top of page

የሀገር ውስጥ ፋብሪካዎችን የማምረት አቅም ለማሳደግ የተሰራው ስራ ውጤት እያመጣ ነው ሲል የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ተናገረ።

  • Mar 27
  • 1 min read

መጋቢት 18/2018


የሀገር ውስጥ ፋብሪካዎችን የማምረት አቅም ለማሳደግ የተሰራው ስራ ውጤት እያመጣ ነው ሲል የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ተናገረ።


ሚኒስቴሩ እንዳለው የፋብሪካዎቹ አማካይ የማምረት አቅም አሁን ላይ 66.3 በመቶ ደርሷል።


ከ8ዓመት በፊት አማካይ የማምረት አቅማቸው 46 በመቶ እንደነበር የሚኒስቴሩ የመንግስት የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ስራ አስፈፃሚ ወይዘሮ አበባ ታመነ ተናግረዋል።



ከመሠረተ ልማት እና ጥሬ ዕቃ አቅርቦት እንዲሁም ከመንግስታዊ አገልግሎቶች ጋር የተያያዙ ችግሮች እንዲፈቱላቸው የተደረገው ጥረት የፋብሪካዎቹ የማምረት አቅም እንዲሻሻል ረድቷል ብለዋል።


የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ጋር በመተባበር የሀገር ውስጥ ፋብሪካዎችን የስራ ሃደት ከትናንት ጀምሮ የተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ባለሞያዎች ተዘዋውረው እንዲመለከቱ እያደረገ ይገኛል።


በመገናኛ ብዙሃኑ ባለሞያዎች ከተጎበኙ ፋብሪካዎች አንዱ ቡራዩ የሚገኘው ቦይዝ ፉድ ኮምፕሌክስ ነው።


የፋብሪካው ባለቤት እና ስራ አስኪያጅ አቶ ዮሴፍ ታደሠ ችግሮች እንዲፈቱ በመንግሥት በተደረገ ድጋፍ በጥሩ የማምረት ሂደት ላይ እንገኛለን ብለዋል።


ከብድርና የጥሬ ዕቃ አቅርቦት ጋር የተገናኙ ችግሮች ግን አሁንም መፍትሔ እንደሚሹ ተናግረዋል።


ንጋቱ ረጋሳ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


YouTube : https://shorturl.at/18TS1

WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx

X :- https://x.com/shegerfm?s=2

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page