top of page

በኢንዱስትሪ ፓርኮችና በከፍተኛ ት/ት ተቋማት የሚገኙ ወጣቶች ለኤችአይቪ ተጋላጭነትን ለመቀነስ የኮንዶም አቅርቦትና ግንዛቤው ላይ መሰራት አለበት ተባለ፡፡

  • Apr 2
  • 2 min read

መጋቢት 24/2018


በኢንዱስትሪ ፓርኮች እንዲሁም በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ የሚገኙ ወጣቶች ለኤች አይ ቪ ተጋላጭነትን ለመቀነስ የኮንዶም አቅርቦትና ግንዛቤው ላይ መሰራት አለበት ተባለ፡፡


በስራቸው እና ዕድሜያቸው ምክንያት ለኤች አይ ቪ እጅግ ተጋላጭ ከሆኑት ውስጥ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ያሉ ወጣቶች በተለይ ሴቶች ይገኙበታል ተብሏል፡፡


ለዚህም የጤና ሚኒስቴር ከለጋሽ ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በመሆን ኮንዶም በነፃ እያቀረበ መሆኑን ነገር ግን ይህም ቢሆን በቂ አለመሆኑን ተናግሯል፡፡


በጤና ሚኒስቴር የኤች አይቪ ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር መሪ ስራ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ ፍቃዱ ያደታ እንደሚናገሩት በተለይ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ላይ ተቀጥረው ከሚሰሩት ውስጥ አብዛኛዎቹ ወጣቶች በመሆናቸው የኤች አይ ቪ ተጋላጭነታቸውን መቀነስ ላይ ይበልጥ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡



በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ የሚሰሩ ሰዎች አብዛኛው ሴት ወጣቶች ናቸው፤ ሴት ወጣቶች ደግሞ በይበልጥ ተጋላጭ ክፍሎች በመሆናቸው በነጻ ኮንዶም ሊቀርብላቸው ከሚገባው ክፍሎች አንደኛዎቹ ናቸውና በነፃ በእያንዳንዱ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ የጤና ሚኒስቴር ከአጋሮቹ ጋር በመሆን ኮንዶም በነፃ ያቀርባል ብለዋል፡፡


በዓለም አቀፍ ለጋሾች ድጋፍ መቀነስና በሌሎችም ችግሮች ምክንያት የኮንዶም አቅርቦቱ ከሚጠበቀው በታች በመሆኑ ግን በመስሪያ ቤቶችና ሌሎች ለኤች አይቪ ተጋላጭ የሆኑ ሰዎች ባሉባቸው ቦታዎች ላይ ኮንዶም እንደልብ ማቅረብ አልተቻለም ብለዋል አቶ ፍቃዱ፡፡


ዓለም አቀፍ ድጋፎችም የቀነሱ ከመምጣታቸው ጋር ተያይዞ በመንግስት እና በተወሰኑ አጋሮች የሚገዛው ኮንዶም እጅግ ተጋላጭ ለሆኑት እንጂ በየትኛውም መንግስት መስሪያ ቤትና በየት/ቤቱ በሁሉም ቦታ ላይ ማቅረብ አይቻልም ብለዋል፡፡


በሌላ በኩል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎችም ላይ ኤች አይ ቪ በመከላከል በኩል የሚጠበቁ ስራዎች አሉ የሚሉት መሪ ስራ አስፈጻሚው ነገር ግን ያለው ሀብት ውስን በመሆኑ የተወሰኑት ላይ ብቻ እየሰራን ነው ሲሉ ይጠቅሳሉ፡፡


በአገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች ያለው የሰላም ችግር የግንዛቤ ማነስ እና በቸልተኝነት አዲስ በኤች አይ ቪ የሚያዙ ሰዎች በተለይ ወጣት ሴቶች ቁጥር እየጨመረ መሆኑ ተነግሯል፡፡


ይህ በወጣቶች ላይ የሚታየው ከፍተኛ የኤች አይ ቪ ተጋላጭነት ስጋት ጠንካራ የመከላከል ስራ ይጠይቃልም ተብሏል፡፡


በኢትዮጵያ በየዓመቱ አዲስ በኤች አይ ቪ ከሚያዙ ሰዎች ውስጥ እድሜያቸው ከ15-24 የሆኑ ወጣቶች 34 በመቶውን እንደሚይዙ ጥናት ያሳያል፡፡


ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ….

ምህረት ስዩም


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


YouTube : https://shorturl.at/18TS1

WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx

X :- https://x.com/shegerfm?s=2

Recent Posts

See All
የመንግስት ግዥ አገልግሎት በዘንድሮው በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት በሽያጭ ከተወገዱ ተሽከርካሪዎች እና ሌሎች ንብረቶች የተገኘ ወደ 323 ሚሊየን ብር የሚጠጋ ገንዘብ ለመንግስት ገቢ አድርጌያለሁ አለ፡፡

ግንቦት 17/2018 የመንግስት ግዥ አገልግሎት በዘንድሮው በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት በሽያጭ ከተወገዱ ተሽከርካሪዎች እና ሌሎች ንብረቶች የተገኘ ወደ 323 ሚሊየን ብር የሚጠጋ ገንዘብ ለመንግስት ገቢ አድርጌያለሁ አለ፡፡ አገልግሎቱ ይህን ያህል ገንዘብ ዘጠኝ ወራት ውስጥ ለመንግስት ገቢ ሲያደርግ በታሪኩ የአሁኑ የጀመ

 
 
 

1 Comment


Hany Macron
Hany Macron
Apr 22

Pokepath TD keeps you engaged by constantly giving you new goals to work toward, whether it’s unlocking evolutions or improving your team composition.

Like
Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page