top of page

ተመካካሪዎች በተመደቡላቸው አጀንዳዎች ላይ መመካከር መጀመራቸውን የምክክር ኮሚሽን ተናገረ፡፡

  • 4 hours ago
  • 1 min read

ሐምሌ 13/2018


 ተመካካሪዎች በ80 ንዑስ ቡድኖች በመከፈል በተመደቡላቸው አጀንዳዎች ላይ መመካከር መጀመራቸውን የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ተናገረ፡፡


የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን እየተካሄደ ባለው የምክክር ጉባኤ የዛሬውን የምክክር ሂደት አስመልክቶ መግለጫ በሰጠው መግለጫው፤ በንዑሳን ቡድኖች የተከፈሉት ተመካካሪዎች በተመደቡበት አጀንዳ ላይ መመካከር መጀመራቸውን ተናግሯል፡፡


የዛሬውን መግለጫ የሰጡት የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አምባሳደር ሙሃሙድ ድሪር በእያንዳንዱ ንዑስ ቡድን ውስጥ 50 ተመካካሪዎች ያሉ ሲሆን በአጠቃላይ 80 አነስተኛ ቡድኖች እየተመካከሩ ይገኛሉ ብለዋል፡፡

በአንድ አጀንዳ ላይ እንዲመካከር የተመደበ ዐብይ የስራ ቡድን 500 ተመካካሪዎችን ሲይዝ በስሩ እያንዳንዳቸው 50 ተመካካሪዎችን የያዙ 10 ንኡሳን ቡድኖችን እንዲይዝ ተደርጎ መዋቀሩንም ተናግረዋል፡፡


በአጠቃላይ 80 ንዑስ ቡድኖች በተመደቡላቸው አጀንዳዎች ላይ እየመከሩ እንደሚገኙ አስረድተዋል፡፡


ሂደቱ በስኬት እንዲከናወን ኮሚሽኑ በስራ ልምዳቸውና በትምህርት ዝግጅታቸው አንቱታን ያተረፉ 160 የሚሆኑ አመካካሪዎችን መመደቡን በመግለጫቸው አመልክተዋል፡፡


ከዚህ በተጨማሪም 256 የሚሆኑ የቃለ ጉባኤ ጸሃፊዎች ተሰማርተው የሀገራዊ ምክክር ጉባኤውን በብቃት እየመሩ ይገኛሉ ሲሉም የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አምባሳደር ሙሃሙድ ድሪር በዛሬው መግለጫቸው አስረድተዋል፡፡



ምንታምር ፀጋው




የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…



















Recent Posts

See All
ከምስራቅ ወለጋ ጉቡ ሰዮ ተፈናቅለው በደብረ ብርሃን መጠለያ የነበሩ ዜጎች

ሐምሌ 13/2018 ከምስራቅ ወለጋ ጉቡ ሰዮ ተፈናቅለው በደብረ ብርሃን መጠለያ የነበሩ ዜጎች ወደ ቀዬአቸው ቢመለሱም እርሻና የመኖሪያ ቤታቸው ሊመለስላቸው እንዳልቻለ ለሸገር ተናግረዋል፡፡ በዚህ ምክንያት ወደ ደብረ ብርሃን መጠለያ ተመልሰናል ብለዋል። የአካባቢው የአደጋ ስጋት ቢሮ የተፈናቃዮቹን መሬት መልሻለው ስለቅ

 
 
 
Sheger App Logo
iOS Store
Google Play
  • Facebook
  • X
  • Youtube
  • TikTok
  • Telegram
  • Whatsapp

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page