top of page

የእስራኤል ጦር ከኢራን ባህር ሀይል ከፍተኛ አዛዦች መካከል አንዱ የነበሩት አል ሬዛ ታንጂ ሲሪን ገደልኩት አለ፡፡

  • 9 hours ago
  • 1 min read

መጋቢት 17/2018


የእስራኤል ጦር ከኢራን ባህር ሀይል ከፍተኛ አዛዦች መካከል አንዱ የነበሩት አል ሬዛ ታንጂ ሲሪን ገደልኩት አለ፡፡


ታንጂ ሲሪ የተገደሉት ኢራን በከፊል ዝግ አድርገው በሰነበተችው የሆርሙዝ ሰርጥ ቅኝት ያደርጉ በነበረበት ወቅት እንደሆነ ቢቢሲ ፅፏል፡፡

ታንጂሲሪ ለሆርሙዝ ሰርጥ መዘጋት ከፍተኛ ድርሻ ከነበራቸው የኢራን የጦር መሪዎች መካከል አንዱ እንደነበሩ የእስራኤሉ የመከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ ተናግረዋል፡፡


ወደ ወር በተቃረበው ጦርነት በአሜሪካ እና እስራኤል ጥምር ድብደባ በርካታ የኢራን ሲቪል እና የጦር መሪዎች መገደላቸው ይነገራል፡፡


ታንጂ ሲሪ በእስራኤል የአየር ጥቃት ተገድለዋል ስለመባሉ ለጊዜው ከኢራን በኩል የተሰማ አስተያየት የለም ተብሏል፡፡


ያም ሆኖ ኢራንን በአሜሪካ እና በእስራኤል ለሚፈፀምባት ድብደባ ምላሽ ከመስጠት አልተቆጠበችም፡፡


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


YouTube : https://shorturl.at/18TS1

WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx

X :- https://x.com/shegerfm?s=2

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page