በትግራይ ክልል የሚደረገው አጀንዳ የማሰባሰብ ስራን በአዲስ አበባ ከተማ ለማከናወን እቅድ መያዙን የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ተናገረ።
- Mar 27
- 1 min read
መጋቢት 18/2018
በትግራይ ክልል የሚደረገው አጀንዳ የማሰባሰብ ስራን በአዲስ አበባ ከተማ ለማከናወን እቅድ መያዙን የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ተናገረ።
የትግራይ ክልልን የምክክር ሂደት በክልሉ ለማካሄድ አስቻይ ሁኔታ ስለሌለ ምክክሩን በአዲስ አበባ ከተማ ከመጋቢት 23 እስከ 25/2018 ድረስ ምክክሩ ይደረጋል ተብሏል።
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ይህንን ያለው የትግራይ ክልልን የምክክር ሂደት በተመለከተ ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ ነው።

ኮሚሽኑ የትግራይ ክልልንም እንደሌሎቹ የኢትዮጵያ ክልሎች ሁሉ በሀገራዊ ምክክሩ ለማካተትና ለማሳተፍ በርካታ ጥረቶችን ሲያደርግ መቆየቱን ተናግሯል።
በዚህም ኮሚሽኑ የትግራይ ክልል በምክክር ሂደቱ እንዲሳተፍ ከክልሉ ጊዜአዊው አስተዳደር፣ ከፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ከሲቪል ማህበረተሰብ ድርጅቶች፣ ከምሁራን እና ከሌሎችም አካላት ጋር ተከታታይነት ያለው ከ22 በላይ ውይይቶችን ሲያከናውን እንደቆየ አንስቷል።
ምክክሩም የክልሉን ሆነ የኢትዮጵያን መሰረታዊ ችግሮች ለመፍታት የሚያስችል መግባባት ላይ የተደረሰ ቢሆንም ኮሚሽኑ ባለው የአሰራር ሥርዓት መሰረት በክልሉ ተሳታፊዎችን የመለየትና አጀንዳ የማሰባሰብ ተግባር ለማከናወን አስቻይ ሁኔታ አልተፈጠረም ተብሏል።
በዚህም የትግራይ ክልል ህዘብና የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በተወካዮቻቸው አማካኝነት የሚሳተፉበት የአጀንዳ ማሰባሰብና የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ተሳታፊዎች ልየታ መድረክ ከመጋቢት 23 እስከ 25 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ እንዲካሄድ በኮሚሽኑ ምክር ቤት መወሰኑን የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ተናግረዋል።
በትግራይ ክልል ያለን አጀንዳ የማሰባሰብ ስራ በአዲስ አበባ ከተማ ለመከወን ሲታሰብም የፖለቲካ ፓርቲዎችን፣ ተቋማት እና ማህበራትን፣ ጊዜአዊው አስተዳደሩን ጨምሮ ሌሎች ባለድርሻዎችን ያካተተ ሰፊ ውይይት መደረጉን መደረጉን ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ አንስተዋል።
በአዲስ አበባ ከተማ ለሶስት ቀናት በሚከናወነው የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ወደ 400 የሚጠጉ የክልሉ ተወካዮች እና አዲስ አበባ ያሉ የትግራይ ተወላጆች ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል ሲል ኮሚሽኑ በመግለጫው አስረድቷል።
ንጋቱ ሙሉ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/
YouTube : https://shorturl.at/18TS1
Telegram : https://shorturl.at/68aeK
Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4
WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx
X :- https://x.com/shegerfm?s=2
LinkedIn: https://shorturl.at/Vfe6i
Tiktok : https://shorturl.at/lhYiv
Instagram: https://shorturl.at/9X4S7




Comments