የካንሰር ህሙማን ለህክምና ወደ ውጪ ሀገራት የሚያደርጉትን ጉዞ እና ወጪ ያስቀራል የተባለለት ግዙፍ ሆስፒታል ሊገነባ መሆኑ ተሰማ፡፡
- Mar 27
- 1 min read
መጋቢት 18/2018
በተለይ የካንሰር ህሙማን ለህክምና ወደ ውጪ ሀገራት የሚያደርጉትን ጉዞ እና ወጪ ያስቀራል የተባለለት ግዙፍ ሆስፒታል ሊገነባ መሆኑ ተሰማ፡፡
ሆስፒታሉን ገንብቶ ለማጠናቀቅ ከ15 ቢሊዮን ብር በላይ እንደሚጠይቅም ተነግሯል።
ሆስፒታሉን የሚያስገነባው ማቴዎስ ወንዱ ፋውንዴሽን የተሰኘው በጎ አድራጎት ድርጅት ሲሆን ግንባታውም በመንግስት ተቋማት፣ በበጎ አድራጎት ድርጅቶችና በህዝብ መዋጮ ጭምር በድጋፍ የሚከወን እንደሆነም ሰምተናል።

ሆስፒታሉ በተለይ የካንሰር ህመም ላይ ዋነኛው ትኩረቱ አድርጎ የሚሰራ ቢሆንም ለተለያዩ ተላላፊ ላልሆኑ እና ተላላፊ ለሆኑ ህመም ጭምር አገልግሎት እንደሚሰጥ የማቴዎስ ወንዱ ፋውንዴሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ወንዱ በቀለ ነግረውናል።
የማቴዎስ ወንዱ ፋውንዴሽን የቦርድ ሊቀመንበር የትናየት አበበ(ዶ/ር) በተለይ ለካንሰር ህክምና የሚጠየቀው ክፍያ ከፍተኛ ነው፤ ወደ ውጪ ሀገራት ለህክምና የሚጓዙ ሰዎችም ጥቂት የማይባሉ መሆናቸውን አንስተው ይህ ሆስፒታል የውጭ ጉዞን ከማስቀረት ባሻገር ከፍለው ለመታከም አቅም ለሌላቸው ሰዎች በነፃ እንዲታከሙም የሚያስችል ነው ብለዋል።
ማቴዎስ ወንዱ የኢትዮጵያ ካንሰር ሶሳይቲ ወደ ማቲዎስ ወንዱ ፋውንዴሽን ትናንት በይፋ ስያሜውን እና አርማውን ቀይሯል።
ፋውንዴሽኑ ከ170 በላይ ህፃናት እና ሴቶች የካንሰር ታማሚዎችን እየረዳ እንደሆነም ነግሮናል።
ከተቋቋመም 22 ዓመታትን እንዳስቆጠረ ሰምተናል።
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….
ፍቅሩ አምባቸው
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/
YouTube : https://shorturl.at/18TS1
Telegram : https://shorturl.at/68aeK
Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4
WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx
X :- https://x.com/shegerfm?s=2
LinkedIn: https://shorturl.at/Vfe6i
Tiktok : https://shorturl.at/lhYiv
Instagram: https://shorturl.at/9X4S7





Comments