top of page

‘’በ5 ዓመት ውስጥ በ1,000 የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ላይ እርምጃ እንዲወሰድ አድርጌአለሁ’’ ኢሰመኮ

  • Jul 9
  • 2 min read

ሐምሌ 2/2018

 

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ባለፉት 5 ዓመታት በ1,000 የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ላይ እርምጃ እንዲወሰድ ማድረጉን እና ከ17,000 በላይ ሰዎችን ከህግ ወጥ እስራት ማስለቀቁን ይፋ  አደረገ።

 

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ከ2019 እስከ 2023 ለአምስት ዓመታት የሚያገለግል ስትራቴጂክ እቅድ ዛሬ ሃምሌ 2 ቀን 2018 ዓ.ም በዋና መስሪያ ቤቱ ይፋ አድርጓል።

 

እቅዱን ለመተግበር 7.6 ቢሊዮን ብር ያስፈልጋል ተብሏል።

 

ኮሚሽኑ ይፋ ያደረገው ስትራቴጂክ እቅድ ከትናንት ሐምሌ 1 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ስራ ላይ መዋሉን ኮሚሽኑ አሳውቋል።

 

ዛሬ ይፋ የተደረገው ስትራቴጂክ እቅድ ከ2014 ጀምሮ እስከ 2018 ሲያገለግል የነበረው እቅድ በማብቃቱ ነው።

 

የሚተገበረው ስትራቴጂክ ዕቅድ የተዘጋጀው በፍጥነት እየተለወጠ ላለው የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ምላሽ ለመስጠትና ኮሚሽኑ ወቅታዊም ሆነ አዳዲስ ችግሮችን ለመቋቋም በሚያስችል ቁመና ላይ እንዲገኝ ለማድረግ ያለመ መሆኑ ተጠቅሷል።

 

በ2014 እስከ 2018 ዓ.ም ስትራቴጂክ ዘመን የተመዘገቡ ስኬቶች ሰነዱ ሲዘረዝር ባለፉት አምስት ዓመታት ከ17,328 በላይ ሰዎችን ከህግ ወጥ እስራት ማስለቀቅ ተችሏል።

 

5,663 ሰዎች ደግሞ የሰብአዊ መብት ጥሰት ሪፖርት አድርገዋል ያለው ሰነዱ 1,116 የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ላይ እርምጃ ተወስዷል።

 

ምን ዓይነት እርምጃ እንደሆነ ግን ኮሚሽኑ ለጊዜው አልዘረዘረም።

 

541 ሰዎች ደግሞ የዋስትና መብታቸው ተከብሮላቸው መለቀቃቸውን ምክትል ኮሚሽነር ሚዛኔ አባተ(ዶ/ር) አስረድተዋል።

 

በውጤቶች ላይ ትኩረት ማድረግ፣ በመከላከል ላይ ትኩረት መስጠት፣ ለተጠያቂነት፣ ለፍትሕና ለትግበራ ትኩረት መስጠት ፣ ጠንካራ ተቋማዊ መሠረቶች መጣል እና ሌሎችም ጉዳዮች ደግሞ ከተጠቀሱት የአዲሱ ስትራቴጂክ እቅድ መለያዎች ውስጥ ጥቂቶቹ ናቸው።

 

"ሴቶች እና ልጆች፣ ሕጻናትና ወጣቶች፣ አካል ጉዳተኞች፣ የአገር ውስጥ ተፈናቃዮች፣ ስደተኞችና ፍልሰተኞች የግጭት ተኮር ጥንቃቄና የጥበቃ ስጋቶች፤ እንዲሁም ለወቅታዊ አዳዲስ የሰብአዊ መብት ጉዳዮች" ደግሞ በስትራቴጂ ዘመኑ ትኩረት የሚሰጥባቸው ናቸው ይላል ሰነዱ።

 

"ሕገ ወጥ የሲቪል ሰዎች ግድያ እና የአካል ጉዳት፣ የዘፈቀደ እና የተራዘመ እስር፣ አስገድዶ መሰወርና ጠለፋ፣ የታጠቁና የጸጥታ አካላት መበራከት እና ደካማና የተበጣጠሱ የጥበቃ ሥርዓቶች" ደግሞ በስትራቴጂክ ዘመን ከፍተኛ ተጽዕኖ ይኖራቸዋል ተብለው የሚጠበቁ ጉዳዮች መሆናቸውን አስረድተዋል።

 

ስትራቴጂክ እቅዱን ለማዘጋጀት 8 ወራት ፈጅቷል የተባለ ሲሆን እቅዱን ለማስፈጸም ደግሞ 7.6 ቢሊዮን ብር ይፈልጋል።

 

ያሬድ እንዳሻው

Recent Posts

See All
የምክክሩ ሂደት አሁን ላይ ከእያንዳንዱ ባለ 500 አባላት የስራ ቡድን የተመረጡ 30 አባላት ከስልታዊ ቡድኖች የቀረቡ የአጀንዳ ምክረ ሀሳቦችን አቀናጅተው፣ 500 አባላት ላሏቸው 7 የስራ ቡድኖች ቅዳሜ ከሰዓት ማቅረብ ጀምረዋል፡፡

ነሐሴ 4 2018 የምክክሩ ሂደት አሁን ላይ ከእያንዳንዱ ባለ 500 አባላት የስራ ቡድን የተመረጡ 30 አባላት ከስልታዊ ቡድኖች የቀረቡ የአጀንዳ ምክረ ሀሳቦችን አቀናጅተው፣ 500 አባላት ላሏቸው 7 የስራ ቡድኖች ቅዳሜ ከሰዓት ማቅረብ ጀምረዋል፡፡ በአዲስ አበባ ላይ እየመከረ ያለው ቡድን ግን ጉዳዩ አከራካሪ ሆኖ በ

 
 
 
የአዲስ ኃይል ማስቀጠያ የዱቤ ክፍያ ወለድን ሙሉ በሙሉ ማንሳቱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ተናገረ፡፡

ነሐሴ 4 2018 የአዲስ ኃይል ማስቀጠያ የዱቤ ክፍያ ወለድን ሙሉ በሙሉ ማንሳቱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ተናገረ፡፡ አገልግሎቱ አዲስ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስቀጠያ ክፍያን በዱቤ ለሚከፍሉ ደንበኞች ይጣል የነበረውን የወለድ ክፍያ ሙሉ በሙሉ ማንሳቱን የአገልግሎቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጅነር ጌቱ ገረመው አስረ

 
 
 

1 Comment


Daniel Brooks
Daniel Brooks
Jul 09

Excellent content from beginning to end. The article provides practical knowledge without making the subject feel overwhelming. I especially liked the balanced approach and clear explanations. I also noted 10.0.0.0.1 in my personal notes as a reminder to come back and read this guide again. Great work.

Like
Sheger App Logo
iOS Store
Google Play
  • Facebook
  • X
  • Youtube
  • TikTok
  • Telegram
  • Whatsapp

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page