ጋዜጠኞች ያላግባብ መታፈንና እስርን የመሰለ የሰብአዊ መብት ጥሰት ሲደርስባቸውም በፍርድ ቤት ጭምር ክርክር የሚያደርግ ድርጅት ስራ ጀምሯል፡፡
- 1 hour ago
- 1 min read
መጋቢት 17/2018
ጋዜጠኞች ደህንነታቸው ተጠብቆ እንዲሰሩ ፣ የሚድያ ምህዳሩ እንዲሰፋ ፣ ጋዜጠኞች ያላግባብ መታፈንና እስርን የመሰለ የሰብአዊ መብት ጥሰት ሲደርስባቸውም በፍርድ ቤት ጭምር ክርክር የሚያደርግ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት በይፋ ስራ ጀምሯል፡፡
በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ተመዝግቦ በይፋ ትናንት ስራ ጀምሯል የተባለው ሎውየርስ ፎረ ሚዲያ (Lawyers for media) የተሰኘ ስያሜ የተሰጠው ተቋም ነው፡፡
በዩኔስኮ እገዛ በፕሮጀክት ደረጃ የጀመርናቸው ስራዎች ራሱን ችሎ በተቋም ደረጃ በስፋት እየሰራ ይቀጥላል ያሉን የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ድርጅቶች ህብረት ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ መሱድ ገበየሁ ናቸው፡፡

በሁሉም ክልሎች የሚሰሩ የህግ ባለሙያዎች የተካተቱበት ለሚድያው ዘርፍ መጠናከርና የሚያስፈልገው የህግ ድጋፍ የሚሰጥ መሰል ማህበር ማቋቋም ያስፈለገበት ምክንያትም የሚድያ ምህዳሩ እየሰፋ እንዲሄድ ለማገዝ ነው ብለዋል፡፡
ከዚህ ባሻገር ጋዜጠኞች ያላግባብ የመታፈንና የመታሰር ችግረ ሲደርስባቸው የህግ ምክር መስጠትና በፍርድ ቤትም ነጻ ጥብቅና እንዲያገኙ ማስቻል ተቋሙ ከሚከውናቸው ስራዎች መካከል ይሆናል ተብሏል፡፡
ከእስር ከተፈቱ በኋላም ቢሆን የስነ ልቦና ድጋፍ እንዲያገኙና ሀላፊነታቸው መወጣታቸውን እንዲቀጥሉ ማገዝ የ*Lawyers for media* ሀላፊነት ነው ብለዋል ዋና ዳይክተሩ አቶ መስኡድ፡፡
ተቋሙ ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ እና መረጃ የማግኘት ፣ መብቶች በህጉ መሰረት እንዲከበሩ ፣ የጋዜጠኞች የመገናኛ ብዙሃን ደህንነት ተጠብቆ እንዲሰሩ ለማስቻል ይሰራል ተብሏል፡፡
ተቋሙ በህግ እውቅና አግኝቶ ራሱን ችሎ እንዲሰራ ያስፈለገው የሚድያ ምህዳሩ እየጠበበ መምጣቱ በተለያየ መንገድ የሚታይ በመሆኑና ይህን ችግር ማሻሻል አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ መሆኑንም ሰምተናል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….
ትዕግስት ዘሪሁን
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/
YouTube : https://shorturl.at/18TS1
Telegram : https://shorturl.at/68aeK
Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4
WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx
X :- https://x.com/shegerfm?s=2
LinkedIn: https://shorturl.at/Vfe6i
Tiktok : https://shorturl.at/lhYiv
Instagram: https://shorturl.at/9X4S7

