top of page


በመካከለኛው ምስራቅ የተቀሰቀሰው ጦርነት በኢትዮጵያ በዋጋ ግሽበት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እንደሚኖረው የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴው ተናገረ፡፡
መጋቢት 22/2018 በመካከለኛው ምስራቅ የተቀሰቀሰው ጦርነት በኢትዮጵያ በዋጋ ግሽበት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እንደሚኖረው የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴው ተናገረ፡፡ የኢራኑ ጦርነት በአለም አቀፍ የነዳጅ ዋጋ ላይ ከፍተኛ ጫና እያሳደረ የአቅርቦት ሰንሰለት መቋረጥም እየፈጠረ መሆኑን ኮሚቴው ማስታወሱን ከብሔራዊ ባንክ ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡ ይህም በሃገር ውስጥ የዋጋ ግሽበት ሁኔታ ላይ ጫና እንደሚፈጥር ጠቅሶ የስጋቱ ጫና ግን መንግስት በሚወስደው የመቆጣጠሪያ እርምጃዎች እና ግጭቱ በሚቆይበት ጊዜ የሚወሰን ይሆናል ብሏል፡፡ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የገንዘብ ፖሊስ ኮሚቴው ስድስተኛ ዙር ስብሰባውን አካሄዶ የተለያዩ ኢኮኖሚያዊ ሁኔታዎችን በመገምገም መግለጫ አውጥቷል፡፡ በቅርቡ ሁለት ገለልተኛና የመስኩ ባለሙያ የሆኑ አባላትን ያካተተው የገንዘብ ፖሊሲ ከታህሳስ ወር
Mar 312 min read


ታሪክን የኋሊት -የማይጨው ጦርነት
#ታሪክን_የኋሊት በኢትዮጵያና በኢጣሊያ መካከል የማይጨው ጦርነት የተደረገው በ1928 ዓ.ም በዛሬው ቀን ነበር፡፡ ኢጣሊያ በሊቢያና በሱማሊያ ከኢትዮጵያ ክፍል ኤርትራን በቅኝ ግዛትነት ይዛ ከቆየች በኋላ፣ ጠቅላላ ኢትዮጵያን በሃይል ለመውረር ጦርነት ከፈተች፡፡ በምፅዋ ወደብ ፣ በኤርትራ በኩል ወደወሰን ዘመናዊ የጦር ሃይሏን አደራጀች፡፡ የወልወልን ግጭት ሆን ብላ ከቀሰቀሰች በኋላ፣ ተበዳይ ሆና ለመቅረብ ሞከረች፡፡ አከታትላም ዋናው የጦር ሃይሏን ባደራጀችባት ኤርትራ በኩል፣ ወሰን ጥሳ፣ በጥቅምት ወር መቀሌን ያዘች፡፡ ከወራሪው የኢጣሊያ ሃይል ጋር ሲወዳዳር፣ ኋላ ቀርና አነስተኛ መሣሪያ ያለው አብዛኛው፣ የኢትዮጵያ ሰራዊት፣ የክተት አዋጁን ተከትሎ፣ ስንቁን ይዞ፣ ጦርና ጋሻውን አንግቦ ወደዘመቻው ተሰማራ፡፡ ኢጣሊያ፣ በሶማሊያ በኩል ባደራጀችው ዘመናዊ የ
Mar 312 min read
በአይነቱ ልዩ የሆነ የሪል ስቴት ኤክስፖ በለንደን እንግሊዝ ከግንቦት 15 እስከ 17/2018 እንደሚካሄድ ተነገረ።
መጋቢት 22/2018 በአይነቱ ልዩ የሆነ የሪል ስቴት ኤክስፖ በለንደን እንግሊዝ ከግንቦት 15 እስከ 17/2018 እንደሚካሄድ ተነገረ። በእንግሊዝና አካባቢዋ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በሀገራቸው የመኖሪያ ቤት ማፍራት የሚችሉበትን ዕድል ለመፍጠር የተዘጋጀ ኤክስፖ ነው ተብሏል። በሪል ስቴት አልሚዎችና በተጠቃሚዎች መካከል ያለውን መተማመን ለማሳደግና አስተማማኝ በሆነ መንገድ ግብይቶች እንዲፈፅሙ የተዘጋጁ ስርዓቶችን ለማስተዋወቅ ያለመ መሆኑም ተጠቅሷል። በኤክስፖው ላይ ከሚመለከታቸው አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ጋር በሚደረግ የመረጃ ልውውጥና የፓናል ውይይት በዘርፉ ስላሉ ችግሮች ይነሳል ተብሎ እንደሚጠበቅም ኤክስፖውን አስመልክቶ ከተዘጋጀ መግለጫ ላይ ተመልክተናል። ባንኮች በውጪ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የቢዝነስ ድ
Mar 311 min read


የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአገራቸው ጦር የኢራን ዋነኛ የነዳጅ ዘይት መናኸሪያ የሆነውን የካርግ ደሴት ሊይዝ እንደሚችል ፍንጭ ሰጡ፡፡
መጋቢት 21/2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች #አሜሪካ የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአገራቸው ጦር የኢራን ዋነኛ የነዳጅ ዘይት መናኸሪያ የሆነውን የካርግ ደሴት ሊይዝ እንደሚችል ፍንጭ ሰጡ፡፡ የካርግ ደሴት የኢራን ዋነኛ የነዳጅ ዘይት ማምረቻ እና ለውጭ ገበያ ከታለመው ነዳጅ 90 በመቶው የሚላከው ከዚሁ ደሴት እንደሆነ ቢቢሲ ፅፏል፡፡ ከወር በላይ ባስቆጠረው የኢራን ጦርነት ምክንያት በአለም ዙሪያ የነዳጅ ዘይት ዋጋ በጣሙን እያሻቀበ ነው ተብሏል፡፡ ኢራን በኢስፍሐን ዩኒቨርስቲ ላይ ለተፈፀመባት ጥቃት በእስራኤል እና በባሕረ ሰላጤው አገሮች በሚገኙ የአሜሪካ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ላይ የአፀፋ ጥቃት እንደምታደርስ ዝታለች፡፡ ኢራን በእስራኤል ደቡባዊ ክፍል የኢንዱስትሪዎች መገኛ ላይ በፈፀመችው የሚሳየል ድብደባ ከባድ ቃጠሎ መድረሱ ታውቋል፡፡
Mar 302 min read


በባህር፣ በየብስ እና በአየር ተጓጉዘው የሚመጡ እቃዎችን ከጉምሩክ መጋዘን በሚያወጡበት የጊዜ ገደብ ላይ ለውጥ ተደርጓል።
መጋቢት 21/2018 በአዲሱ የጉምሩክ አዋጅ ማሻሻያ ረቂቅ ላይ አስመጪዎች በባህር፣ በየብስ እና በአየር ተጓጉዘው የሚመጡ እቃዎችን ከጉምሩክ መጋዘን በሚያወጡበት የጊዜ ገደብ ላይ ለውጥ ተደርጓል። በባህር እና በየብስ ተጓጉዘው የሚመጡ እቃዎችን ከጉምሩክ መጋዘን ማውጫ ጊዜው ከ15 ቀን ወደ 45 ቀን፤በአየር ተጓጉዘው የሚመጡ እቃዎችን ማውጫ ጊዜ ገደቡ ከ10 ቀን ወደ 30 ቀን ይሻሻላል ተብሏል። ይህንን የፈቀደው ባለፈው ሳምንት እንደገና ተሻሽሎ ለህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የቀረበው የጉምሩክ አዋጅ ነው፡፡ በአንድ ዲክላራሲዮን ወደ አገር ውስጥ የገቡ እቃዎች በአንድነት መለቀቅ እንዳለባቸውም አሁን በስራ ላይ ያለው አዋጅ ያስገድዳል። ይህ ግን ብዙ ጊዜ አስመጪው በገንዘብ እጥረት ምክንያት በእቃዎች ላይ ሊከፍል የሚገባውን ቀረጥ እና ታክስ በአንድነት
Mar 301 min read


በኢትዮጵያ የተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎች የሚያስፈልጋቸውን የፋይናንስ አቅርቦት
መጋቢት 21/2018 በኢትዮጵያ የተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎች የሚያስፈልጋቸውን የፋይናንስ አቅርቦት አግኝተው ምርታማ እንዲሆኑ የፋይናንስ ተቋማት በየዓመቱ ከሰባት ትሪሊዮን ብር በላይ ብድር ፈሰስ ማድረግ እንዳለባቸው መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ ይሁንና የሚቀርበው ብድር ከሚያስፈልገው ከግማሽ በታች መሆኑን ከሰሞኑ የብሔራዊ ባንክ ያወጣው ሪፖርት አሳይቷል፡፡ እንደ ማሳያ የግብርናው ዘርፍ በየዓመቱ ከሁለት ትሊዮን ብር በላይ #ብድር እያስፈለገው ያገኘው ግን 8 በመቶ ብቻ ነው፡፡ ካገኘው ብድሩ መካከልም አብዛኛው ለማዳበሪያ ማስመጫ የተሰጠ ብድር መሆኑን የብሔራዊ ባንክ ሪፖርት አሳይቷል፡፡ ለአምራች ኢንዱስትሪውና ቤት መግዛት ለሚፈልጉም የሚቀርበው ብድርም እዚህ ግባ የሚባል አይደለም፡፡ በተለይ ለቤት ገዥዎች የሚያስፈልገው ብድር ቢቀርብ እንኳን በተለይ ተቀጣሪው የመበ
Mar 301 min read


የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን፤ ከትምህርት ዘርፉ እንዲወጡ ቢታዘዙም እስካሁን አልወጡም ያላቸው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዝርዝር ይፋ አደረገ፡፡
መጋቢት 21/2018 የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን፤ ከትምህርት ዘርፉ እንዲወጡ ቢታዘዙም እስካሁን አልወጡም ያላቸው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዝርዝር ይፋ አደረገ፡፡ ቁጥራቸውም 52 ነው፡፡ ባለስልጣኑ ውሳኔው ያሳለፍኩት የትህምህርት ተቋማቱ የዘርፉን ጥራት ለመቆጣጠር በማደርገው ሒደት ያሳለፍኳቸውን ውሳኔዎች ተግባራዊ ባለማድረጋቸው ነው ብሏል፡፡ ከዘርፉ እንዲወጡ ከታዘዙ በኋላም ለምን እንዳልወጡ ለመጠየቅ በተደጋጋሚ መጥተው እንዲያስረዱ ብጠይቅም ተግባራዊ አላደረጉም ብሏል፡፡ ስለሆነም ተቋማቱ የተላለፈውን ውሳኔ ተግባራዊ ባለማድረጋቸው ህጋዊነታቸው የተቋረጠ በሚል የዘረዘራቸውን ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በዜጎች ላይ ጉዳት እንዳያደርሱ የከፍተኛ ትምህርት አገልግሎት መስጠት እንዲያቆሙ እንድታደርጉልን ሲል ለክልሎች እና ለከተማ አስተዳደሮች በደብዳቤ
Mar 302 min read


የመኪና ባለቤት እናደርጋችኋለን በሚል የ1.7 ቢሊዮን ብር ጉዳት ባደረሱት የፊንቴክ ኢንቨስትመንት ድርጅት መስራችና ባለቤቶች ላይ ምርመራ አጣርቶ ለዐቃቤ ሕግ በመላክ ክስ መመስረቱ ተሰማ።
መጋቢት 19/2018 የመኪና ባለቤት እናደርጋችኋለን በሚል የ1.7 ቢሊዮን ብር ጉዳት ባደረሱት የፊንቴክ ኢንቨስትመንት ድርጅት መስራችና ባለቤቶች ላይ ምርመራ አጣርቶ ለዐቃቤ ሕግ በመላክ ክስ መመስረቱ ተሰማ። ድርጅቱን ሲያስተዋውቁ የነበሩ ታዋቂ ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለው ፍርድ ቤት ቀርበው የጊዜ ቀጠሮ ጠይቆባቸው ፍርድ ቤትም እስከ መጋቢት 30 ቀን 2018 ዓ.ም መፍቀዱ ተነግሯል ፡፡ ፊንቴክ ኢንቬስትመንት የግል ድርጅት መስራችና ባለቤቶች የሆኑት ዳንኤል ዮሃንስ ኢየሱስ እና ግርማይ ገ/ሚካኤል ይህደጎ የተባሉት ተጠርጣሪዎች ታዋቂና ተፅዕኖ ፈጣሪዎችን በመጠቀም ከ1200 በላይ ዜጎችን በማጭበርበር የ1.7 ቢሊዮን ብር ጉዳት በማድረሳቸው በ19 ዓይነት የተለያዩ ወንጀሎች ምርመራ አጣርቶባቸው ለዐቃቤ ሕግ በመላክ ዓቃቤ ሕግ ክስ መመስረቱን የኢትዮጵያ ፌደ
Mar 283 min read


በኢትዮጵያ በተለይ በከተማና ኑሮ ጋር በተገናኘት የመኖሪያ ቤት እጥረት አሁንም አለ።
መጋቢት 19/2018 በኢትዮጵያ በተለይ በከተማና ኑሮ ጋር በተገናኘት የመኖሪያ ቤት እጥረት አሁንም አለ። የመኖሪያ ቤት ከነዋሪው ጋር ፈጽሞ የማይመጣን በመሆኑ መንግስት የተለያየ ፕሮጀክቶችን እየቀረጸ ፤ ለማቅረብ ቢሞክርም አሁንም ከፈላጊው አንጻር ሲታይ አልተነቃነቀም። ጎን ለጎንም የግል የቤት አልሚዎች ለቤት ፈላጊው የተቻለውን ያህል እየገነቡ እንደሆነ ይሰማል። የሆነው ሆኖ ከግንባታ ጋር በተገናኘ ሌላኛው ፈተና የዋጋ ንረት እና ተለዋዋጭ የቢዝነስ ጠባይ ገንቢዎችን ምን ያህል እየፈተነ ነው። በዚህ ጉዳይ በሪል ስቴት ገበያና ቢዝነስ ከ20 ዓመት በላይ የቆየውን ጊፍት ሪል ስቴት ማርኬቲንግ ዳይሬክተሩን አቶ ብርቁ ይርጋ ጠይቀናል ። እሳቸው ይህ ተለዋዋጭ ገበያ ፈተና እንደሆነ ተናግረው ተናግረዋል ። ዛሬም ከቤትና ሪል ስቴት ሽያጭ ጋር በተገናኘ ደምበ
Mar 281 min read


የሀገር ውስጥ ፋብሪካዎች አሁን ላይ ከ45 በመቶ በላይ የሚሆነውን የሀገር ውስጥ ምርት ፍላጎት እየሸፈኑ ነው ተባለ።
መጋቢት 19/2018 የሀገር ውስጥ ፋብሪካዎች አሁን ላይ ከ45 በመቶ በላይ የሚሆነውን የሀገር ውስጥ ምርት ፍላጎት እየሸፈኑ ነው ተባለ። እንደ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር መረጃ የሀገር ውስጥ ፋብሪካዎች ከውጪ ይገቡ የነበሩትን ምርቶች እዚሁ በማምረት በከፊልም ቢሆን ፍላጎቱን እየሸፈኑ ነው። በዚህም ፋብሪካዎቹ ምርቶችን ወደ ተለያዩ ሀገራት በመላክ የውጭ ምንዛሪ ከማስገኘት ባሻገር የሀገር ውስጥ ፍላጎትን ማሟላት ላይም ጥሩ ስራ እየሰሩ እንደሚገኙ መረዳት ይቻላል ሲሉ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ድኤታ ታረቀኝ ቡሉልታ ተናግረዋል። ከአገልግሎት አሰጣጥ ፣ ከመሠረተ ልማት እና ብድር አቅርቦት ጋር የተገናኙ የፋብሪካዎቹ ችግሮች እንዲፈቱ የተደረገው ጥረት ውጤቶቹ እንዲገኙ አግዘዋል ብለዋል። የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ጋር በመተባበር በአዲስ አበ
Mar 281 min read


ዘንድሮ በሚደረገው ሀገራዊ ምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎች በነፃ ለምርጫ ቅስቀሳ እንዲጠቀሙበት የተዘጋጀ የአየሮ ሰዓትና የጋዜጣ አምድ መጠን ይፋ ሆነ።
መጋቢት 19/2018 ዘንድሮ በሚደረገው ሀገራዊ ምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎች በነፃ ለምርጫ ቅስቀሳ እንዲጠቀሙበት የተዘጋጀ የአየሮ ሰዓትና የጋዜጣ አምድ መጠን ይፋ ሆነ። በዚህም በራዲዮ 782.5 ሰዓት እንዲሁም በቴሌቪዥን ደግሞ 570 ሰዓት ለፖለቲካ ፓርቲዎች እና የግል እጩዎች ተዘጋጅቶላቸዋል ተብሏል። የአየር ሰዓቱ በ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ወቅት ከነበረው በ10 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል። በጋዜጦች ደግሞ 576 አምድ መዘጋጀቱ ተነግሯል ። በዛሬው እለት የ7 ኛው ጠቅላላ ምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎች ነፃ የአየር ሰዓት ድልድል ዕጣ አወጣጥ ስነስርዓት እየተካሄ ነው። በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ 24 ራዲዮ ጣቢያዎች፣ 20 ቴሌቪዥን እንዲሁም 6 ጋዜጦች የፖለቲካ ፓርቲዎች እና የግል እጩዎች ፖሊሲያቸውን፣ አላማና ፕሮግራማቸውን ለህዝብ እንዲያስተዋውቁበት መመረጣቸውን
Mar 281 min read


ነገር በነገው ትውልድ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እንዳያሳድር በምን መሳይ አማራጭ ከትምህርት እንዳይርቁ ማድረግ ይቻል ይሆን?
መጋቢት 18/2018 በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው እንደተፈናቀሉ መሆናቸውን መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ በተለይ ተፈናቅለው በየመጠለያዎች የሚገኙ እና የፀጥታ ችግር ባለባቸው አካባቢዎች ህፃናት ለአመታት የት/ቤት ደጃፍ አልረገጡም፡፡ ታዲያ እንዲህ ያለው ነገር በነገው ትውልድ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እንዳያሳድር በምን መሳይ አማራጭ ከትምህርት እንዳይርቁ ማድረግ ይቻል ይሆን? በጦርነት ውስጥ ሆናም ቢሆን በተቻለ መጠን የትምህርት ስርዓት እንዳይጎዳ፣ እንዳይቋረጥ ማድረግ እንችላለን የሚሉት ያነጋገርናቸው የትምህርት ባለሙያዎች ትምህርትን በሬዲዮ እንዲገኙ ማድረግም እንችላለን ሲሉ ምክረ ሀሳባቸውን ይሰጣሉ፡፡ እነዚህ የመፍትሄ ሀሳቦች ከዚህ ቀደም ተማሪዎች ሲማሩበት የነበረውን መንገድ በሙሉ ይተካል ማለት ሳይሆን ልጆቹ ከመስመር እንዳይወጡ በተወሰነ ደ
Mar 271 min read


የታይዋኗ ርዕሠ ከተማ ታይፔ የቀድሞ ከንቲባ በጉቦ ቅሌት የ17 አመታት የእስር ቅጣት ተከናነቡ፡፡
መጋቢት 18/2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች #ታይዋን የታይዋኗ ርዕሠ ከተማ ታይፔ የቀድሞ ከንቲባ በጉቦ ቅሌት የ17 አመታት የእስር ቅጣት ተከናነቡ፡፡ ኮ ዌን ጄ የተባሉት የታይፔ የቀድሞ ከንቲባ ለ17 አመታት እስር ቅጣት የተዳረጉት የ532 ሺህ የአሜሪካ ዶላር የምንዛሪ ግምት ያለው ገንዘብ በጉቦ መቀበላቸው ተረጋግጦባቸው እንደሆነ AFP ፅፏል፡፡ በተሰጣቸው ጉቦ ለውጥ ለሪል ስቴት አልሚዎች ከተፈቀደላቸው በላይ ሰፊ መሬት መምራታቸው ታውቋል፡፡ ግለሰቡ በጠበቆቻቸው አማካይነት ይግባኝ መጠየቃቸው ተጠቅሷል፡፡ ጉዳያቸው በይግባኝ እስኪታይም በዋስ ሆነው ውጤቱን ይጠባበቃሉ ተብሏል፡፡ #አሜሪካ የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን በሰላሙ ጉዳይ ያለ አንዳች ማንገራገር ካልተስማማች ከእስካሁኑም የከፋ ከባድ ድብደባ ይጠብቃታል ሲሉ
Mar 273 min read


በትግራይ ክልል የሚደረገው አጀንዳ የማሰባሰብ ስራን በአዲስ አበባ ከተማ ለማከናወን እቅድ መያዙን የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ተናገረ።
መጋቢት 18/2018 በትግራይ ክልል የሚደረገው አጀንዳ የማሰባሰብ ስራን በአዲስ አበባ ከተማ ለማከናወን እቅድ መያዙን የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ተናገረ። የትግራይ ክልልን የምክክር ሂደት በክልሉ ለማካሄድ አስቻይ ሁኔታ ስለሌለ ምክክሩን በአዲስ አበባ ከተማ ከመጋቢት 23 እስከ 25/2018 ድረስ ምክክሩ ይደረጋል ተብሏል። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ይህንን ያለው የትግራይ ክልልን የምክክር ሂደት በተመለከተ ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ ነው። ኮሚሽኑ የትግራይ ክልልንም እንደሌሎቹ የኢትዮጵያ ክልሎች ሁሉ በሀገራዊ ምክክሩ ለማካተትና ለማሳተፍ በርካታ ጥረቶችን ሲያደርግ መቆየቱን ተናግሯል። በዚህም ኮሚሽኑ የትግራይ ክልል በምክክር ሂደቱ እንዲሳተፍ ከክልሉ ጊዜአዊው አስተዳደር፣ ከፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ከሲቪል ማህበረተሰብ ድርጅቶች፣ ከምሁራን እና
Mar 271 min read


የካንሰር ህሙማን ለህክምና ወደ ውጪ ሀገራት የሚያደርጉትን ጉዞ እና ወጪ ያስቀራል የተባለለት ግዙፍ ሆስፒታል ሊገነባ መሆኑ ተሰማ፡፡
መጋቢት 18/2018 በተለይ የካንሰር ህሙማን ለህክምና ወደ ውጪ ሀገራት የሚያደርጉትን ጉዞ እና ወጪ ያስቀራል የተባለለት ግዙፍ ሆስፒታል ሊገነባ መሆኑ ተሰማ፡፡ ሆስፒታሉን ገንብቶ ለማጠናቀቅ ከ15 ቢሊዮን ብር በላይ እንደሚጠይቅም ተነግሯል። ሆስፒታሉን የሚያስገነባው ማቴዎስ ወንዱ ፋውንዴሽን የተሰኘው በጎ አድራጎት ድርጅት ሲሆን ግንባታውም በመንግስት ተቋማት፣ በበጎ አድራጎት ድርጅቶችና በህዝብ መዋጮ ጭምር በድጋፍ የሚከወን እንደሆነም ሰምተናል። ሆስፒታሉ በተለይ የካንሰር ህመም ላይ ዋነኛው ትኩረቱ አድርጎ የሚሰራ ቢሆንም ለተለያዩ ተላላፊ ላልሆኑ እና ተላላፊ ለሆኑ ህመም ጭምር አገልግሎት እንደሚሰጥ የማቴዎስ ወንዱ ፋውንዴሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ወንዱ በቀለ ነግረውናል። የማቴዎስ ወንዱ ፋውንዴሽን የቦርድ ሊቀመንበር የትናየት አበበ(ዶ/ር) በተለይ
Mar 271 min read


የሀገር ውስጥ ፋብሪካዎችን የማምረት አቅም ለማሳደግ የተሰራው ስራ ውጤት እያመጣ ነው ሲል የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ተናገረ።
መጋቢት 18/2018 የሀገር ውስጥ ፋብሪካዎችን የማምረት አቅም ለማሳደግ የተሰራው ስራ ውጤት እያመጣ ነው ሲል የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ተናገረ። ሚኒስቴሩ እንዳለው የፋብሪካዎቹ አማካይ የማምረት አቅም አሁን ላይ 66.3 በመቶ ደርሷል። ከ8ዓመት በፊት አማካይ የማምረት አቅማቸው 46 በመቶ እንደነበር የሚኒስቴሩ የመንግስት የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ስራ አስፈፃሚ ወይዘሮ አበባ ታመነ ተናግረዋል። ከመሠረተ ልማት እና ጥሬ ዕቃ አቅርቦት እንዲሁም ከመንግስታዊ አገልግሎቶች ጋር የተያያዙ ችግሮች እንዲፈቱላቸው የተደረገው ጥረት የፋብሪካዎቹ የማምረት አቅም እንዲሻሻል ረድቷል ብለዋል። የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ጋር በመተባበር የሀገር ውስጥ ፋብሪካዎችን የስራ ሃደት ከትናንት ጀምሮ የተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ባለሞያዎች ተዘዋውረው እንዲመለከቱ
Mar 271 min read


በሶማሌ ክልል የአቦ ሸማኔ ንግድ የተጧጧፈ ሆኗል ተባለ።
መጋቢት 17/2018 በሶማሌ ክልል የአቦ ሸማኔ ንግድ የተጧጧፈ ሆኗል ተባለ። አቦሸማኔዎች በህገ-ወጥ የዱር እንስሳት አዘዋዋሪዎች ምክንያት የከፋ አደጋ እየደረሰባቸው ነው ተብሏል። በተለይም ግልገሎቹ እንደ ተወለዱ ከእናታቸው ተነጥለውለው ለንግድ ተግባራት እንደሚውሉ ተነግሯል። ይህ ህገ ወጥ ድርጊት በዋናነት የሚፈጸመው በአካባቢው በሚገኙ አርብቶ አደሮች አማካኝነት እንደሆነም የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለስልጣን ተናግሯል። እነዚህ ግልገሎች ገና በጨቅላነታቸው ታድነው ተይዘው ፣ ህገ-ወጥ አዘዋዋሪዎች በ70 እና በ80 የአሜሪካ ዶላር ዋጋ ከአርብቶ አደሮቹ እንደሚረከቧቸው በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ህግ ማስከበር ዴስክ ሀላፊ አቶ ዳንኤል አሰፋ ነግረውናል። ህገ ወጥ የአቦሸማኔ ዝውውሩን እያጧጧፉት ያሉት በዋናነት ተጠቃሚ ሀገራት እንደሆነ የጠቀ
Mar 261 min read


የእስራኤል ጦር ከኢራን ባህር ሀይል ከፍተኛ አዛዦች መካከል አንዱ የነበሩት አል ሬዛ ታንጂ ሲሪን ገደልኩት አለ፡፡
መጋቢት 17/2018 የእስራኤል ጦር ከኢራን ባህር ሀይል ከፍተኛ አዛዦች መካከል አንዱ የነበሩት አል ሬዛ ታንጂ ሲሪን ገደልኩት አለ፡፡ ታንጂ ሲሪ የተገደሉት ኢራን በከፊል ዝግ አድርገው በሰነበተችው የሆርሙዝ ሰርጥ ቅኝት ያደርጉ በነበረበት ወቅት እንደሆነ ቢቢሲ ፅፏል፡፡ ታንጂሲሪ ለሆርሙዝ ሰርጥ መዘጋት ከፍተኛ ድርሻ ከነበራቸው የኢራን የጦር መሪዎች መካከል አንዱ እንደነበሩ የእስራኤሉ የመከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ ተናግረዋል፡፡ ወደ ወር በተቃረበው ጦርነት በአሜሪካ እና እስራኤል ጥምር ድብደባ በርካታ የኢራን ሲቪል እና የጦር መሪዎች መገደላቸው ይነገራል፡፡ ታንጂ ሲሪ በእስራኤል የአየር ጥቃት ተገድለዋል ስለመባሉ ለጊዜው ከኢራን በኩል የተሰማ አስተያየት የለም ተብሏል፡፡ ያም ሆኖ ኢራንን በአሜሪካ እና በእስራኤል ለሚፈፀምባት ድብደባ ምላሽ ከመ
Mar 261 min read


በአዲስ አበባ መንገዶች ከተሰሩበት አላማ ውጪ እየዋሉ መሆኑን የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ተናገረ፡፡
መጋቢት 17/2018 በአዲስ አበባ መንገዶች ከተሰሩበት አላማ ውጪ እየዋሉ መሆኑን የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ተናገረ፡፡ ባለስልጣኑ እንዳለው በኮሪደር ልማቱ ስራ የመኪና ማቆሚያዎች በተለያዩ ስፍራዎች ተገንብተዋል ያለ ሲሆን በከተማው መውጪያ እና መግቢያ አካባቢ ትላልቅ መኪኖች እቃ ጭነው ለረጅም ሰዓት ሲቆሙ እየተመለከትሁኝ ነው ብሏል፡፡ የባለስልጣኑ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ እያሱ ሰለሞን ባለፉት 8 ወራት ውስጥ 111 ኪሎ ሜትር የአስፓልት መንገድ ጥገና መከናወኑን ነግረውናል፡፡ ክረምት እየመጣ መሆኑን ተከትሎ የጎርፍ ስጋ ባለባቸው አካባቢዎች የሚገኙ ድልድዮች፣ የፍሳሽ ማስወገጃ ቱቦዎች ጥገና እየተከናወነ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ አዲስ አበባ ወስጥ መንገዶች በየጊዜው ነው እድሳት የሚደረግላቸው ምክንያቱ ደግሞ ህብረተሰቡ የኔነት ስሜት ኖሮት መ
Mar 261 min read


በአንድ ይዞታ ላይ ሁለት እና ሶስት ካርታ ወይም የይዞታ ማረጋገጫ ለምን ሊወጣ ይችላል?
መጋቢት 17/2018 በአዲስ አበባ ከመሬትና መሬት ነክ ጉዳዮች ጋር በተገናኘ ዛሬም አሁንም ከፍተኛ ቅሬታና የአፈፃፀም ችግር እንዳለ ይሰማል። ከተማ አስተዳደሩ በተለያየ ዙር በሊዝ የጨረታ ቦታዎችን እያወዳደረ ለባለሀብቶች እያስተላለፈ ነው። የተወሰኑ የልማት ተነሺዎችም ሆኑ በጨረታ ከከተማ አስተዳደሩ አሸንፈው የወሰዱ ፤ ቦታ ለማግኘት ከማእከል ከጨረሱ በኋላ የተሰጣቸውን ቦታ ለመቀበል እንደተቸገሩ ሰምተናል። የዚህ ዋነኛ ችግር ደግሞ በተለይ የአርሶ አደር ቦታ ነው ፤ ካሳ አልተሰጠንም አልተወሰደም እና ሌሎች ምክንያቶችም ለከተማ አስተዳደሩ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ራስ ምታት እንደሆነበት ሰምተናል። ለመሆኑ የፕላን ተቃርኖ ያለበት ወይም ለአረንጓዴ ስፍራ ቦታ የተያዘ ቦታ የሆነ አገልግሎት ግንባታ የተፈጸመበት ቦታስ ሊስተካከልና አገልግሎቱ ሊስማማ የ
Mar 261 min read


ጋዜጠኞች ያላግባብ መታፈንና እስርን የመሰለ የሰብአዊ መብት ጥሰት ሲደርስባቸውም በፍርድ ቤት ጭምር ክርክር የሚያደርግ ድርጅት ስራ ጀምሯል፡፡
መጋቢት 17/2018 ጋዜጠኞች ደህንነታቸው ተጠብቆ እንዲሰሩ ፣ የሚድያ ምህዳሩ እንዲሰፋ ፣ ጋዜጠኞች ያላግባብ መታፈንና እስርን የመሰለ የሰብአዊ መብት ጥሰት ሲደርስባቸውም በፍርድ ቤት ጭምር ክርክር የሚያደርግ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት በይፋ ስራ ጀምሯል፡፡ በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ተመዝግቦ በይፋ ትናንት ስራ ጀምሯል የተባለው ሎውየርስ ፎረ ሚዲያ (Lawyers for media) የተሰኘ ስያሜ የተሰጠው ተቋም ነው፡፡ በዩኔስኮ እገዛ በፕሮጀክት ደረጃ የጀመርናቸው ስራዎች ራሱን ችሎ በተቋም ደረጃ በስፋት እየሰራ ይቀጥላል ያሉን የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ድርጅቶች ህብረት ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ መሱድ ገበየሁ ናቸው፡፡ በሁሉም ክልሎች የሚሰሩ የህግ ባለሙያዎች የተካተቱበት ለሚድያው ዘርፍ መጠናከርና የሚያስፈልገው የህግ ድጋፍ የሚሰጥ
Mar 261 min read
ፕሮግራሞች
bottom of page

