የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች በተልዕኮ ተለይተው በተወሰኑ የትምህርት መስኮች ላይ ትኩረት አድርገው እንዲያሰተምሩ መደረጉ
- 1 day ago
- 1 min read
ሐምሌ 9/2018
የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች በተልዕኮ ተለይተው በተወሰኑ የትምህርት መስኮች ላይ ትኩረት አድርገው እንዲያሰተምሩ መደረጉ ለውጥ ማምጣቱን ጥናት አሳይቷል፡፡
በኢትዮጵያ የትምህርት ጥራት መጓደልን ለማስተካከል በዘርፉ የተለያዩ የለውጥ ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነ ይነገራል፡፡
በተለይም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በተልዕኮ እና በትኩረት ተለይተው እንዲሰሩ ማድረግ ለትምህርት ጥራትና ለሀገር ኢኮኖሚ ወሳኝ ነው ተብሎ ታምኖበት ወደ ስራ መገባቱ ይታወሳል፡፡
በዚህ መሰረት ሶስት ዋና ዋና ተልዕኮ ተለይቶ መተግበራቸው የሚታወስ ሲሆን የምርምር ዩኒቨርሲቲዎች አፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርስቲዎች እንዲሁም አጠቃላይ ዩኒቨርስቲዎች በሚል መለየታቸው ተነግሯል፡፡
እነዚህ ተልዕኮዎች አሁን ላይ ለውጥ እያመጡ ነው ሲሉ በጉዳዩ ላይ ጥናት ያደረጉት በአንቦ ዩኒቨርሲቲ መምህር እና አሁን ላይ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሶስተኛ ዲግሪያቸውን በመስራት ላይ የሚገኙ ጀማል ሹክሩ ነግረውናል፡፡
ይሁንና ተማሪዎችን በታሰበው ልክ ብቁ ለማድረግ ከፍተኛ በጀት የሚጠይቅ በመሆኑ የታሰበው ውጤት ላይ ለመድረስ ገና እንደሚቀረው አሰረድተዋል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ….
ማርታ በቀለ
_edited.jpg)
