top of page

ነገር በነገው ትውልድ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እንዳያሳድር በምን መሳይ አማራጭ ከትምህርት እንዳይርቁ ማድረግ ይቻል ይሆን?

  • Mar 27
  • 1 min read

መጋቢት 18/2018


በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው እንደተፈናቀሉ መሆናቸውን መረጃዎች ያሳያሉ፡፡


በተለይ ተፈናቅለው በየመጠለያዎች የሚገኙ እና የፀጥታ ችግር ባለባቸው አካባቢዎች ህፃናት ለአመታት የት/ቤት ደጃፍ አልረገጡም፡፡


ታዲያ እንዲህ ያለው ነገር በነገው ትውልድ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እንዳያሳድር በምን መሳይ አማራጭ ከትምህርት እንዳይርቁ ማድረግ ይቻል ይሆን?



በጦርነት ውስጥ ሆናም ቢሆን በተቻለ መጠን የትምህርት ስርዓት እንዳይጎዳ፣ እንዳይቋረጥ ማድረግ እንችላለን የሚሉት ያነጋገርናቸው የትምህርት ባለሙያዎች ትምህርትን በሬዲዮ እንዲገኙ ማድረግም እንችላለን ሲሉ ምክረ ሀሳባቸውን ይሰጣሉ፡፡


እነዚህ የመፍትሄ ሀሳቦች ከዚህ ቀደም ተማሪዎች ሲማሩበት የነበረውን መንገድ በሙሉ ይተካል ማለት ሳይሆን ልጆቹ ከመስመር እንዳይወጡ በተወሰነ ደረጃ ሊያግዛቸው እንደሚችልም ይናገራሉ፡፡


ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ…..



ፋሲካ ሙሉወርቅ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


YouTube : https://shorturl.at/18TS1

WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx

X :- https://x.com/shegerfm?s=2

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page