top of page


በጋሞ ዞን በየመሬት መንሸራተት አደጋ መሞታቸው ከተረጋገጡ 125 ሰዎች አስክሬናቸው የተገኘው የ81 ሰዎች ብቻ ነው ተባለ፡፡
መጋቢት 7/2018 በጋሞ ዞን ከሳምንት በፊት በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ መሞታቸው ከተረጋገጡ 125 ሰዎች እስካሁን አስከሬናቸው የተገኘው የ81 ሰዎች ብቻ ነው ተባለ፡፡ የቀሪዎቹን አስከሬን ለማውጣት ሲደረግ የቆየው በቁፋሮ የታገዘ የማፈላለግ ስራም እንዲቆም መደረጉን ሰምተናል፡፡ ይህን ያለው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ነው። እንደ ቢሮው መረጃ ከሆነ አስክሬን የማፈላለግ ስራው ቆሞ የ44 ሰዎች አስከሬን አደጋው በተከሰተበት በዚያው ስፍራ የቀብር ቦታው ሆኖ እንዲቀጥል ተወስኗል ተብሏል፡፡ እዚህ ውሳኔ ላይ የተደረሰው አስከሬኑ 7 ቀን አልፎታል በሚል ነው፡፡ በአደጋው ምክንያትም ከ16 ሺህ በላይ ሰዎች ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸውንም የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት ሃላፊ አቶ ኃይለማርያም ተ
8 hours ago1 min read


በኢትዮጵያ የኦዲት ስራ በዝቅተኛ ዋጋ የሚከወን እና ጥራቱን ያልጠበቀ በመሆኑ በገበያው ችግር እየፈጠረ ነው ተብሏል።
መጋቢት 7/2018 በሀገር የፋይናንስ ሥርዓት ከሚረበሹበት፤ ከሚታመሙበት ጉዳዮች መካከል አንደኛው የተዝረከረ የሂሳብ አያያዝና ጥራት የሌለው ጥንቅቅ ያላለ የኦዲት ሪፖርት ነው ። የኦዲት ሪፖርት ጥራቱ የደረጃውን ጠብቆ ካልተሰራ ዞሮ ዞሮ የሕዝብ ጥቅም ያለባቸውን ተቋሞች መነካካቱ አይቀርም። በፋይናንስ ሥርዓት በባንክ ፤ ማይክሮ ፋይናንስ ፤ኢንሹራንስና ሌላውም የሚደረገው የኦዲት ስራ የህዝብ ጥቅም የሀገርን ኢኮኖሚ በአንድም ሆነ በሌላ ስለሚነካ ከፍተኛ ጥንቃቄ መደረግ እንዳለበት ባለሙያዎች ይመከራሉ። በኢትዮጵያ የኦዲት ስራ በዝቅተኛ ዋጋ የሚከወን እና ጥራቱን ያልጠበቀ በመሆኑ በገበያው ችግር እየፈጠረ ነው ተብሏል። በዚህም ምክንያት ምክንያታዊ የኦዲት ክፍያ ስራ ላይ እንዲውል ያግዛል የተባለ አዲስ መመሪያ መውጣቱ ተሰምቷል፡፡ የኦዲት ስራ ደረጃው ዝቅ
8 hours ago1 min read


ከአዲስ አበባ ከተማ መሬት 52 በመቶው ለመንገድ፤ ለወንዝ ዳርቻ እና ለአረንጓዴ ልማት የተያዘ ነው ተብሏል።
መጋቢት 7/2018 ከአዲስ አበባ ከተማ መሬት 52 በመቶው ለመንገድ፤ ለወንዝ ዳርቻ እና ለአረንጓዴ ልማት የተያዘ ነው ተብሏል። ለመኖሪያ እንዲሁም ለመስሪና ማምረቻ ሊውል የሚችለው የከተማዋ መሬት 48 በመቶ ብቻ እንደሆነ የከተማ ልማት ባለሞያው አቶ ሢሣይ ዘነበ ይናገራሉ። ፍላጎቱን ከአቅርቦቱ ጋር እንዳይጣጣም ያደረገው አንዱ ምክንያትም ይኸው እንደሆነ ባለሞያው ይጠቅሳሉ። በየጊዜው የሚጨምረው የህዝብ ቁጥር እና ወደ ከተማዋ የሚደረግ ፍልሰት ነገሩን ከድጡ ወደ ማጡ አድርጎታልም ብለዋል። የከተማ አስተዳደሩ ይህን እጥረት ያለበት ሃብት ለግለሰቦች ከሚያስተላልፍባቸው መንገዶች አንዱ ሊዝ እንደሆነ የጠቀሱት አቶ ሢሣይ የዚህ ክፍያ ግን ከፍተኛ እንደሆነ ተናግረዋል። ይህ ከፍተኛ ክፍያ ደግሞ ግለሰቡ መሬቱ ላይ ገንዘቡን ስለሚጨርስ ለግንባታ የሚተርፈው ነገር እ
9 hours ago1 min read


በስራቸው ውጤታማ የሆኑ የአዲስ አበባ አነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንዱስትሪዎች የቆይታ ጊዜያቸው
መጋቢት 7/2018 በስራቸው ውጤታማ የሆኑ የአዲስ አበባ አነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንዱስትሪዎች የቆይታ ጊዜያቸው ቢያበቃም በተሰጣቸው የማምረቻ ቦታ ለተጨማሪ አንድ ዓመት እንዲሰሩ በከተማዋ ካቢኔ ከሠሞኑ እንደተፈቀደላቸው ተነገረ። የከተማ አስተዳደሩ በ43 ሄክታር መሬት ላይ ያስገነባቸባቸውን የማምረቻ ሼዶች በቅርቡ ለመካከለኛ እና አነስተኛ አምራች ኢንዱስትሪዎች ሊያስረክብ እንደሆነም ሠምተናል። በአነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንዱስትሪዎች የተሰማሩ አንቀሳቃሾች በተሰጣችሁ የማምረቻ ቦታ ላይ ለአምስት ዓመት ከሰራችሁ በኋላ ፤ ለሌሎች መልቀቅ አለባቸው የሚለው መመሪያ ስጋት ላይ እንደጣላቸው ተናግረዋል፡፡ በአንዳንድ አካባቢዎች የተፈቀደላችሁ ጊዜ አብቅቷል በሚል ሼዶች እየታሸጉ ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ንግድ ምክር ቤት ከሠሞኑ ባዘጋጀው አንድ መድረክ ላይ
11 hours ago1 min read


በጋሞ ዞን በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ 3,461 ሰዎች ከመኖሪያ ቤታቸው ተፈናቅለው ለከፍተኛ ሰብአዊ ቀውስ መጋለጣቸውን ኢሰመኮ ተናገረ፡፡
መጋቢት 4/2018 በጋሞ ዞን በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ ህይወታቸው ካለፈው ሰዎች በተጨማሪ 3,461 ሰዎች ከመኖሪያ ቤታቸው ተፈናቅለው ለከፍተኛ ሰብአዊ ቀውስ መጋለጣቸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ተናገረ፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ሙሉ በሙሉ የወደሙ መኖሪያ ቤቶች እና ማሳዎችን ጨምሮ በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን ኢሰመኮ አረጋግጫለሁ ብሏል። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ ጋሞ ዞን፣ ጋጮ ባባ፣ ቦንኬ፣ ካምባ ዙሪያ እና ምዕራብ አባያ ወረዳዎች በሚገኙ 6የተለያዩ ቀበሌዎች የተከሰቱ የመሬት መንሸራተት፣ የናዳ እና የጎርፍ አደጋዎችን ተከትሎ የደረሱ ጉዳቶችን እየተከታተለ አንደሆነ አስረድቷል። ኮሚሽኑ መግለጫውን ዛሬ እስካወጣበት ቀን ድረስ በድምሩ የ65 ሰዎች ሕይወ
4 days ago1 min read


547 - ስለ ህገወጥ የስራ ስምሪት እና ጉዳቶቹ በተግባር ካለፉበት በላይ ማን ሊያወራ ይችላል?
ስለ ህገወጥ የስራ ስምሪት እና ጉዳቶቹ በተግባር ካለፉበት በላይ ማን ሊያወራ ይችላል? ሙሉ ዝግጅቱን ያድምጡ…… አዘጋጅ የኔነህ ሲሳይ
4 days ago1 min read


በጋሞ ዞን ሰሞኑን በተከሰተው የመሬት መንሸራተት እና የጎርፍ አደጋ የሟቾች ቁጥር 64 መድረሱ ተነገረ።
መጋቢት 3/2018 በጋሞ ዞን ሰሞኑን በተከሰተው የመሬት መንሸራተት እና የጎርፍ አደጋ የሟቾች ቁጥር 64 መድረሱ ተነገረ። የተጎዱትን በህይወት የማትረፉ ስራ ከዚህ በውሃላ ብዙም ተስፋ የለውም፣ቀሪ የአስከሬን ፍለጋ ላይ ትኩረት ተደርጎ እየተሠራ ነው ተብሏል። የሟቾቹ ቁጥር 52 ስለመድረሱ አስቀድመን ነግረናችሁ የነበረ ሲሆን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ የተጨማሪ ሰዎች አስክሬን መገኘቱን ተናግሯል። እስካሁን አስከሬናቸው የተገኘ የሟቾች ቁጥርም 64 ደርሷል ብሏል። የዞኑ ፖሊስ መምሪያ በአካባቢው ነዋሪ የነበሩና በአደጋው የጠፉ ሰዎች ቁጥር 128 መሆኑን ተናግሯል። እስካሁን ባለው መረጃ ከዚህ ውስጥ የ64ቱ ሰዎች አስክሬን መገኘቱን የጋሞ ዞን ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር አብረሀም ቡሔ ተናግረዋል። ኢንስፔክተሩ በሶስት ወረዳዎች አደጋ ተመዝጋቧል ያሉ ሲሆን ከሁሉም
4 days ago1 min read


የዱር እንስሳት አደንና ሽያጭ ፣ የፓርኮች መራቆት፣ ግጭት እና የፋይናንስ እጥረት የዱር እንስሳትና የፓርኮች ጥበቃ ስራ ፈተና ሆኗል ተባለ።
መጋቢት 3/2018 የዱር እንስሳት አደንና ሽያጭ ፣ የፓርኮች መራቆት፣ ግጭት እና የፋይናንስ እጥረት የዱር እንስሳትና የፓርኮች ጥበቃ ስራ ፈተና ሆኗል ተባለ። ይህ የተባለው የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን የተመሰረተበትን 60ኛ ዓመት ዛሬ ሲያከብር ነው። የቱሪዝም ሚኒስትር ድኤታው አቶ ስለሺ ግርማ የኢኮ ቱሪዝምና የብርቅዬ እንስሳት ቱሪዝም ኢትዮጵያ ውስጥ እየሰፋ መጥቷል ብለዋል። ላለፉት 60 ዓመታት ህገወጥ የዱር እንስሳት አደንና ሽያጭ፣ የፓርኮች መራቆት፣ የአየር ንብረት ለውጥ እና የፋይናንስ እጥረት ዘርፉን ሲገጥሙት የነበሩ ችግሮች ናቸው ተብሏል። የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ኩመራ ዋቅጅራ በኢትዮጵያ 30 ፓርኮች፣ ከ90 በላይ ጥብቅ ስፍራዎች ስለመኖራቸው ተናግረዋል። ከነዚህ ውስጥ የባሌ ብሔርራዊ ፓርክና ሰሜን
4 days ago1 min read


ህገ ወጦች ጤነኛ ህፃናት የአካል ጉዳተኛ እያደረጓቸው ለጎዳና ላይ ልመና እንደሚያሰማሯቸው ጥናት አሳየ።
መጋቢት 2/2018 ህገ ወጦች ጤነኛ ህፃናት እና አቅመ ደካሞችን የአካል ጉዳተኛ እያደረጓቸው ለጎዳና ላይ ልመና እንደሚያሰማሯቸው ጥናት አሳየ። የተሻለ ህይወት ትኖራላችሁ እየተባሉ ከክፍለ ሃገር ወደ ከተማ የሚመጡ ጤነኛ ህፃናት ጭምር ሰዎችን ለማራራት በሚል ዓይነ ስውር እየተደረጉ ለልመና መሰማራታቸውን ጥናቱ ጠቅሷል። ጥናቱን ፖፕሌሽን ካውንስል የተባለና ትኩረቱን በጤና ነክ ምርምሮች ላይ ያደረገ መንግስታዊ ያልሆነ ተቋም የተሰራ ሲሆን በጥናቱ አዲስ አበባ፣ ድሬዳዋ እና መቀሌ መካተታቸው ተነግሯል። ህፃናት እና አቅመ ደካሞችን እየመለመሉ ለልመና የሚያሰማሩ ሰዎች የአካል ጉዳት የሌለባቸውን ጭምር የአካል ጉዳተኛ እንደሚያደርጓቸው የነገሩን የፖፑሌሽን ካውንስል የኢትዮጵያ ተወካይ ጌታቸው ተሾመ(ዶ/ር) ናቸው። ከቤተሰቦቻቸው ተለይተው ከትውልድ ስፍራቸው የሚመ
5 days ago1 min read


በኢትዮጵያ የነፍስ ወከፍ ገቢን መሰረት ያደረገ ገቢ ግብር ተግባራዊ ማድረግ ይቻላል?
መጋቢት 2/2018 በኢትዮጵያ የነፍስ ወከፍ ገቢን መሰረት ያደረገ ገቢ ግብር ተግባራዊ ማድረግ ይቻላል? የአገሪቱ ኢኮኖሚው የሚመነጨውን ያክል ገቢ እየተሰበሰበ እንዳልሆነ በተደጋጋሚ ሲነገር ይሰማል። በዚህም የተነሳ የታክስ አይነቱ በላይ በላዩ ሆኖ ይታያል። የገንዘብ ሚኒስቴር በጠራው በገቢ ግብር ማሻሻያ ረቂቅ ደንብ ወይይት ላይ የተገኙት የተመሰከረለት የሂሳብ ባለሞያው አቶ አወቀ አስፋው ኢኮኖሚያችንን ብናያው ሲሉ ይመክራሉ፡፡ በለሙያው በአገሪቱ ኢኮኖሚው የሚመነጨውን ያክል ገቢ እየተሰበሰበ አይደለም የሚል ሃሳብ ሁሌ እንደሚነሳ አስታውሰው፤ በቅርብ በተሰሩ እና በወጡ መረጃዎች መሰረት ኢትዮጵያ በህዝብ ብዛት 138 ሚሊዮን በመያዝ ከ233 አገራት 10ኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ ይህም ትልቅ ቁጥር መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ የጥቅል ዓመታዊ ምር
5 days ago2 min read


ጀነራል አስራት ዴኔሮ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋውን ተክተው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው ተሾሙ፡፡
መጋቢት 2/2018 ጀነራል አስራት ዴኔሮ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋውን ተክተው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው ተሾሙ፡፡ ሹመቱን የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ናቸው፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ባወጣው መረጃ መሰረት ረዳት ኮሚሽነር ቶፊቅ መደድ እና አቶ ኤርዚቅ ኢሳ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ሆነው ተሹመዋል፡፡
6 days ago1 min read


በጋሞ ዞን የጎርፍ ናዳ 30 ሰዎችን ገደለ።
መጋቢት 1/2018 በጋሞ ዞን የጎርፍ ናዳ 30 ሰዎችን ገደለ። በጋሞ ዞን በተለያዩ አካባቢዎች በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት፣ በተለይም በደጋማ አካባቢዎች በተከሰተ የናዳና የጎርፍ አደጋ የ30 ስዎች ህይወት ማለፉን የዞኑ አስተዳደር ተናግሯል። የዞኑ አስተዳደር በአሁኑ ወቅት ተጨማሪ ጉዳት እንዳይደርስ አስፈላጊውን ክትትልና ድጋፍ እያደረኩ ነው ብሏል። የ30 ህይወት የቀጠፈው የጎርፍ አደጋ መቼ እንዳጋጠመ ዞኑ ያለው ነገር የለም። የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ "በጋሞ ዞን በደጋማ አካባቢዎች በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት በተከሰተ የመሬት ናዳና የጎርፍ አደጋ የ30 ወገኖቻችን ህይወት በማለፉ የተሰማኝን ጥልቅ ሀዘን በራሴና በክልሉ መንግስት ስም እገልጻለሁ"ብለዋል። እንደ አርባ ምንጭ እና ገረሴ ከተሞች ባለፋት ሁለት ቀናት በአ
6 days ago1 min read


መጋቢት 2/2018 - ከፍተኛ ትችት የቀረበባቸው እና የገቢ ግብር ማሻሻያ ረቂቅ ደንብ ላይ የተካተቱ የህግ ክፍሎች እንዲሻሻሉ ቢጠየቅም አዋጁ ስለጸደቀ ድንጋጌዎችን ማሻሻል አይቻልም ተባለ።
መጋቢት 2/2018 ከፍተኛ ትችት የቀረበባቸው እና የገቢ ግብር ማሻሻያ ረቂቅ ደንብ ላይ የተካተቱ የህግ ክፍሎች እንዲሻሻሉ ቢጠየቅም አዋጁ ስለጸደቀ ድንጋጌዎችን ማሻሻል አይቻልም ተባለ። ይህን ያለው የገንዘብ ሚኒስቴር ነው። የገንዘብ ሚኒስቴር መጋቢት ትላንት፤ ባለፈው ዓመት መጨረሻ ለጸደቅው የግቢ ግብር ማስፈጸሚ ረቂቅ ደንብ ላይ በመስሪያ ቤቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ የሞያ፣የስራ እና የድርጅት ተወካይዎች ጋር ከ5 ሰዓት በላይ የፈጀ ወይይት አካሂዷል ። በወይይቱ ላይ ጥያቄ ካቀረቡት ከ20 በላይ ተሳታፊዎች ውስጥ የሚበዙት ተመሳሳይ ጥያቄ እና ሀሳብ ስጥተዋል ። የተጣለው የ2.5 በመቶ የአማራጭ አነስተኛ ግብር እንዲነሳ፣ድርጅቶች ወይንም ተቋማት የሂሳብ መዝገብ እንዲይዙ ያሚያስገድድው የህግ ከፍል እና በየሩብ ዓመት ግብር እንዲሰበሰብ የሚያዘው የህ
6 days ago3 min read


ከውስብስብ የአንጎል አፈጣጠር ችግር ጋር የተወለደች ህፃንን በተሳካ ቀዶ ህክምና ማከም መቻሉ ተነገረ፡፡
መጋቢት 1/2018 ከውስብስብ የአንጎል አፈጣጠር ችግር ጋር የተወለደች ህፃንን በተሳካ ቀዶ ህክምና ማከም መቻሉ ተነገረ፡፡ ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ… ቴዎድሮስ ወርቁ የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… Website፡ https://www.shegerfm.com/ YouTube : https://shorturl.at/18TS1 Telegram : https://shorturl.at/68aeK Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4 WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx X :- https://x.com/shegerfm?s=2 LinkedIn: https://shorturl.at/Vfe6i Tiktok : https://shorturl.at/lhYiv Instagram: https://shorturl.at/9X4S7
6 days ago1 min read


በየሳምንቱ 1 ሚሊዮን ሰዎች የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ እየተመዘገቡ ነው ተባለ።
መጋቢት 1/2018 በየሳምንቱ 1 ሚሊዮን ሰዎች የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ እየተመዘገቡ ነው ተባለ። በአሁኑ ሰዓት በአጠቃላይ የፋይዳ መታወቂያ የተመዘገቡ ሰዎች ቁጥር 37.5 ሚሊዮን መድረሱን የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ፅ/ቤት ዋና ዳይሬክተር ዮዳሄ አርአያስላሴ ተናግረዋል። ዋና ዳሬክተሩ ይህን ያሉት ፅ/ቤታቸው ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ጋር በመተባበር ለግል መገናኛ ብዙኀን ፋይዳ መታወቂያ በተመለከተ የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራም ላይ ባደረጉት ንግግር ነው። እስከ መጪው ሰኔ ወር ድረስ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ተመዝጋቢዎችን ብዛት 90 ሚሊዮን ለማድረስ ታቅዶ እየተሰራ እንደሆነ አቶ ዮዳሄ አስረድተዋል። የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ለመልካም አስተዳደር፣ ለማህበራዊ እና ደህንነት ጉዳዮች ከፍተኛ ጥቅም እንዳለው በፕሮግራሙ ላይ ሲነገር ሰምተናል።
7 days ago1 min read


ከመጋቢት አጋማሽ ጀምሮ በ16 ጉዳዮች ላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች የክርክር መድረክ ማካሄድ እንደሚጀምር ምርጫ ቦርድ ተናገረ።
የካቲት 30/2018 ከመጋቢት አጋማሽ ጀምሮ በ16 ጉዳዮች ላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች የክርክር መድረክ ማካሄድ እንደሚጀምር ምርጫ ቦርድ ተናገረ። ቦርዱ ይህን ያለው ባለፈው ቅዳሜ በኢዲስ ኢንትርናሽናል ኮንቬንሽን ሴንተር የሲቪል ማህበረሰብ ደርጅቶች ለዲሞክራሲያዊ ምርጫ ያላቸው ድርሻ በሚል ርዕስ በተሰናዳ የወይይት መድረክ ላይ ነው። ነጻ፣ ፍትሐዊ፣ ዴሞክራሲያዊ፣ አካታች እና ታዓማኒ ምርጫ ለማካሄድ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምን እያሰራ ነው? የሚል ጥያቄ በወይይቱ ላይ ለምርጫ ቦርድ ቀርቧል። ቦርዱን ወክለው በውይይቱ ላይ የታደሙት የምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ተስፋዬ ነዋይ የመራጮች ምዝገባ በአንዳንድ ክልሎች መጀምሩን እና የዕጩዎች መዝገባ መጠናቀቁን ተናግረዋል። አቶ ተስፋዬ ነዋይ ዘንድሮ ቦርዱ እሰራለሁ ያለው ትልቁ ስራ የፖለቲካ ፓ
Mar 91 min read


ኢትዮዽያ በአለም የሎጅስቲክስ ሜዳ
የካቲት 27/2018 የሎጅስቲክስ ስራ ፍፁም የሰላም መስመር እና እውቀት ይፈልጋል፡፡ ሎጅስቲክስ በኢትዮጵያ እንዲዘምን፣ እንዲቀላጠፍ አሁንም ብርቱ ስራ ይጠይቃል። እቃዎችን ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ለማንቀሳቀስ፣ መያዝ፣ ማከማቸት እና ማስተናገድ ፤ በየትኛውም የአለም መሮጫ ኮሪደር እና ባህር ማገላበጥ ፤ በአየር በየብስ ምድር ለመላወስ ጥንቅቅ ያለ የሎጅስቲክስ ስራ ይፈልጋል። ለዚህ ደግሞ በየጊዜው በአለም በሚደረጉ ጉባኤዎች እና የሎጅስቲክስ ማህበራት ላይ በኃላፊነት ቦታ መገኘት እንደሚያስፈልግ ይታመናል። በተለይ ከአፍሪካ ብቸኛው የአለም ፍሬይት ፎርዋርደርስ ማህበር ፊያታ የቦርድ አባል እና በ ኢትዮጵያም የማህበሩ ፕሬዝዳንት አቶ ዳዊት ውብሸት በዚህ ጉዳይ ስጋት እንዳላቸው ነግረውናል። ኢትዮዽያ በአለም የሎጅስቲክስ ሜዳ ፤ በጭነት መርከቦች እና አጠቃላ
Mar 61 min read


ደንበኞች ባሉበት ሆነው የእጅ ስልካቸውን በመጠቀም ብቻ የቆጣሪ ንባባቸውን የሚያስገቡበት አሰራር በሙከራ ደረጃ መጀመሩን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አግልግሎት ተናገረ፡፡
የካቲት 27/2018 ደንበኞች ባሉበት ሆነው የእጅ ስልካቸውን በመጠቀም ብቻ የቆጣሪ ንባባቸውን የሚያስገቡበት አሰራር በሙከራ ደረጃ መጀመሩን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አግልግሎት ተናገረ፡፡ ይህም በተደጋጋሚ ከደንበኞች የሚነሱ ቅሬታዎችን ለመፍታት ይረዳኛል ብሏል። የሙከራ ትግበራው ከ16 ሺህ በላይ የድህረ ክፍያ ተጠቃሚ ደንበኞች ባሉበት የሰሜን አዲስ አበባ ሪጅን መጀመሩን የተቋሙ የኮሙኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ አቶ አንዋር አብራር ነግረውናል ፡፡ ሥራ አስፈፃሚው የዲጂታል አሰራሩ ለደንበኞች በቀላሉ ተደራሽ ለመሆን፣ የፍጆታ ሂሳብን በወቅቱ ለመፈጸም፣ ጥራት ያለው አገልግሎት ለመስጠት እንዲሁም ጊዜና ወጪን ለመቆጠብ ያስችላል ብለውናል፡፡ በዚህም ከየካቲት 13 ቀን እስከ የካቲት 23 ቀን 2018 ዓ.ም ደንበኞች የፍጆታ ንባባቸውን በቀላሉ በቤታቸው ሆነው ለዚሁ አ
Mar 61 min read


የባቱ - አርሲ ነገሌ 57 ኪሎ ሜትር የፍጥነት መንገድ ግንባታ ዋና ዋና ሥራዎቹ ተጠናቅቀዋል ተባለ።
የካቲት 26/2018 የሞጆ - ሐዋሳ የፍጥነት መንገድ አካል የሆነው የባቱ - አርሲ ነገሌ 57 ኪሎ ሜትር የፍጥነት መንገድ ግንባታ ዋና ዋና ሥራዎቹ ተጠናቅቀዋል ተባለ። የመንገድ ኮሪደሩ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ እና ምዕራብ አርሲ ዞኖች የሚገኙትን የባቱ ከተማን፣ የአዳሚ ቱሉ እና አርሲ ነገሌ ወረዳዎችን ጨምሮ ከ17 በላይ ቀበሌዎችን ያስተሳስራል ተብሏል። የመንገድ ግንባታው የአዲስ አበባ - ሞያሌ - ናይሮቢ - ሞምባሳ የመንገድ ኮሪደር አካል መሆኑ ተነግሯል። ግንባታውን ለማከናወን ከዓለም ባንክ የተገኘ 5.3 ቢሊዮን ብር ወጪ መሆኑ ተነግሯል። 57 ኪሎ ሜትር የሚሸፍነው የባቱ - አርሲ ነገሌ የፍጥነት መንገድ ግንባታ በ90 ሜትር የመንገድ ወሰን ውስጥ የሚገኝ ሲሆን፤ የጎን ስፋቱ የመንገድ አካፋይን ጨምሮ 31.6 ሜትር መሆኑን የኢትዮጵያ መን
Mar 52 min read


በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት ዓመታት በነበሩ ግጭቶች ከ300 በላይ ትምህርት ቤቶች ተዘግተው እንደነበር ተነግሯል።
የካቲት 26/2018 በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት ዓመታት በነበሩ ግጭቶች ከ300 በላይ ትምህርት ቤቶች ተዘግተው እንደነበር ተነግሯል። ይህም የክልሉን አጠቃላይ 20 በመቶ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ማራቁን የክልሉ ምክትል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በሽር አብዱረሂም ተናግረዋል። አሁን ላይ ግን በክልሉ በተሰሩ ስራዎች በአብዛኛው በሚባል ደረጃ ትምህርት ቤቶች ወደ መደበኛ የመማር ማስተማር ሂደታቸው መመለሳቸውን ኃላፊው አንስተዋል። ኃላፊው ይህንን ያሉት ኩሶ ኢንተርናሽናል የተባለ የተራድኦ ተቋም በክልሉ ባለፉት 6 ዓመታት ሴት ተማሪዎችን ለዩንቨርሲቲ የማብቃት ፕሮጀክት (U_Girls project) የማጠቃለያ መድረክ ላይ ነው። የትምህርት ቢሮ ኃላፊው በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመማር ማስተማር ችግሮችን በመፍታት ሂደት ውስጥ የኩሶ ኢንተርናሽናልን
Mar 51 min read


ፆታዊ ጥቃት የደረሰባቸውን ሴቶች ለመደገፍ የሚያስችል ሁለተኛ ዙር ፕሮጀክት ወደ ስራ መግባቱ ተነገረ፡፡
የካቲት 26/2018 በተለያዩ አካባቢዎች ባለ የሰላም እጦት እና የሰሜኑ ጦርነት ምክንያት ፆታዊ ጥቃት የደረሰባቸውን ሴቶች ለመደገፍ የሚያስችል ሁለተኛ ዙር ፕሮጀክት ወደ ስራ መግባቱ ተነገረ፡፡ በአለም ባንክ የሚደገፈው እና ለ5 ዓመታት ይቆያል የተባለው ይህ ፕሮጀክት ሊጠናቀቅ 2 ዓመታት እንደቀረው ሲነገር ሰምተናል፡፡ በዚህም ሁለተኛው ምዕራፍ እና በሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል ይተገበራል የተባለው ስራ ወደ ትግበራ መግባቱ ተነግሯል፡፡ በጦርነት ምክንያት ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶች የጤና ድጋፍ እንዲያገኙ፣ የኢኮኖሚ ምስቅልቅል የገጠማቸው ወደ ቀድሞ ስራቸው እንዲመለሱ እና ሌሎች ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ጉዳዮቻቸው ላይ የሚሰራ ፕሮጀክት መሆኑ ተነግሮለታል፡፡ ፕሮጀክቱም በ5 ክልሎች የሚተገበር ሲሆን አማራ፣ ትግራይ፣ ኦሮሚያ፣ አፋር፣ ቤኒሻን
Mar 51 min read
ፕሮግራሞች
bottom of page

