top of page

ከተሽከርካሪ መድን ሽፋን ባሻገር ያሉ የመድን ሽፋን አገልግሎቶች ለምን ትኩረት ተነፈጋቸው?

  • 3 hours ago
  • 1 min read

ሐምሌ 8/2018


በኢትዮጵያ የመድን አገልግሎት መሰጠት ከጀመረ አንድ ክፍለ ዘመን ተሻግሯል።


በተለይ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በዘርፉ የሚቀላቀለው ባለ መዋለነዋይ እየጨመረ መምጣት የመድን አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን ቁጥር ወደ 19 እንዳደረሰውም መረጃዎች ያሳያሉ።


ሰዎች በተለይ የጤና፣ የህይወት፣ የቁስ እና የረዥም ጊዜ የአካል ጉዳት የመድን አገልግሎትን እንዲጠቀሙ የዘርፉ ባለሙያዎች ይመክራሉ።


ይሁን እንጂ በኢትዮጵያ በብዛት የተለመደው የሞተር ወይም የተሽከርካሪ ኢንሹራንስ ነው።


አገልግሎቱን የሚሰጡ ተቋማት የግብርና ኢንሹራንስን ጨምሮ ሌሎችንም የመድን ሽፋኖች ቢሰጡም ግን ሌሎች አገልግሎቶች ላይ ክፍተት እንዳለባቸው ይነገራል።



ለመሆኑ ለተሽከርካሪ መድን ሽፋን አገልግሎት የተሰጠውን ትኩረት ያህል ሌሎቹ የመድን ሽፋን አገልግሎቶች ለምን ትኩረት ተነፈጋቸው? ምክንያቱስ ምንድነው?


የኢትዮጵያ ጠለፋ መድን አክሲዮን ማህበር የስትራቴጂ እና ቢዝነስ ዴቨሎፕመንት ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ፍቅሩ ፀጋዬን ጠይቀናቸዋል።


የጤና ፣ የህይወትና የግብርና የመድን ሽፋን ትኩረት አነስተኛ የሆነበት ምክንያት ዘርፈ ብዙ ነው ይላሉ።


የህብረተሰቡ የግንዛቤ ክፍተት እና በቴክኖሎጂ የተደገፈ የመድን ሽፋን አለመቅረብ ከምክንያቶቹ ውስጥ መሆኑን ጠቅሰዋል።


እነዚህ የመድን ሽፋን አገልግሎቶች እንደ መሰረታዊ ፍላጎቶች ሊታዩ እና ከፍተኛ ትኩረትም ሊሰጣቸው ይገባል ብለዋል።


የመድን ሽፋን አገልግሎት እንዲስፋፋ በመንግስት በኩል ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራበት መሆኑን አቶ ፍቅሩ ነግረውናል።


ነገር ግን ከተሸከርካሪ የመድን ሽፋን ውጪ ያሉ አገልግሎቶችን ህብረተሰቡ እንዲጠቀማቸው ለማድረግ መንግስት አስገዳጅ መመሪያዎችን ማዘጋጀት እንዳለበትም ያነሳሉ። ይህም በዘርፉ ላለው ችግርም መፍትሄ ይሆናል ብለው ያምናሉ።


በኢትዮጵያ የመድን ሽፋን እየሰጡ ያሉ ተቋማት የአገልግሎት አሰጣጥ ስርዓታቸው ከቀድሞው በተሻለ መልኩ እያደገ መምጣቱንም አቶ ፍቅሩ ፀጋዬ ተናግረዋል።


ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ…



ፍቅሩ አምባቸው

Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page