top of page


የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ለትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር በድጋሚ የአብረን እንስራ ጥሪ አቀረበ።
መጋቢት 25/2018 የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ለትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር በድጋሚ የአብረን እንስራ ጥሪ አቀረበ። ላለፉት 3 ቀናት በአዲስ አበባ ከትግራይ ክልል ተወላጆች ጋር ሲካሄድ የቆየው የመጀመሪያ ዙር የአጀንዳ ማሰባሰብ ምክክር ዛሬ ተጠናቅቋል። በማጠናቀቂያው መርሃ ግብር መልዕክት ያስተላለፉት ፤ የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ የመከርነው ለትግራይ ሰላም እንጂ ትግራይን ለመጉዳት አይደለም፤ ከዚህም በኋላ አብሮ ለመስራት በራችን ክፍት ነው ሲሉ ለትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ጥሪ አቅርበዋል። በምክክሩ የተነሱት ጉዳዮች ደረጃቸው ሊለያይ ይችል ይሆናል እንጂ፤ አብዛኞቹ በሁሉም ክልሎችና የከተማ መስተዳድር ከተነሱት ጋር ተቀራራቢ ናቸው ብለዋል። ይሁንና አንዳንዶቹ ጉዳዮች የትግራይ ብቻ የሆኑ መሆናቸውን አስተው
Apr 31 min read


ዳሸን ባንክ ልዩ የሱፐር አፕ ማስተዋወቅ ውድድር ሽልማትን ጨምሮ አራት አዳዲስ አገልግሎቶችን ዛሬ አስጀመረ።
መጋቢት 24/2018 ዳሸን ባንክ ልዩ የሱፐር አፕ ማስተዋወቅ ውድድር ሽልማትን ጨምሮ አራት አዳዲስ አገልግሎቶችን ዛሬ አስጀመረ። ባንኩ የሱፐር አፕ ተጠቃሚዎችን ለማበረታት እንዲሁም የአገልግሎቱን ተደራሽነት ለማስፋት የቲክቶክ ይዘት ፈጠራ ውድድር ማዘጋጀቱን ይፋ አድርጓል። በዚህ ውድድር ለሚያሸንፉ የይዘት ፈጣሪዎች በድምሩ ስድስት ሚሊዮን ብር የገንዘብ ሽልማት እንዳዘጋጀ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የንግድ ሥራ ትምህርት ቤት (ኮሜርስ) በተዘጋጀ ስነ ስርአት ላይ ተነግሯል። በዳሸን ሱፐር አፕ ቲክቶክ ቻሌንጅ አሸናፊ ለመሆን ይዘት ፈጣሪዎች ስለ ዳሸን ባንክ ሱፐር አገልግሎቶች የሚገልፅ የቲክቶክ ቪዲዮ በመስራት ማጋራት ይጠበቅባቸዋል ተብሏል። የሰሩት ቪዲዮ በቲክቶክ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ዕይታ ሲያገኝ፣ በዳሸን ሱፐር አፕ ውስጥ በሚገኘው የዳሸን ክሬቲቭ አ
Apr 21 min read


ከቴምር ፕሮፐርቲ መኖሪያ ቤት የሚገዙ ደንበኞች ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ልዩ የሼባ ማይልስ ስጦታ የሚያገኙበት ዕድል መዘጋጀቱ ተነገረ።
መጋቢት 24/2018 ከቴምር ፕሮፐርቲ መኖሪያ ቤት የሚገዙ ደንበኞች ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ልዩ የሼባ ማይልስ ስጦታ የሚያገኙበት ዕድል መዘጋጀቱ ተነገረ። የኢትዮጵያ አየር መንገድ የደንበኞች ሎያሊቲ ክፍል ማናጀር አቶ ሰለሞን መኮንን እና የቴምር ፕሮፐርቲ የኢቨንት እና ፕሮሞሽን ዳይሬክተር አቶ ዑስማን መሀመድ ስምምነቱን በሰጡት መግለጫ ይፋ አድርገዋል። በዚህ ስምምነት መሰረት የቴምር ሪል ስቴት ደንበኞች የሚገዙትን የቤት ወይም የሱቅ አይነት መሰረት ያደረገና የከፈሉትን መጠን ያማከለ የዓለም አቀፍ በረራ የማይልስ ዕድል ያገኛሉ ተብሏል። የቴምር ደንበኞች በዚህ ስምምነት መነሻነት የሼባማይልስ ደረጃቸው እንደ ክፍያቸው ሁኔታ እያደገ የሚሄድ ሲሆን፤ ከብሉ ወደ ሲልቨር፣ ከሲልቨር ወደ ጎልድ ወይም ከብሉ ወደ ጎልድ የማሳደግ ዕድልንም ይሰጣል መባሉን ሰም
Apr 21 min read


ቪዛ እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባለ ቪዛ ካርድ ደንበኞች የ2026 የዓለም ዋንጫን በአካል ተገኝተው የሚመለከቱበትን ዕድል ይዘው መቅረባቸውን ተናገሩ።
መጋቢት 24/2018 ቪዛ እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባለ ቪዛ ካርድ ደንበኞች የ2026 የዓለም ዋንጫን በአካል ተገኝተው የሚመለከቱበትን ዕድል ይዘው መቅረባቸውን ተናገሩ። ዕድሉ የምድብ ጨዋታዎችን በአካል ለመመልከት የሚያስችል መሆኑ ተነግሯል። ይህ ከመጋቢት 5 እስከ ሚያዝያ 6 ቀን 2018 ዓ.ም የሚቆይ ንቅናቄ፣ በመላው ኢትዮጵያ ለሚገኙ የባንኩ የዴቢትም ሆነ የቅድመ ክፍያ ቪዛ ካርድ ተጠቃሚዎች በሙሉ ክፍት ነው ተብሏል። ደንበኞቹ በቪዛ ካርዳቸው የሚፈጽሙት እያንዳንዱ ግብይት እንደ አንድ ዕጣ ይቆጠራል የተባለ ሲሆን ለዚህ ምዝገባ አይጠየቅም ተብሏል። በቪዛ የምሥራቅ አፍሪካ ክላስተር ሓላፊ የሆኑት ያሬድ እንዳለ፣ የካርድ ተጠቃሚዎችን በየቀኑ እየፈጸሟቸው ለሚገኙ ግብይቶች ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር ተባብረን በመሸለማችን ደስተኞች ነን'' ብለዋል።
Apr 21 min read


አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ከሌሎች ተማሪዎች እኩል የማይማሯቸው ትምህርቶች በመኖራቸው ተወዳዳሪነታችንን ይቀንስብናል ብለዋል።
መጋቢት 24/2018 በኢትዮጵያ አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ቀላል የማይባል ችግር እንደሚያጋጥማቸው በተደጋጋሚ ይናገራሉ፡፡ የመሰረተ ልማት አለመሟላት፣ እነሱን ተቀብሎ የሚያስተምር ትምህርት ቤት አለማግኘት፣ የቁሳቁስ አለመሟላት፣ በስራ ቅጥር ወቅት እድል አለማግኘት እና በሌሎች ፈተናዎች እንደሚያልፉ ይነገራል፡፡ አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ከሌሎች ተማሪዎች እኩል የማይማሯቸው ትምህርቶች በመኖራቸው ተወዳዳሪነታችንን ይቀንስብናል ብለዋል። በዚህም ምክንያት አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ትምህርታቸውን አጠናቀው ወደ ገበያ ሲቀላቀሉ ከሌሎች ተማሪዎች ጋር እኩል ተወዳዳሪ ለመሆን እንደሚቸገሩ አንስተዋል። ከቅድመ አንደኛ ደረጃ ጀምሮ እስከ ሁለተኛ ደረጃ የትምህርት ክፍል ድረስ አካል ጉዳተኞች የማይማሯቸው የትምህርት ዓይነቶች በመኖራቸው ተወዳዳሪነታቸው ላይ ችግር እየፈጠረባቸው
Apr 21 min read


ታሪክን የኋሊት - ንግስተ ነገስታት ንግስት ዘውዲቱ
በኢትዮጵያ የመሪዎች ታሪክ ፣ ባለፉት 1000 ዓመታት ውስጥ የመጀመሪያዋ ሴት ንግስተ ነገስታት የነበሩት ንግስት ዘውዲቱ ፣ ያረፉት በ1922 ዓ.ም በዛሬው ቀን ነበር፡፡ ንግስተ ነገስታት ዘውዲቱ፣ በ10ኛ ክፍለ ዘመን የኢትዮጵያ መሪ እንደነበረች ከሚነገርላት ዮዲት ጉዲት ወዲህ ፣ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ሴት መሪ ነበሩ፡፡ ንግስት ዘውዲቱ ፣ የኢትዮጵያን ንግስና ያገኙት ፣ በጊዜው የነበሩት የጦር አለቆች ፣ አገረ ገዥዎች ፣ መኳንንት የቤተ መንግስቱ የጥበቃ ወታደሮች ምርጫ እንጂ እንደቀደምቶቻቸው በውርስና በውጊያ አልነበረም፡፡ ከአዲስ አበባ ቤተ መንግስት የተላኩ የጦር መኮንኖች ፣ መሳፍንቱ መኳንንቱ ሕዝብና ሰራዊት፣ በአንድነት ተስማምተው ፣ ነግስተ ነገስታት ዘውዲቱ ተብለው ፣ በአባትዋ በአፄ ምኒልክ ዙፋን እንዲቀመጡ “መርጦዎታል” ተብለው የተነገሩት
Apr 22 min read


የእሳት እራት ተብሎ የሚጠራው ነፍሳት በኢትዮጵያ በአፅዋት ላይ ምንም ጉዳት የማያስከትል ቢሆንም አውሮፓ ከገባ ግን ከ100 በላይ የእፅዋት ዓይነቶችን ቀርጥፎ የሚበላ ሌላ ባህሪ ያለው ተባይ ይሆናል፡፡
መጋቢት 24/2018 የእሳት እራት ተብሎ የሚጠራው ነፍሳት በኢትዮጵያ በአፅዋት ላይ ምንም ጉዳት የማያስከትል ቢሆንም አውሮፓ ከገባ ግን ከ100 በላይ የእፅዋት ዓይነቶችን ቀርጥፎ የሚበላ ሌላ ባህሪ ያለው ተባይ ይሆናል፡፡ በዚህም ምክንያት ከአመታት በፊት በኢትዮጵያ የአበባ እርሻዎች ውስጥ መገኘቱን ተከትሎ የአውሮፓ ህብረት ተባዩ ከምርቱ ጋር ወደኛ እንዳይመጣብን የሚል ማሳሰቢያ ሰትቶ ነበር፡፡ የአበባ ምርት ወደ ህብረቱ እንዳይገባ ከመታገዱ በፊት ምን እርምጃ ተወሰደ፡፡ በእንግሊዝኛው ምህጻረ ቃል F C M የሚሰኘው ተባይ የቢራቢሮ ዝርያ ሲሆን በእኛ አገር የእሳት እራት በመባል ይታወቃል ። በሀገራችንአብዛኞቹ ዕፅዋት የዚህ ተባይ መኖሪያ ሆነው እንደሚያገለግሉ የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ወንዳለ ሃብታሙ ነግረውናል፡፡
Apr 21 min read


በኢንዱስትሪ ፓርኮችና በከፍተኛ ት/ት ተቋማት የሚገኙ ወጣቶች ለኤችአይቪ ተጋላጭነትን ለመቀነስ የኮንዶም አቅርቦትና ግንዛቤው ላይ መሰራት አለበት ተባለ፡፡
መጋቢት 24/2018 በኢንዱስትሪ ፓርኮች እንዲሁም በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ የሚገኙ ወጣቶች ለኤች አይ ቪ ተጋላጭነትን ለመቀነስ የኮንዶም አቅርቦትና ግንዛቤው ላይ መሰራት አለበት ተባለ፡፡ በስራቸው እና ዕድሜያቸው ምክንያት ለኤች አይ ቪ እጅግ ተጋላጭ ከሆኑት ውስጥ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ያሉ ወጣቶች በተለይ ሴቶች ይገኙበታል ተብሏል፡፡ ለዚህም የጤና ሚኒስቴር ከለጋሽ ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በመሆን ኮንዶም በነፃ እያቀረበ መሆኑን ነገር ግን ይህም ቢሆን በቂ አለመሆኑን ተናግሯል፡፡ በጤና ሚኒስቴር የኤች አይቪ ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር መሪ ስራ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ ፍቃዱ ያደታ እንደሚናገሩት በተለይ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ላይ ተቀጥረው ከሚሰሩት ውስጥ አብዛኛዎቹ ወጣቶች በመሆናቸው የኤች አይ ቪ ተጋላጭነታቸውን መቀነስ ላይ ይበልጥ መስራት ያ
Apr 22 min read


የአቪዬሽን ዘርፍ ባለሙያዎች በሚፈለገው ልክ ማሰልጠን እና ያሉትንም የማቆየቱ ፈተና እንዴት እየሆነ ይሆን?
መጋቢት 24/2018 በአቪዬሽን ዘርፍ የሚሰማሩ የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች፣ ኦዲት ኢንስፔክተሮች እና ሌሎች ባለሞያዎችን መቅጠር፣ ያሉትንም ማቆየት የኢትዮጵያ የአቪዬሽን ዘርፍ ያልተፈታ ፈተና ነው። በክፍያ ምክንያት የሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን እነዚህን የአቪዬሽን ዘርፍ የጀርባ አጥንት የሆኑትን ባለሙያዎች በሚፈለገው ልክ ለማግኘትና፣ የገቡትንም ለማቆየት እንደሚቸገር በየጊዜው ይነሳል። ኢትዮጵያ ከዓለም ተወዳዳሪ፣ ከአፍሪካ ቀዳሚ የሆነ ግዙፍ ዓለም አቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ እየገነባች ነው፣ የአቪዬሽኑ ዘርፍ በፍጥነት እያደገ ነው፣ የሀገር ውስጥ በረራን የሚሰጡ አዳዲስ አውሮፕላን ማረፊያዎችም በየክልሉ እየተገነቡ ነው። ለመሆኑ ለዚህ ሁሉ ስራ የግድ የሆኑትን፣ የአቪዬሽኑን ዘርፍ ከጀርባ ሆነው የሚደግፉትን፣ የበረራ ደህንነትን የሚያረጋግጡትን ባለሙያዎች
Apr 21 min read
የኤሌክትሪክ ኬብሎችን የዘረፉ ግለሰቦች በህግ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ መደረጉን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ተናገረ።
መጋቢት 23/2018 የኤሌክትሪክ ኬብሎችን የዘረፉ ግለሰቦች በህግ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ መደረጉን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ተናገረ። ከ3.8 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኤሌክትሪክ ኬብሎችን የዘረፉ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አገልግሎቱ ተናግሯል። የየካ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የደረሰውን ጥቆማ መሰረት በማድረግ ከምስራቅ አዲስ አበባ ሪጅን ህግ ቢሮ ጋር ባደረገው ኦፕሬሽን ተጠርጣሪዎቹን ካከማቹት በርካታ የኤሌክትሪክ ኬብልና ገመድ ጋር በቁጥጥር ሥር ማዋል ችለዋል ተብሏል። ኮተቤ ኪዳነ-ምህረት አካባቢ ተከማችተው የተገኙት የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማቶች 4 ሺ 895 ሜትር ኤቢሲና ዩጂ የኤሌክትሪክ ኬብሎች፣ 350 ኪ.ግ የሚመዝኑ የተለያዩ አልሙኒየምና መዳቦች ናቸው ተብሏል። አጠቃላይ የዋጋ ግምታቸውም 3 ሚሊየን 895 ሺህ 81
Apr 11 min read


ሀገራዊ ምክክሩ የትግራይ ነገ የተረጋጋ እንዲሆን የክልሉ ህዝብ የድርሻውን የሚወጣበት መሆኑን የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ተናገረ።
መጋቢት 23/2018 ሀገራዊ ምክክሩ የትግራይ ነገ የተረጋጋ እንዲሆን የክልሉ ህዝብ የድርሻውን የሚወጣበት መሆኑን የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ተናገረ። ለበርካታ ጊዜያት ሊከናወን ቀጠሮ ሲያዝ ሲራዘም የነበረው የትግራይ ክልል አጀንዳ የማሰባሰብ ምክክር ዛሬ በአዲስ አበባ ተጀምሯል። ከዛሬ መጋቢት 23 እስከ አርብ መጋቢት 25 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ በሚካሄደው የመጀመሪያውን ዙር የአጀንዳ ማሰባሰብ መድረክ ከክልሉ የመጡና በአዲስ አበባ ያሉ የትግራይ ተወላጆች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሲቪክ ማህበራት፣ የሃይማኖት ተወካዮች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻዎች እየተሳተፉ ነው። በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ትግራይ የሌለችበት ምክክር ግቡን የማይመታ በመሆኑ ከብዙ ጥረቶች በኋላ በአዲስ አበባ እንድ
Apr 11 min read


መጋቢት 22/2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች
#ጀርመን በጀርመን ከሚኖሩ ስደተኞች 80 በመቶዎቹ ወደ አገራቸው እንደሚሸኙ መራሄ መንግስት ፍሬድሪክ ሜርዝ ተናገሩ፡፡ ሶሪያውያኑ ስደተኞች በመጪዎቹ 3 አመታት ከጀርመን ወደ አገራቸው ይሸኛሉ መባሉን ቢቢሲ ፅፏል፡፡ መራሄ መንግስት ሜርዝ 80 በመቶዎቹ ሶሪያውያን ስደተኞች በ3 አመታት ጊዜ ወደ አገራቸው እንደሚሸኙ እወቁልን ያሉት ከሶሪያው ጊዜያዊ ርዕሰ ብሔር አህመድ አልሻራ ጋር በበርሊን ከተነጋገሩ በኋላ ነው ተብሏል፡፡ ብዙዎቹ ሶሪያውያን ስደተኞች ጀርመን የገቡት በአገራቸው ተቀስቅሶ የነበረው ውስብስብ የእርስ በርስ ጦርነት በተፋፋመበት ወቅት ነበር፡፡ አሁን ስደተኞቹን ከጀርመን መመለስ ይጀመራል ቢባልም ዝርዝሩ ገና አልታወቀም፡፡ ሶሪያ በአሁኑ ወቅት ከ10 ዓመት በፊት ከነበረው በእጅጉ የተሻለ ፀጥታ እንደሚስተዋልባት መረጃው አስታውሷል፡፡ #አሜሪካ አ
Mar 312 min read


ኢትዮጵያ በኢራኑ ጦርነት ምክንያት ከ180 ሺህ ሜትሪክ ቶን ነዳጅ በላይ ገዝታ ማቅረብ ባለመቻሏ የነጭ ናፍጣ የቀን አቅርቦት በግማሽ ቀንሷል ተባለ፡፡
መጋቢት 22/2018 ኢትዮጵያ በኢራኑ ጦርነት ምክንያት ከ180 ሺህ ሜትሪክ ቶን ነዳጅ በላይ ገዝታ ማቅረብ ባለመቻሏ የነጭ ናፍጣ የቀን አቅርቦት በግማሽ ቀንሷል ተባለ፡፡ ኢትዮጵያ ከመካከለኛው ምስራቅ ሃገራት ጋር የረዥም ጊዜ የነዳጅ ግብይት ውል የነበራት ሲሆን በጦርነቱ ምክንያት ምርት ማቅረብ እንደማይችሉ ነግውኛል ብላለች፡፡ በመሆኑም ያለውን እጥረት መሰረት በማድረግ ከማዲያዎች ቅድሚያ የሚሰጣቸው ሰባት አካላት ተለይተው በመንግስት ይፋ ተደርገዋል፡፡ በነዳጅ አቅርቦት ላይ ያጋጠመውን ችግር ለመቋቋም የሚያስችለውን ውሳኔ ዛሬ ይፋ ያደረገው የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ነው፡፡ ሚኒስትሩ ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር) በሰጡት መግለጫ በየቀኑ የነጭ ናፍጣ አቅርቦት 9 ነጥብ 2 ሚሊዮን ሊትር የነበረ ሲሆን አሁን ወደ 4 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሊትር ዝቅ ማለታቸው ተሰ
Mar 311 min read


ለትርፍ የተቋቋሙ የመንግስት ተቋማት ጭምር በበጎ አድራጎት ስራ ላይ ተሰማርተው ማህበራዊ ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ ተጠየቀ፡፡
መጋቢት 22/2018 ለትርፍ የተቋቋሙ የመንግስት ተቋማት ጭምር በበጎ አድራጎት ስራ ላይ ተሰማርተው ማህበራዊ ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ ተጠየቀ፡፡ እንደ ባንኮች፣ አምራች እንዱስትሪዎችና ሌሎችም የመንግስትና የግል አትራፊ ተቋማት በጎ አድራጎት ላይ በመሳተፍ ማህበራዊ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ተጠይቋል። የተቋማቱ አትራፊነትና ስኬት ምንጭ ህዝብ እንደመሆኑ፣ አቅመ ደካሞችን በመርዳት ፣ ጎዳና ላይ የወደቁትን በማንሳት፣ ወላጅ አልባ ህፃናትን በማስተማርና በሌሎችም በጎ አድራጎት ሥራዎች ላይ በመሳተፍ የማህበራዊ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ የተጠየቀው ሙዳይ የበጎ አድራጎት ማህበር "የፍቅር ሳምንት" የተሰኘ ዓመታዊ መርሃ ግብሩን አስመልክቶ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው። #ሙዳይ_በጎ_አድራጎት_ማህበር ህፃናት፣ ሴቶችና አካል ጉዳተኞችን ከልመና፣ ከጎዳና ተዳዳሪነትና
Mar 311 min read


በመካከለኛው ምስራቅ የተቀሰቀሰው ጦርነት በኢትዮጵያ በዋጋ ግሽበት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እንደሚኖረው የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴው ተናገረ፡፡
መጋቢት 22/2018 በመካከለኛው ምስራቅ የተቀሰቀሰው ጦርነት በኢትዮጵያ በዋጋ ግሽበት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እንደሚኖረው የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴው ተናገረ፡፡ የኢራኑ ጦርነት በአለም አቀፍ የነዳጅ ዋጋ ላይ ከፍተኛ ጫና እያሳደረ የአቅርቦት ሰንሰለት መቋረጥም እየፈጠረ መሆኑን ኮሚቴው ማስታወሱን ከብሔራዊ ባንክ ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡ ይህም በሃገር ውስጥ የዋጋ ግሽበት ሁኔታ ላይ ጫና እንደሚፈጥር ጠቅሶ የስጋቱ ጫና ግን መንግስት በሚወስደው የመቆጣጠሪያ እርምጃዎች እና ግጭቱ በሚቆይበት ጊዜ የሚወሰን ይሆናል ብሏል፡፡ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የገንዘብ ፖሊስ ኮሚቴው ስድስተኛ ዙር ስብሰባውን አካሄዶ የተለያዩ ኢኮኖሚያዊ ሁኔታዎችን በመገምገም መግለጫ አውጥቷል፡፡ በቅርቡ ሁለት ገለልተኛና የመስኩ ባለሙያ የሆኑ አባላትን ያካተተው የገንዘብ ፖሊሲ ከታህሳስ ወር
Mar 312 min read


ታሪክን የኋሊት -የማይጨው ጦርነት
#ታሪክን_የኋሊት በኢትዮጵያና በኢጣሊያ መካከል የማይጨው ጦርነት የተደረገው በ1928 ዓ.ም በዛሬው ቀን ነበር፡፡ ኢጣሊያ በሊቢያና በሱማሊያ ከኢትዮጵያ ክፍል ኤርትራን በቅኝ ግዛትነት ይዛ ከቆየች በኋላ፣ ጠቅላላ ኢትዮጵያን በሃይል ለመውረር ጦርነት ከፈተች፡፡ በምፅዋ ወደብ ፣ በኤርትራ በኩል ወደወሰን ዘመናዊ የጦር ሃይሏን አደራጀች፡፡ የወልወልን ግጭት ሆን ብላ ከቀሰቀሰች በኋላ፣ ተበዳይ ሆና ለመቅረብ ሞከረች፡፡ አከታትላም ዋናው የጦር ሃይሏን ባደራጀችባት ኤርትራ በኩል፣ ወሰን ጥሳ፣ በጥቅምት ወር መቀሌን ያዘች፡፡ ከወራሪው የኢጣሊያ ሃይል ጋር ሲወዳዳር፣ ኋላ ቀርና አነስተኛ መሣሪያ ያለው አብዛኛው፣ የኢትዮጵያ ሰራዊት፣ የክተት አዋጁን ተከትሎ፣ ስንቁን ይዞ፣ ጦርና ጋሻውን አንግቦ ወደዘመቻው ተሰማራ፡፡ ኢጣሊያ፣ በሶማሊያ በኩል ባደራጀችው ዘመናዊ የ
Mar 312 min read
በአይነቱ ልዩ የሆነ የሪል ስቴት ኤክስፖ በለንደን እንግሊዝ ከግንቦት 15 እስከ 17/2018 እንደሚካሄድ ተነገረ።
መጋቢት 22/2018 በአይነቱ ልዩ የሆነ የሪል ስቴት ኤክስፖ በለንደን እንግሊዝ ከግንቦት 15 እስከ 17/2018 እንደሚካሄድ ተነገረ። በእንግሊዝና አካባቢዋ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በሀገራቸው የመኖሪያ ቤት ማፍራት የሚችሉበትን ዕድል ለመፍጠር የተዘጋጀ ኤክስፖ ነው ተብሏል። በሪል ስቴት አልሚዎችና በተጠቃሚዎች መካከል ያለውን መተማመን ለማሳደግና አስተማማኝ በሆነ መንገድ ግብይቶች እንዲፈፅሙ የተዘጋጁ ስርዓቶችን ለማስተዋወቅ ያለመ መሆኑም ተጠቅሷል። በኤክስፖው ላይ ከሚመለከታቸው አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ጋር በሚደረግ የመረጃ ልውውጥና የፓናል ውይይት በዘርፉ ስላሉ ችግሮች ይነሳል ተብሎ እንደሚጠበቅም ኤክስፖውን አስመልክቶ ከተዘጋጀ መግለጫ ላይ ተመልክተናል። ባንኮች በውጪ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የቢዝነስ ድ
Mar 311 min read


የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአገራቸው ጦር የኢራን ዋነኛ የነዳጅ ዘይት መናኸሪያ የሆነውን የካርግ ደሴት ሊይዝ እንደሚችል ፍንጭ ሰጡ፡፡
መጋቢት 21/2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች #አሜሪካ የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአገራቸው ጦር የኢራን ዋነኛ የነዳጅ ዘይት መናኸሪያ የሆነውን የካርግ ደሴት ሊይዝ እንደሚችል ፍንጭ ሰጡ፡፡ የካርግ ደሴት የኢራን ዋነኛ የነዳጅ ዘይት ማምረቻ እና ለውጭ ገበያ ከታለመው ነዳጅ 90 በመቶው የሚላከው ከዚሁ ደሴት እንደሆነ ቢቢሲ ፅፏል፡፡ ከወር በላይ ባስቆጠረው የኢራን ጦርነት ምክንያት በአለም ዙሪያ የነዳጅ ዘይት ዋጋ በጣሙን እያሻቀበ ነው ተብሏል፡፡ ኢራን በኢስፍሐን ዩኒቨርስቲ ላይ ለተፈፀመባት ጥቃት በእስራኤል እና በባሕረ ሰላጤው አገሮች በሚገኙ የአሜሪካ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ላይ የአፀፋ ጥቃት እንደምታደርስ ዝታለች፡፡ ኢራን በእስራኤል ደቡባዊ ክፍል የኢንዱስትሪዎች መገኛ ላይ በፈፀመችው የሚሳየል ድብደባ ከባድ ቃጠሎ መድረሱ ታውቋል፡፡
Mar 302 min read


በባህር፣ በየብስ እና በአየር ተጓጉዘው የሚመጡ እቃዎችን ከጉምሩክ መጋዘን በሚያወጡበት የጊዜ ገደብ ላይ ለውጥ ተደርጓል።
መጋቢት 21/2018 በአዲሱ የጉምሩክ አዋጅ ማሻሻያ ረቂቅ ላይ አስመጪዎች በባህር፣ በየብስ እና በአየር ተጓጉዘው የሚመጡ እቃዎችን ከጉምሩክ መጋዘን በሚያወጡበት የጊዜ ገደብ ላይ ለውጥ ተደርጓል። በባህር እና በየብስ ተጓጉዘው የሚመጡ እቃዎችን ከጉምሩክ መጋዘን ማውጫ ጊዜው ከ15 ቀን ወደ 45 ቀን፤በአየር ተጓጉዘው የሚመጡ እቃዎችን ማውጫ ጊዜ ገደቡ ከ10 ቀን ወደ 30 ቀን ይሻሻላል ተብሏል። ይህንን የፈቀደው ባለፈው ሳምንት እንደገና ተሻሽሎ ለህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የቀረበው የጉምሩክ አዋጅ ነው፡፡ በአንድ ዲክላራሲዮን ወደ አገር ውስጥ የገቡ እቃዎች በአንድነት መለቀቅ እንዳለባቸውም አሁን በስራ ላይ ያለው አዋጅ ያስገድዳል። ይህ ግን ብዙ ጊዜ አስመጪው በገንዘብ እጥረት ምክንያት በእቃዎች ላይ ሊከፍል የሚገባውን ቀረጥ እና ታክስ በአንድነት
Mar 301 min read


በኢትዮጵያ የተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎች የሚያስፈልጋቸውን የፋይናንስ አቅርቦት
መጋቢት 21/2018 በኢትዮጵያ የተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎች የሚያስፈልጋቸውን የፋይናንስ አቅርቦት አግኝተው ምርታማ እንዲሆኑ የፋይናንስ ተቋማት በየዓመቱ ከሰባት ትሪሊዮን ብር በላይ ብድር ፈሰስ ማድረግ እንዳለባቸው መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ ይሁንና የሚቀርበው ብድር ከሚያስፈልገው ከግማሽ በታች መሆኑን ከሰሞኑ የብሔራዊ ባንክ ያወጣው ሪፖርት አሳይቷል፡፡ እንደ ማሳያ የግብርናው ዘርፍ በየዓመቱ ከሁለት ትሊዮን ብር በላይ #ብድር እያስፈለገው ያገኘው ግን 8 በመቶ ብቻ ነው፡፡ ካገኘው ብድሩ መካከልም አብዛኛው ለማዳበሪያ ማስመጫ የተሰጠ ብድር መሆኑን የብሔራዊ ባንክ ሪፖርት አሳይቷል፡፡ ለአምራች ኢንዱስትሪውና ቤት መግዛት ለሚፈልጉም የሚቀርበው ብድርም እዚህ ግባ የሚባል አይደለም፡፡ በተለይ ለቤት ገዥዎች የሚያስፈልገው ብድር ቢቀርብ እንኳን በተለይ ተቀጣሪው የመበ
Mar 301 min read


የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን፤ ከትምህርት ዘርፉ እንዲወጡ ቢታዘዙም እስካሁን አልወጡም ያላቸው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዝርዝር ይፋ አደረገ፡፡
መጋቢት 21/2018 የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን፤ ከትምህርት ዘርፉ እንዲወጡ ቢታዘዙም እስካሁን አልወጡም ያላቸው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዝርዝር ይፋ አደረገ፡፡ ቁጥራቸውም 52 ነው፡፡ ባለስልጣኑ ውሳኔው ያሳለፍኩት የትህምህርት ተቋማቱ የዘርፉን ጥራት ለመቆጣጠር በማደርገው ሒደት ያሳለፍኳቸውን ውሳኔዎች ተግባራዊ ባለማድረጋቸው ነው ብሏል፡፡ ከዘርፉ እንዲወጡ ከታዘዙ በኋላም ለምን እንዳልወጡ ለመጠየቅ በተደጋጋሚ መጥተው እንዲያስረዱ ብጠይቅም ተግባራዊ አላደረጉም ብሏል፡፡ ስለሆነም ተቋማቱ የተላለፈውን ውሳኔ ተግባራዊ ባለማድረጋቸው ህጋዊነታቸው የተቋረጠ በሚል የዘረዘራቸውን ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በዜጎች ላይ ጉዳት እንዳያደርሱ የከፍተኛ ትምህርት አገልግሎት መስጠት እንዲያቆሙ እንድታደርጉልን ሲል ለክልሎች እና ለከተማ አስተዳደሮች በደብዳቤ
Mar 302 min read
ፕሮግራሞች
bottom of page

