top of page


‘’በ5 ዓመት ውስጥ በ1,000 የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ላይ እርምጃ እንዲወሰድ አድርጌአለሁ’’ ኢሰመኮ
ሐምሌ 2/2018 የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ባለፉት 5 ዓመታት በ1,000 የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ላይ እርምጃ እንዲወሰድ ማድረጉን እና ከ17,000 በላይ ሰዎችን ከህግ ወጥ እስራት ማስለቀቁን ይፋ አደረገ። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ከ2019 እስከ 2023 ለአምስት ዓመታት የሚያገለግል ስትራቴጂክ እቅድ ዛሬ ሃምሌ 2 ቀን 2018 ዓ.ም በዋና መስሪያ ቤቱ ይፋ አድርጓል። እቅዱን ለመተግበር 7.6 ቢሊዮን ብር ያስፈልጋል ተብሏል። ኮሚሽኑ ይፋ ያደረገው ስትራቴጂክ እቅድ ከትናንት ሐምሌ 1 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ስራ ላይ መዋሉን ኮሚሽኑ አሳውቋል። ዛሬ ይፋ የተደረገው ስትራቴጂክ እቅድ ከ2014 ጀምሮ እስከ 2018 ሲያገለግል የነበረው እቅድ በማብቃቱ ነው። የሚተገበረው ስትራቴጂክ ዕቅድ የተዘጋጀው በፍጥነት እየተለ
Jul 92 min read


በማህበራዊ ትስስር ገፆች የሚፈፀሙ ማጭበርበሮች
ሐምሌ 1/2018 ማህበራዊ ትስስር ገፆች ለብዙዎች የስራ እድል መፍጠሪያ እንደመሆናቸው ለአንዳንዶች ደግሞ የመጭበርበር ምክንያት እየሆኑ ነው፡፡ ኮሚሽን ታገኛላችሁ ፣ በኦን ላይን የስራ ዘርፍ ተሰማርታላችሁ ገንዘብ ትሰራላችሁ በሚሉ አታላዮች ጥሪታቸውን ለአጭበርባሪዎች የገበሩ ተበድረው ጭምር የከሰሩ ብዙዎች መሆናቸውን ጠቅላይ ዐቃቢ ሕግ ተናግሯል፡: ጉዳያቸው በሕግ የተያዙ ያሉ እንዳሉም ሰምተናል፡፡ ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ…… ገዛ ጌታሁን
Jul 81 min read


ለዓሣ እርባታ አመቺ የሚባል የውሃ አካል የሌላት አዲስ አበባ ዓሣ ማምረት ጀምራለች ተብሏል፡፡
ሐምሌ 1/2018 ለዓሣ እርባታ አመቺ የሚባል የውሃ አካል የሌላት አዲስ አበባ ዓሣ ማምረት ጀምራለች ተብሏል፡፡ ለመሆኑ የአዲስ አበባ የአየር ንብረት ዓሣ ለማምረት አመቺ ነው ወይ? አሁን እየተመረተ ያለው እንዴት ነው ስንል ጠይቀናል፡፡ ይህ ስራ የተጀመረው በከተማዋ የኮሪደር ልማት መሰራት ከተጀመረ ወዲህ እንደሆነ የነገረን የአዲስ አበባ የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን በከተማዋ ዓሣ እየተመረተ ያለው አነስ ያሉ ሰው ሰራሽ ኩሬዎችን በማዘጋጀት ነው፤ በዚህ ዓመትም ከ23 ሺህ ኪሎ ግራም በላይ ዓሣ መመረቱን ጠቅሷል፡፡ በኮሚሽኑ የእስሳት እርባታ ባለሙያ የሆኑት አቶ ቢኒያም አድማሱ ብዙዎች ባይረዱትም እንኳን አዲስ 43 ማህበራት በዚህ መንገድ እያመረቱ ነው፤ ለዚህ አካባቢ ተስማሚ የዓሣ ዝርያዎችም ቆሮሶ ወይም በባለሙያዎቹ አጠራር ቴላፒያና ካት
Jul 82 min read
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ትላንት ለተፎካካሪ ፓርቲ አባላት በፓርላማው ያቀረቡት የአብረን እንስራ ጥሪ ተጨማሪ ውይይት ይፈልጋል ሲሉ ፓርቲዎቹ ተናግረዋል፡፡
ሐምሌ 1/2018 ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ትላንት ለተፎካካሪ ፓርቲ አባላት በፓርላማው ያቀረቡት የአብረን እንስራ ጥሪ ተጨማሪ ውይይት ይፈልጋል ሲሉ ፓርቲዎቹ ተናግረዋል፡፡ ትናንት በስድስተኛው ፓርላማ የመጨረሻ ስብሰባውን አካሂዶ የአመቱንም የአምስተኛ ዘመኑንም የስራ ጊዜ ቋጭቷል። በፓርላማው የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በእስር ላይ ያሉ እንዲፈቱ በጫካም ያሉ ወደ ሰላሙ እንዲመለሱ መንግስት በሆደ ሰፊነት ይሰራል ብለዋል። በፓርላማው ለቆዩ የተሮካካሪ ፓርቲ አባላትም የአብረን እንስራ ጥያቄ አቅርበዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያለፉትን አምስት አመታት በፓርላማ የቆዩ የተፎካካሪ ፖርቲ አባላት ሀሳባቸውን በግልፅ ያቀረቡ እንደራሴዎችንም ትላንት በነበረው የፓርላማ ንግግራቸው አመስግነዋል። የትብብር መስክ ፓርላማ ብቻ አይደለም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስት
Jul 81 min read


ዩክሬይን የአየር መከላከያ ያለህ እያለች ነው፡፡
#ዩክሬይን ዩክሬይን የአየር መከላከያ ያለህ እያለች ነው፡፡ ዩክሬይን የተጨማሪ የአየር መከላከያ ሥርዓት ጥያቄ ያቀረበችው ሩሲያ በዩክሬይኗ ርዕሰ ከተማ ኪየቭ እና በሌሎችም ስፍራዎች የሚሳየል እና የድሮን ጥቃቷን ባከፋችባት አጋጣሚ እንደሆነ ቢቢሲ ፅፏል፡፡ ጥያቄው ዛሬ በቱርክ አንካራ ከሚከፈተው የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ድረጅት /ኔቶ/ የመሪዎች ጉባኤ ጋር ተገጣጥሟል፡፡ የዩክሬይን ሹሞች አብዛኞቹን የሩሲያ ሚሳየሎች እና ድሮኖች ብናከሽፍባትም የአየር መከላከያዎቻችን ተመናምነውብናል ማለታቸው ተሰምተምቷል፡፡ በኪየቭ እና በዙሪያ ገባዋ በሩሲያ ጥቃት 22 ሰዎች እንደተገደሉባቸው ተናግረዋል፡፡ ዛሬ በአንካራ የመከፈተው የኔቶ የመሪዎች ጉባኤ የዩክሬይኑ ጦርነት አንዱ መነጋገሪያው እንደሚሆን መረጃው አስታውሷል፡፡ #ፍልስጤም የፍልስጤማውያኑ የጦር እና
Jul 72 min read


‘’የሕዝብ አደራተ ቀብለው የሚሰርቁ አሉ፤ ነገር ግን ሌብነቱ ተቋማዊ አይደለም’’ ሲሉ ዐቢይ አሕመድ ተናገሩ።
ሰኔ 30/2018 ‘’የሕዝብ አደራተ ቀብለው የሚሰርቁ አሉ፤ ነገር ግን ሌብነቱ ተቋማዊ አይደለም’’ ሲሉ ዐቢይ አሕመድ ተናገሩ። ቃለ መሐላ ፈጽመው፣ የመንግሥትንና የሕዝብን አደራ ተቀብለው ከዚህ ምስኪን ሕዝብ የሚሰርቁ ግለሰቦች አሉ፤ ሆኖም ግን በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ የታየው ሌብነት ተቋማዊ ሳይሆን በግለሰቦች ደረጃ የሚፈጸም መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ተናግረዋል። ሌብነት ጸያፍና ቆሻሻ ተግባር እንደሆነ የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፣ ሆኖም ግን ጉዳዩ ሰዎች በየመድረኩ እንደሚናገሩት ቀላል አለመሆኑንና እርምጃ ለመውሰድ በቅድሚያ በተጨባጭና በሕግ የሚያስጠይቅ ነገር መኖር እንዳለበት ጠቁመዋል። በአሁኑ ወቅት ከሌብነት ጋር በተያያዘ በርካታ አሉባልታዎች ይሰማሉ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ እነዚህ አሉባልታዎች በሁለት መንገድ እንደሚከሰቱ አስረድተዋል። አን
Jul 71 min read


የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በኢትዮጵያ ኮዲንግ ሰልጣኞች ቁጥር እንዲያድግ ስታደርግ የነበረውን ድጋፍ እንደምትቀጥል ተናገረች።
ሰኔ 30/2018 የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በኢትዮጵያ ኮዲንግ ሰልጣኞች ቁጥር እንዲያድግ ስታደርግ የነበረውን ድጋፍ እንደምትቀጥል ተናገረች። 5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ወጣቶችን በኮዲንግ ለማሰልጠን ታቅዶ የነበረው እቅድ ከጊዜው ቀድሞ ተሳክቷል መባሉ ይታወሳል። በዚህ እቅድ ድጋፍ ማድረጓን ያስታወሰችው የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ፕሮጀክቱ ከተቀመጠለት የጊዜ ሰሌዳ አስቀድሞ በመሳካቱ የሰልጣኞችን ቁጥር ወደ 7 ሚሊዮን ከፍ ለማድረግ በሁለቱ አገራት አማካኝነት መወሰኑን አስታውሳለች። በዚህም መሰረት ተጨማሪ 2 ሚሊዮን ወጣቶች የኮዲንግ ስልጠና ኦንዲወስዱ ያስችላቸዋል ተብሏል። ይህም በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ዲጂታል አቅምን የመገንባት፣ የመንግሥት ሥራዎችን የማዘመን እና የወጣቶችን ተጠቃሚነት የማረጋገጥ ስትራቴጂካዊ አጋርነት ይበልጥ ያጠናክረዋል ተብ
Jul 71 min read


‘’በእስር ላይ ያሉ ሰዎችን ለመፍታት፣ በጫካ እና በውጭ ያሉትን ደግሞ በይቅርታ ለማስገባት ልባችን ሰፊ መሆን ይኖርበታል" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ
ሰኔ 30/2018 "የመንግስት ሀላፊዎችና ፖለቲከኞች የሀይማኖት አባቶችንና ትላልቅ ሰዎችን ተጠቅመን በተቻለ መጠን በእስር ላይ ያሉ ሰዎችን ለመፍታት፣ በጫካ እና በውጭ ያሉትን ደግሞ በይቅርታ ለማስገባት ልባችን ሰፊ መሆን ይኖርበታል" ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተናገሩ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ በፓርላማ በነበራቸው ቆይታ ማጠቃለያ ላይ ይህንን ማድረግ የሚያስፈልገው ለኢትዮጵያ ሲባል ነው ብለዋል። “TPLF 'ም ጭምር ቀልብ ከገዛ፣ አእምሮ ከገዛ ለመነጋገርና ሰላም ለማምጣት ጥረት ማድረግ ያስፈልጋል” ሲሉም አስረድተዋል። “ከሰላም ሙከራ ውጪ ያለው አይጠቅመንም፣የሚያስፈልገን ብልፅግና ላማት ነው” ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ያለፉትን አምስት አመታት በፓርላማ የቆዩ የተፎካካሪ ፖርቲ አባላት ሀሳባቸውን በግልፅ ያቀረቡ እንደራሴዎችንም አመ
Jul 71 min read


በአርሲው ግጭት የ11 ሰዎች ህይወት ማለፉን ከዚህ ውስጥ 8ቱ የፀጥታ አካላት መሆናቸወን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተናገሩ፡፡
ሰኔ 30/2018 በአርሲው ግጭት የ11 ሰዎች ህይወት ማለፉን ከዚህ ውስጥ 8ቱ የፀጥታ አካላት መሆናቸወን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተናገሩ፡፡ በዚህ ግጭት 22 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል ያሉ ሲሆን ከ90 በመቶ በላይ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው መመለሳቸወን አስረድተዋል፡፡ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ይህንን ያሉት የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት 30ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ተገኝተው ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሳላቸው ጥያቄዎች ምላሽ እየሰጡ ባለበት ወቅት ነው። ከሃይማኖት ግጭቶች ጋር በተያያዘ ለተነሳላቸው ጥያቄ ምላሽ ሲሰጡ በቅርቡ በአርሲ የነበረውን ግጭት አንስተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአርሲው ግጭት ምርጫውን ለማደናቀፍ ጥረት ሲያደርጉ ነበር ያሏቸው ኃይሎች በአዲስ አበባ እና በምርጫ አከባቢ ከፍተኛ የፀጥታ ጥበቃ ሲደረግ ስለነበር ወደ
Jul 71 min read


የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ ለስራ ጉብኝት አዲስ አበባ መግባታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ይፋ አድርጓል።
ሰኔ 30/2018 የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ ለስራ ጉብኝት አዲስ አበባ መግባታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ይፋ አድርጓል። ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአውሮፓና አሜሪካ ጉዳይ ዳይሬክተር ጄነራል አምባሳደር መለሰ ዓለም አቀባበል ተደርጎላቸዋል። የቱርኩ አናዶሉ እና የሩሲያ መገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት የሰርጌይ ላቭሮቭ የኢትዮጵያ የስራ ጉብኝት የአፍሪካ ሀገራትን የመጎብኘት እቅዳቸው አካል እና መጀመሪያ ነው። በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታም ዛሬ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጌዲዮን ጤሞቲዮስ እና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ጋር ይመክራሉ ተብሏል። በኢትዮጵያ የሚገነባው የኒውክሊየር ሀይል ማመንጫ ማዕከልን የተመለከተው ጉዳይ አንደኛው መነጋገሪያ ነጥብ ሊሆን ይችላል ብለዋል የመረጃ ምንጮቹ። ካለፈው
Jul 71 min read


ህገወጥ ደላሎች፤ ሰዎች በህገወጥ መንገድ ጉዞ ለመጀመር ሲያስቡ ወይም ህገወጥ ስደትን እዲያስቡ ከሚያደርጓቸው ከቀዳሚ ምክንያቶች መካከል ይጠቀሳል።
ሰኔ 26/2018 በየአካባቢው ያሉ ህገወጥ ደላሎች፤ ሰዎች በህገወጥ መንገድ ጉዞ ለመጀመር ሲያስቡ ወይም ህገወጥ ስደትን እዲያስቡ ከሚያደርጓቸው ከቀዳሚ ምክንያቶች መካከል ይጠቀሳል። እነዚህ ደላሎች ኢትዮጵያውያኑ በህገ- ወጥ መንገድ ከሀገራቸው እንዲወጡ የተለያዩ ማማለያዎች በመጠቀም በሺዎች የሚቆጠሩትን አስወጥተዋል፡፡ ነገር ግን በዚሁ መንገድ ከሚወጡት ሰዎች መካከል የአውሬ እራት የሚሆኑ እና ካሰቡበት ሳይደርሱ መንገድ ላይ የሚቀሩትም ብዙ ናቸው፡፡ ይህንን ስራ የሚሰሩት ደላሎችም ቢሆኑ ለህግ ሲቀርቡ እንደማይስተዋል የተነገረ ሲሆን ማህበረሰቡ ቢያውቃቸውም ደፈር ብሎ ለህግ አካላት አሳልፎ የመስጠት ልምድ እንደሌለውም በጉዳዩ ላይ የሚሰሩ ባለሙያዎች ያስረዳሉ፡፡ ህገወጥ ደላሎች ህግ ፊት ለማቅረብ ማህበረሰቡ እንዲጠቁም ለማድረግ ቢሞክርም ያ ሲሆን እንደማይ
Jul 31 min read
ትልልቅ የሚባሉ ባንኮች ኪሳራ ሊያስከትል የሚችል የብድር አሰጣጥ አሰራርን እንደሚከተሉ ጥናት አሳየ፡፡
ሰኔ 25/2018 ትልልቅ የሚባሉ ባንኮች ኪሳራ ሊያስከትል የሚችል የብድር አሰጣጥ አሰራርን እንደሚከተሉ ጥናት አሳየ፡፡ ትልልቅ ካፒታል ያላቸው ባንኮች ለኪሳራ ሊያጋልጡ የሚችሉ አሰራሮችን ስራ ላይ የሚያውሉበት አንደኛው ምክንያት አደጋ ቢያጋጥመን መንግስት ያግዘናል የሚል አስተሳብ ስላላቸው ነው ተብሏል፡፡ በጥናቱ 31 የመንግስትና የግል ባንኮችን እንደተካተቱበትና በባንኮቹ መሃል ውድድር ሲኖርና ሳይኖር ያለው ልዩነት በጥናቱ ተለይቷል፡፡ ይህንን ለማረጋገጥ የ31ን ባንኮች የፋይናንስ መረጃዎችን መመልከታቸውንም በቅድስት ማርያም ዩኒቨርሲቲ የአካዉንቲንግ እና ፋይናስ መምህርና ተመራማሪው እንዲሁም አጥኚው ነዋይ አያሌው ነግረውናል። አሁን ላይ ባንኮች በከፍተኛ ውድድር ውስጥ እየገቡ መሆኑን አንስተው ይህ ደግሞ የችግሩን መጠን እንደሚቀንስ በጥናታቸው ማረጋገጣ
Jul 21 min read


በ2018 ወደ ውጪ ከተላከ ቡና 3 ቢሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱን የግብርና ሚ/ር ተናገረ፡፡
ሰኔ 25/2018 በ2018 በጀት ዓመት ወደ ውጪ ከተላከ ቡና 3 ቢሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱን የግብርና ሚኒስቴር ተናገረ፡፡ በጀት ዓመቱ ከቡና ወጪ ንግድ 3 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር ለማግኘት የተያዘው ዕቅድ ማሳካቱን ሚኒስቴር መ/ቤቱ አስረድቷል፡፡ በባለፈው በጀት ዓመት ከቡና ወጪ ንግድ 2.65 ቢሊዮን ዶላር መገኘቱን ሚኒስቴር መ/ቤቱ አስታውሷል፡፡ መንግስት ለዘርፉ በሰጠው ትኩረት የቡናውን ዘርፍ ምርትና ምርታማነትን የሚያሳድጉ ስራዎች እየተሰሩ ነው ያለው የግብርና ሚኒስቴር በዚህም ለውጥ መጥቷል ሲል አስረድቷል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ አሁን ላይ 5.8 ሚሊዮን ገበሬ በቡና አምራችነት ተሰማርቶ የሚገኝ ሲሆን ገበሬው ከሰራው ስራ ወደ ኪሱ የተጣራ ገቢ የሚያገኘው 40 ከመቶውን ብቻ መባሉ ይታወሳል፡፡ ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ….. በረከት አካሉ
Jul 21 min read


የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት በየጊዜው ገበያው በሚፈልገው ልክ እያጠኑ የሚሰጡትን ስልጠና እንደማይከልሱ ጥናት አሳየ፡፡
ሰኔ 25/2018 የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት በየጊዜው ገበያው በሚፈልገው ልክ እያጠኑ የሚሰጡትን ስልጠና እንደማይከልሱ ጥናት አሳየ፡፡ ሰልጣኞቻቸው የወሰዱትን ስልጠና እንዴት ወደ ቢዝነስ መለወጥ እንዳለባቸው የሚያስችል ጥራት ያለው ስልጠና የማይሰጡም አሉ ተብሏል፡፡ አቶ ሀብታሙ አለማየሁ በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ የመንግስት ቴክኒክና ሞያ ማሰልጠኛ ተቋማት ውስጥ ያለው የስልጠና አካሄድን በተመለከተ ጥናት አድርገዋል፡፡ በዚህ ጥናታቸው 14 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር ያሉ የቴክኒክና ሞያ ስልጠና ተቋማትን የተመለከቱ ሲሆን በተቋማቱ ውስጥ ወጥ የሆነ አሰራር እየተተገበረ አይደለም ይላሉ፡፡ አንዳንድ ማሰልጠኛ ተቋማት የሚሰጡት ስልጠና ወቅቱ በምን መንገድ ይፈልገዋል የሚለውን በትክክል አያጠኑም ሲሉም የስረዳሉ፡፡ ይህ ዘርፍ በየጊዜው የሚሰጡ ስ
Jul 21 min read


ተሻሽሎ ስራ ላይ መዋል ከጀመረ አንድ ዓመት ያስቆጠረው የፌዴራል ገቢ ግብር አዋጅ ነባራዊ ሁኔታዎችን ያላገናዘቡ አንዳንድ ጥብቅ ድንጋጌዎች ያሉበት ነው ተባለ።
ሰኔ 25/2018 ተሻሽሎ ስራ ላይ መዋል ከጀመረ አንድ ዓመት ያስቆጠረው የፌዴራል ገቢ ግብር አዋጅ ነባራዊ ሁኔታዎችን ያላገናዘቡ አንዳንድ ጥብቅ ድንጋጌዎች ያሉበት ነው ተባለ። ድርጅቶች ቢከስሩ እንኳን ከዓመታዊ ሽያጫቸው 2.5 በመቶ ግብር መክፈል አለባቸው የሚለው አንዱ ድንጋጌ መሆኑ ተጠቅሷል። የድንጋጌው መነሻ ነጋዴዎች እያተረፉም ጭምር ከስረናል በሚል ያሳውቃሉ ከሚል እንደሆነ ተነግሯል። በኢንተር ሌግዠሪ ሆቴል በሚካሄደው ውይይት ድንጋጌው በግሉ ዘርፍ ላይ ተፅዕኖ እያሳደረ እንደሚገኝ ትኩረቱን በታክስ ዙርያ አድርጎ ተነስቷል። በተለይ ከፍተኛ ሽያጭ ያላቸው ግን ደግሞ የትርፍ ህዳጋቸው አነስተኛ የሆኑ እንደ ማኑፋክቸሪንግ እና ጅምላ ንግድ ያሉ ዘርፎች እየተጎዱ ነው። በአንድ የግብይት ወቅት ከ50 ሺህ ብር በላይ በጥሬ ገንዘብ የተከፈለን ወጪ ከታክስ
Jul 21 min read


በዋናው ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ የሚሳተፉ ከ4,000 በላይ ተወካዮች በመጪው ሳምንት አዲስ አበባ ይገባሉ ተባለ።
ሰኔ 25/2018 በዋናው ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ የሚሳተፉ ከ4,000 በላይ ተወካዮች በመጪው ሳምንት አዲስ አበባ ይገባሉ ተባለ። ተወካዮች ከትግራይ ክልል ውጪ ከተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የተወከሉ እና የተለያዩ የማህበረሰብ ከፍሎችን የወከሉ ናቸው። በምክክሩ ወቅት 4ሺዎች ጉባዔተኞች በስምንት ቡድን ተከፋፍለው ይመክራሉ ሲሉ የተናገሩት ምክትል ኮሚሽነር ሂሩት ገብረስላሴ ናቸው። በእያንዳንዱ ቡድን 500 ጉባኤተኞች ይካተታሉ ተብሏል፡፡ ምክትል ኮሚሽነር ሂሩት ገብረ ስላሴ ይህን የተናገሩት ሐምሌ 8 ቀን 2018 በሚጀመረው ዋናው የምክክር ጉባኤ ወቅት ሙያዊ ማብራሪያ ከሚያቀርቡ ( Panel of experts) ጋር በስካይ ላይት ሆቴል ውይይት ሲደረግ ነው:: በምክክር ወቅት ሞያዊ ማብራሪያ የሚቀርበው ቡድን ከተለያዩ የትምህርት ተቋማት እና የሞያ ዘር
Jul 22 min read


በኢትዮጵያ በተለያዩ የትምህርት ተቋማት እንደሚደረጉ ጥናትና ምርምሮች
ሰኔ 23 2018 በኢትዮጵያ በየዓመቱ ከ14,000 በላይ ጥናቶች እና ምርምሮች በተለያዩ የትምህርት ተቋማት እንደሚደረጉ ይነገራል። ከእነዚህ ጥናቶችና ምርምሮች ስራ ላይ ውለው የህብረተሰቡን ችግር ለመፍታት እያገዙ ያሉት ግን ጥቂቶቹ ናቸው ተብሏል። ጥናቶቹ የህብረተሰቡን ችግር መነሻ አድርገው አለመካሄዳቸው እና በጋራ መድረክ አለመገምገማቸው የችግሩ መነሻ እንደሆነ ተጠቅሷል። በተለያዩ የሙያ ዘርፎች የሚገጥሙ ችግሮችን ለመፍታት በተማሪዎች እና በምሁራን እንዲሁም በተመራማሪዎች የሚደረጉ ጥናትና ምርምሮች በአንድ መድረክ ቀርበው ውይይት ቢደረግባቸው መፍትሄ ያመጣሉ ተብሏል። ይህ የተባለው ቅድስት ማርያም ዩኒቨርሲቲ ባካሄደው 18ተኛው የዘርፈ ብዙ ጥናት እና ምርምር ጉባኤ ላይ ነው። በጉባኤው በተለያዩ ዘርፎች ማለትም በቢዝነስ እና ኢንድስትሪ በፋይናስ በግብ
Jul 11 min read


በኢትዮጵያ የጭነት ማስተላለፍ ስራ ለውጭ ባለሃብቶች ሙሉ በሙሉ ክፍት እንዲሆን ተወስኗል።
ሰኔ 24/2018 በኢትዮጵያ የጭነት ማስተላለፍ ስራ ለውጭ ባለሃብቶች ሙሉ በሙሉ ክፍት እንዲሆን ተወስኗል። ከዚህ ቀደም የውጭ ኩባንያዎች ከ49 በመቶ ያልበለጠ ድርሻ ይዘው ከአገር ውስጥ ባለሃብቶች ጋር በጥምረት እንዲሰሩ ነበር የሚፈቀድላቸው። ገደቡ የሎጂስቲከስ ዘርፉ የሚፈለገው ያህል የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገባ እንቅፋት ሆኖ መቆየቱን ፤ውሳኔውን ይፋ ያደረገው የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ቦርድ አመልክቷል። ዝርዝር የህግ ማዕቀፎችን የማጠናቀቅ ስራ በሚመለከታቸው የመንግስት ተቋማት በኩል እየተከወነ እንደሚገኝም ጠቅሷል። የኢትዮጵያ የሎጅስቲክስ አገልግሎት አሰጣጥ ዝቅተኛ እንደሆነ በየጊዜው የሚወጡ የአለም ባነክ ሪፖርቶች ያሳያሉ የሚሉት ፤ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሎጂስቲክስ እና የንግድ ሠንሠለት ማኔጅመንት ክፍል መምህር ፕሮ
Jul 12 min read


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሚያስተዳድራቸው መ/ቤቶች የተገኘባቸውን የኦዲት ከፍተቶች በ10 የስራ ቀናት ውስጥ የማስተካከያ እርምጃ እንዲወስዱ የሚያስገድድ መመሪያ ወጣ፡፡
ሰኔ 24/2018 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሚያስተዳድራቸው መስሪያ ቤቶች የተገኘባቸውን የኦዲት ከፍተቶች በ10 የስራ ቀናት ውስጥ የማስተካከያ እርምጃ እንዲወስዱ የሚያስገድድ መመሪያ ወጣ፡፡ የኦዲት መረጃዎችን ማየት የፈለገ ማንኛውም አካል ደግሞ የኦዲት አድራጊ መስሪያ ቤቶችን ኃላፊዎች ፍቃድ ማግኘት ግዴታ አለበት ይላል መመሪያው፡፡ የመንግስት ንብረት ኦዲት መመሪያ ቁጥር190/2018 ኦዲት ተደራጊ መስሪያ ቤት ሥራ አመራርና የህንፃና ንብረት ሰራተኞች ኃላፊነታቸውን በብቃት መወጣታቸውን ለመረዳት ያስችላል ተብሏል፡፡ በተጨማሪም ንብረቶች ለታለመላቸው ዓላማ መዋላቸውን እና በስራ ላይ ባለ የህንፃና ንብረት አስተዳደር ሕጎች መሠረት ሥራዎች መከናወናቸውን ማረጋገጥ እና በኦዲት ግኝቱ መሠረት ኦዲት ተደራጊ መሥሪያ ቤቶች የእርምት እርምጃ መውሰዳቸውን መ
Jul 12 min read


በኢትዮጵያ ሰዎች የጤና እክል ሲገጥማቸው የተሻለ ህክምናም ሲያስፈልጋቸው ምን ማድረጋቸው ይጠበቅባቸዋል ?
የሰኔ 24/2018 ሰው ጤናው ሲጓደል ለፈውስም መፍትሄ ሲፈልግ መካሪው ብዙ ሆኖ ይታያል፡፡ ሰዎች አንዳች የጤና ክልል ሲገጥማቸው፣ ምን ማድረግ እንዳለባቸው ሐሳብ ሲገባቸው የሚያግዛቸውን ፣ የተሻለ ህክምና አገልግሎትም ሲያሻቸው የሚጠቁማቸውንና የሚያማክራቸውን የጤና ማማከር አገልግሎትን ምርጫቸው ማድረግ በተለይ በውጩው አለም የተለመደ ነው ይባላል። ለመሆኑ በኢትዮጵያ ሰዎች የጤና እክል ሲገጥማቸው የተሻለ ህክምናም ሲያስፈልጋቸው ምን ማድረጋቸው ይጠበቅባቸዋል ? የጌትዌል ሜዲካል ትራቭል መስራች እና ስራ አስኪያጅ የሆኑትን ዶ/ር በጋሻው ባይለየኝን ጠይቀናል። ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ….. ፍቅሩ አምባቸው የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… Website፡ https://www.shegerfm.com/ YouTube : https://shorturl.at
Jul 11 min read


ለሴቶችና ወጣቶች የስራ እድል ለመፍጠር ኑሯቸውን ለማሻሻል ሲተገበር የቆየው የሊዌ ፕሮጀክት የስራ ፈጣሪዎችን አቅም አሻሽሎታል ተባለ፡፡
የሰኔ 24/2018 ለሴቶችና ወጣቶች የስራ እድል ለመፍጠር ኑሯቸውን ለማሻሻል በኔዘርላንድስ የልማት ድርጅት ድጋፍ ሲተገበር የቆየው የሊዌ ፕሮጀክት የስራ ፈጣሪዎችን አቅም አሻሽሎታል ተባለ፡፡ የኔዘርላንድስ የልማት ድርጅት (SNV) ከመርሲ ኮርፕስ (Mercy Corps) ጋር በመተባበር በአዲስ አበባ ከተማ ሲተገብር የቆየው የሴቶች እና ወጣቶች የኑሮ ማሻሻያ (LIWAY) ፕሮግራም ተመዝግበዋል የተባሉ ለውጦችን የታዩበት ዝግጅት በትናንትናው እለት ተካሂዷል፡፡ ፕሮጀክቱ ለስራ ፈጣሪዎች ማስያዣ ሳይጠየቁ ከባነኮች ብድር የሚያገኙበትን ሁኔታ ፈጥሯል አንዲሁም መቀጠር ለሚፍሉጉ ድግሞ የቅም ግንባታ ስልጠና እንዲያገኙ ተድረጓል ሲሉ የፕሮጀክቱ ሃላፊ ሄለን ጌታቸው አስረድተዋል፡፡ በዚህም ላለፉት 4 ዓመታት 402,000 ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ወጣቶችና ሴቶችን የራሳቸው
Jul 11 min read
ፕሮግራሞች
bottom of page
_edited.jpg)
