top of page

በአይነቱ ልዩ የሆነ የሪል ስቴት ኤክስፖ በለንደን እንግሊዝ ከግንቦት 15 እስከ 17/2018 እንደሚካሄድ ተነገረ።

  • Mar 31
  • 1 min read

መጋቢት 22/2018


በአይነቱ ልዩ የሆነ የሪል ስቴት ኤክስፖ በለንደን እንግሊዝ ከግንቦት 15 እስከ 17/2018 እንደሚካሄድ ተነገረ።


በእንግሊዝና አካባቢዋ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በሀገራቸው የመኖሪያ ቤት ማፍራት የሚችሉበትን ዕድል ለመፍጠር የተዘጋጀ ኤክስፖ ነው ተብሏል።


በሪል ስቴት አልሚዎችና በተጠቃሚዎች መካከል ያለውን መተማመን ለማሳደግና አስተማማኝ በሆነ መንገድ ግብይቶች እንዲፈፅሙ የተዘጋጁ ስርዓቶችን ለማስተዋወቅ ያለመ መሆኑም ተጠቅሷል።


በኤክስፖው ላይ ከሚመለከታቸው አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ጋር በሚደረግ የመረጃ ልውውጥና የፓናል ውይይት በዘርፉ ስላሉ ችግሮች ይነሳል ተብሎ እንደሚጠበቅም ኤክስፖውን አስመልክቶ ከተዘጋጀ መግለጫ ላይ ተመልክተናል።


ባንኮች በውጪ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የቢዝነስ ድጋፍ አቅርቦቶችን እንደሚያስተዋውቁበትም ተነግሯል።


ኤክስፖውን በለንደን የኢትዮጵያ ኤምባሲ፣ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ አገልገሎት፣ የኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር ፣ የአዲስ አበባ ንግድ ምክር ቤት እና ኤድማር ቬንቸርስ የተባለ ትውልደ ኢትዮጵያዊ ተቋም በመተባበር ያዘጋጁታል ተብሏል።


ንጋቱ ረጋሳ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


YouTube : https://shorturl.at/18TS1

WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx

X :- https://x.com/shegerfm?s=2

Recent Posts

See All
የመንግስት ግዥ አገልግሎት በዘንድሮው በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት በሽያጭ ከተወገዱ ተሽከርካሪዎች እና ሌሎች ንብረቶች የተገኘ ወደ 323 ሚሊየን ብር የሚጠጋ ገንዘብ ለመንግስት ገቢ አድርጌያለሁ አለ፡፡

ግንቦት 17/2018 የመንግስት ግዥ አገልግሎት በዘንድሮው በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት በሽያጭ ከተወገዱ ተሽከርካሪዎች እና ሌሎች ንብረቶች የተገኘ ወደ 323 ሚሊየን ብር የሚጠጋ ገንዘብ ለመንግስት ገቢ አድርጌያለሁ አለ፡፡ አገልግሎቱ ይህን ያህል ገንዘብ ዘጠኝ ወራት ውስጥ ለመንግስት ገቢ ሲያደርግ በታሪኩ የአሁኑ የጀመ

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page