መሰንበቷን አናዶሉ አስታውሳል፡፡ አዲሱ አሰራሯን ከ10 ቀናት ባልበለጠ ጊዜ ተግባራዊ ማድረግ እንደምትጀምር ታውቋል፡፡ የማሊ መንግስት መግለጫም ለአዲሱ የአሜሪካ የቪዛ መመሪያ ምላሽ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡ የማላዊ እና የዛምቢያ መንገደኞች የአሜሪካ ቪዛ ለማግኘት ለቃለ መጠይቅ ከመቅረባቸው አስቀድሞ ከ5 እስከ 15 ሺህ የአሜሪካ ዶላር በዋስትና ማስያዝ እንደሚጠበቅባቸው መረጃው አስታውሷል፡፡ #ካሜሮን ካሜሩናውያን ቀጣይ ፕሬዘ
Oct 132 min read


መስከረም 28 2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች
#ፈረንሳይ ፖለቲካዊ ቀውሷ እየተባባሰ የመጣው የፈረንሳይ ፕሬዘዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ስልጣን እንዲለቁ እና አጣዳፊ ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ ሊጠሩ ይገባል ተባለ፡፡ ሀሳቡን ያቀረቡት በአስተዳደራቸው የመጀመሪያው ጠቅላይ...
Oct 82 min read


መስከረም 26 2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች
#ሶማሊያ የሶማሊያው ፅንፈኛ ቡድን /አልሸባብ/ በርዕሰ ከተማዋ ሞቃዲሾ በሚገኝ እስር ቤት ላይ ጥቃት መፈፀሙ ተሰማ፡፡ በአልሸባብ ታጣቂዎች ጥቃት ደርሶበታል የተባለው የእስር ማዕከል በአገሪቱ ቤተ መንግስት አቅራቢያ...
Oct 62 min read


መስከረም 23 2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች
#ደቡብ_አፍሪካ የደቡብ አፍሪካው ፕሬዘዳንት ሲሪል ራማፎሣ ለጋዛ ፍልስጤማውያን ሰብአዊ እርዳታ ለማቅረብ በጀልባ ሲያመሩ በእስራኤል ጦር ተይዘው የታሰሩት በጎ ፈቃደኞች እንዲለቀቁ ጠየቁ፡፡ ከታሰሩት የብዙ አገሮች ዜጎች...
Oct 32 min read


መስከረም 23 2018 - ወጋገን ባንክ በስዊፍት የሚላክን ዓለም አቀፍ ክፍያ ወጋገን ሞባይል መተግበሪያን በመጠቀም በኦንላይን መከታተል የሚያስችላቸውን አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ተናገረ
ወጋገን ባንክ በስዊፍት የሚላክን ዓለም አቀፍ ክፍያ ወጋገን ሞባይል መተግበሪያን በመጠቀም በኦንላይን መከታተል የሚያስችላቸውን አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ተናገረ፡፡ አገልግሎቱ በተለይም በገቢ እና ወጪ ንግድ ዘርፍ...
Oct 31 min read


መስከረም 22 2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች
#ኒጀር_እና_ማሊ የኒጀር እና የማሊ ወታደራዊ መንግስታት በምክክር ላይ ናቸው ተባለ፡፡ የሁለቱ አገሮች ምክክር አስተናጋጅ ማሊ እንደሆነች አፍሪካ ኒውስ ፅፏል፡፡ የኒጀሩ ወታደራዊ መንግስት መሪ ጄኔራል አብዱራሂማኔ...
Oct 22 min read


መስከረም 20 2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች
#አሜሪካ የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ የጋዛ የሰላም እቅድ በአውሮፓ እና በመካከለኛው ምስራቅ የብዙ አገሮችን ድጋፍ እያገኘ ነው ተባለ፡፡ እቅዱ ትራምፕ እና የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ...
Sep 302 min read


መስከረም 19 2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች
#ሱዳን የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ካሚል ኢድሪስ የአለም ማህበረሰብ RSFን በአሸባሪነት ይፈረጅልን አሉ፡፡ በሌተና ጄኔራል ሞሐመድ ሐምዳን ዳጋሎ የሚመራው RSF ፈጥኖ ደራሽ ሀይል ከሱዳን መንግስት ጦር ጋር ሲዋጋ ከ2...
Sep 292 min read


መስከረም 16 2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች
#እስራኤል የእስራኤል የጦር በየመኗ ርዕሰ ከተማ ሰንዓ ከባድ የአየር ድብደባ ፈፀመ ተባለ፡፡ በድብደባው ከ10 የማያንሱ የእስራኤል የጦር አውሮፕላኖች መካፈላቸው ታውቋል፡፡ ከየመን ሁቲዎች ጋር ቅርበት አለው የሚባለው...
Sep 262 min read


መስከረም 16 2018 - ኢትዮጵያ እና ሩሲያ የኒውክሌር ልማት ፕሮጀክት ስምምነት መፈራረማቸው ተሰማ
ሩሲያ እና ኢትዮጵያ በኢትዮጵያ የኑክሌር ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ልማት ዙሪያ በሮሳቶም እና በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል መካከል የድርጊት መርሃ ግብር ተፈራረመዋል ሲል ስፑትኒክ ዘግቧል። የሮሳቶም ዋና ሥራ አስፈጻሚ...
Sep 261 min read


መስከረም 15 2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች
#አሜሪካ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአየር ክልላችን በሩሲያ የጦር አውሮፕላኖች ተጥሶብናል የሚሉ አባል የኔቶ አገሮች አውሮፕላኖቹን መትተው መጣል አለባቸው አሉ፡፡ ቀደም ሲል ኢስቶኒያ እና ሮማንያ የአየር...
Sep 252 min read


መስከረም 14 2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች
#ጀርመን ጀርመን የወታደሮቿን ብዛት እና የመከላከያ ወጪዋን በእጅጉ ልትጨምር ነው ተባለ፡፡ አገሪቱ በብዙ ሺህዎች የሚቆጠሩ ወታደሮችን ለመመልመል መሰናዳቷን አሶሼትድ ፕሬስ ፅፏል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የጀርመን የጦር...
Sep 241 min read


መስከረም 13 2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች
#ደቡብ_ሱዳን የደቡብ ሱዳኑ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዘዳንት ሪያክ ማቻር የፍርድ ሒደት ትናንት ተጀመረ፡፡ ማቻር በብርቱ ብርቱ ወንጀሎች የተከሰሱት ከመንፈቅ በፊት በናሲር በሚገኝ የመንግስት ሰራዊት የጦር ሰፈር ላይ...
Sep 232 min read
ፕሮግራሞች
bottom of page








