በሶማሌ ክልል የአቦ ሸማኔ ንግድ የተጧጧፈ ሆኗል ተባለ።
- 4 hours ago
- 1 min read
መጋቢት 17/2018
በሶማሌ ክልል የአቦ ሸማኔ ንግድ የተጧጧፈ ሆኗል ተባለ።
አቦሸማኔዎች በህገ-ወጥ የዱር እንስሳት አዘዋዋሪዎች ምክንያት የከፋ አደጋ እየደረሰባቸው ነው ተብሏል።
በተለይም ግልገሎቹ እንደ ተወለዱ ከእናታቸው ተነጥለውለው ለንግድ ተግባራት እንደሚውሉ ተነግሯል።
ይህ ህገ ወጥ ድርጊት በዋናነት የሚፈጸመው በአካባቢው በሚገኙ አርብቶ አደሮች አማካኝነት እንደሆነም የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለስልጣን ተናግሯል።
እነዚህ ግልገሎች ገና በጨቅላነታቸው ታድነው ተይዘው ፣ ህገ-ወጥ አዘዋዋሪዎች በ70 እና በ80 የአሜሪካ ዶላር ዋጋ ከአርብቶ አደሮቹ እንደሚረከቧቸው በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ህግ ማስከበር ዴስክ ሀላፊ አቶ ዳንኤል አሰፋ ነግረውናል።
ህገ ወጥ የአቦሸማኔ ዝውውሩን እያጧጧፉት ያሉት በዋናነት ተጠቃሚ ሀገራት እንደሆነ የጠቀሱት ሀላፊው ሳውዲ አረቢያ፣ ኩዌት እና ኳታር ለመዝናኛነት በሚል ሰበብ የአቦ ሸማኔ ግልገሎችን ከሚፈልጉ ሀገራት መካከል ናቸው ብለዋል።
ይህንን የድንበር ተሻጋሪ የወንጀል ሰንሰለት በማንቀሳቀስ ረገድ የኢትዮጵያ፣ የኬንያ እና የየመን ዜግነት ያላቸው ግለሰቦች በደላላነትና በአዘዋዋሪነት እንደሚሳተፉበት ተነግራል።
ድርጊቱ የሚፈጸመው በምስራቅ አፍሪካ በኩል አልፎ በየመን ተሻግሮ ወደ መካከለኛው ምስራቅ በሚያደርስ የኮንትሮባንድ መስመር መሆኑም አቶ ዳንኤል አስታውሰዋል።
የዱር እንስሳት ለሀገር ገጽታም ሆነ ለቱሪዝም ዘርፉ ያላቸውን ፋይዳ የተጠቆሙት ሃላፊው፣ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ይህንን ችግር ለመቅረፍ የተለያዩ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።
የአሜሪካው ኮሎራዶ ስቴት ዩኒቨርሲቲ በዚህ ዙሪያ ጥናት ከሰሩ ተቋማት አንዱ ስለመሆኑም አቶ ዳንኤል ተናግረዋል።
ከጎረቤት ሀገራትና ከዓለም አቀፍ የፀጥታ አካላት ጋር በቅንጅት መስራቱን ማጠናከር፣ የንግድ መስመሩን መዝጋት ችግሩን ለመቅረፍ የነገ የማይባል የቤት ስራ ነው መባሉንም ሰምተናል።
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….
ገዛ ጌታሁን
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/
YouTube : https://shorturl.at/18TS1
Telegram : https://shorturl.at/68aeK
Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4
WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx
X :- https://x.com/shegerfm?s=2
LinkedIn: https://shorturl.at/Vfe6i
Tiktok : https://shorturl.at/lhYiv
Instagram: https://shorturl.at/9X4S7





Comments