የአገራዊ ምክክር ጉባኤ ላይ ጋዜጠኞች ኮሚሽነሮችን ፣ተሳታፊዎችን እና ባለሙያዎች ቃለ መጠየቅ መስራት የሚችሉት የወኪሎቻቸውን ፍቃድ ሲያገኙ መሆኑን የሚደነግግ መመሪያ ኮሚሽኑ ይፋ አደረገ።
- 1 hour ago
- 2 min read
ሐምሌ 7/2018
የአገራዊ ምክክር ጉባኤ ላይ ጋዜጠኞች ኮሚሽነሮችን ፣ተሳታፊዎችን እና ባለሙያዎች ቃለ መጠየቅ መስራት የሚችሉት የወኪሎቻቸውን ፍቃድ ሲያገኙ መሆኑን የሚደነግግ መመሪያ ኮሚሽኑ ይፋ አደረገ።
የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከተለያዩ የህብረተሰብ ከፍሎች የተወከሉ 4ሺ ጉባኤተኞች የሚመክሩበትን ምክክር መገናኛ ብዙሃን እንዴት መዘገብ አንዳለባቸው የዘገባ መመሪያ አውጥቷል ።

መገናኛ ብዙሃኑ በመመሪያው የተደነገጉትን ህግጋት ከተላለፉ ኮሚሽኑ ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ጋር በተመባበር በህግ ተጠያቂ እንደሚደረግ ተደንግጓል ።
ከሃምሌ አንድ ቀን ጀምሮ ስራ ላይ የዋለው መመሪያ በመገናኛ ብዙሃን በሚሰሩት ዘገባ በምክክር ጉባዔው ሁሉም ኢትዮጵያን ባለቤት መሆናቸውን የሚጠቁሙ መሆን እንዳለባቸው ዘርዝሯል፡፡
በተጨማሪም መገናኛ ብዙሃኑ ጉባኤው ሊያሳካ የቆመላቸውን ዓላማዎች ማሳያት እና ከምክክሩ ማብቃት በኋላ ሊኖሩ የሚችሉ ሂደቶችን ማሳወቅ አለባቸው ይላል።
የመገናኛ ብዙሃን መብቶች እና ሃላፊነትን በዘረዘረበት ክፍል ደግሞ ማንኛውም መገናኛ ብዙሃን ጋዜጠኛ ሂደቱን የመዘገብ መብት እንዳለው አሳውቋል፡፡
በተጨማሪም ጋዜጠኞች ከየትኛውም አካል ነፃ ሆኖ መስራት እንደሚችሉ ጠቅሷል፡፡
ሃላፊነቶችን በተመለከተ መገናኛ ብዙሃኑ ስለምክክሩ በሚሰሩት ዘገባ ሁሉም አካላት የማሳተፍ ሃላፊነት አለባቸው፡፡
ዘገባዎቹ የኮሚሽንኑ ታዓማኒነትን የሚያጠናክሩ መሆን እንዳለባቸውና የኮሚሽነሮችን ስም ማጉደፍ እንደሌለባቸው ያሳስባል፡፡
እንደኮሚሽኑ መምሪያ የመገናኛ ብዙሃን በለሙያዎች ወይንም ጋዜጠኞች አከራካሪ እና ግጭትን ሊቀሰቅሱ የሚችሉ ጉዳዮችንም ሲዘግቡ በከፍተኛ ጥንቃቄ መሆን አለበት ብሏል፡፡
የምስል እና የድምጽ አጠቃቀም ጭቅጭቆችን እና ማስፈራሪያዎችን ያካተቱ መሆን የለባቸውም ፡፡
የምክክር ሂደቱን የሚሰሩ ዘጋቢዎች ወይንም ፕሮግራሞች የህዝቦችን አንድነት የሚያስቀድሙ ፣ የጋራ መግባባትን የሚፈጥሩ ዜጎች በሃገራዊ ምክክር ሂደት ላይ ያላቸውን መተማማን የሚያሳድጉ መሆን አለባቸው ተብሏል፡፡
በመመሪያው መሰረት ስራዎችን በማይሰሩ መገናኛ ብዙሃ ላይ ከመገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ጋር በመተባባር ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ በመመሪያው አስጠንቅቋል፡፡
ነገ ሃምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ አዲስ ኮንቬንሼን ማዕከል ይካሄዳል ተብሎ የሚጠበቀው የምክክር ጉባኤ ላይ ከ4 ሺ በላይ ተወካዮች ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ጉባኤተኞቹ በኮሚሽኑ በተለዩ ስምንት ዋና ዋና አጀንዳዎች ላይ ለሳምንታት ይመክራሉ፡፡
የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ ባለቤትነት ጉዳይ ፣የህገ መንግስቱ ፣ የመሬት ባለቤትንት የክልሎች አወቃቀር እና መሰል ጉዳዮች ከሚመከርባቸው አጀንዳዎች ውስጥ መሆናቸው ይታወቃል፡፡
ያሬድ እንዳሻው



Comments