top of page

በችግሮች እየተፈተኑ ያሉት ቴአትር ቤቶች

  • 3 hours ago
  • 1 min read

ሐምሌ 2/2018


በተመልካች ቁጥር ማነስና በሌሎችም ችግሮች እየተፈተኑ ያሉትን የኢትዮጵያን የቴአትር ቤቶች ከችግራቸው ለማውጣት መንግስት በትኩረት ሊሰራ ይገባል ተባለ፡፡


ከገንዘብ እጥረት እስከ ግብአት እጥረት ቲያትር ቤቶቹ በበረታ ችግር ውስጥ ናቸው ተብሏል፡፡


ረዘም ላሉ ዓመታት በቴአትር ሙያ ላይ የሰሩት አርቲስት አፅናፉ መኩሪያ የቲያትር ቤቶች መዳከም ብዙ ምክንያቶች ቢኖሩትም ትልቁ ችግር ግን መንግስት ለኪነ ጥበቡ ዘርፍ ትኩረት አለመስጠቱ ነው ይላሉ።

ስለ ቴአትር በቂ ዕውቀት የሌላቸው ሰዎች በቴአትር ቤቶች አስተዳደር ውስጥ ሲሾሙ ይታያል፣ ይህም የቴአትር ዘርፉን እንደጎዳው ያስረዳሉ።


ሌለኛው የቴአትር ባለሙያ አርቲስት መርዕድ ነጋሽ ደግሞ በኪነ-ጥበቡ ላይ መንግስት የጣለው ታክስ ቀድሞውኑ እምብዛም ገቢ የሌለው የቲያትር ዕድገት ላይ ተፅዕኖ አሳድሯል ይላል።


ከዚህም በተጨማሪ አንድ የቴአትር ደራሲ ከገቢው ላይ የ30 በመቶ ክፍያ ብቻ ነው የሚያገኘው የሚለው አርቲስት መርዕድ ይህም አዳዲስ የቲያትር ድርሰቶች ከመድረኩ እንዲጠፉ ምክንያት እንደሆነ ያስረዳል።


የባለሙያዎች ቁርጠኝነት ማነስ፣ የቴክኖሎጂ መስፋፋት እና የውጪ ፊልሞች ተፅዕኖ ዘርፉን ካዳከሙት ምክንያቶች መካከል ናቸው ሲሉ ባለሙያዎቹ አስረድተዋል።


ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ……


ንጋት መኮንን

Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page