top of page

የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን፤ ከትምህርት ዘርፉ እንዲወጡ ቢታዘዙም እስካሁን አልወጡም ያላቸው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዝርዝር ይፋ አደረገ፡፡

  • Mar 30
  • 2 min read

መጋቢት 21/2018


የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን፤ ከትምህርት ዘርፉ እንዲወጡ ቢታዘዙም እስካሁን አልወጡም ያላቸው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዝርዝር ይፋ አደረገ፡፡


ቁጥራቸውም 52 ነው፡፡


ባለስልጣኑ ውሳኔው ያሳለፍኩት የትህምህርት ተቋማቱ የዘርፉን ጥራት ለመቆጣጠር በማደርገው ሒደት ያሳለፍኳቸውን ውሳኔዎች ተግባራዊ ባለማድረጋቸው ነው ብሏል፡፡


ከዘርፉ እንዲወጡ ከታዘዙ በኋላም ለምን እንዳልወጡ ለመጠየቅ በተደጋጋሚ መጥተው እንዲያስረዱ ብጠይቅም ተግባራዊ አላደረጉም ብሏል፡፡


ስለሆነም ተቋማቱ የተላለፈውን ውሳኔ ተግባራዊ ባለማድረጋቸው ህጋዊነታቸው የተቋረጠ በሚል የዘረዘራቸውን ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በዜጎች ላይ ጉዳት እንዳያደርሱ የከፍተኛ ትምህርት አገልግሎት መስጠት እንዲያቆሙ እንድታደርጉልን ሲል ለክልሎች እና ለከተማ አስተዳደሮች በደብዳቤ ጠይቋል፡፡


በተጨማሪወም እስካሁን ያደረሱት ጉዳት ካለ በመፈተሽ አስፈላጊ የህግ እርምት እርምጃ እንዲወሰድባቸው ጠይቋል፡፡


ከዘርፉ እንዲወጡ ቢታዘዙም እስካሁን አልውጡም የተባሉት የተቋማት ስም ዝርዝር የሚከተሉት ናቸው ተብሏል፡፡


1 አቢሲኒያ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ

2 አፍራን ቀሎ ኮሌጅ

3 አገው ምድር ቢዝነስ እና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ

4 አዲስ ፋና ኮሌጅ

5 ቢኤ ኮሌጅ

6 ኡቡንቱ ቢዝነስና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ

7 ፈጣም ኮሌጅ

8 ግሪን የምርምርና የልማት ተቋም

9 ሴንቸሪ ኮሌጅ

10 ኮቻ ኪድማስ የቢዝነስና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ

11 ካንድል ላይት የርቀት ትምህርት ኮሌጅ

12 ቀይ ባህር ኮሌጅ

13 ማራኪ ቴክኖሎጂ እና ቢዝነስ ኮሌጅ

14 ኒው ዲፕሎማት ኮሌጅ

15 ፒቢቲ አፍሪካ ኮሌጅ

16 ኳሊቲ ስኮላር ኮሌጅ

17 ራዲካል ኢንተርናሽናል ኮሌጅ

18 ውቅያኖስ ኮሌጅ

19 የኔታ ኢንጅነሪንግ ኮሌ

20 ቪዥነሪስ የድህረ ምረቃ ኮሌጅ

21 ባቱ ግሎባል ኮሌጅ

22 ባህረ ጥበብ ጤናና ቢዝነስ ኮሌጅ

23 ማይክሮ ቢዝነስ ኮሌጅ

24 ማያ ኮሌጅ

25 ትሪፕል ኮሌጅ

26 ቤታሎጎ ኮሌጅ

27 ቤካ ኮሌጅ

28 ቀስተ ደመና ኮሌጅ

29 ብራይት ቪዥን ኮሌጅ

30 ኤ.አር.ቲ ሜዲካል ኮሌጅ

31 ኢሊያስ ኮሌጅ

32 ሳይፕሮ ኮሌጅ

33 ዳይናሚክ ኮሌጅ

34 ግራንድ ማርክ ኮሌጅ

35 ዱርማን ኮሌጅ

36 ህብረት ቴክኖሎጂ ኮሌጅ

37 አይቤክስ ሆቴልና ቱሪዝም ኮሌጅ

38 አይ ኪው ኮሌጅ

39 ገራይ ኮሌጅ

40 ጋላክሲ ቢዝነስና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ

41 ቪዥን ላንድ ኮሌጅ

42 መራ ሄመንገድ ኮሌጅ

43 ዩናይትድ ኦሮሚያ ኮሌጅ

44 ኢንተርናሽናል ሊደርሺፕ ኮሌጅ

45 ሲምለስ የርቀት ትምህርት ኮሌጅ

46 ዛክቦን ኮሌጅ

47 ኤም ኤስ ኤል ጂ ኮሊጅ

48 ስሪሳይ ኮሌጅ

49 ፋም ኮሌጅ

50 ስማርት ቢዝነስና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ

51 ሊድስታር ኮሌጅ ኦፍ ቢዝነስና ሊደርሺፕ

52 ዳሎል የቲክኖሎጂና ቢዝነስ ኮሌጅ

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page