top of page

ዘንድሮ በሚደረገው ሀገራዊ ምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎች በነፃ ለምርጫ ቅስቀሳ እንዲጠቀሙበት የተዘጋጀ የአየሮ ሰዓትና የጋዜጣ አምድ መጠን ይፋ ሆነ።

  • Mar 28
  • 1 min read

መጋቢት 19/2018


ዘንድሮ በሚደረገው ሀገራዊ ምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎች በነፃ ለምርጫ ቅስቀሳ እንዲጠቀሙበት የተዘጋጀ የአየሮ ሰዓትና የጋዜጣ አምድ መጠን ይፋ ሆነ።


በዚህም በራዲዮ 782.5 ሰዓት እንዲሁም በቴሌቪዥን ደግሞ 570 ሰዓት ለፖለቲካ ፓርቲዎች እና የግል እጩዎች ተዘጋጅቶላቸዋል ተብሏል።


የአየር ሰዓቱ በ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ወቅት ከነበረው በ10 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።


በጋዜጦች ደግሞ 576 አምድ መዘጋጀቱ ተነግሯል ።


በዛሬው እለት የ7 ኛው ጠቅላላ ምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎች ነፃ የአየር ሰዓት ድልድል ዕጣ አወጣጥ ስነስርዓት እየተካሄ ነው።


በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ 24 ራዲዮ ጣቢያዎች፣ 20 ቴሌቪዥን እንዲሁም 6 ጋዜጦች የፖለቲካ ፓርቲዎች እና የግል እጩዎች ፖሊሲያቸውን፣ አላማና ፕሮግራማቸውን ለህዝብ እንዲያስተዋውቁበት መመረጣቸውን ሰምተናል።


የፖለቲካ ፖርቲዎቹ እና የግል እጩዎች ከመጪው ረቡዕ መጋቢት 23 ጀምሮ እስከ ግንቦት 19/2019 ድረስ የእረፍት እና የበዓላት ቀንን ሳይጨምር ለ40 ቀናት በየመገናኛ ብዙሃኑ በሚወጣላቸው እጣ የምረጡኝ ዘመቻ ማድረግ ይችላሉ ተብሏል።


በ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ በራዲዮ 711 ሰዓት ለፖለቲካ ፓርቲዎች ተመድቦ የነበረ ቢሆንም የተጠቀሙት ግን 53.8 በመቶውን ብቻ እንደነበር ተነግሯል።


በተመሳሳይ በቴሌቪዥን 558.9 ሰዓት ቢመደብም ጥቅም ላይ የዋለው 60 በመቶው ብቻ መሆኑን ሲነገር ሰምተናል።


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


YouTube : https://shorturl.at/18TS1

WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx

X :- https://x.com/shegerfm?s=2

Recent Posts

See All
በሀገሪቱ ምን ያህል ቋንቋዎች እንዳሉ ከግምት በዘለለ ይታወቃል?

ሰኔ 18/2018 በኢትዮጵያ ቋንቋ ከማንነት ጋር ከፍተኛ ቁርኝት ያለው ቢሆንም፤ በሀገሪቱ ምን ያህል ቋንቋዎች እንዳሉ ከግምት በዘለለ ይታወቃል? ጥናትስ ተካሄዶበታል ወይ? ስንል ጠይቀናል፡፡ ቋንቋ በአብዛኛው ከማንነት ጋር ተያይዞ በሚነገርበትና የየቋንቋው ተናጋሪዎች አሁን አሁን በተሻለ መንገድ እየተጠቀሙበት ነው በ

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page