top of page
በኢትዮጵያ እስካሁን በረቂቅ ደረጃ ያለውና የታሸጉና በፋብሪካ የተቀነባበሩ ምግቦችን የሚቆጣጠር ህግ
ሐምሌ 14/2018 በኢትዮጵያ እስካሁን በረቂቅ ደረጃ ያለውና የታሸጉና በፋብሪካ የተቀነባበሩ ምግቦችን የሚቆጣጠር ህግ ፈጥኖ ሥራ ላይ ካልዋለ ከዚህ ጋር በተያያዘ የሚደርሰው የጤና ጉዳት እየተባባሰ ለመከላከል የሚጠይቀው ወጪ ከፍተኛ መሆኑ አይቀርም ተባለ። አሁንም ኢትዮጵያ ተላላፊ ባልሆኑ ህመሞች ምክንያት ለሚመጡ የጤና ችግሮች በየአመቱ 31 ቢሊየን ብር ታወጣለች ተብሏል። የስኳር፣ የጨውና የቅባት መጠናቸው ከፍተኛ እንዲሁም በፋብሪካ የተቀነባበሩ የታሸጉ ምግቦችን ለመቆጣጠር የተዘጋጀው ረቂቅ ህግ በፍጥነት ሥራ ላይ ካልዋለ በህብረተሰቡ ጤና ላይ የሚደርሰው ጉዳት እየጨመረ እንደሚሄድ ባለሙያዎች አስጠንቅቀዋል። በዚሁ ጉዳይ ላይ ዛሬ ማቴዎስ ወንዱ ፋውንዴሽን ከመንግሥት ተቋማት፣ ከጤና ባለሙያዎች፣ ከሲቪል ማኅበራት፣ ከሸማቾች ተወካዮች እና ሌሎች ከሚመለከታ
Jul 212 min read


የተጀመረው የኢኮኖሚ ማሻሻያ አንዱ ግብ የግሉ ዘርፍ የሚመራው ኢኮኖሚን እውን ማድረግ ነው፡፡
ሐምሌ 13/2018 የተጀመረው የኢኮኖሚ ማሻሻያ አንዱ ግብ የግሉ ዘርፍ የሚመራው ኢኮኖሚን እውን ማድረግ ነው፡፡ የግሉ ዘርፍ እንዲበረታ ደግሞ የብድር አቅርቦት ይፈልጋል፡፡ የብሔራዊ ባንክ ጥብቅ የገንዘብ ፖሊሲውን በማስቀጠል ብድር ወለዱ ከፍ እንዲልና ውድ እንዲሆን የሚያደርጉ የፖሊሲ ለውጦችን እያደረገ ነው፡፡ ይህ ደግሞ በተለይ የግሉ ዘርፍ ብድር እንዳያገኝ በማድረግ ያዳክመዋል፡፡ ኢንቨስትመንት እንዲቀንስም ያደርጋል፡፡ የኢንቨስትመንት መዳከም ደግሞ የስራ አጥነትም እየሰፋ እንዲሄድ ያደርጋል፡፡ በጉዳዩ ላይ የፋይናንስ ባለሙያ ጠይቀናል፡፡ ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ… ትዕግስት ዘሪሁን የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… Website፡ https://www.shegerfm.com/ YouTube : https://shorturl.at/18TS1 Teleg
Jul 201 min read


የሂሳብና ኦዲት ባለሙያዎች ፍቃድ አሰጣጥን ለውጭ ሃገራት ባለሙያዎች ክፍት እንዲያደረግ ከአለም ዓቀፍ ተቋማት ጥያቄ እየቀረበለት መሆኑን የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ ተናገረ፡፡
ሐምሌ 13/2018 የሂሳብና ኦዲት ባለሙያዎች ፍቃድ አሰጣጥን ለውጭ ሃገራት ባለሙያዎች ክፍት እንዲያደረግ ከአለም ዓቀፍ ተቋማት ጥያቄ እየቀረበለት መሆኑን የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ ተናገረ፡፡ ቦርዱ በሃገር ቤት ያሉ ባለሙያዎችን ብቁ ሳናደርግ ዘርፉን ለውጭ ሃገራት ቢከፈት የውጭ ባለሙያዎች ማራገፊያ መሆንን ያመጣል፤ የአካውንቲንግ ዘርፍን ያቀጭጫል፤ ሃገር ከዘርፉ የምታገኘው ገቢ ተመልሶ ከሃገር እንዲወጣ ምክንያት ይሆናል ሲልም ይሞግታል፡፡ የኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ በሃገር ቤት ላሉ የሂሳብና ኦዲት ባለሙያዎች የሙያ ፍቃድ ይሰጣል፤በተሰጣቸው ፍቃድ መሰረት ህጉን ተከትለው እየሰሩ መሆኑን እየተቆጣጠረ እርምጃ የሚወስድ መንግስታዊ ተቋም ነው፡፡ በኢትዮጵያ የሂሳብ ስራ በዘፈቀደ ነው የሚሰራው የሚለው ቦርዱ የኢኮኖሚው ዘርፍ በብዙ መንገድ ለ
Jul 202 min read


ተመካካሪዎች በተመደቡላቸው አጀንዳዎች ላይ መመካከር መጀመራቸውን የምክክር ኮሚሽን ተናገረ፡፡
ሐምሌ 13/2018 ተመካካሪዎች በ80 ንዑስ ቡድኖች በመከፈል በተመደቡላቸው አጀንዳዎች ላይ መመካከር መጀመራቸውን የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ተናገረ፡፡ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን እየተካሄደ ባለው የምክክር ጉባኤ የዛሬውን የምክክር ሂደት አስመልክቶ መግለጫ በሰጠው መግለጫው፤ በንዑሳን ቡድኖች የተከፈሉት ተመካካሪዎች በተመደቡበት አጀንዳ ላይ መመካከር መጀመራቸውን ተናግሯል፡፡ የዛሬውን መግለጫ የሰጡት የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አምባሳደር ሙሃሙድ ድሪር በእያንዳንዱ ንዑስ ቡድን ውስጥ 50 ተመካካሪዎች ያሉ ሲሆን በአጠቃላይ 80 አነስተኛ ቡድኖች እየተመካከሩ ይገኛሉ ብለዋል፡፡ በአንድ አጀንዳ ላይ እንዲመካከር የተመደበ ዐብይ የስራ ቡድን 500 ተመካካሪዎችን ሲይዝ በስሩ እያንዳንዳቸው 50 ተመካካሪዎችን የያዙ 10 ንኡሳን ቡድኖችን እንዲይዝ ተደርጎ መዋቀሩ
Jul 201 min read
ከምስራቅ ወለጋ ጉቡ ሰዮ ተፈናቅለው በደብረ ብርሃን መጠለያ የነበሩ ዜጎች
ሐምሌ 13/2018 ከምስራቅ ወለጋ ጉቡ ሰዮ ተፈናቅለው በደብረ ብርሃን መጠለያ የነበሩ ዜጎች ወደ ቀዬአቸው ቢመለሱም እርሻና የመኖሪያ ቤታቸው ሊመለስላቸው እንዳልቻለ ለሸገር ተናግረዋል፡፡ በዚህ ምክንያት ወደ ደብረ ብርሃን መጠለያ ተመልሰናል ብለዋል። የአካባቢው የአደጋ ስጋት ቢሮ የተፈናቃዮቹን መሬት መልሻለው ስለቅሬታው ምንም አላውቅም ብሏል፡፡ ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ…. ማርታ በቀለ የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… Website፡ https://www.shegerfm.com/ YouTube : https://shorturl.at/18TS1 Telegram : https://shorturl.at/68aeK Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4 WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx X :- https://x.com/sh
Jul 201 min read


በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ሀይማኖቶች ወሳኝ መሆናቸውን ሀገራዊ ምክከር ኮሚሽን ተነገረ።
ሐምሌ 11/2018 በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ሀይማኖቶች ወሳኝ መሆናቸውን ሀገራዊ ምክከር ኮሚሽን ተነገረ። በስራ ላይ ካሉት ኮሚሽነሮች አንዱ እና ከስምንቱ አጀንዳዎች ውስጥ ሀይማኖትን የሚመለከተው ቡድን መሪ ኮሚሽነር የሆኑት መላኩ ወልደማርያም ትናንት ሃምሌ 10 ቀን 2018 ዓ.ም የምክከር ጉባዔ አስመልክተው ለጋዜጠኞች በሰጡት ማብራሪያ ኮሚሽኑ 4,000 ተሳታፊዎችን በ8 ቡድን ማዋቀሩን ተናግረዋል። ኮሚሽኑ የምክክር ጉባዔው ሃምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨማሮ የአፍሪካ ህብረት ተወካዮች በተገኙበት በይፋ መጀመሩን ቢያበስርም "ቴክኒካል"ባላቸው ችግሮች ምክንያት እስከ ሃምሌ 10 ቀን ጉባዔ ማካሄድ እንዳልቻለ ኮሚሽነሩ አስረድተዋል። ትናንት ሃምሌ 10 ቀን 2018 ዓ.ም ግን 4,000ውን ጉባዔተኛ በ8 ቡድን በአምስት አምስት መቶ አድ
Jul 182 min read


ባለፉት 5 ዓመታት በም/ቤት አባልነት የቆዩት እንደራሴዎችአሳካነው የሚሉት ድል ምንድን ነው?
ሐምሌ 10/2018 ሰባተኛውን ሀገራዊ ምርጫ ተከትሎ ኢትዮጵያን ለመጪዎቹ 5 ዓመታት የሚመራው መንግስት በመስከረም ወር ይሰየማል። በስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫ ያሸነፈው የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤትም ለሰባተኛው ተመራጭ ቦታውን ያስረክባል። ለመሆኑ የስድስተኛው የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የስራ ዘመን እንዴት ያለ ነበር? በፓርላማው የነበሩና በሰባተኛው ምርጫው ዳግም ያሸነፉ የህዝብ እንደራሴዎችን አነጋግረናቸዋል፡፡ ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ…. ያሬድ እንዳሻው የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… Website፡ https://www.shegerfm.com/ YouTube : https://shorturl.at/18TS1 Telegram : https://shorturl.at/68aeK Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4 WhatsApp :
Jul 171 min read


ኢትዮጵያ የትንባሆ ኢንዱስትሪዎች የሚያደርሱትን ተፅዕኖ በመቋቋም ከዓለም 6ኛ መሆኗን ሪፖርት አሳየ፡፡
ሐምሌ 10/2018 ኢትዮጵያ የትንባሆ ኢንዱስትሪዎች የሚያደርሱትን ተፅዕኖ በመቋቋም ከዓለም 6ኛ ከአፍሪካ 2ኛ መሆኗን አለም አቀፉ የትንባሆ ተፅዕኖ ተጋላጭነት ሪፖርት አሳየ፡፡ ለዚህም ምክንያቱ ጠንካራ የትንባሆ ቁጥጥር ህግ ያላት መሆኑና ኢንዱስትሪዎቹ ጫና እንዳያደርጉ መቆጣጠር በመቻሏ ነውም ተብሏል፡፡ ኢትዮጵያ በ2011ዓ.ም ባወጣችው የምግብና መድሃኒት አስተዳደር አዋጅ የትንባሆ ኢንዱስትሪን ጣልቃ ገብነት ስለመቆጣጠር በሰፈረው ድንጋጌ የትንባሆ ኢንዱስትሪዎች ከመንግስት አካላት ጋር ምንም አይነት የጥቅም ትስስር እንዳይኖራቸው ይከለክላል፡፡ እነዚህ ኢንዱስትሪዎች ለመንግስት አካላት በስጦታ ገንዘብ እንዳይሰጡ፤ የበጎ አድራጎት ስራ ላይ እንዳሰማሩ አዋጁ ይከለክላል፡፡ ይህም የሆነበት ምክንያት በድጋፍ ስም የትንባሆ ምርት እንዳያስተዋውቁ፤ ስማቸውን እ
Jul 172 min read


ተከለከሉ የተባሉት የፕላስቲክ ምርቶች አምርቶ የሚሸጠው ማን ነው?
ሐምሌ 10/2018 የፕላስቲክ ከረጢት በጤና እና አካባቢ ላይ የሚያደርሰውን ተፅእኖ ለመቀነስ በሚል የወጣው የደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ አዋጅ ተግባራዊ መሆን ከጀመረ 5 ወር አልፎታል። አሁንም ግን የት እንደተመረቱ የማይታወቅ የተከለከሉ ፕላስቲኮች በገበያው ሲሸጡ ይታያል። እነዚህን ፕላስቲኮች አምርቶ የሚሸጠው ማነው? ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ…. ፍቅሩ አምባቸው የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… Website፡ https://www.shegerfm.com/ YouTube : https://shorturl.at/18TS1 Telegram : https://shorturl.at/68aeK Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4 WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx X :- https://x.com/shegerfm?s=2 LinkedIn
Jul 171 min read


ከ3,800 በላይ ሰዎችን በሕገ-ወጥ መንገድ አዘዋውረዋል የተባሉት እነ ይትባረክ ዳዊት ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጣቸው፡፡
ሐምሌ 10/2018 ከ3,800 በላይ ሰዎችን በሕገ-ወጥ መንገድ አዘዋውረዋል የተባሉት እነ ይትባረክ ዳዊት ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጣቸው፡፡ ከ3,800 በላይ ሰዎችን በሕገ-ወጥ መንገድ በማደራጀትና በማዘዋወር፣ ለ133 ሰዎች ሞት እንዲሁም ለ116 ሴቶች መደፈር ምክንያት ሆነዋል በሚል ክስ የተመሠረተባቸው እነ ይትባረክ ዳዊት ላይ ፍርድ ቤት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። በአጠቃላይ 16 ክሶች የቀረቡባቸው 11 ተከሳሾች ሲሆኑ፤ ከእነዚህ መካከል ስድስቱ በቁጥጥር ስር ውለው የዋስትና መብታቸው በመታገዱ በማረሚያ ቤት ሆነው ጉዳያቸውን እየተከታተሉ ይገኛሉ። ቀሪዎቹ 5 ተከሳሾች ግን በሌሉበት ክስ ተመስርቶባቸው ጉዳያቸው በችሎቱ እየታየ ነው። በዐቃቤ ሕግ ከቀረቡት 16 ክሶች መካከል ከኢትዮጵያ፣ ሶማሊያ እና ኤርትራ እስከ ሱዳንና ሊቢያ የሚዘልቅ ዓለም አቀፍ የወንጀል ቡድን
Jul 171 min read


የፍሊንስቶን ሆምስ ሪልስቴት እና ደንበኞቹን ሲያከራክር የቆየው ጉዳይ የመጨረሻ ውሳኔ አግኝቷል፡፡
ሐምሌ 9/2018 የፍሊንስቶን ሆምስ ሪልስቴት እና ደንበኞቹን በፍርድ ቤት ለዓመታት ሲያከራክር የቆየው ጉዳይ ትናንት የመጨረሻ ውሳኔ አግኝቷል፡፡ ተቋሙ በሁለት አመት ከመንፈቅ አስረክባችኋለሁ ያለውን ቤት በጊዜው ለደንበኞቹ ባለማስረከቡ ካሳ እንዲከፍል የፌደራል ከፍተኛው ፍርደ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ትናንት በዋለው ችሎት መዎሰኑ ተሰምቷል፡፡ ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ…. ገዛ ጌታሁን የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… Website፡ https://www.shegerfm.com/ YouTube : https://shorturl.at/18TS1 Telegram : https://shorturl.at/68aeK Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4 WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx X :- https://x.com/shege
Jul 161 min read


በእጅጉ ለመጥፋት የተጋለጠ በሚል ደረጃ የተመደበው ዋልያ
ሐምሌ 9/2018 ዓለም አቀፉ የተፈጥሮ ጥበቃ ህብረት ከኢትዮጵያ ብርቅዬ እንስሳት መካከል ዋልያን በእጅጉ ለመጥፋት የተጋለጠ በሚል ደረጃ መመደቡ አፋጣኝ የጥበቃ እርምጃ እንደሚያስፈልገው የሚያሳይ ነው ተባለ፡ በሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ የዋልያዎች ብዛት ከዓመታት በፊት ከነበረው በግማሽ ቀንሶ 300 ያህል እንደሆነ የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን ተናግሯል፡፡ ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ…. ንጋቱ ረጋሳ
Jul 161 min read


የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች በተልዕኮ ተለይተው በተወሰኑ የትምህርት መስኮች ላይ ትኩረት አድርገው እንዲያሰተምሩ መደረጉ
ሐምሌ 9/2018 የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች በተልዕኮ ተለይተው በተወሰኑ የትምህርት መስኮች ላይ ትኩረት አድርገው እንዲያሰተምሩ መደረጉ ለውጥ ማምጣቱን ጥናት አሳይቷል፡፡ በኢትዮጵያ የትምህርት ጥራት መጓደልን ለማስተካከል በዘርፉ የተለያዩ የለውጥ ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነ ይነገራል፡፡ በተለይም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በተልዕኮ እና በትኩረት ተለይተው እንዲሰሩ ማድረግ ለትምህርት ጥራትና ለሀገር ኢኮኖሚ ወሳኝ ነው ተብሎ ታምኖበት ወደ ስራ መገባቱ ይታወሳል፡፡ በዚህ መሰረት ሶስት ዋና ዋና ተልዕኮ ተለይቶ መተግበራቸው የሚታወስ ሲሆን የምርምር ዩኒቨርሲቲዎች አፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርስቲዎች እንዲሁም አጠቃላይ ዩኒቨርስቲዎች በሚል መለየታቸው ተነግሯል፡፡ እነዚህ ተልዕኮዎች አሁን ላይ ለውጥ እያመጡ ነው ሲሉ በጉዳዩ ላይ ጥናት ያደረጉት በአንቦ ዩኒቨርሲቲ
Jul 161 min read


አንድሮሜዳ የግል ት/ቤት የትምህርት ክፍያ በእጥፍ መጨመሩ ጥያቄ አስነስቶበታል፡፡
ሐምሌ 9/2018 በአዲስ አበባ አንድሮሜዳ የተባለው የግል ትምህርት ቤት በእጥፍ የትምህርት ቤት ክፍያ መጨመሩ የህጋዊነት ጥያቄ አስነስቶበታል፡፡ የከተማ አስተዳደሩ አምና ባወጣው ደንብ መሰረት የግል ትምህርት ቤቶች ከ65 በመቶ በላይ ጭማሪ ማድረግ እነደማይችሉ ጭማሪዉም ለሶስት አመት እንዲያገለግል መደንገጉ ይታወሳል፡፡ የተጠቀሰው ትምህርት ቤት ግን አምና ካደረገው ጭማሪ ባለፍ ዘንድሮም 100 በመቶ ጭማሪ ማድረጉን ወላጆች ተናግረዋል፡፡ የወላጆችን ቅሬታ ተቀብለን ትምህርት ቤቱንም ጠይቀናል፡፡ ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ…. ገዛ ጌታሁን
Jul 161 min read


በኤአይ የሚሰሩ የፈጠራ ውጤቶች በኢትዮጵያ የህግ ከለላና ጥበቃ ያገኛሉ ወይ?
ሐምሌ 8/2018 የሰው ልጅ በተፈጥሮ ያለውን እምቅ የፈጠራ አቅም ተጠቅሞ የሚሰራቸው ልዩ ልዩ ውጤቶች አዕምሯዊ ንብረቶቹ ሆነው በህግ እንዲጠበቁለት ይደረጋል፡፡ ይህ የህግ ጥበቃ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ( #AI ) የሚሰሩ የፈጠራ ውጤቶችን ይመለከታል ወይ? በሰው ሰራሽ አስተውሎት የሚሰሩ የስራ ፈጠራዎች እንዳሉ ሁሉ የሌላን ሰው ስራ በ AI በመታገዝ እንደራሳቸው የፈጠራ ስራ የሚያቀርቡ እንዳሉ ሰምተናል፡፡ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ወይም የሚሰሩ የፈጠራ ውጤቶች በኢትዮጵያ የህግ ከለላና ጥበቃ ያገኛሉ ወይ? ስንል ጠይቀናል፡፡ በመደወላብ ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት ቤት ውስጥ ረዳት ፕ/ሮ የሆኑት ዓለሙ ባልቻ በጉዳዩ ላይ ጥናት አድርገዋል፡፡ ሆኖም ኢትዮጵያ በሰው ሰራሽ አስተውሎት የሚሰሩ የፈጠራ ውጤቶችን ከለላና ጥበቃ ምታደርግበት የህግ ማዕቀፍ የላትም ብ
Jul 161 min read


የኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሪ የመጠባበቂያ ክምችት ከወራት በኋላ ወደ ስድስት ቢሊዮን ዶላር እንደሚጠጋ አለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት IMF ተናገረ፡፡
ሐምሌ 8/2018 የኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሪ የመጠባበቂያ ክምችት ከወራት በኋላ ወደ ስድስት ቢሊዮን ዶላር እንደሚጠጋ አለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት IMF ተናገረ፡፡ ይህም ከሁለት ወራት በላይ የውጭ ሸመታዋን ለመከወን የሚያስችል ነው ብሏል፡፡ ኢትዮ ከተቋሙ ጋር የጀመረችው የኢኮኖሚ ማሻሻያ ሲጠናቀቅ ለሶስት ወር ተኩል ሸመታ የሚበቃ መጠባበቂያ ክምችት እንዲኖራት ይጠበቃል ብሏል፡፡ ይሁንና ይህ ግብ እንዳይሳካ እንቅፋት ሊሆኑ የሚችሉ ስጋቶች መኖራቸውንም IMF በስጋትነት አንስቷል፡፡ ተቋሙ የኢኮኖሚ ሪፎርሙ ከተጀመረ ወዲህ አምስተኛው ዙር ግምገማ አካሂዶ ሙሉ ሪፖርቱን ይፋ አድርጓል፡፡ 132 ገፅ በያዘው ሪፖርቱ አጠቃላይ ስለ ኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እድገት ሁኔታና ስለተረጋገጡበት ስጋቶች በስፋት ተንትኗል፡፡ እስካሁን ጠንካራ የማክሮ ኢኮኖሚ አፈፃፀም መኖሩንና
Jul 153 min read


ኤም.ኤስ.አይ ከጤና ሚኒስቴር ጋር በትብብር የሚተገብረው የቤተሰብ ዕቅድና ሥነ-ተዋልዶ ጤና ፕሮጀክት ባለፈው 1 ዓመት ለ750,000 በላይ ሰዎች አገልግሎት መስጠቱ ተነገረ።
ሐምሌ 8/2018 ኤም.ኤስ.አይ (MSI) ከጤና ሚኒስቴር ጋር በትብብር የሚተገብረው የቤተሰብ ዕቅድና ሥነ-ተዋልዶ ጤና ፕሮጀክት ባለፈው 1 ዓመት ለ750,000 በላይ ሰዎች አገልግሎት መስጠቱ ተነገረ። በጌትስ ፋውንዴሽን አንድ ቢሊዮን ብር የገንዘብ ድጋፍ ከአመት በፊት የተጀመረው የስነ-ተዋልዶ ጤና እና ቤተሰብ ዕቅድ ፕሮጀክት በአራት ክልሎች (በኦሮሚያ፣ በአማራ፣ በሲዳማ እና በትግራይ ክልሎች) እየተተገበረ ይገኛል። ፕሮጀክቱ በተለይም በጦርነቱ ምክንያት ከአካባቢያቸው ለተፈናቀሉና የጤና ተቋማት አገልግሎት መስጠት ባልቻሉባቸው አካባቢዎች ለሚገኙ ሰዎች የስነ ተዋልዶና የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት ለመስጠት ያለመ መሆኑ ተጠቅሷል። እስካሁን ከ750 ሺህ በላይ ሰዎች የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት ተጠቃሚ አድርጓል፣ አጠቃላይ የቆይታው ጊዜም አራት አመት ነው ተብሏ
Jul 151 min read


የዳግማዊ ሚኒሊክ ሪፈራል ሆስፒታል የዲኢንኤ፣ የሥነ-ምረዛ እና የጥቃት ምርመራዎችን ለመጀመር ዝግጅት እያደረገ እንደሆነ ተናገረ፡፡
ሐምሌ 8/2018 የዳግማዊ ሚኒሊክ ሪፈራል ሆስፒታል ከዚህ ቀደም ሲሰጣቸው ከነበሩ እንደ አስከሬን፣ የእድሜ እና የጉዳት ምርመራዎች በተጨማሪ፣ ሌሎች አዳዲስ አገልግሎቶችን በቅርቡ ለመጀመር ዝግጅት እያደረገ መሆኑ ተነገረ። በፎረንሲክ ሕክምናና ሥነ-ምረዛ ክፍል ይሰጣሉ የተባሉት አገልግሎቶች የዲ.ኤን.ኤ (DNA)፣ የሥነ-ምረዛ እና የጥቃት ምርመራዎች መሆናቸው ታውቋል። አገልግሎቱን ለመጀመር አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችና መሣሪያዎች የተሟሉ ሲሆን፣ ባለሙያዎችም ሥልጠና እየወሰዱ እንደሚገኙ የፎረንሲክ ሕክምናና ሥነ-ምረዛ ክፍል ኃላፊ ዶክተር ወይንሸት ዘውዴ ነግረዉናል። ይሁን እንጂ ኃላፊዋ አገልግሎቱ በይፋ የሚጀመርበትን ትክክለኛ ጊዜ ከመናገር ተቆጥበዋል። በቅርቡ ሥራ ከሚጀምሩት አገልግሎቶች መካከል አንዱ የአባትና የልጅ ዘረ-መል (DNA) የመለየት ሥራ ነው።
Jul 151 min read


ከተሽከርካሪ መድን ሽፋን ባሻገር ያሉ የመድን ሽፋን አገልግሎቶች ለምን ትኩረት ተነፈጋቸው?
ሐምሌ 8/2018 በኢትዮጵያ የመድን አገልግሎት መሰጠት ከጀመረ አንድ ክፍለ ዘመን ተሻግሯል። በተለይ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በዘርፉ የሚቀላቀለው ባለ መዋለነዋይ እየጨመረ መምጣት የመድን አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን ቁጥር ወደ 19 እንዳደረሰውም መረጃዎች ያሳያሉ። ሰዎች በተለይ የጤና፣ የህይወት፣ የቁስ እና የረዥም ጊዜ የአካል ጉዳት የመድን አገልግሎትን እንዲጠቀሙ የዘርፉ ባለሙያዎች ይመክራሉ። ይሁን እንጂ በኢትዮጵያ በብዛት የተለመደው የሞተር ወይም የተሽከርካሪ ኢንሹራንስ ነው። አገልግሎቱን የሚሰጡ ተቋማት የግብርና ኢንሹራንስን ጨምሮ ሌሎችንም የመድን ሽፋኖች ቢሰጡም ግን ሌሎች አገልግሎቶች ላይ ክፍተት እንዳለባቸው ይነገራል። ለመሆኑ ለተሽከርካሪ መድን ሽፋን አገልግሎት የተሰጠውን ትኩረት ያህል ሌሎቹ የመድን ሽፋን አገልግሎቶች ለምን ትኩረት ተነፈጋቸው?
Jul 151 min read


''የሰሜን የኢትዮጵያ አካባቢዎች ላይ በክረምቱ የሚኖረው ዝናብ አነስተኛ ነው'' የሜትሮሎጂ ኢንስቲትዩት
ሐምሌ 8/2018 የሰሜንና የሰሜን የኢትዮጵያ አካባቢዎች ላይ በክረምቱ የሚኖረው ዝናብ አነስተኛ ነው ሲል የኢትዮጵያ ሜትሮሎጂ ኢንስቲትዩት ተናገረ፡፡ በዚህም ምክንያት የሚኖረው የዝናብ መጠን አነስተኛ ነው ህብረተሰቡም በቂ ዝግጅት እንዲያደርግ ኢንስቲትዩቱ ተናግሯል፡፡ የክረምት ዝናብ አሁን ላይ ባላገኙ አንዳንድ አካባቢዎች በሚቀጥሉት ቀናት የተሻለ ዝናብ እንደሚያገኙ ጠቅሷል፡፡ የዝናብ እጥረት በሚታይባቸው አካባቢዎችም በመጪዎቹ ቀናት የተሻለ የዝናብ መጠን ሊያገኙ እንደሚችልም ኢንስቲትዩቱ ትንበያውን ነግሮናል፡፡ በመጪዎቹ 10 ቀናት በአብዛኛው የዝናብ ተጠቃሚ አካባቢዎች የሚኖረው የዝናብ መጠን ከቀላል እስከ መካከለኛ ነው ተብሏል፡፡ በመካከለኛው የአማራ አካባቢዎች ፣ የምዕራብ ሻዋ ፣ ምዕራብ ኦሮሚያ እና ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል አካባቢዎች ከባድ መጠን ያ
Jul 151 min read


የአገራዊ ምክክር ጉባኤ ላይ ጋዜጠኞች ኮሚሽነሮችን ፣ተሳታፊዎችን እና ባለሙያዎች ቃለ መጠየቅ መስራት የሚችሉት የወኪሎቻቸውን ፍቃድ ሲያገኙ መሆኑን የሚደነግግ መመሪያ ኮሚሽኑ ይፋ አደረገ።
ሐምሌ 7/2018 የአገራዊ ምክክር ጉባኤ ላይ ጋዜጠኞች ኮሚሽነሮችን ፣ተሳታፊዎችን እና ባለሙያዎች ቃለ መጠየቅ መስራት የሚችሉት የወኪሎቻቸውን ፍቃድ ሲያገኙ መሆኑን የሚደነግግ መመሪያ ኮሚሽኑ ይፋ አደረገ። የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከተለያዩ የህብረተሰብ ከፍሎች የተወከሉ 4ሺ ጉባኤተኞች የሚመክሩበትን ምክክር መገናኛ ብዙሃን እንዴት መዘገብ አንዳለባቸው የዘገባ መመሪያ አውጥቷል ። መገናኛ ብዙሃኑ በመመሪያው የተደነገጉትን ህግጋት ከተላለፉ ኮሚሽኑ ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ጋር በተመባበር በህግ ተጠያቂ እንደሚደረግ ተደንግጓል ። ከሃምሌ አንድ ቀን ጀምሮ ስራ ላይ የዋለው መመሪያ በመገናኛ ብዙሃን በሚሰሩት ዘገባ በምክክር ጉባዔው ሁሉም ኢትዮጵያን ባለቤት መሆናቸውን የሚጠቁሙ መሆን እንዳለባቸው ዘርዝሯል፡፡ በተጨማሪም መገናኛ ብዙሃኑ ጉባኤው ሊያ
Jul 142 min read
ፕሮግራሞች
bottom of page
_edited.jpg)
