top of page

ኢትዮጵያ በ2018 በጀት አመት በ9 ወራት ውስጥ ከወጪ ንግድ 7 ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር ገቢን አግኝታለች፡፡

  • 1 day ago
  • 1 min read

ሐምሌ 7/2018


ኢትዮጵያ በ2018 በጀት አመት በ9 ወራት ውስጥ ከወጪ ንግድ 7 ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር ገቢን አግኝታለች፡፡


ከውጪ አስፈላጊ ለምትላቸው እቃዎች ግዢ 16 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ወጪ አውጥታለች፡፡


በዘጠኝ ወራቱ ኢትዮጵያ ወደ ውጪ ከላከችው እቃ ያገኘችው ገቢና ወደ ሀገር ውስጥ ላስገባችው እቃ ያወጣችው ወጪ መካከል ያለው ልዩነት የ8 ነጥብ 9 ቢሊዮን ዶላር ነው፡፡


ይህም በወቅቱ የኢትዮጵያ የንግድ ሚዛን ጉድለት መጠኑን ያሳያል፡፡


በ2017 በጀት አመት የኢትዮጵያ የንግድ ሚዛን ጉድለት 10 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ሲሆን የበጀት አመቱ አጠቃላይ የንግድ ሚዛን ጉዱለት ከዚህ ሊቀንስ እንደሚችል ተነግሯል፡፡


በ2018 በጀት አመት 11 ቢሊዮን ዶላር ከወጪ ንግድ ያገኘችው ኢትዮጵያ ከባለፈው አመት ጋር ሲመሳከር የ2 ነጥብ 8 ቢሊዮን ዶላር ጭማሪ ያሳያል፡፡


ታዲያ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የንግድ ሚዛን ጉድለት ምን ቢሰራ ማጥበብ ይቻላል ? በስንት ጊዜስ ? የዘርፉ ባለሙያን ጠይቀናል፡፡


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ....



በረከት አካሉ

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page