top of page

በአዲስ አበባ መንገዶች ከተሰሩበት አላማ ውጪ እየዋሉ መሆኑን የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ተናገረ፡፡

  • 17 minutes ago
  • 1 min read

መጋቢት 17/2018


በአዲስ አበባ መንገዶች ከተሰሩበት አላማ ውጪ እየዋሉ መሆኑን የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ተናገረ፡፡


ባለስልጣኑ እንዳለው በኮሪደር ልማቱ ስራ የመኪና ማቆሚያዎች በተለያዩ ስፍራዎች ተገንብተዋል ያለ ሲሆን በከተማው መውጪያ እና መግቢያ አካባቢ ትላልቅ መኪኖች እቃ ጭነው ለረጅም ሰዓት ሲቆሙ እየተመለከትሁኝ ነው ብሏል፡፡


የባለስልጣኑ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ እያሱ ሰለሞን ባለፉት 8 ወራት ውስጥ 111 ኪሎ ሜትር የአስፓልት መንገድ ጥገና መከናወኑን ነግረውናል፡፡



ክረምት እየመጣ መሆኑን ተከትሎ የጎርፍ ስጋ ባለባቸው አካባቢዎች የሚገኙ ድልድዮች፣ የፍሳሽ ማስወገጃ ቱቦዎች ጥገና እየተከናወነ መሆኑን አስረድተዋል፡፡


አዲስ አበባ ወስጥ መንገዶች በየጊዜው ነው እድሳት የሚደረግላቸው ምክንያቱ ደግሞ ህብረተሰቡ የኔነት ስሜት ኖሮት መንገዶችን እየጠበቃቸው ባለመሆኑ ነው ብለዋል፡፡


በተያዘው አመት ለመንገድ አዲስ ግንባታ እና ጥገና አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ያዘው በጀት 31 ቢሊዮን ብር መሆኑን ሰምተናል፡፡


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….


ወንድሙ ሀይሉ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


YouTube : https://shorturl.at/18TS1

WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx

X :- https://x.com/shegerfm?s=2

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page