top of page


በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴው በሰጠው ምክረ ሀሳብ መሰረት የተረጋጋ ገበያ እንዲኖር ያግዛሉ የተባሉ የተለያዩ ውሳኔዎች ፀድቀዋል፡፡
ሐምሌ 7/2018 በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴው በሰጠው ምክረ ሀሳብ መሰረት የተረጋጋ ገበያ እንዲኖር ያግዛሉ የተባሉ የተለያዩ ውሳኔዎች ፀድቀዋል፡፡ ላኪዎች ከሚያገኙት የውጭ ምንዛሬ 70 በመቶውን እንዲያዙበት ተደርጎ ለባንኮች በአስገዳጅነት ይሸጡት የነበረው የውጭ ምንዛሬ ከ50 በመቶ ወደ 30 በመቶ ዝቅ ተደርጓል፡፡ ይህም ከፍትሃዊነት ባሻገር ባንኮችም ደንበኛ ተኮር አገልግሎት በመስጠት ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የሚያግዛቸው ነው ተብሏል፡፡ ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ.... ትዕግስት ዘሪሁን
Jul 141 min read
ኢትዮጵያ በ2018 በጀት አመት በ9 ወራት ውስጥ ከወጪ ንግድ 7 ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር ገቢን አግኝታለች፡፡
ሐምሌ 7/2018 ኢትዮጵያ በ2018 በጀት አመት በ9 ወራት ውስጥ ከወጪ ንግድ 7 ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር ገቢን አግኝታለች፡፡ ከውጪ አስፈላጊ ለምትላቸው እቃዎች ግዢ 16 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ወጪ አውጥታለች፡፡ በዘጠኝ ወራቱ ኢትዮጵያ ወደ ውጪ ከላከችው እቃ ያገኘችው ገቢና ወደ ሀገር ውስጥ ላስገባችው እቃ ያወጣችው ወጪ መካከል ያለው ልዩነት የ8 ነጥብ 9 ቢሊዮን ዶላር ነው፡፡ ይህም በወቅቱ የኢትዮጵያ የንግድ ሚዛን ጉድለት መጠኑን ያሳያል፡፡ በ2017 በጀት አመት የኢትዮጵያ የንግድ ሚዛን ጉድለት 10 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ሲሆን የበጀት አመቱ አጠቃላይ የንግድ ሚዛን ጉዱለት ከዚህ ሊቀንስ እንደሚችል ተነግሯል፡፡ በ2018 በጀት አመት 11 ቢሊዮን ዶላር ከወጪ ንግድ ያገኘችው ኢትዮጵያ ከባለፈው አመት ጋር ሲመሳከር የ2 ነጥብ 8 ቢሊዮን ዶላር ጭማሪ
Jul 141 min read
ሐምሌ 7/2018 - ዓለም አቀፍ ወሬዎች
#ኢራን የኢራን አብዮታዊ ዘብ የቀድሞ አዛዥ ሆሴን ካናኒ የአሜሪካውን ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕን ዋይት ሐውስ ድረስ ዘልቀን እንገድለዋን ሲሉ ዛቱ፡፡ ካናኒ ኢራን ደግሞ ለዚህ አቅሙም ችሎታውም አላት ማለታቸውን ሚድል ኢስት ሞኒተር ፅፏል፡፡ በቅርቡ ለሟቹ የኢራን የቀድሞ ጠቅላይ መሪ ስንብት እና የቀብር ሥነ ሥርዓት ሲከናወን ትራምፕን የመግደል ዛቻ ሲስተጋባ ነበር ተብሏል፡፡ የቀድሞው የኢራን ጠቅላይ መሪ አያቶላ ዓሊ ኻሚኒ ከቤተሰብ አባሎቻቸው ጋር የተገደሉት በጦርነቱ መጀመሪያ አሜሪካ እና እስራኤል በፈፀሙት ጣምራ ድብደባ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ዓሊ ኻሚኒን በመተካት ልጃቸው ሞጅታባ ኻሚኒ አዲሱ ጠቅላይ መሪ ሆነው መመረጣቸው ይታወቃል፡፡ ትራምፕ ኢራኖች እሳቸውን ለመግደል ከሞከሩ በአገሪቱ ላይ ሺህ ሚሳየሎችን አዘንብባታለሁ ሲሉ መዛታቸውን መረጃው አስታውሷል
Jul 142 min read


አሟሟታቸው አጠራጣሪ የሆኑ ግለሰቦች አስከሬን እንዲመረመርለት ፖሊስ አገልግሎቱን በመስጠት ስሙ በቀዳሚነት ወደ ሚጠቀሰው ዳግማዊ ሚኒሊክ ሪፈራል ሆስፒታል ይልካል።
ሐምሌ 7/2018 አሟሟታቸው አጠራጣሪ የሆኑ ግለሰቦች አስከሬን እንዲመረመርለት ፖሊስ አገልግሎቱን በመስጠት ስሙ በቀዳሚነት ወደ ሚጠቀሰው ዳግማዊ ሚኒሊክ ሪፈራል ሆስፒታል ይልካል። አንዳንዴ ግን በሟች ቤተሰቦች በኩል ኩላሊት ይወጣል ፤ ልብ ይሰረቃል በሚል ስጋት የአስከሬን ምርመራውን የመቃወም ዝንባሌ እንደሚታይ ሆስፒታሉ አመልክቷል። ስጋቶቹ ትክክልም ፤ ምክንያታዊም አይደሉም ሲሉ አንድ የሆስፒታሉ ባለሞያ ሳይንሳዊ እና ህጋዊ መሰረቶችን ጠቅሰው ነግረውናል። ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ.... ገዛ ጌታሁን
Jul 141 min read


ታሪክን_የኋሊት
ሐምሌ 7/2018 የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፣ ሁለተኛው ኢትዮጵያዊ ፓትርያርክ ፣ በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደሉት ፣በ1971 ዓ.ም በዛሬው ቀን ነበር፡፡ ፓርትርያክ ብፁዕ ወቅዱስ አባ ቴዎፍሎስ በግፍ የተገደሉት በኮሎኔል መንግስቱ ኃ/ማርያም በሚመራው ወታደራዊ አስተዳደር ደርግ ትዕዛዝ ነው፡፡ ደርግ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፣ የንጉሱን አስተዳደር የምትደግፍና ፣ ለሶሻሊዝም ሥርዓት እንቅፋት ነች ብሎ ስላመነ ፣ ለማጥቃት የሚፈልግበትን መንገድ ሲያደራጅና የስም ማጥፋት ፕሮፓጋንዳ ሲያከናውን ቆየ፡፡ ከአንድ አመት በኋላም ፓትርያርኩንና ሊቃነ ጳጳሳትን አሰረ፡፡ ብጹዕ ወቅዱስ አባ ቴዎፍሎስ ፣ ሁለተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ሆነው የተሰየሙት፣ የመጀመሪያውን ኢትዮጵያዊ ፓትርያርክ ፣ ብጹዕ ወ
Jul 142 min read


''በኢትዮጵያ አብዛኞቹ የሂሳብ ባለሙያዎች ሙያዊ ብቃት ያላቸው አይደሉም'' የኢትዮጵያ የተመሰከረላቸው የሂሳብ ባለሙያዎች ኢንስቲትዩት
ሐምሌ 6/2018 በኢትዮጵያ እየሰሩ ያሉ አብዛኞቹ የሂሳብ ባለሙያዎች ፕሮፌሽናል (ሙያዊ ብቃት ያላቸው)አይደሉም ተባለ። ሙያዊ ብቃት ያላቸው የሂሳብ ባለሙያዎች ከ500 ያልበለጡ በመሆናቸው ትልልቅ ድርጅቶች ባለሙያዎችን ከውጭ አያስመጡ እንደሚያሰሩ የኢትዮጵያ የተመሰከረላቸው የሂሳብ ባለሙያዎች ኢንስቲትዩት ተናግሯል። ሙያዊ ብቃት የግድ እየሆነ በመምጣቱ 700 የሂሳብ ባለሙያዎች የትም ሄደው መስራት የሚያስችላቸው አለም አቀፍ መስፈርቶችን ያሟላ ስልጠና እየወሰዱ ነውም ተብሏል። ኢትዮጵያ ያሏት ከ500 ያልበለጡ ፕሮፌሽናል ባለሙያዎች ጎረቤት ሃገር ኬንያ ካላት 60ሺህ ጋር ንፅፅር ውስጥ የሚገባ አይደለም ያለው ኢንስቱትዩቱ፤ ኢኮኖሚው እየሰፋና በሙያው የተረጋገጠ ብቃት ያላቸውን የሂሳብ ባለሙያዎችን የሚፈልግበት ጊዜ ላይ ደርሰናል፤ እያሰለጠንን ሙያዊ ብቃት ያ
Jul 131 min read


የዋጋ ግሽበቱ በመጪዎቹ 6 ወራት ሁለት አሃዝ ሆኖ ሊቀጥል እንደሚችል ብሔራዊ ባንክ ተናገረ።
ሐምሌ 6/2018 የዋጋ ግሽበቱ በመጪዎቹ 6 ወራት ሁለት አሃዝ ሆኖ ሊቀጥል እንደሚችል ብሔራዊ ባንክ ተናገረ። ይህን ለመቋቋም ያግዝ ዘንድም በባንኮች ላይ ተጥሎ የቆየው የብድር ገደብ ቢነሳም ጥብቅ የገንዘብ ፖሊሲው እንዲቀጥል ተወስኗል ብሏል። በባንኩ ስር የተቋቋመው የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ ሰባተኛውን ስብሰባ አካሂዶ የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፏል። የገንዘብ ኮሚቴው ያሳለፋቸውን ውሳኔዎች በተመለከተ የብሔራዊ ባንክ ገዥ እዮብ ተካልኝ(ዶ/ር) ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል። በዚህም በዚህ አመት ታህሳስ ወር ላይ የዋጋ ግሽበት ወደ አንድ አሃዝ 9 ነጥብ 7 በመቶ ወርዶ እንደነበረ አስታውሰዋል። ይሁንና የኢራኑን ጦርነት ተከትሎ የዋጋ ግሽበቱ ወደ ሁለት አሃዝ ከፋ ብሎ ባለፈው ሚያዝያ ወር 11.7 በግንቦት ወር ደግሞ ወደ 13. 4 በመቶ ከፍ ብሏል ብለዋል ዋና
Jul 131 min read


ኢትዮጵያ የብሪክስ ልማት ባንክ አባል ብትሆን ምን ይጠቅማት ይሆን?
ሐምሌ 6/2018 ኢትዮጵያ የብሪክስ ልማት ባንክ አባል ለመሆን ዳር ዳር እያለች ነው፡፡ የብሪክስ ልማት ባንክ ቦርድ ባለፈው ጥቅምት ወር ኢትዮጵያን በእጩ አባልነት መቀበሉን ይፋ አድርጓል፡፡ የብሪክስ ህብረት አባል የሆነችው ኢትዮጵያ አሁን ደግሞ በህብረቱ የተመሰረተው የልማት ባንክ አባል መሆኗ ምን ይጠቅማት ይሆን? የልማት ባንኩ አሰራርና የብድር ሥርዓትስ ከቀደሙት ከነዓለም ባንክ የተለየ ይሆን? ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ…. ንጋቱ ረጋሣ
Jul 131 min read


በምክክሩ የሚሳተፉ ታዛቢዎችን ለጉባኤው ዝግጁ የማድረጉ ስራ እንዴት እየሆነ ነው?
ሐምሌ 4/2018 በአዲስ አበባ የሚካሄደው የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ በመጪው ሳምንት ረቡዕ ይጀመራል። የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችና ሌሎችም በምክክሩ በታዛቢነት እንዲገኙ ኮሚሽኑ ጥሪ አቅርቧል። ለመሆኑ በዓለም አቀፍ መስፈርቱ መሰረት በምክክሩ የሚሳተፉ ታዛቢዎችን ለጉባኤው ዝግጁ የማድረጉ ስራ እንዴት እየሆነ ነው? በተቀመጡ አለም አቀፍ መስፈርቶች መሰረት መሰል የምክክር ሂደቶችን የመታዘብ ስራ ምክክሩ ከመካሄዱ 45 ቀን በፊት ጀምሮ መጀመር እንዳለበት ከባለሙያዎች ሰምተናል። የኢትዮጵያ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤትን ጨምሮ ሌሎችም ተቋማት ማቅረብ ያለባቸው የታዛቢዎች ቁጥር ተወስኖ እንዲያቀርቡ ኮሚሽኑ ጥሪ ማስተላለፉና ተቋማቱም ታዛቢዎቹን እያዘጋጁ መሆኑን በኮሚሽኑ የተደራሽነት እና አጋርነት ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ፍሬሰናይ ገበየሁ ጠቁመዋል።
Jul 112 min read


ዲጂታል ባንኪንግ ስራን ያቀለለ መሆኑ ቢነገርለትም በሌላ በኩል ለዲጂታል መጭበርበርም እያጋለጠ መሆኑ ይነገራል፡፡
ሐምሌ 4/2018 ዲጂታል ባንኪንግ ስራን ያቀለለ መሆኑ ቢነገርለትም በሌላ በኩል ለዲጂታል መጭበርበርም እያጋለጠ መሆኑ ይነገራል፡፡ ከእነዚህም የማታለያ ስልቶች መካከል አንዱ ሃሰተኛ የድጅታል ደረሰኝ ሰርቶ ሻጮችን ማጭበርበር እየተበራከተ መጥቷል። ስለ ጉዳዩ ያነጋገርናቸው ነጋዴዎች፣ አጭበርባሪዎች ከባንክ ሂሳባቸው ገንዘብ ተቀናሽ ሳያደርጉ ትክክለኛውን የሚመስል ሃሰተኛ ድጅታል ደረሰኝ እያሳዩአቸው ብዙ ገንዘብ እንደተጭበረበሩ ነግረውናል፡፡ አታላዮች ይህንን ሃሰተኛ ድጅታል ደረሰኝ ለመስራት ህገ ወጥ ሶፍትዌሮችን የሚጠቀሙ ሲሆን እነዚህ ሶፍትዌሮች የፈለጉትን የገንዘብ መጠን እና የደንበኛ ስም መፃፍ እንደሚያስችሏቸው ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡ በባንክ ተቋማት ውስጥ የቢዝነስ ዴቨሎፕመንት እና ስትራቴጂ ባለሙያ የሆኑት አቶ ሃብተማርያም አደረ ባንኮች አሁን በሚከ
Jul 111 min read


ዩክሬይን ለራሷ መከላከያ የፓትሪዮት ሚሳየል እንድትሰራ የአሜሪካን ፈቃድ ልታገኝ ነው፡፡
ሐምሌ 3/2018 - ዓለም አቀፍ ወሬዎች #ዩክሬይን ዩክሬይን ለራሷ መከላከያ የፓትሪዮት ሚሳየል እንድትሰራ የአሜሪካን ፈቃድ ልታገኝ ነው፡፡ የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ዩክሬይን የፓትሪዮት የሚሳየል ጋሻን እንድትሰራ ፈቃድ እንደሚሰጧት መናገራቸውን አሶሼትድ ፕሬስ ፅፏል፡፡ ትራምፕ ዩክሬይን የሚሳየል መከላከያ ጋሻውን በራሷ እንድትሰራ የአሜሪካን ፈቃድ እንደምታገኝ ፍንጭ የሰጡት በቱርክ በተካሄደው የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅ (ኔቶ) የመሪዎች ጉባኤ በተጓዳኝ ነው ተብሏል፡፡ ዩክሬይን በጦርነቱ ሂደት ይኸው የሚሳየል መከላከያ ጋሻ እንዲቀርብላት ስትጎተጉት ቆይታለች፡፡ አሜሪካ ከዚህ ቀደም ሚሳየሉ በሌላ አገር መመረቱን ስታከላክል መቆየቷን መረጃው አስታውሷል፡፡ ትራምፕ ዩክሬይን የፓትሪዮት ሚሳየልን በራሷ እንድታመርት መፍቀዳቸው ከሩሲ
Jul 102 min read


በሰባተኛው ሃገራዊ ምርጫ የተከሰቱ ችግሮች እንዳይደገሙ የህግ ማሻሻያ በማድረግ እንዲታረሙ ተጠየቀ፡፡
ሐምሌ 3/2018 በሰባተኛው ሃገራዊ ምርጫ የተከሰቱ ችግሮች መልሰው እንዳይደገሙ የህግ ማሻሻያ እና የአፈፃፀም ማስተካከያ በማድረግ እንዲታረሙ ተጠየቀ፡፡ ባለፈው ሰኔ 2 ቀን 2018 ዓ.ም በተፈናቃይ ካምፖች በተቋቋሙ ልዩ የምርጫ ጣቢያዎች የተካሄደው ምርጫ የራሱ መመሪያ ወጥቶለት የተካሄደ አዲስ አሰራር ነበር፡፡ በልዩ ሁኔታ ምርጫ ስለሚካሄድባቸው ምርጫ ጣቢያዎች ማቋቋሚያ መመሪያ ወጥቶ ተፈናቃዮች የመምረጥ መብታቸውን እንዲጠቀሙ መደረጉ መልካም መሆኑ በልዩ የምርጫ ጣቢያዎች በገለልተኝት ምርጫውን የታዘበው የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ድርጅቶች ህብረት ተናግሯል፡፡ ይሁንና ተፈናቃዮች የሚሰጡት ድምፅ ወደ ተፈናቀሉበት ቀዬ ሂዶ የሚቆጠር መሆኑ ለምርጫው ፍላጎት እንዲያጡ አድርጓቸዋል ብሏል፡፡ ለዚህም እንደማሳያ ከ20 ሺህ በላይ ተፈናቃዮች በነበሩበት ካምፕ 4
Jul 101 min read


የሀገር ውስጥ ችግርና የአለም አቀፍ ጫና እና ተፅዕኖ ምን እና ምን ናቸው?
ሐምሌ 3/2018 የውስጥ ፖለቲካዊ ችግሯን በራሷ መፍታት የቻለች ሀገር ለውጪው ተፅዕኖ ተጋላጭ አትሆንም ይላሉ ባለሙያዎች፡፡ ኢትዮጵያም ከምንም ነገር በፊት በሀገር ውስጥ ያላትን ሰላም ታረጋግጥ እየተባለ ተደጋግሞ ሲመከር ይሰማል፡፡ ለመሆኑ የሀገር ውስጥ ችግርና ፖለቲካዊ ውጥረት እንዲሁም የአለም አቀፍ ጫና እና ተፅዕኖ ምን እና ምን ናቸው? ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ…… ያሬድ እንዳሻው
Jul 101 min read


በችግሮች እየተፈተኑ ያሉት ቴአትር ቤቶች
ሐምሌ 2/2018 በተመልካች ቁጥር ማነስና በሌሎችም ችግሮች እየተፈተኑ ያሉትን የኢትዮጵያን የቴአትር ቤቶች ከችግራቸው ለማውጣት መንግስት በትኩረት ሊሰራ ይገባል ተባለ፡፡ ከገንዘብ እጥረት እስከ ግብአት እጥረት ቲያትር ቤቶቹ በበረታ ችግር ውስጥ ናቸው ተብሏል፡፡ ረዘም ላሉ ዓመታት በቴአትር ሙያ ላይ የሰሩት አርቲስት አፅናፉ መኩሪያ የቲያትር ቤቶች መዳከም ብዙ ምክንያቶች ቢኖሩትም ትልቁ ችግር ግን መንግስት ለኪነ ጥበቡ ዘርፍ ትኩረት አለመስጠቱ ነው ይላሉ። ስለ ቴአትር በቂ ዕውቀት የሌላቸው ሰዎች በቴአትር ቤቶች አስተዳደር ውስጥ ሲሾሙ ይታያል፣ ይህም የቴአትር ዘርፉን እንደጎዳው ያስረዳሉ። ሌለኛው የቴአትር ባለሙያ አርቲስት መርዕድ ነጋሽ ደግሞ በኪነ-ጥበቡ ላይ መንግስት የጣለው ታክስ ቀድሞውኑ እምብዛም ገቢ የሌለው የቲያትር ዕድገት ላይ ተፅዕኖ አሳድ
Jul 91 min read


ኢትዮጵያ የሰው ሰራሽ አስተውሎትን ከመጠቀም ባለፈ በዘርፉ አለም አቀፍ የምርምር ስራንም እየሰራች ነው ተባለ፡፡
ሐምሌ 2/2018 ኢትዮጵያ የሰው ሰራሽ አስተውሎትን ከመጠቀም ባለፈ በዘርፉ አለም አቀፍ የምርምር ስራንም እየሰራች ነው ተባለ፡፡ በአለም አቀፍ ህትመቶች ላይ የቀረቡ ከ60 በላይ ጥናቶች እስካሁን መሰራታቸው ተነግሯል፡፡ ይህን የተናገረው የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ነው። እነዚህ ጥናትና ምርምሮች በሳይንሱና በአካዳሚው አለም ከፍተኛ የምርምር እውቀና እና ማረጋገጫ አግኝተው በአለም አቀፍ ጆርናሎች እየታተሙ ነውም ተብሏል። በሌላ በኩል የኢትዮጵያ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ስነ-ምግባራዊ የሰው ሰራሽ አስተውሎት መርህን የተከተለ እንደሆነም ኢንስቲትዩቱ ተናግሯል። የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ዘውዴ በተቋማትም ሆነ በግለሰቦች ደረጃ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴ
Jul 91 min read


የሀገራዊ ምክክር ሂደቱን ፍትሃዊነትና አካታችነት የሚታዘቡ 10 ታዛቢዎችን እንደሚያሰማራ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ተናገረ።
ሐምሌ 2/2018 የሀገራዊ ምክክር ሂደቱን ፍትሃዊነትና አካታችነት የሚታዘቡ 10 ታዛቢዎችን እንደሚያሰማራ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ተናገረ። የኢትዮጵያ ሃገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሃምሌ 8 ለሚጀመረው ሃገራዊ የምክክር ጉባኤ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት 10 ታዛቢዎችን እንዲያቀርብ ኮታ እንደሰጠው ምክር ቤቱ ነግሮናል። ታዛቢዎቹ የምክክሩ ሂደት አካታችና ተደራሽ መሆን አለመሆኑን የሚከታተሉበት ሰነድ ተዘጋጅቶ ስልጠና እየተሰጠ መሆኑን የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ ተረፈ ደጌቲ ነግረውናል። ታዛቢዎቹ የተመረጡቱ የምክር ቤቱ አባል ከሆኑ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች መሆኑን የጠቀሱት አቶ ተረፈ፤ እነዚህ 50 የምር ቤቱ አባላት ዛሬ የተሰጠውን ስልጠና ወስደው ከመካከላቸው 10 ለታዛቢነት ይመረጣሉ ብለዋል። በተ
Jul 91 min read


ከ7 ቢሊዮን ብር በላይ የሚፈጀው የኢሰመኮ የ5 ዓመት ስትራቴጂክ እቅድ
ሐምሌ 2/2018 የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን "የታጠቁ የጸጥታ አካላት መበራከት" ለትግበራው እንቅፋት ሊሆንበት እንደሚችል ስጋቱን ጠቅሶ ከ7 ቢሊዮን ብር በላይ የሚፈጀውን የ5 ዓመት ስትራቴጂክ እቅድ ይፋ አድርጓል፡፡ ኮሚሽኑ ከ2019 እስከ 2023 የሚያገለግለውን የ5 ዓመት የሰብአዊ መብት ስትራቴጂክ እቅድ ዛሬ ሐምሌ 2 ቀን 2018 ዓ.ም የተለያዩ አካላት በተገኙበት በዋና መስሪያ ቤቱ ይፋ አድርጓል። የኢትዮጵያ ሰብብዊ መብቶች ኮሚሽን ዛሬ ይፋ ያደረገው እና ከትናንት ጀምሮ መተግበር የጀመረው እቅድ ከ7.6 ቢሊዮን ብር በላይ የሚፈጅ መሆኑ ተነግሯል፡፡ ይህኛው የስትራቴጂክ እቅድ የተዘጋጀው በ2014 ጀምሮ እስከ 2018 ያገለገለውን እቅድ በማብቃቱ ነው። በተጠናቀቀው ስትራቴጂ እቅድ ከ5,300 በላይ ለሚሆኑ አቤቱታዎች ምላሽ ተሰጥቷል። ከ1,10
Jul 92 min read


በዚህ ዓመት ዝርያቸው ከተዳቀሉ 4.4 ሚሊዮን ከብቶች ውስጥ 2.4 ሚሊዮን የተዳቀሉ ከብቶች ሳይሳካ ቀርቷል ተብሏል።
ሐምሌ 2/2018 በዚህ ዓመት ዝርያቸው ከተዳቀሉ 4.4 ሚሊዮን ከብቶች ውስጥ 2.4 ሚሊዮን የተዳቀሉ ከብቶች ሳይሳካ ቀርቷል ተብሏል። ከተዳቀሉት ውስጥ የተወለዱት ጥጃዎች 2 ሚሊዮን ብቻ ነው ተብሏል፡፡ ይህ የተባለው የግብርና ሚኒስቴር ላለፉት 4 ዓመታት እየተተገበረ ያለውን የሌማት ትሩፋትና የበጀት ዓመቱን የእንስሳትና የዓሣ ምርትን በተመለከተ በተሰጠው መግለጫ ነው። የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ፍቅሩ ረጋሳ (ዶ/ር)ባለፉት አመታት 228 የመኖ ማቀነባበርያዎች ወደ ስራ መግባታቸው የጠቀሱ ሲሆን ነገር ግን አሁንም ድረስ የእንስሳት መኖች ችግር አልተቀረፈም ብለዋል። የተሰሩት ማቀነባበርያዎች እና የሚመረተው የመኖ ምርት ከእንስሳቱ ቁጥር ጋር ግን የተመጣጠነ እና በቂ አይደለም ተብሏል። በበጀት ዓመቱ 420 ሺህ ቶን ማር ፣ 250 ሺህ ቶን የዶሮ ስጋ
Jul 91 min read


‘’በ5 ዓመት ውስጥ በ1,000 የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ላይ እርምጃ እንዲወሰድ አድርጌአለሁ’’ ኢሰመኮ
ሐምሌ 2/2018 የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ባለፉት 5 ዓመታት በ1,000 የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ላይ እርምጃ እንዲወሰድ ማድረጉን እና ከ17,000 በላይ ሰዎችን ከህግ ወጥ እስራት ማስለቀቁን ይፋ አደረገ። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ከ2019 እስከ 2023 ለአምስት ዓመታት የሚያገለግል ስትራቴጂክ እቅድ ዛሬ ሃምሌ 2 ቀን 2018 ዓ.ም በዋና መስሪያ ቤቱ ይፋ አድርጓል። እቅዱን ለመተግበር 7.6 ቢሊዮን ብር ያስፈልጋል ተብሏል። ኮሚሽኑ ይፋ ያደረገው ስትራቴጂክ እቅድ ከትናንት ሐምሌ 1 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ስራ ላይ መዋሉን ኮሚሽኑ አሳውቋል። ዛሬ ይፋ የተደረገው ስትራቴጂክ እቅድ ከ2014 ጀምሮ እስከ 2018 ሲያገለግል የነበረው እቅድ በማብቃቱ ነው። የሚተገበረው ስትራቴጂክ ዕቅድ የተዘጋጀው በፍጥነት እየተለ
Jul 92 min read


በማህበራዊ ትስስር ገፆች የሚፈፀሙ ማጭበርበሮች
ሐምሌ 1/2018 ማህበራዊ ትስስር ገፆች ለብዙዎች የስራ እድል መፍጠሪያ እንደመሆናቸው ለአንዳንዶች ደግሞ የመጭበርበር ምክንያት እየሆኑ ነው፡፡ ኮሚሽን ታገኛላችሁ ፣ በኦን ላይን የስራ ዘርፍ ተሰማርታላችሁ ገንዘብ ትሰራላችሁ በሚሉ አታላዮች ጥሪታቸውን ለአጭበርባሪዎች የገበሩ ተበድረው ጭምር የከሰሩ ብዙዎች መሆናቸውን ጠቅላይ ዐቃቢ ሕግ ተናግሯል፡: ጉዳያቸው በሕግ የተያዙ ያሉ እንዳሉም ሰምተናል፡፡ ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ…… ገዛ ጌታሁን
Jul 81 min read


ለዓሣ እርባታ አመቺ የሚባል የውሃ አካል የሌላት አዲስ አበባ ዓሣ ማምረት ጀምራለች ተብሏል፡፡
ሐምሌ 1/2018 ለዓሣ እርባታ አመቺ የሚባል የውሃ አካል የሌላት አዲስ አበባ ዓሣ ማምረት ጀምራለች ተብሏል፡፡ ለመሆኑ የአዲስ አበባ የአየር ንብረት ዓሣ ለማምረት አመቺ ነው ወይ? አሁን እየተመረተ ያለው እንዴት ነው ስንል ጠይቀናል፡፡ ይህ ስራ የተጀመረው በከተማዋ የኮሪደር ልማት መሰራት ከተጀመረ ወዲህ እንደሆነ የነገረን የአዲስ አበባ የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን በከተማዋ ዓሣ እየተመረተ ያለው አነስ ያሉ ሰው ሰራሽ ኩሬዎችን በማዘጋጀት ነው፤ በዚህ ዓመትም ከ23 ሺህ ኪሎ ግራም በላይ ዓሣ መመረቱን ጠቅሷል፡፡ በኮሚሽኑ የእስሳት እርባታ ባለሙያ የሆኑት አቶ ቢኒያም አድማሱ ብዙዎች ባይረዱትም እንኳን አዲስ 43 ማህበራት በዚህ መንገድ እያመረቱ ነው፤ ለዚህ አካባቢ ተስማሚ የዓሣ ዝርያዎችም ቆሮሶ ወይም በባለሙያዎቹ አጠራር ቴላፒያና ካት
Jul 82 min read
ፕሮግራሞች
bottom of page
_edited.jpg)
