በአንድ ይዞታ ላይ ሁለት እና ሶስት ካርታ ወይም የይዞታ ማረጋገጫ ለምን ሊወጣ ይችላል?
- 1 hour ago
- 1 min read
መጋቢት 17/2018
በአዲስ አበባ ከመሬትና መሬት ነክ ጉዳዮች ጋር በተገናኘ ዛሬም አሁንም ከፍተኛ ቅሬታና የአፈፃፀም ችግር እንዳለ ይሰማል።
ከተማ አስተዳደሩ በተለያየ ዙር በሊዝ የጨረታ ቦታዎችን እያወዳደረ ለባለሀብቶች እያስተላለፈ ነው።
የተወሰኑ የልማት ተነሺዎችም ሆኑ በጨረታ ከከተማ አስተዳደሩ አሸንፈው የወሰዱ ፤ ቦታ ለማግኘት ከማእከል ከጨረሱ በኋላ የተሰጣቸውን ቦታ ለመቀበል እንደተቸገሩ ሰምተናል።
የዚህ ዋነኛ ችግር ደግሞ በተለይ የአርሶ አደር ቦታ ነው ፤ ካሳ አልተሰጠንም አልተወሰደም እና ሌሎች ምክንያቶችም ለከተማ አስተዳደሩ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ራስ ምታት እንደሆነበት ሰምተናል።
ለመሆኑ የፕላን ተቃርኖ ያለበት ወይም ለአረንጓዴ ስፍራ ቦታ የተያዘ ቦታ የሆነ አገልግሎት ግንባታ የተፈጸመበት ቦታስ ሊስተካከልና አገልግሎቱ ሊስማማ የሚችለው እንዴት ነው?
መሬትን የሚያስተዳድረው መንግስት ሆኖ ሳለ ፤ የካርታ መደራረብ አለ፤ በአንድ ይዞታ ላይ ሁለት እና ሶስት ካርታ ወይም የይዞታ ማረጋገጫ ለምን ሊወጣ ይችላል?
በዚህ ጉዳይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ሀላፊውን አቶ መኮንን ያኢን ጠይቀናል።
ሃላፊው አቶ መኮንን በአዲስ አበባ ከመሬት ጋር የሚገናኙ ችግሮች አሁንም አሉ ግን እየተፈቱ ነው ይላሉ፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….
ተህቦ ንጉሴ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/
YouTube : https://shorturl.at/18TS1
Telegram : https://shorturl.at/68aeK
Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4
WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx
X :- https://x.com/shegerfm?s=2
LinkedIn: https://shorturl.at/Vfe6i
Tiktok : https://shorturl.at/lhYiv
Instagram: https://shorturl.at/9X4S7





Comments