top of page

''በኢትዮጵያ አብዛኞቹ የሂሳብ ባለሙያዎች ሙያዊ ብቃት ያላቸው አይደሉም'' የኢትዮጵያ የተመሰከረላቸው የሂሳብ ባለሙያዎች ኢንስቲትዩት

  • 8 hours ago
  • 1 min read

ሐምሌ 6/2018


በኢትዮጵያ እየሰሩ ያሉ አብዛኞቹ የሂሳብ ባለሙያዎች ፕሮፌሽናል (ሙያዊ ብቃት ያላቸው)አይደሉም ተባለ።


ሙያዊ ብቃት ያላቸው የሂሳብ ባለሙያዎች ከ500 ያልበለጡ በመሆናቸው ትልልቅ ድርጅቶች ባለሙያዎችን ከውጭ አያስመጡ እንደሚያሰሩ የኢትዮጵያ የተመሰከረላቸው የሂሳብ ባለሙያዎች ኢንስቲትዩት ተናግሯል።


ሙያዊ ብቃት የግድ እየሆነ በመምጣቱ 700 የሂሳብ ባለሙያዎች የትም ሄደው መስራት የሚያስችላቸው አለም አቀፍ መስፈርቶችን ያሟላ ስልጠና እየወሰዱ ነውም ተብሏል።


ኢትዮጵያ ያሏት ከ500 ያልበለጡ ፕሮፌሽናል ባለሙያዎች ጎረቤት ሃገር ኬንያ ካላት 60ሺህ ጋር ንፅፅር ውስጥ የሚገባ አይደለም ያለው ኢንስቱትዩቱ፤ ኢኮኖሚው እየሰፋና በሙያው የተረጋገጠ ብቃት ያላቸውን የሂሳብ ባለሙያዎችን የሚፈልግበት ጊዜ ላይ ደርሰናል፤ እያሰለጠንን ሙያዊ ብቃት ያለው ባለሙያ ማውጣት ካልቻልን የኢትዮጵያን ገበያ የውጭ ባለሙያዎች መቆጣጠራቸው አይቀርም ያሉን የኢኒስቱትዩቱ ሊቀመንበር አቶ ፍቃዱ አጎናፍር ናቸው።

ይህንን ሙያዊ ችግር ለመቅረፍ ሲባል በመንግስት ሃሳብ አመንጪነትና ድጋፍ የዛሬ ዓመት በአዋጅ የተቋቋመው የኢትዮጵያ የተመሰከረላቸው የሂሳብ ባለሙያዎች ኢንስቲትዩት፤ ዋናው ተግባሩ የኢሳብ ባለሙያዎችን በማሰልጠን ሙያዊ ብቃት እንዲኖራቸው ማድረግ እንደሆኑ ከሊቀመንበሩ ሰምተናል።


በብቃት ማረጋገጫ ስልጠናው ተማሪዎችን ተቀብለው ለምዘናው ብቁ ከሚያደርጉለት 11 የትምህርትና ስልጠና ተቋማት ጋር በዛሬው እለት የውል ስምምነት አስሯል።


ከኢኒስቲትዩቱ ጋር ስምምነቱን የተፈራረሙት የአዲስ አበባና የጎንደር ዩንቨርሲቲን ጨምሮ 8 የመንግስት ዩንቨርሲቲዎችና ከግል ደግሞ ዩኒቲ ዩንቨርሲቲና ሌሎች 2 የስልጠና ተቋማት ናቸው ያሉን አቶ ፍቃዱ የስልጠናውን ይዘትም ዘርዝረዋል።


የኢሳብና ኦዲት ባለሙያዎች ከእውቀት በተጨማሪ ከፍተኛ የስነ ምግባር ችግር እንዳለባቸው ተደጋግሞ ይነሳል፤ ከአሰሪዎቻቸው ጋር ግብር እንዲቀንስላችሁ አደርጋለሁ በምላሹ ይህንን ያህል ክፈሉ፤ በሚል የሚደራደሩ አሉ፤ አሁን የሚሰጠው ሙያዊ ስልጠና እንዲህ ዓይነት ችግሮችን ለመፍታት ምን ያህል ይረዳል ላልናቸው አቶ ፍቃዱ ተከታዩን መልሰዋል።


ይህ በሁለት ደረጃ የሚሰጠው ሙያዊ ብቃትን ለማረጋገጥ የሚያግዘው ስልጠና በእነዚህ 11 ተቋማት እንደሚቀጥልና በቅርብ ዓመታት በ6 እና 7 ዓመታት ውስጥ የሙያ ብቃት ያላቸው ባለሙያዎችን ቁጥር 10 ሺህ የማድረስ ውጥን እንዳላቸው ከሊቀመንበሩ ከአቶ ፍቃዱ አጎራፍር ሰምተናል።


ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ…


ምንታምር ፀጋው

Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page