top of page

ዲጂታል ባንኪንግ ስራን ያቀለለ መሆኑ ቢነገርለትም በሌላ በኩል ለዲጂታል መጭበርበርም እያጋለጠ መሆኑ ይነገራል፡፡

  • 56 minutes ago
  • 1 min read

ሐምሌ 4/2018


ዲጂታል ባንኪንግ ስራን ያቀለለ መሆኑ ቢነገርለትም በሌላ በኩል ለዲጂታል መጭበርበርም እያጋለጠ መሆኑ ይነገራል፡፡


ከእነዚህም የማታለያ ስልቶች መካከል አንዱ ሃሰተኛ የድጅታል ደረሰኝ ሰርቶ ሻጮችን ማጭበርበር እየተበራከተ መጥቷል።


ስለ ጉዳዩ ያነጋገርናቸው ነጋዴዎች፣ አጭበርባሪዎች ከባንክ ሂሳባቸው ገንዘብ ተቀናሽ ሳያደርጉ ትክክለኛውን የሚመስል ሃሰተኛ ድጅታል ደረሰኝ እያሳዩአቸው ብዙ ገንዘብ እንደተጭበረበሩ ነግረውናል፡፡

አታላዮች ይህንን ሃሰተኛ ድጅታል ደረሰኝ ለመስራት ህገ ወጥ ሶፍትዌሮችን የሚጠቀሙ ሲሆን እነዚህ ሶፍትዌሮች የፈለጉትን የገንዘብ መጠን እና የደንበኛ ስም መፃፍ እንደሚያስችሏቸው ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡


በባንክ ተቋማት ውስጥ የቢዝነስ ዴቨሎፕመንት እና ስትራቴጂ ባለሙያ የሆኑት አቶ ሃብተማርያም አደረ ባንኮች አሁን በሚከተሉት የዲጅታል ክፍያ አሰራር እንዲህ ዓይነቱን ሀሰተኛ ዲጅታል ደረሰኝ መከላከል አይችሉም ብለውናል።


ታድያ መፍትሔው ምንድነው?


ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ….


ንጋት መኮንን


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…



YouTube : https://shorturl.at/18TS1






Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page