''የሰሜን የኢትዮጵያ አካባቢዎች ላይ በክረምቱ የሚኖረው ዝናብ አነስተኛ ነው'' የሜትሮሎጂ ኢንስቲትዩት
- 4 hours ago
- 1 min read
ሐምሌ 8/2018
የሰሜንና የሰሜን የኢትዮጵያ አካባቢዎች ላይ በክረምቱ የሚኖረው ዝናብ አነስተኛ ነው ሲል የኢትዮጵያ ሜትሮሎጂ ኢንስቲትዩት ተናገረ፡፡
በዚህም ምክንያት የሚኖረው የዝናብ መጠን አነስተኛ ነው ህብረተሰቡም በቂ ዝግጅት እንዲያደርግ ኢንስቲትዩቱ ተናግሯል፡፡
የክረምት ዝናብ አሁን ላይ ባላገኙ አንዳንድ አካባቢዎች በሚቀጥሉት ቀናት የተሻለ ዝናብ እንደሚያገኙ ጠቅሷል፡፡
የዝናብ እጥረት በሚታይባቸው አካባቢዎችም በመጪዎቹ ቀናት የተሻለ የዝናብ መጠን ሊያገኙ እንደሚችልም ኢንስቲትዩቱ ትንበያውን ነግሮናል፡፡

በመጪዎቹ 10 ቀናት በአብዛኛው የዝናብ ተጠቃሚ አካባቢዎች የሚኖረው የዝናብ መጠን ከቀላል እስከ መካከለኛ ነው ተብሏል፡፡
በመካከለኛው የአማራ አካባቢዎች ፣ የምዕራብ ሻዋ ፣ ምዕራብ ኦሮሚያ እና ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል አካባቢዎች ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ሊዘንብ እንደሚችል አስረድቷል፡፡
ህብረተሰቡን ከባድ ዝናብ በሚጥልባቸው አካባቢዎች አስፈላጊው ጥንቃቄ እንዲያደርግ ኢንስቲትዩቱ ጠይቋል፡፡
የዝናብ እጥረት ሊከሰትባቸው ይችላል በተባሉ አካባቢዎች ላይ ደግሞ የግብርና ስራዎች ሲሰራ አስፈላጊው ዝግጅትና አማራጮች እንዲወሰድም መክሯል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ…
ፍቅሩ አምባቸው

