top of page

የሀገር ውስጥ ፋብሪካዎች አሁን ላይ ከ45 በመቶ በላይ የሚሆነውን የሀገር ውስጥ ምርት ፍላጎት እየሸፈኑ ነው ተባለ።

  • Mar 28
  • 1 min read

መጋቢት 19/2018


የሀገር ውስጥ ፋብሪካዎች አሁን ላይ ከ45 በመቶ በላይ የሚሆነውን የሀገር ውስጥ ምርት ፍላጎት እየሸፈኑ ነው ተባለ።


እንደ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር መረጃ የሀገር ውስጥ ፋብሪካዎች ከውጪ ይገቡ የነበሩትን ምርቶች እዚሁ በማምረት በከፊልም ቢሆን ፍላጎቱን እየሸፈኑ ነው።


በዚህም ፋብሪካዎቹ ምርቶችን ወደ ተለያዩ ሀገራት በመላክ የውጭ ምንዛሪ ከማስገኘት ባሻገር የሀገር ውስጥ ፍላጎትን ማሟላት ላይም ጥሩ ስራ እየሰሩ እንደሚገኙ መረዳት ይቻላል ሲሉ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ድኤታ ታረቀኝ ቡሉልታ ተናግረዋል።

ከአገልግሎት አሰጣጥ ፣ ከመሠረተ ልማት እና ብድር አቅርቦት ጋር የተገናኙ የፋብሪካዎቹ ችግሮች እንዲፈቱ የተደረገው ጥረት ውጤቶቹ እንዲገኙ አግዘዋል ብለዋል።


የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ጋር በመተባበር በአዲስ አበባና አካባቢዋ ያሉ ፋብሪካዎችን የስራ እንቅስቃሴ የተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ባለሞያዎች እንዲመለከቱ አድርገዋል።


ፋብሪካዎቹ በጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ፣ በቆዳ ፣ በምግብ ማቀነባበር ፣ በኤሌክትሮኒክስ ስራ እና በመሣሠሉት የተሠማሩ ናቸው።


ያሉባቸው ችግሮች እንዲፈቱላቸው በመንግስት ዕገዛ እንደተደረገላቸው ጠቅሰው አሁንም ያለባቸውም መፍትሔ እንዲያገኙ ለመንግሥት ጥያቄ አቅርበዋል።


ንጋቱ ረጋሳ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


YouTube : https://shorturl.at/18TS1

WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx

X :- https://x.com/shegerfm?s=2

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page