በኤአይ የሚሰሩ የፈጠራ ውጤቶች በኢትዮጵያ የህግ ከለላና ጥበቃ ያገኛሉ ወይ?
- 1 day ago
- 1 min read
ሐምሌ 8/2018
የሰው ልጅ በተፈጥሮ ያለውን እምቅ የፈጠራ አቅም ተጠቅሞ የሚሰራቸው ልዩ ልዩ ውጤቶች አዕምሯዊ ንብረቶቹ ሆነው በህግ እንዲጠበቁለት ይደረጋል፡፡
ይህ የህግ ጥበቃ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ( #AI ) የሚሰሩ የፈጠራ ውጤቶችን ይመለከታል ወይ?
በሰው ሰራሽ አስተውሎት የሚሰሩ የስራ ፈጠራዎች እንዳሉ ሁሉ የሌላን ሰው ስራ በ AI በመታገዝ እንደራሳቸው የፈጠራ ስራ የሚያቀርቡ እንዳሉ ሰምተናል፡፡

በሰው ሰራሽ አስተውሎት ወይም የሚሰሩ የፈጠራ ውጤቶች በኢትዮጵያ የህግ ከለላና ጥበቃ ያገኛሉ ወይ? ስንል ጠይቀናል፡፡
በመደወላብ ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት ቤት ውስጥ ረዳት ፕ/ሮ የሆኑት ዓለሙ ባልቻ በጉዳዩ ላይ ጥናት አድርገዋል፡፡
ሆኖም ኢትዮጵያ በሰው ሰራሽ አስተውሎት የሚሰሩ የፈጠራ ውጤቶችን ከለላና ጥበቃ ምታደርግበት የህግ ማዕቀፍ የላትም ብለውናል፡፡
አክለውም ኢትዮጵያ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ወይንም AI የተመለከት ዩኒቨርሲቲ ልትገነባ እንደሆነ ተናግረው ይህ ጉዳይ ሊታሰብበት ይገባልም ብለውናል፡፡
ከሌሎች ሃገራት ልምድ መውስድ ይቻላል ሲሉም ያስረዳሉ፡፡
የእምሯዊ ንብረት ባለስልጣን በዚህ ጉዳይ ምን አስቧል?
ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ….
ማርታ በቀለ
_edited.jpg)
