top of page


የኢራን አዲሱ ጠቅላይ መሪ አያቶላህ ሞጅታባ ሐሚኒ አሜሪካ እና እስራኤልን ሳናንበረክክ የተኩስ አቁም አናደርግም ማለታቸው ተሰማ፡፡
መጋቢት 10/2018 - አለም ዓቀፍ ወሬዎች #ኢራን የኢራን አዲሱ ጠቅላይ መሪ አያቶላህ ሞጅታባ ሐሚኒ አሜሪካ እና እስራኤልን ሳናንበረክክ የተኩስ አቁም አናደርግም ማለታቸው ተሰማ፡፡ ሞጅታባ ሐሚኒ ምንም ዓይነት የተኩስ አቁም አናደርግም ያሉት የመጀመሪያቸው በሆነ ፖሊሲ ነክ ምክክር በመሩበት አጋጣሚ እንደሆነ በስም ያልተጠቀሱ የኢራን ሹም መናገራቸውን ሬውተርስ ፅፏል፡፡ በአሜሪካ እና በእስራኤል ላይ የኢራን አፀፋ ከባድ እና የከፋ ይሆናል ሲሉ ሞጅታባ ዝተዋል ተብሏል፡፡ አዲሱ የኢራን ጠቅላይ መሪ አሜሪካ እና እስራኤልን ገና የእምብርክክ እናስኬዳቸዋለን ማለታቸውን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ሹም ተናግረዋል፡፡ የሞጅታባ ሐሚኒ ጠንከር ያለ አስተያየት የተሰነዘረው በውጥረት ማርገቢያ ጉዳይ ለቀረበላቸው ሀሳብ እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡ በኢራን የጠቅላይ መሪነቱ ሹመት
Mar 192 min read


በቤት ሰራተኞች እና በአሰሪዎች መካከል ያለውን ግንኙነት ህጋዊ መስመር የሚያስይዝ አዲስ ደንብ እየተዘጋጀ ነዉ ተባለ
መጋቢት 10/2018 በቤት ሰራተኞች እና በአሰሪዎች መካከል ያለውን ግንኙነት ህጋዊ መስመር የሚያስይዝ እና የህገ-ወጥ ደላሎችን ጣልቃ ገብነት የሚገታ አዲስ ደንብ እየተዘጋጀ ነዉ ተባለ። በስራና ክህሎት ሚንስቴር እየተዘጋጀ ያለው ይህ ደንብ፣ በቤት ሰራተኞች ላይ የሚደርሱ አካላዊና ስነ-ልቦናዊ ጥቃቶችን ለመከላከል እንዲሁም የአሰሪዎችን መብትና ደህንነት ለማስጠበቅ ያለመ መሆኑ ተነግረሯል። ብዙ ጊዜ የቤት ሰራተኛ ሲባል ሰዉ የሚገነዘበዉ 70 በመቶ የሚሆኑትን ሴት የቤት ሰራተኞችን ብቻ ቢሆንም በዚህ ደንብ ግን አትክልተኛ፣ ሹፌሮችና ሌሎችም በመኖሪያ ቤት ተቀጥረዉ የሚሰሩ ሰራተኛችን ጭምር እንደሚያካትት ተጠቁሟል። በሚኒስቴሩ የኢንዱስትሪ ግንኙነትና የስራ ሁኔታዎች ቁጥጥር መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ጥዑመዝጊ በርሔ አዲሱ ደንብ በቀጣሪም በተቀጣሪም በኩል
Mar 192 min read


ካንሰርን ለማከም ጥቅም ላይ የሚውልና ሌሎች በሀገር ውስጥ ተመርተው የሚያውቁ መድሃኒቶችን ለማምረት የአዋጭነት ጥራት ተጠናቅቆ ሙከራ መጀመሩ ተሰማ ፡፡
የመጋቢት 10/2018 ካንሰርን ለማከም ጥቅም ላይ የሚውልና ሌሎች በሀገር ውስጥ ተመርተው የሚያውቁ መድሃኒቶችን ለማምረት የአዋጭነት ጥራት ተጠናቅቆ ሙከራ መጀመሩ ተሰማ ፡፡ የአርማወርሀሰን የምርምር ኢንስቲትዩት ይህ እንዲሳካ ጥረት እያደረኩ ነው ብሏል፡፡ አምራቾች በካንሰር መድሀኒቶች ላይ የአዋጭነት ጥናት አስጠንተው በፕሮጀክት ደረጃ በቂሊንጦ ኢንደስትሪ ፓርክ ስራዎች ስለመጀመራቸውም ተነግሯል። ይህን የሰማነው ከአርማወር ሀንሰን የምርምር ኢኒስቲትዩት ነው። ኢኒስቲትዩቱ እንደ ካንሰርን ለማከም የሚያገለግሉ ከውጭ የሚገቡ መድኃኒቶች በቅርብ ጊዜ ውስጥ በሀገር ውስጥ እንዲመረቱ የበኩሉን ድርሻ እንደሚወጣ ተናግሯል። የካንሰርና ከኩላሊት ንቅለ ተከላ በኋላ ለረዥም ጊዜ የሚወሰዱ መድሃኒቶች ኢትዮጵያ ከውጭ ሀገራት በውድ ዋጋ ከምታስገባቸው መድሀኒቶች መካከል
Mar 191 min read


የመድሃኒትና የህክምና እቃዎችን የሚያመርቱ ከውጭ ግብአቶችን ለማስመጣት የመጫኛ ዋጋው ብቻ በኮንቴነር ከ7 ሺህ ዶላር በላይ እንደጨመረባቸው ተናገሩ፡፡
መጋቢት 9/2018 የመድሃኒትና የህክምና እቃዎችን የሚያመርቱ ፋብሪካዎች ከውጭ ግብአቶችን ለማስመጣት የመጫኛ ዋጋው ብቻ በኮንቴነር ከ7,000 ዶላር በላይ እንደጨመረባቸው ተናገሩ፡፡ የዋጋ ጭማሪው በመካከለኛው ምስራቅ የተፈጠረው ጦርነት ባስከተለው የነዳጅ ውድነት እና እጥረት ምክንያት የተከሰተ ነው ተብሏል፡፡ አምራቾቹም መንግስት ድጋፍ እንዲያደርግላቸው ጠይቀዋል፡፡ ለአብነት የህክምና ማምረቻ ግብአቶችን ከህንድ ሀገር ለማስመጣት ለአንድ ኮንቴነር 3800 ዶላር ይጠየቅ የነበረው ክፍያ አሁን ላይ 10,800 ዶላር መሆኑን የኢትዮጵያ መድሀኒትና መገልገያ መሳሪያዎች አምራች ዘርፍ ማህበር ነግሮናል። ማህበሩ በመካከለኛው ምስራቅ የተፈጠረው ቀውስ የሚቀጥል ከሆነ ለትራንስፖርት ከሚጠየቀው ክፍያ መናር ባሻገር የኮንቴነር እና የማጓጓዣ እጥረት
Mar 181 min read


ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የጥቃቅን፤ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የብድር ፍላጎት ወደ አንድ ትሪሊየን ብር እንደሚጠጋ ተነግሯል።
መጋቢት 9/2018 ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የጥቃቅን፤ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የብድር ፍላጎት ወደ አንድ ትሪሊየን ብር እንደሚጠጋ ተነግሯል። ፍላጎታቸው በሀገሪቱ ካለው አጠቃላይ ገንዘብ ትልቁን ድርሻ የሚይዝ እንደሆነ ተጠቅሷል። ባንኮችን እና የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማትን በማሳመን ይህን ከፍተኛ የሆነ የብድር ፍላጎታቸውን ለማማሏት ኢንተርፕራይዞቹ ብዙ መስራት ይጠበቅባቸዋል ተብሏል። ኢትዮጵያ ውስጥ ሁለት ሚሊየን የሚጠጉ ጥቃቅን፤ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች እንዳሉ የዓለም ባንክ መረጃ ያሳያል። የእነዚህ ኢንተርፕራይዞች አጠቃላይ የፋይናንስ ፍላጎት አንድ ትሪሊየን ብር እንደሚጠጋ የባንክ ባለሞያ የሆኑት አቶ ቴዎድሮስ ሃይሌ የባንኩን መረጃ ጠቅሰው ተናግረዋል። መደበኛ ባልሆነ የንግድ ስራ ከተሰማሩት ጋር ሲደመሩ ደግሞ የ
Mar 182 min read


የኢትዮጵያ ባንኮች አቅም እንዲኖራቸው እና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ይዋሃዱ ዘንድ ተመክረዋል።
መጋቢት 9/2018 የኢትዮጵያ ባንኮች አቅም እንዲኖራቸው እና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ይዋሃዱ ዘንድ ተመክረዋል። ግን ባንኮች እንዴት በመርጅ ኤንድ አክዩዜሽን ይዋሀዱ የሚለውን መስመር ለማሳየት ብሔራዊ ባንክ መንገድ መለየቱ ተሰምቷል። አንዱ ባንክ እንዴት ሌላኛውን ይግዛው? የሚል የህግ ማዕቀፍ እየተዘጋጀ እንደሆነ የብሔራዊ ባንክ ተናግሯል። ይህም የሐገር ቤት ንግድ ባንኮች አቅም እንዲኖራቸው እና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ፤ አንዱ ባንክ እንዴት ሌላኛውን መግዛት እንደሚችል የሚያግዝ የህግ ማዕቀፍ ነው። በዚህ ጉዳይ የጠይቅናቸው የብሔራዊ ባንክ ገዥ ዶ/ር እዮብ ተካልኝ ይህ እየተዘጋጀ ያለው መንገድ ባንኮች እንዲዋሀዱ ይረዳቸዋል ብለዋል። በተያያዘ ወሬ ፤ በኢትዮጵያ የውጭ ባንኮች በተለያየ አማራጭ ገብተው እንዲሰሩ ከተፈቀደ በኋላ አንዳንድ የውጭ ባንኮች የሀገር ው
Mar 181 min read


በልዩ የኢኮኖሚ ዞን ውስጥ ገብተው እንዲሰሩ የሚፈቀድላቸው ባንኮች የውጪ ምንዛሪ አገልግሎት የመስጠት ግዴታ እንዳለባቸው ተነገረ።
መጋቢት 9/2018 በልዩ የኢኮኖሚ ዞን ውስጥ ገብተው እንዲሰሩ የሚፈቀድላቸው ባንኮች የውጪ ምንዛሪ አገልግሎት የመስጠት ግዴታ እንዳለባቸው ተነገረ። የልዩ ኢኮኖሚ ዞን አዋጅ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፀድቆ ስራ ላይ መዋሉ ይታወቃል። አዋጁ ከደነገጋቸው ግዴታዎች አንዱ በልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ውስጥ በሚቋቋም የአንድ መስኮት አገልግሎት ባንኮችም ገብተው አገልግሎት መስጠት አለባቸው የሚለው እንደሆነ ተጠቅሷል። አሁን ላይ በኢትዮጵያ 32 ባንኮች እንዳሉ ያመለከተው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ከእነዚህ መካከል ከ15 እስከ 20 የሚሆኑት በልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ገብተው ለመስራት የሚያስችላቸውን ፍቃድ ይወስዳሉ ተብሎ ይጠበቃል ብሏል። የዉጪ ባንኮችም ፍቃድ ይወስዳሉ ተብሎ እንደሚጠቅ ተናግሯል። ከአዋጁ መወጣት በፊት በልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች በዋናነት አገልግሎት ሲሰጥ
Mar 181 min read


ላይፍቦይ፣ ኦሞ፣ ክኖር፣ ሰንላይት እና ሲግናልን የሚያርተው የኒሊቨር በኢትዮጵያ ገበያ እየቀናው እንደሆነ ተነገረ፡፡
መጋቢት 9/2018 ላይፍቦይ፣ ኦሞ፣ ክኖር፣ ሰንላይት እና ሲግናልን የሚያርተው የኒሊቨር በኢትዮጵያ ገበያ እየቀናው እንደሆነ ተነገረ፡፡ ኩባንያው በዓመት 1.4 ቢሊዮን የክኖር (Knorr) እንኳሮችን ለገበያ አንደሚያቀርብ ተናግሯል፡፡ በተጨማሪም ኩባንያው በየወሩ 12 ሚሊዮን ሳሙና አንደሚሸጥ፣ በየዓመቱ ከሁለት ቢሊዮን ብር በላይ ግብር አንደሚከፍል አስረድቷል፡፡ የኒሊቨር ኢትዮጵያ በሲግናል አማካኝነት ከኢትዮጵያ የጥርስ ህክምና ባለሙያዎች ማህበር ጋር በመተባበር ዛሬ የአለም የአፍና ጥርስ ጤና ቀን በኢትዮጵያ አክብሯል፡፡ በዝግጅቱም የጥርስ ሕክምና ባለሙያዎችና በጎ ፈቃደኞች፣ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን የማህበረሰብ ከፍሎች ጨምሮ፣ ሰፈው ማኅበረሰብ የተሻለ የአፍ ጤና ግንዛቤ እንዲያገኝ ለማገዝ ትምህርቶችን፣ የምርመራ አገልግሎቶችን እና የግንዛቤ ማስጨ
Mar 181 min read


የእስራኤሉ የመከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ የኢራኑን የደህንነት ሚኒስትር ኢስማኢል ካቲብንም ገደልነው አሉ፡፡
መጋቢት 9/2018 የእስራኤሉ የመከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ የኢራኑን የደህንነት ሚኒስትር ኢስማኢል ካቲብንም ገደልነው አሉ፡፡ ቀደም ሲል እስራኤል የኢራን የደህንነት ምክር ቤት ሰብሳቢ የነበሩትን ዓሊ ላርጃኒን መግደሏን ቢቢሲ አስታውሷል፡፡ የላርጃኒን መገደል የኢራን ሹሞችም አረጋግጠዋል፡፡ ስለ ኢስማኢል ካቲብ መገደል ግን የሰጡት ማረጋገጫም ይሁን ማስተባበያ የለም፡፡ በጦርነቱ መጀመሪያ በአሜሪካ እና በእስራኤል ጣምራ ድብደባ የቀድሞው የኢራን ጠቅላይ መሪ አያቶላህ ዓሊ ሐሚኒ አና ሌሎች ከፍተኛ ሃላፊዎች መገደላቸው ይታወቃል፡፡ የኢራን ባለስልጣናት በመሪዎቻችን ላይ የተፈፀመውን ግድያ እንበቀላለን እያሉ ነው፡፡ የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… Website፡ https://www.shegerfm.com/ YouTube : https:/
Mar 181 min read


የፕላስቲክ ቆሻሻን መልሰው ጥቅም ላይ ለሚያውሉ የገንዘብ እርዳታ ሊደረግላቸው ነው፡፡
መጋቢት 9/2018 የፕላስቲክ ቆሻሻን መልሰው ጥቅም ላይ ለሚያውሉ የገንዘብ እርዳታ ሊደረግላቸው ነው፡፡ ቆሻሻን መልሶ ጥቅም ላይ በማዋሉ ዘርፍ ሴቶች እንዲሰማሩ ይበረታታሉ ብሏል፡፡ አለም አቀፍ የመልሶ ጥቅም ላይ የማዋል ቀንን ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ እያከበረች ነው። በየዓመቱ መጋቢት 9 ቀን ወይም እንደ እ.ኤ.አ ማርች 18 ቀን በአለም አቀፍ ደረጃ የሚከበረውን የመልሶ ጥቅም ላይ የማዋል ቀን ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ እየተከበረ መሆኑን ሰምተናል። "ቆሻሻ መልሶ ጥቅም ላይ መዋል የሚችል ሀብት ነው" በሚል መሪ ቃል እየተከበረ የሚገኘውን አለም አቀፍ ኩነትን መሰረት በማድረግ "ቆሻሻን ወደ ዕድል እንቀይር ሴቶችንና ወጣቶችን በኢኮኖሚ እናብቃ" በሚል ሀሳብም በአዲስ አበባ እየተከበረ ይገኛል። የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ፔትኮ ኢትዮጵያ ከተባለ
Mar 181 min read


ብሔራዊ ባንክ ይፋ ባደረገው የፋይናንስ መረጋጋትን በሚያመለክተው ሪፖርቱ ከፍተኛ ገንዘብ የቆጠቡ 10 ደንበኞቻቸው ገንዘባቸውን ቢያወጡ የኪሳራ አደጋ የሚደርስባቸው ባንኮች ቁጥር መቀነሱን አሳየ፡፡
መጋቢት 9/2018 ብሔራዊ ባንክ ይፋ ባደረገው የፋይናንስ መረጋጋትን በሚያመለክተው ሪፖርቱ ከፍተኛ ገንዘብ የቆጠቡ 10 ደንበኞቻቸው ገንዘባቸውን ቢያወጡ የኪሳራ አደጋ የሚደርስባቸው ባንኮች ቁጥር መቀነሱን አሳየ፡፡ በ2024/2025 አስር በመቶ ቆጣቢዎቻቸው ገንዘባቸውን ቢያወጡ 20 ባንኮች ኪሳራ ያጋጥማቸው ነበር ተብሏል፡፡ አሁን ቁጥሩ ወደ 16 ባንኮች ዝቅ ብሏል ይላል ሪፖርቱ፡፡ 62 ገፅ ባለው የባንኩ ሪፖርት ሌሎች የፋይናንስ ተቋማትና የአሰራር ሥርዓቱን የተመለከቱ ነጥቦች በዝርዝር ተካተዋል፡፡ ከመካከሉ በዲጂታል መንገድ የሚገላበጠው ገንዘብ እጥፍ በሚባል ደረጃ አድርጎ 18 ነጥብ 5 ትሪሊዮን ብር መድረሱን የሚያሳየው ይገኝበታል፡፡ ይህም የፋይናንስ አካታችነትን ውጤታማነት ያሳያል ቢባልም በፍጥነት አድጓል የተባለው የዲጂታል የፋይናንስ ስርዓቱ ለሳይ
Mar 182 min read


የህክምና አገልግሎትን ያሻሽላሉ የተባሉ ቴክኖሎጂዎችን የሚያቀርቡ 8 ሀገራት ተቋሞቻቸውን የሚያሳትፉበት ዓለም አቀፍ ጉባኤ ሊካሄድ ነው።
መጋቢት 9/2018 የህክምናውን ዘርፍ ያሳድጋሉ፣ የህክምና አገልግሎትን ያሻሽላሉ የተባሉ ቴክኖሎጂዎችን እና መፍትሄዎችን የሚያቀርቡ ከተለያዩ 8 ሀገራት ተቋሞቻቸውን የሚያሳትፉበት ዓለም አቀፍ ጉባኤ ሊካሄድ ነው። ከ10ኛው ኢትዮ ኸልዝ ጉባኤ ጎን ለጎን 2ኛው የሀገር ውስጥ የህክምና ግብዓት ምርትና ፈጠራዎች ኤግዚቢሽን ከመጋቢት 24 እስከ 26/2018 ዓ.ም በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ሴንተር ይካሄዳል ተብሏል። ኤግዚቢሽኑ የሀገር ውስጥ የህክምና መሣሪያዎች፣ የመድኃኒት አምራቾች እና የጤና ቴክኖሎጂ ፈጠራዎችን ለማበረታታትና ለገበያ ለማቅረብ የሚረዳ መሆኑም ተነግሯል። በተጨማሪም የሀገር ውስጥ አምራቾች ከዓለም አቀፍ አምራቾች ጋር እንዲተሳሰሩ፣ አዳዲስ የፈጠራ ስራዎቻቸውን እንዲያስተዋውቁ እና በዘርፉ ካሉ ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን የንግድ ተስስ
Mar 181 min read


በሚቀጥሉት 4 ዓመታት ውስጥ 300 ሚሊዮን ዶላር ብድር ለአነስተኛ ማሳ ላላቸው ገበሬዎች ሊቀርብ መሆኑን ተነገረ፡፡
መጋቢት 9/2018 በሚቀጥሉት 4 ዓመታት ውስጥ 300 ሚሊዮን ዶላር ብድር ለአነስተኛ ማሳ ላላቸው ገበሬዎች ሊቀርብ መሆኑን ተነገረ፡፡ ይህ የሰማነው የኢትዮጵያ ግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን እና ለእርሻ ድርጅት ባደረጉት አብሮ የመስራት ስምምነት ላይ ነው፡፡ ለእርሻ ደርጅት በሚቀጥሉት 4 ዓመታት አነስተኛ ማሳ ላላቸው ገበሬዎች ብድር ለማመቻቸት አቅዶ እየሰራ መሆኑን የተናገረ ሲሆን ከዚህ በፊት በሙከራ ደረጃ በሰራው ስራ ገበሬዎች ውጤታማ መሆናቸውን ተጠቅሷል፡፡ የለእርሻ ድርጅት ስራ አስፈፃሚ አቶ አብርሃም እንድርያስ በዚህ ዓመት ብቻ ለ65 ሺህ ገበሬዎች ብድር ለማቅረብ እቅድ መያዛቸውን የሚናገሩ ሲሆን ለስራውም ከተለያዩ ባንኮች ጋር እንደሚሰሩም አስረድተዋል፡፡ በሙከራ የስራ ወቅት ገበሬው በትክክል የሚፈልገው ብድር ከተሰጠው ያለምንም ችግር ብድሩን መክፈ
Mar 181 min read


በኢትዮጵያ የፋይናንስ ተቋማት የሚገላበጠው አብዛኛው ገንዘብ ወይም ከ73 በመቶ በላዩ የሚዟዟረው በዲጂታል መንገድ ነው፡፡
መጋቢት 8/2018 በኢትዮጵያ የፋይናንስ ተቋማት የሚገላበጠው አብዛኛው ገንዘብ ወይም ከ73 በመቶ በላዩ የሚዟዟረው በዲጂታል መንገድ ነው፡፡ በተያዘው የበጀት ዓመት በ6ት ወራት ውስጥ ብቻ 14.56 ትሪሊዮን ብር በዲጂታል መንገድ ተገላብጧል፡፡ ይህ በዲጂታል ገንዘብ ማስተላለፍ ጊዜን የሚቆጥብ፣ ምቹ መሆኑ ቢጠቀስም የአገልግሎት ክፍያውና ሌሎች ተቆራጮች መኖርና ለአጭበርባሪዎች የተጋለጠ ነው በሚልም ይወቀሳል፡ መንግስታዊ ተቋማት ለሚሰጡት አገልግሎት ክፍያቸውን ወደ ድርጅት ባንኪንግ ማዞራቸውን ተከትሎ ከማህበረሰቡ ለአገልግሎት እየተባለ የሚቆረጠው ገንዘብ እየበዛ መጥቷል፡፡ ደመወዝተኛውም ይሁን በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች ለተለያዩ የክፍያ ስርዓቶች የሚያደርጉት የገንዘብ ልውውጥ ተደራራቢ ታክስ እንዲከፍሉ አያደርግም? በጉዳዩ ላይ
Mar 171 min read


ለሀገሪቱ ዱር እንስሳት ጥበቃና ከለላ ጠያቂውና ጠባቂው የት አለ?
መጋቢት 8/2018 ሰሞኑንን በአርባ ምንጭ 11 ሜትር የሚረዝም እባብ መግደላችን ይታወቅልን ያሉ ሰዎች ከሞተው እባብ ጋር ፎቶ ተነስተው በየማህበራዊ ሚዲያው ታይተዋል፡፡ የቤት እንሰሳትን አጠቁ፣ የህዝብም ስጋት ሆነዋል እየተባለ፤ ሌላም ምክንያት እየተሰጠ የዱር እንስሳት ይገደላሉ፡፡ ግን ሀገሪቱ ለዱር እንስሳት ጥበቃና ከለላ እንድትሰጥ ህግ ያስገድዳታል፡፡ ታዲያ ጠያቂውና ጠባቂው የት አለ? ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ….. ቴዎድሮስ ወርቁ
Mar 171 min read


''የኢራኑን የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት ሀላፊ ዓሊ ላርጃኒን ገድለነዋል'' እስራኤል
መጋቢት 8/2018 የእስራኤሉ የመከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ የኢራኑን የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት ሀላፊ ዓሊ ላርጃኒን ገድለነዋል አሉ፡፡ ካትዝ እንደተናገሩት ላርጃኒ የተገደሉት እስራኤል ትናንት ለዛሬ አጥቢያ ኢራን ውስጥ በፈፀመችው ድብደባ ነው፡፡ ዓሊ ላርጃኒ ከሁለት ሳምንታት በፊት በአሜሪካ እና በእስራኤል ጣምራ ጥቃት የተገደሉትን የቀድሞውን ጠቅላይ መሪ አያቶላ ዓሊ ሐሚኒን ለመተካት በእጩነት ከቀረቡት አንዱ ነበሩ፡፡ አባታቸውን በመወከል በጠቅላይ መሪነት የተመረጡት ሞጅታባ ሐሚኒ መሆናቸው ይታወቃል፡፡ ዓሊ ላርጃኒ በእስራኤል ጥቃት ተገድለዋል ስለመባሉ እስካሁን ከኢራን በኩል ማረጋገጫም ይሁን ማስተባበያ እንዳልተሰጠ ሬውተርስ ፅፏል፡፡
Mar 171 min read


በክልል እና በፌዴራል ደረጃ ያሉ ሁሉም የመንግስትና የፕሮጀክት ተሽከርካሪዎች ሙሉ በሙሉ ወደ ኤሌክትሪክ እንዲዞሩ የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር የትብብር ጥሪ አቀረበ፡፡
መጋቢት 8/2018 በክልል እና በፌዴራል ደረጃ ያሉ ሁሉም የመንግስትና የፕሮጀክት ተሽከርካሪዎች ሙሉ በሙሉ ወደ ኤሌክትሪክ እንዲዞሩ የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር የትብብር ጥሪ አቀረበ፡፡ አውቶብሶችን፣ ባቡርንና ሌሎች የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎቶችን በስፋትና በአግባቡ መጠቀም፤ አገልግሎቱም በወጣለት ታሪፍና መርሃ-ግብር ያለ መቆራረጥ እንዲሰጥ ሚኒስቴር መ/ቤቱ ጠይቋል፡፡ የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር "የኢትዮጵያን የትራንስፖርት ዘርፍ ወደ ኤሌክትሪክና የተፈጥሮ ጋዝ የማሸጋገር እና የነዳጅ ቁጠባ ሀገራዊ ጥሪ" በሚል ርዕስ መግለጫ አውጥቷል፡፡ በአሁኑ ወቅት በመካከለኛው ምስራቅ በተከሰተው ጦርነት ምክንያት የዓለም የነዳጅ ገበያ ከፍተኛ ጭማሪ እያሳየ ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድም በትናትናው ዕለት ባወጡት መግለጫ ‘’ነዳጅን
Mar 171 min read


የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የአሜሪካ ዜግነት ያላቸው ትውልደ ኢትዮጵያዊያን መክፈል የሚጠበቅባቸው የቅጣት ገንዘብ ላይ ምሕረት ማድረጉን ተናገረ።
መጋቢት 8/2018 የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የአሜሪካ ዜግነት ያላቸው ትውልደ ኢትዮጵያዊያን መክፈል የሚጠበቅባቸው የቅጣት ገንዘብ ላይ ምሕረት ማድረጉን ተናገረ። ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ከተፈቀደላቸው ጊዜ በላይ በተለያየ ምክንያት የቆዩ ሰዎች ከቪዛ ጊዜ በላይ ለቆዩበት በየቀኑ በዶላር የሚሰላ ቅጣት ይጣልባቸዋል። የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት እንዳለው ለገንዘብ መቀጮ የተዳረጉ የአሜሪካ ዜግነት ያላቸው ትውልደ ኢትዮጵያዊያኑ ገንዘቡን የመክፈል አቅም እንደሌላቸው ጠቅሰው ቅጣቱ እንዲነሳላቸው ጥያቄ አቅርበዋል ብሏል። በጥያቄው መሰረት ጉዳዩን ተመልክቼዋለው ያለው ተቋሙ ከ18 ዓመት በታች ለሆኑ ቅጣቱ ሙሉ ለሙሉ ተነስቶላቸዋል፤ከ18 ዓመት በላይ ለሆኑ ደግሞ ከቅጣቱ ግማሹን እንዲከፍሉ ወስኛለሁ ብሏል። ይህ በትውልድ ኢትዮጵያዊ፣በዜግነት አሜሪካዊ ለ
Mar 171 min read


በጋሞ ዞን በየመሬት መንሸራተት አደጋ መሞታቸው ከተረጋገጡ 125 ሰዎች አስክሬናቸው የተገኘው የ81 ሰዎች ብቻ ነው ተባለ፡፡
መጋቢት 7/2018 በጋሞ ዞን ከሳምንት በፊት በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ መሞታቸው ከተረጋገጡ 125 ሰዎች እስካሁን አስከሬናቸው የተገኘው የ81 ሰዎች ብቻ ነው ተባለ፡፡ የቀሪዎቹን አስከሬን ለማውጣት ሲደረግ የቆየው በቁፋሮ የታገዘ የማፈላለግ ስራም እንዲቆም መደረጉን ሰምተናል፡፡ ይህን ያለው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ነው። እንደ ቢሮው መረጃ ከሆነ አስክሬን የማፈላለግ ስራው ቆሞ የ44 ሰዎች አስከሬን አደጋው በተከሰተበት በዚያው ስፍራ የቀብር ቦታው ሆኖ እንዲቀጥል ተወስኗል ተብሏል፡፡ እዚህ ውሳኔ ላይ የተደረሰው አስከሬኑ 7 ቀን አልፎታል በሚል ነው፡፡ በአደጋው ምክንያትም ከ16 ሺህ በላይ ሰዎች ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸውንም የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት ሃላፊ አቶ ኃይለማርያም ተ
Mar 161 min read


በኢትዮጵያ የኦዲት ስራ በዝቅተኛ ዋጋ የሚከወን እና ጥራቱን ያልጠበቀ በመሆኑ በገበያው ችግር እየፈጠረ ነው ተብሏል።
መጋቢት 7/2018 በሀገር የፋይናንስ ሥርዓት ከሚረበሹበት፤ ከሚታመሙበት ጉዳዮች መካከል አንደኛው የተዝረከረ የሂሳብ አያያዝና ጥራት የሌለው ጥንቅቅ ያላለ የኦዲት ሪፖርት ነው ። የኦዲት ሪፖርት ጥራቱ የደረጃውን ጠብቆ ካልተሰራ ዞሮ ዞሮ የሕዝብ ጥቅም ያለባቸውን ተቋሞች መነካካቱ አይቀርም። በፋይናንስ ሥርዓት በባንክ ፤ ማይክሮ ፋይናንስ ፤ኢንሹራንስና ሌላውም የሚደረገው የኦዲት ስራ የህዝብ ጥቅም የሀገርን ኢኮኖሚ በአንድም ሆነ በሌላ ስለሚነካ ከፍተኛ ጥንቃቄ መደረግ እንዳለበት ባለሙያዎች ይመከራሉ። በኢትዮጵያ የኦዲት ስራ በዝቅተኛ ዋጋ የሚከወን እና ጥራቱን ያልጠበቀ በመሆኑ በገበያው ችግር እየፈጠረ ነው ተብሏል። በዚህም ምክንያት ምክንያታዊ የኦዲት ክፍያ ስራ ላይ እንዲውል ያግዛል የተባለ አዲስ መመሪያ መውጣቱ ተሰምቷል፡፡ የኦዲት ስራ ደረጃው ዝቅ
Mar 161 min read


ከአዲስ አበባ ከተማ መሬት 52 በመቶው ለመንገድ፤ ለወንዝ ዳርቻ እና ለአረንጓዴ ልማት የተያዘ ነው ተብሏል።
መጋቢት 7/2018 ከአዲስ አበባ ከተማ መሬት 52 በመቶው ለመንገድ፤ ለወንዝ ዳርቻ እና ለአረንጓዴ ልማት የተያዘ ነው ተብሏል። ለመኖሪያ እንዲሁም ለመስሪና ማምረቻ ሊውል የሚችለው የከተማዋ መሬት 48 በመቶ ብቻ እንደሆነ የከተማ ልማት ባለሞያው አቶ ሢሣይ ዘነበ ይናገራሉ። ፍላጎቱን ከአቅርቦቱ ጋር እንዳይጣጣም ያደረገው አንዱ ምክንያትም ይኸው እንደሆነ ባለሞያው ይጠቅሳሉ። በየጊዜው የሚጨምረው የህዝብ ቁጥር እና ወደ ከተማዋ የሚደረግ ፍልሰት ነገሩን ከድጡ ወደ ማጡ አድርጎታልም ብለዋል። የከተማ አስተዳደሩ ይህን እጥረት ያለበት ሃብት ለግለሰቦች ከሚያስተላልፍባቸው መንገዶች አንዱ ሊዝ እንደሆነ የጠቀሱት አቶ ሢሣይ የዚህ ክፍያ ግን ከፍተኛ እንደሆነ ተናግረዋል። ይህ ከፍተኛ ክፍያ ደግሞ ግለሰቡ መሬቱ ላይ ገንዘቡን ስለሚጨርስ ለግንባታ የሚተርፈው ነገር እ
Mar 161 min read
ፕሮግራሞች
bottom of page

