በሰባተኛው ሃገራዊ ምርጫ የተከሰቱ ችግሮች እንዳይደገሙ የህግ ማሻሻያ በማድረግ እንዲታረሙ ተጠየቀ፡፡
- 5 hours ago
- 1 min read
ሐምሌ 3/2018
በሰባተኛው ሃገራዊ ምርጫ የተከሰቱ ችግሮች መልሰው እንዳይደገሙ የህግ ማሻሻያ እና የአፈፃፀም ማስተካከያ በማድረግ እንዲታረሙ ተጠየቀ፡፡
ባለፈው ሰኔ 2 ቀን 2018 ዓ.ም በተፈናቃይ ካምፖች በተቋቋሙ ልዩ የምርጫ ጣቢያዎች የተካሄደው ምርጫ የራሱ መመሪያ ወጥቶለት የተካሄደ አዲስ አሰራር ነበር፡፡
በልዩ ሁኔታ ምርጫ ስለሚካሄድባቸው ምርጫ ጣቢያዎች ማቋቋሚያ መመሪያ ወጥቶ ተፈናቃዮች የመምረጥ መብታቸውን እንዲጠቀሙ መደረጉ መልካም መሆኑ በልዩ የምርጫ ጣቢያዎች በገለልተኝት ምርጫውን የታዘበው የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ድርጅቶች ህብረት ተናግሯል፡፡

ይሁንና ተፈናቃዮች የሚሰጡት ድምፅ ወደ ተፈናቀሉበት ቀዬ ሂዶ የሚቆጠር መሆኑ ለምርጫው ፍላጎት እንዲያጡ አድርጓቸዋል ብሏል፡፡
ለዚህም እንደማሳያ ከ20 ሺህ በላይ ተፈናቃዮች በነበሩበት ካምፕ 40 የማይሞሉ ሰዎች የመረጡበት አጋጣሚ መኖሩን ጠቅሷል፡፡
በመሆኑም ለመጭው ምርጫ የህግ ማሻሻያ ያስፈልገዋል ሲል ነግሮናል፡፡
በጉዳዩ ላይም ከምርጫ ቦርድ እና ከመጭው ፓርላማ ጋር ልነጋገርበት እቅድ ይዣለሁም ብሏል፡፡
እንዲሁም የመረጃ እጥረት እና ሕፃናት ጭምር በምርጫ እንዲሳተፉ የተደረጉበት የአፈፃፀም ችግሮችም ለወደፊቱ ትምህርት ሆነው ሊታሙ የሚገቡ ናቸው ሲል አሳስቧል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ……
ትዕግስት ዘሪሁን
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/
YouTube : https://shorturl.at/18TS1
Telegram : https://shorturl.at/68aeK
Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4
WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx
LinkedIn: https://shorturl.at/Vfe6i
Tiktok : https://shorturl.at/lhYiv
Instagram: https://shorturl.at/9X4S7





Comments