top of page

ኢትዮጵያ የሰው ሰራሽ አስተውሎትን ከመጠቀም ባለፈ በዘርፉ አለም አቀፍ የምርምር ስራንም እየሰራች ነው ተባለ፡፡

  • 3 hours ago
  • 1 min read

ሐምሌ 2/2018


ኢትዮጵያ የሰው ሰራሽ አስተውሎትን ከመጠቀም ባለፈ በዘርፉ አለም አቀፍ የምርምር ስራንም እየሰራች ነው ተባለ፡፡


በአለም አቀፍ ህትመቶች ላይ የቀረቡ ከ60 በላይ ጥናቶች እስካሁን መሰራታቸው ተነግሯል፡፡


ይህን የተናገረው የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ነው።


እነዚህ ጥናትና ምርምሮች በሳይንሱና በአካዳሚው አለም ከፍተኛ የምርምር እውቀና እና ማረጋገጫ አግኝተው በአለም አቀፍ ጆርናሎች እየታተሙ ነውም ተብሏል።

በሌላ በኩል የኢትዮጵያ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ስነ-ምግባራዊ የሰው ሰራሽ አስተውሎት መርህን የተከተለ እንደሆነም ኢንስቲትዩቱ ተናግሯል።


የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ዘውዴ በተቋማትም ሆነ በግለሰቦች ደረጃ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ የአጠቃቀም ባህል እያደገ መጥቷል ብለዋል።


በዘርፉ ላይ የክህሎት፣ የመሰረተ ልማት ግብአቶች በስፋት ማልማት እና መጠቀም ላይ የበለጠ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራበት ነውም ይላሉ።


የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ በተለይ የተቋማትን አገልግሎት አሰጣጥ እንዳሻሻለውም ይናገራሉ።


የግለሰቦችን የሰው ሰራሽ አስተውሎት አጠቃቀም ምን ይመስላል? የሚለውን ለማወቅ እራሱን የቻለ ጥናት እንደሚያስፈልገው ያነሱት አቶ ተስፋዬ ግለሰቦችም ሆኑ ተቋማት ሰው ሰራሽ አስተውሎትን ሲጠቀሙ ለበጎ አላማና ኃላፊነት በተሞላበት መሆን እንዳለበትም አሳስበዋል።


ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ……


ፍቅሩ አምባቸው

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page